loader

Topics (26)


loader Loading content ...

Explanations (30)


 • @አማን   2 weeks ago
  Stop waiting for the perfect moment. Take the moment you've and make it perfect.

  ረዳት ፕሮፌሰር ደበበ ሰይፉ በኢትዮጵያ የኪነ-ጥበብ ታሪክ ሁለገብ አስተዋፅዖ ከነበራቸው ጥቂት ምሁራን አንዱ ናቸው:: ደበበ ሰይፉ በሥነ-ተውኔትና ሥነ-ፅሁፍ መምህርነት፣ በተውኔት ደራሲነትና ተርጓሚነት፣ በገጣሚነትና በሃያሲነት ብዙ ተግባራትን አከናውነዋል:: ደበበ ሰይፉ ከአባታቸው ከበጅሮንድ ሰይፉ አንተንይስጠኝ እና ከእናታቸው ከወ/ የማርያምወርቅ አስፋው ሐምሌ 5 ቀን 1942 .. በሲዳሞ ውስጥ በይርጋለም ከተማ ተወለዱ:: እድሜአቸው ለትምህርት በደረስ ጊዜ በተወለዱበት አካባቢ የቤተ-ክርስቲያን ትምህርት ተምረዋል:: ቀጥሎም በራስ ደስታ ዳምጠው ስም ይጠራ በነበረው /ቤት ገብተው እስከ ስምንተኛ ክፍል ተምረዋል:: ከዚያም ወደ አዲስ አበባ ከተማ መጥተው በኮከበ ፅባህ /ቤት ገብተው የሁለተኛ ደረጃ ትምህርታቸውን አጠናቀቁ:: በማስከተልም በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የአርትስ ፋካልቲ ገብተው በመማር 1965 .. በኢትዮጵያ ቋንቋዎችና ሥነ-ፅሁፍ በማዕረግ በቢኤ ዲግሪ ተመረቁና በዚያው በዩኒቨርሲቲው መምህር ሆነው ተቀጠሩ:: 1970 . . ደግሞ በእንግሊዘኛ ሥነ-ዕሁፍ አሁንም በማዕረግ የኤም ዲግሪያቸውን አገኙ:: ደበበ የመጀመሪያ ዲግሪያቸውን ካገኙበት 1965 .. አንስቶ ለሃያ ዓመታት በኢትዮጵያ ሥነ-ፅሁፍና በቲያትር ጥበባት ትምህርት ክፍሎች አስተምረዋል:: ደበበ ከማስተማሩም ጐን ለጐን የምርምር ፅሁፎችን በመፃፍ በአገር ውስጥና በውጭ መድረኮች አቅርበዋል የተወሰኑትንም አሳትመዋል:: የኩራዝ አሳታሚ ድርጅት አባል፣ በኢትዮጵያ ሬዲዮ የኪነ-ጥበቡ ዘርፍ አማካሪ፣ የቋንቋዎች ተቋም ጆርናል አሳታሚ ኮሚቴ ሊቀ-መንበ ር፣ የኢትዮጵያ ደራሲያን ማህበር ሊቀ-መንበር፣ በኢትዮጵያ ደራሲያን ማህበር ሥር የሚታተመው "ብሌን ̈ መፅሄት አሳታሚ ኮሚቴ ሊቀ-መንበር እና በፖለቲካውም የኢትዮጵያ ሠርቶ አደሮች ፓርቲ (ኢሠፓ) አባል በመሆን አገልግለዋል:: ደበበ የፃፏቸው ግጥሞችም የብርሃን ፍቅር እና ለራስ _ የተፃፈ ደብዳቤ በሚሉ ሁለት መድብሎች ታትመው ወጥተዋል:: የመጀመሪያው መድብል ደበበ ራሣቸው በህይወት በነበሩ ጊዜ 1980 .. የታተመ ሲሆን ለራስ የተፃፈ ደብዳቤ የሚለው መድብል ደግሞ ከዚህ ዓለም በሞት በተለዩበት 1992 .. በሜጋ አሳታሚ ድርጅት አማካኝነት ታትመዋል:: ደበበ ሰይፉ የቡና _ ቤት ሥዕሎችና _ ሌሎች ወጕች የሚለው የመስፍን ብተማርያም ኢ-መደበኛ የወ ስብስብ በታተመ መግቢያውን የፃፉት እሳቸው ናቸው፡፡ "ብድር በምድርእንዲሉ የደበበ ሁለተኛ የግጥም ስብስብ የሆነው ለራስ የተፃፈ ደብዳቤ በታተመ ጊዜ ደግሞ መግቢያውን የፃፉት መስፍን ሃብተማርያም ናቸው:: በዚሁ ፅሁፋቸው መስፍን ስለደበበ ግጥሞች አጠቃላይ ባህሪያት እንዲህ ብለዋል:: "ደበበ ሰይፉ በርዕስ አመራረጡና በሚያስተላልፋቸው ልብ የሚነኩ መልዕክቶች ብቻ ሳይሆን በስንኞቹ አወራረድና በቤት አመታቱ በአጠቃላይ በውብ አቀራረቡ ተደራሲያንን የሚመስጥ ገጣሚ ነው:: ስለተፈጥሮ ሲገጥም ፀሐይና ጨረቃ፣ ቀስተ ዳመናና የገደል ማሚቶ ያጅቡታል፡፡ ስለፍቅር ስንኞች ሲቋጥር የፍቅረኞችን ልብ እንደስዕል ቆንጆ አድርጐ በቃላት ቀለማት ያሳያል:: ክህደት ላይ እንደ አንዳንድ ገጣሚያን አያላዝንም:: ይልቁንም ውበትና ህይወትን አገናዝቦ 'ያውላችሁ ስሙት፣ እዩት' ማለትን ይመርጣል:: ... እኔ እንደማውቀው ደበበ ሰይፉ በገጣሚነቱ ሁሌም ዝምተኛ ነው:: አይጮህም:: ጮሆም አያስበረግግም :: ይልቁንስ ለዘብ ለስለስ አድርጐ ' እስቲ አጢኑት' ይለናል:: ደጋግመን እንድናነብለት የሚያደርገንም ይኸው ችሎታው ነውብለዋል::

  የደበበ ሰይፉ ግጥሞች አልፎ አልፎ እንደ " ለራስ የተፃፈ ደብዳቤ ̈ ያሉት እረጅም የሚባሉ ከመኖራቸው በቀር ብዙዎቹ አጫጭሮች ናቸው:: ግጥሞቻቸው አጫጭር ይሁኑ እንጂ የተፈለገውን መልዕክት በማስተላለፍ ረገድ ጉልበት ያላቸውና ለትንታኔም የሚመቹ ናቸው:: ለምሳሌም "ያላዋቂ ጠያቂ" በሚል ርዕስ የሚጠራውን ግጥማቸውን ቀጥሎ እንመ ልከተው::

  ከመቼው፣

  ከመቼው በል ጦነቸኸው?

  የገሉህን ልትገድል፣

  የጣሉህን ልትጥል፣

  ከመቼው በል ከመቼው ጦነቸኸው?

  ብለው፣

  መቼ .... መቼ ገና አየህና

  ጉልበቴን ለካህና፣

  ብሎ አለፍ እንዳለ፣

  ከፈን በላዬ ተጣለ::

  ደበበ ሰይፉ ከግጥም መድብሎች ሌላ ሶስት አጫጭር ልቦለድ ታሪኮች 1960 . ማርክሲዝምና የቋንቋ ችግሮች (1973) እና የቲያትር ጥበብ ከፀሐፊ ተውኔቱ አንፃር (1973) የተባሉ መዕፃፍትን አሳትመዋል:: ከነዚህም ሌላ ደበበ ቀጥለው የተዘረዘሩትን ተውኔቶችን ፈውና ተርጉመው ብዙዎቹን ለመድረክ አብቅተዋል ::

  1. ከባህር የወጣ አሳ፣

  2. እናትና ልጆቹ ፣

  3. እነሱ እነሷ፣

  4. ሳይቋጠር ስ.ተረተር፣

  5. የህፃን ሽማግሌ፣

  6. ክፍተት፣

  7. ማክቤ እና

  8. ጋሊሊዮ ጋሊሊ ናቸው::

  ደበበ በሃያሲነትም በልዩ ልዩ የኪነጥበብ ፕሮግራሞች ታትመው የሚወጡና ተዘጋጅተው በመድረክ ላይ ይቀርቡ በነበሩ የፈጠራ ሥራዎች ላይ ጥልቀት ያለው ሙያዊ ትንታኔ በመስጠት ይታወቃሉ:: ብዙዎቹ ተውኔታዊ ዳዬ ቃላትም አቻ የአማርኛ ፍቺ የተፈለገላቸው በደበበ ሰይፉ እንደሆነ ይታወቃል:: ደበበ ሰይፉ ወደአማርኛ ከመለሷቸው ተውኔታዊ ቃላት መካከል "ገፀ-ባህሪ፣ ሴራ መቼት፣ ቃለ-ተውኔትእና የመሳሰሉት ተጠቃሾች ናቸው:: ደበበ ከግንቦት 1985 .. አንስቶ የማስተማሩን ሥራ አቁመው ለሰባት ዓመታት ያህል ከቤት ውለው ነበር:: አንዳንድ ወገኖች ከሚናገሩት እና እንዲሁም አንዳንድ ጋዜጦች ከፃፉት ለመረዳት እንደሚቻለው ደበበ በሃላፊነት ላይ በነበሩበት ዘመን ከብልሹ ምግባራቸው እንዲታረሙ የታገሏቸው ወገኖች የተደረገውን የመንግሥት ለውጥ እንደአጋጣሚ ተጠቅመው በደርግ-ኢሠፓ ዘመን በደል እንዳደረሱ አስመስለው አውርተው በማስወራት ክፉኛ ያበሳቸው ነበር:: ደበበ ሰይፉ ሚያዚያ 16 ቀን 1992 .. ከዚህ ዓለም በሞት ተለይተው በቅዱስ ዮሴፍ ቤተ-ክርስቲያን ተቀበሩ:: 

  ምንጭ:- ታሪካዊ መዝገበ-ሰብ 

 • loader Loading content ...
 • @አማን   2 weeks ago
  Stop waiting for the perfect moment. Take the moment you've and make it perfect.

  አፄ ገላውዴዎስ የአፄ ልብነድንግል እና የእቴጌ ሰብለወንጌል ልጅ፣ የአፄ ናኦድ የልጅ ልጅ እና የአፄ ሠርፀ-ድንግል አጐት ናቸው:: አፄ ገላውዴዎስ ከአፄ ልብነድንግል አራት ልጆች ሁለተኛው ናቸው:: የመጀመሪያው የአፄ ልብነድንግል ልጅ ፊቅጦር 1531 .. ሸዋ ውስጥ ከግራኝ አህመድ ወታደሮች ጋር ሲዋጋ ጦር ሜዳ ላይ ሞተ:: ሶስተኛው ወንድ ልጃቸው ሚናስ ትግራይ ውስጥ ከግራኝ አህመድ ወታደሮች ጋር ሲዋጋ ተማርኮ ወደ የመን አገር ተሸጠ:: አፄ ልብነድንግል በሞቱ ጊዜ የተረፉት ወንዶች ልጆች ሁለተኛው ልጅ ገላውዴዎስና አራተኛው ልጃቸው ያዕቆብ ብቻ ነበሩ:: ከፊቅጦር ሞት በኋላ በትምህርት ኮትኩተው ያሳደጓቸው ገላውዴዎስ አልጋ ወራሽ ሆኑ:: በታሪከ ነገሥት እንደተፃፈው አፄ ልብነድንግል በትምህርት የጐለመሱ ሊቅ ስለነበሩ ወጣቱን ገላውዴዎስን ቅዱሣ መፃህፍትን ከነትርጓሜያቸው እያስተማሩ አሳደጓቸው:: ከዚህም ሌላ ገላውዴዎስ ፈረስ ግልቢያን፣ አውሬ አደንን፣ ቀስት ውርወራን፤ የጦር ስልትን እየተማሩ አደጉ:: ገላውዴዎስ ከልጅነት ዘመናቸው ጀምሮ ለትምህርት ጥማት ስለነበራቸው አባታቸው የሚያስተምሯቸውን ሁሉ በብሩህ ልቡና ሲማሩ አደጉ:: ብዙ የታሪክ ፀሐፊዎች እንደፃፉት አፄ ልብነድንግል ከትልቁ ልጃቸው የበለጠ ብልህ መሆናቸውን በመገመት የአስተዳደርንና የቤተ-ክህነትን እውቀት በተለየ ትኩረት እያስተማሩ አሳደጓቸው::

  በ18 ዓመታቸው ገላውዴዎስ በእናታቸው ከእቴጌ ሰብለወንጌል ረዳትነት በትረ-መንግሥቱን ይዘው በጐንደር፣ በትግራይ፣ በጐጃም፣ በሽዋበወሎ ልዩ ልዩ ሥፍራዎች ከግራኝ አህመድ ግዙፍ ጦር ጋር ውጊያ ሲያደርጉ ኃላፊነታቸውን ለመወጣት አልከበዳቸውም። ገላውዴዎስ የውጊያ ችሎታቸውን ያህል በባህሪያቸው ደግና ትዕግሥተኛ ከመሆናቸውም እኩል መሃሪ ነበሩ:: በታሪካቸው መቅድም ስለበዛው ደግነታቸውና መሃሪነታቸው ስለመልካም ገዥነታቸው የሚከተለው ሰፍሮ ይገኛል:: “ለአፍና ለጉሮሮ ከማርና ንኮራ አገዳ የሚጣፍጥ ለሚሰሙ ጆሮዎች መደነቅን የሚያበዛ፣ ለሚሰሙትም እንደዘፈን ደስታ የሚሰጥ ስሙ የተከበረ፤ ትሩፋቱ የተነገረ ሥርዓቱ ያማረ፣ ልቡ ንፁህ የሆነ፣ ግብረገብ፣ የተመሰገነ፣ ፍርዱ የቀና ትዕዛዙ የፀና በኢትዮጵያ በደጋዋ በቆላዋ በመስኮቿና በተራራዎቿም፤ በባህሮቿና በደሴቶቿም፣ በብልሆቹና በሰነፎች ሁሉ ከፅንፍ እስከፅንፍ ተከራካሪ ሳይኖርበት ከአዲም በር እስከ አዲም ስለነገሠው ስለአፄ ገላውዴዎስ ታሪክ እንጀምራለንይላል:: 

  አፄ ገላውዴዎስ በእርግጥም አስተዋይ ስለነበሩ ወንድማቸውን ሚናስን የሸጠባቸውን የኢማም ኢብራሂምን ልጅ በጦር ሜዳ ማርከው በእጃቸው በገባ ጊዜ በወንድማቸው ልዋጭ ወደአገሩ እስኪ መለስ ድረስ አንድም ስቃይ ሳይደርበት በክብር እንዲቀመጥ አድርገውታል:: አፄ ገላውዴዎስ በትረ-መንግሥቱን ይዘው ወታደራዊ አቋማቸውን እንዳደራጁ በግራኝ አህመድ ላይ ተከታታይ የመልሶ ማጥቃት ጦርነት አደረጉ:: በተለይም በትግራይ ተንቤንና በጐንደር ሰሜን ተራራ አካባቢ ተዋግተው ሁለት ወሳኝ ድሎችን ካገኙ በኋላ የመልሶ ማጥቃት ጦርነቶችን እያሰፉ መጡ:: የውጭ የታሪክ ዘጋቢዎች ካሰፈሩት ለመረዳት እንደሚቻለው አፄ ገላውዴዎስ ግራኝ አህመድን ለማሸነፍ ያበቋቸውን ጦርነት ያደረጉት 1535 .. ሲሆን ሲል ከተደረጉ ጦርነቶች የተረፉ የዘመናዊ ጦር መሣሪያ ተኳሽ የነበሩ 200 የፖርቱጋል ወታደሮች ሳትፈዋል:: የኢትዮጵያ ቀደምትና ታላላቅ ዑላማዎች ታሪክ የተባ ሃፍ ይህንኑ የአፄ ገላውዴዎስንና የግራኝ አህመድን የመጨረሻ ጦርነት አስመልክቶ ቀጣዩን አስፍሯል:: ”አህመድ ግራኝ መላ ሀበሻን ለኣስ አምስት ዓማታት ከገዙ በኋላ እንዴት ተሸነፉ የሚል ጥያ መነሳቱ አግባብነት አለው:: ቅቱ ሀበሻ ንጉሥ ለክርስቲያን ፈረንጆች የድረሱልኝ ጥያቄ በስፋ አቀረቡ:: እነሱም አፋጣኝ ምላሽ ይሆን ዘንድ መሣሪያና ወታደር ወደ ሀበሻ በመላካቸ በለሱ ዞረና ነሳራዎች (የክርቶስ ከታዮች) ሊያሸንፉ እና አህ ግራኝ ወታደር ሊሸነፍ ችሏል:: ነሳራዎችም ዚህ በፊት በማንኛቸውም የጦር ግንባር ይቶ በማይታወቅ መልኩ ሰይፍና ጦር በታጠቀው የአህመድ ግራኝ ጦር ላይ ጠብመንጃና ሌላም ዘመናዊ የጦር መሳሪያ ተጠቅመው ያልተቋረጠ ድብደባ ፈፀ:: በዚህም ወቅት ኢማም አህመድ ግራኝ በመስዋዕትነት ወደቁብሏል:: የአገር ውስጥና የውጭ ደራሲዎች እንደፃፉት የአውሮፓውያን ክርስቲያኖች በተለይም የፖርቹጋልን እገዛ የጠየቁት አፄ ገላውዴዎስ ሳይሆኑ አባታቸው አፄ ልብነድንግል ናቸው:: አፄ ልብነድንግል የአውሮፓ ክርስቲያኖችን እርዳታ የጠየቁበት ምክንያት ግራኝ አህመድ ከቱርክ መንግሥት ዘመናዊ መሣሪያና በአጠቃላይም ወታደራዊ እርዳታ እያገኘ ስላጠቃቸው ይህንን ጥቃት ለመቋቋም ሲሉ ያደረጉት መሆኑ ተፅፏል::

  አፄ ገላውዴዎስ ሥልጣን ከያዙበት 1533 .. አንስቶ ያለእረፍት አስር ዓመታትን ሲዋጉ ቆይተው የካቲት 21 ቀን 1543 .. ወይናደጋ ላይ ትልቅ ጦርነት ተደርጐ ግራኝ መገደሉን ጋስፒሪኒ ፅፈዋል:: አፄ ውዴዎስ በትግራይ፣ በጐንደርና በጐጃም ያሉ ግዛቶችን በሙሉ ድል አድርገው ከተቆጣጠሩ በኋላ በወሎ በኩል አድርገው ወደሸዋ በመሻገር ከተረፈው የግራኝ አህመድ ጦር ጋር መዋጋት ቀጠሉ:: በሪሁን ከበደ የአቶ አጽሜን የታሪክ መፅሃፍ ጠቅሰው የአፄ ኃይለ ሥላሴ ታሪክ በተባለው መፅሃፍ እንዳብራሩት አፄ ገላውዴዎስ የመጨረሻውን ጦርነት ያደረጉት 1551 .. ነው:: አፄ ገላውዴዎስ አሚር ኑር ከተባለ የጦር መሪ ጋር ተዋግተው ድል ካደረጉ በኋላ እንደገና ባገረሸው ጦርነት ተገደሉ:: ከሶስት መቶ አመታት በኋላ አፄ ዮሐንስ አራተኛ መተማ ላይ ሲዋጉ በሞቱ ጊዜ ጭንቅላታቸው ተቆርጦ እንደ ተወሰደ ሁሉ አሚር ኑርም የአፄ ገላውዴዎስን ጭንቅላት ቆርጦ በአህያ በመጫን ወደሀረር ወስዷል:: የግራኝ አህመድ የእህት ልጅ የሆነው አሚር ኑር የተቆረጠውን የአፄ ገላውዴዎስን አንገት ይዞ አዲስ ላገባት የአጐቱ ሚስት ባቲ ድል ወንበራ ግዳይ ለመጣል በመገስገስ ላይ እንዳለ አዛሎ በተባለ ቦታ ላይ በደረሰ ጊዜ አድፍጠው ይጠብቁት ከነበሩ ኦሮሞዎች ጋር ጦርነት ገጠመ። አሚር ኑር ከኦሮሞዎች ጋር ባደረገው ጦርነት አብዛኛው ጦሩ አልቆበት ጥቂት ራሱን ሆኖ ፈረስ አምልጦ ሀረር ገባ:: አፄ ገላውዴዎስ እንደሞቱ ወዲያ ወንድማቸው አፄ ሚናስ (የአፄ ሠርፀ-ድንግል አባት) ተተኩና ሐመልማል በተባለ የጦር አበጋዝ የሚመራ ጦር የአፄ ገላውዴዎስን አንገት ቆርጦ የወሰደውን አሚር ኑርን እንዲወጋ ወደ ሀረር ላኩ:: ሐመልማል ወደሀረር በመገስገስ ላይ እንዳለ ተቆርጦ የተወሰደው የአፄ ገላውዴውስ አንገት እንደተመለሰ ከውንድማቸው ከአቤቶ ያዕቆብ መቃብር መንዝ ውስጥ ገማ ኮረብታ በሚገኘው ቤተ-ክርስቲያን እንዲያርፍ ተደረጓል:: ዋናው የአፄ ገላውዴዎስን አካል ግን ሲዋጉ ከሞቱበት  ከፈጠጋር እንደ ተቀበረ በልዩ ልዩ መፅሃፍት ተፅፎ ይገኛል:: 

  ምንጭ:- ታሪካዊ መዝገበ-ሰብ 

 • loader Loading content ...
 • @አማን   3 weeks ago
  Stop waiting for the perfect moment. Take the moment you've and make it perfect.

  ከጎራው ዘልቄ - እስኪ ልነጋገር

  ካለሰው ቢወዱተ - ምን ያደርጋል አገር?

  ህንፃ መች ሆነና - የድንጋይ ክምር፣

  መንገድ መች ሆነና - የድንጋይ አጥር፣

  ህንፃው ምን ቢረዝም - ምን ቢፀዳ ቤቱ፣

   መንገዱ ቢሰፋ - ቢንጣለል አስፋልቱ፣

   ሰው ሰው ካልሸተተ - ምንድነው ውበቱ?

   የኔ ውብ ከተማ - የኔ ውብ አገር፣ የሰው ልጅ ልብ ነው፣

   የሌለው ዳርቻ - የሌለው ድንበር፣

  (ግጥም - በአሉ ግርማ)

   

 • loader Loading content ...
 • @አማን   3 weeks ago
  Stop waiting for the perfect moment. Take the moment you've and make it perfect.

  ፕሮፌሰር አስራት ላው አማራ ህዝብ ድርጅት መስራችና መሪ ናቸው:: ፕሮፌሰር አስራት ወልደየስ ሰኔ 12 ቀን 1920 .. በአዲስ አበባ ተወለዱ:: የሶስት አመት እድሜ እንዳስቆጠሩ ከቤተሰብ ጋር ወደ ድሬዳዋ ከተማ ሄዱ:: ገና በህፃንነት እድሜ እንዳሉ ባህላዊ ትምህርት በመግባት ዳዊትን አጠናቀው መድገም እስከሚችሉ ድረስ ተማሩ:: ቀጥሎም በፈረንሣይኛ ቋንቋ ይሰጥ ወደነበረው ዘመናዊ ትምህርት ቤት ለመግባት በመዘጋጀት ላይ እንዳሉ የጣሊያን ጦርነት መጣና ምኞታቸው ተሰናከለ:: ወላጅ አባታቸው አቶ ወልደየስ በጠላት ተይዘው ከመገደላቸውም በላይ አያታቸው ቀኛዝማች ወረደ ቃል ወደጣሊያን አገር ተወስደው ታሰሩ:: ወላጅ እናታቸውም እንዲሁ ሃዘኑና ችግሩ ፀንቶባቸው ብዙ ሳይሰነብቱ በሞት ተለዩ:: በዚህ ሁኔታ የቤተሰቡ ኑሮ በመናጋቱ ፕሮፌሰር አስራት ከትምህርት ገበታቸው እርቀው ተቀመጡ:: አያታቸው ከሶስት አመት ተኩል እስር በኋላ ተለቀው ወደአገራቸው ተመለሱ:: ወጣቱ አስራትም ከአያታቸው ጋር ወደትውልድ አገራቸው አዲስ አበባ እንደ ገና ተመልሰው መጡ:: ነፃነት ተመልሶ አንድ አመት ከተቆጠረ በኋላ 1934 .. በተፈሪ መኰንን /ቤት ዘመናዊ ትምህርት መማር ቀጠሉ:: 1935 .. የትምህርት ዘመን ከክፍላቸው ከሁ ተማሪ የላቀ ውጤት ለማስመዝገብ በመቻላቸው ተሸለሙ:: በሁለቱ ዓመታት የተማሯቸው ትምህርቶች የከፍተኛ ትምህርት ለመከታተል እንደቅድመ ዝግጅት የሚቆጠሩ ስለነበሩ አመት ግብፅ አሌክስሣንደሪያ ሄደው ቪክቶርያ ኮሌጅ በሚባለው ከፍተኛ የትምህርት ተቋም ገቡ:: በመጀመሪያው ግማሽ ወሰነ-ትምህርት ባስመዘገቡት ከፍተኛ ውጤት የተነሳ ወደሁለተኛ ደረጃ እንዲሸጋገሩ ተደረገ:: በግብፅ-አሌክሣንድሪያ የሚሰጠውን ትምህርት ለአምስት ዓመታት ተምረው በጥሩ ውጤት እንዳጠናቀቁ ወደ እንግሊዝ አገር ተጉዘው ስኮትላንድ ውስጥ በሚገኘው ኤዳንብራ ዩኒቨርስቲ በመግባት በህክምና ትምህርታቸውን ቀጠሉ:: ለስድስት ዓመታት የሚሰጠውን ትምህርት ተምረው እንዳጠናቀቁ ለአንድ ዓመት በየሆስፒታሉ ልምምድ አድርገው ንድፈሃሣብን ከተግባር ያጣመረ ልምድ በማካበት በ1947 .. የዶክትሬት ዲግሪ ተቀብለው ወደ አገራቸው ተመለሱ::

  1948 .. በልዕልት ፀሐ ሆስፒታ ራቸውን ከመጀመቸው በፊት ከቀዳማዊ ኃይለሥላሴ ፊት ቀርበው የሚከተለውን መመሪያ መቀበላቸውን መጋቢት 11 ቀን 1991 .. የታተመው "አንድነት" ጋዜጣ ዘግቧል:: "እስከዛሬ የህክምና ትምህርት ተምረህ አገርህንና ወገንህን እንድታገለግል በማለት እኛ በበኩላችን የተቻለንን ያህል ደክመናል:: አሁን ደግሞ የድካማችንን ፍሬ የምንቀበለው ካንተ ነውና በርትተህ በተማርከው ትምህርት አገርህንና ወገንህን እንድታገለገል እግዚአብሄር ዳህ የሚል ነበር:: ፕሮፌሰር አስራት ከዚህ በኋላ በልዕልት ፀሐይ ሆስፒታል (በአሁኑ ጦር ኃይሎች) ለአምስት ዓመታት አገልግሎት ከሰጡ በኋሳ እንደገና ወደእንግሊዝ አገር ሄደው ሮያል ኮሌጅ ኦፍ ሰርጀንስ በቀዶ ህክምና ልዩ ትምህርት ተምረው ተመለሱ:: ፕሮፌ ሰር አስራት በጠቅላላው ለሠላሣ አምስት ዓመታት በልዕልት ፀሐይ እና በጥቁር አንበሳ ሆስፒታሎች በህክምና በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ደግሞ በመምህርነት ያለ እረፍት አገልግለዋል:: ከሙያ ባልደረቦቻቸው አስተያየት ለመረዳት እንደሚቻለው ፕሮፌሰር አስራት በቀዶ ህክምና ተግባራቸው ተወዳዳሪ የላቸውም ከሚባሉ ኢትዮጵያውያን አንዱ ነበሩ:: ልጅ ሚካኤል እምሩ ግንቦት 1992 .. ታትሞ ለወጣው "ምኒልክ ̈ መፅሄት በሰጡት ቃለ-መጠይቅ ፕሮፌሰር አስራት በባህሪያቸው ሚዛናዊ፣ በትምህርታቸው ጐበዝ እና በአጠቃላይ ብዕናቸው የተሟሉ ሆነው እንዲያድጉ በመቅረፀ ረገድ ሃኪም ወርቅነህ እሸቴና የእናታቸው አባት ቀኛዝማች ወረደቃል ትልቅ ድርሻ እንደነበራቸው መስክረዋል። 

  በመማር ማስተማሩም ዘርፍ ብዙ ጥናቶችን ከማበርከታቸውም በላይ በቀዽሞው የቀዳማዊ ኃይለሥላሴ ዩኒቨርሲቲ የመጀመሪያው ኢትዮጵያዊ የህክምና ፋካልቲ ዲን በመሆን ሠርተዋል፡፡ የህክምናውን ዘር በተመለከተም መንግሥት በሚያወጣቸው ሊሲዎች ሁሉ ግንባር ቀደም ተዋናይ በመሆን አገልግለዋል:: የህክምና ዳይሬክተር በነበሩበት ጊዜ የልዕልት ፀሐይ ሆስፒታል እንዲሰፋ እንዲናከር አድርገዋል:: ፕሮፌሰር አስራት 1970ዎቹ ወደመጀመሪያ የአገር ድንበር ለማስከበር በሰሜንና ምሥራቅ የዘመተውን ሠራዊት በህክምና ለመርዳት አብረው ዘምተዋል:: እንደ አንድ ተዋጊ ወታደርም በምሽግና በድንኳን ውስጥ ተቀምጠው በሞትና በህይወት መካከል የሚገኙ ቁስለኞችን በማከም ህይወታቸውን ታድገዋል:: የመንግሥት ለውጥ ከተደረገበት 1983 .. አንስቶ ፕሮፌሰር አስራት ብዙ ፖለቲካዊ ችግሮችን ለመጋፈጥ ተገደዋል:: በሰኔ ወር በተካሄደው የሽግግር ወቅት ቻርተር ኮንፈረንስ አዲስ አበባ ዩኒርሲቲን በመከል በስብሰባው ላይ በመገኘት አገሪቱን ይበጣጥሳል በሚል በቻርተሩ የፀደቁ ድንጋጌዎችን በይፋ ተቃውመዋል:: ከዚያው ዘመን መጨረሻ አንስቶ በአማራ ተወላጆች ላይ ከሥራና ከመኖሪያ አካባቢያቸው መፈናቀል፣ የንብረት ዝርፊያ፣ ስደት እና የጅምላ ፍጅት በተለይም በሀረር፣ በአርሲና በወለጋ ተባብሶ በመቀጠሉ / አልማዝ በሚባሉ ሴት አማካኝነት የዓላማ ደጋፊዎቻቸውን በማሰባሰብ የመላው ዐማራ ህዝብ ድርጅትን (መዐህድን) መሠረቱ:: የድርጅቱም ፕሬዝዳንት ሆኑ:: "በዚች አገር ውስጥ በድህነት ጠርዝ ላይ እየኖረ፣ በየአመቱ በርሃብ አለንጋ እየተገረፈ፣ የለውጥ አየር በነፈሰ ቁጥር ሊፈናቀል፣ ሊዘረፍና ሊጨፈጨፍ አይገባም፤ በአማራ ላይ ወንጀል የፈፀሙትም ለፍርድ ሊቀርቡ ይገባል" በሚል አቤቱታ ለሽግግር መንግሥቱ ማቅረብ ቀጠሉ:: ፕሮፌሰር አስራት "የአማራ ህዝብ የአስተዳደር በደል ደረሰበት፣ ተሰደደ፣ እጅ እግሩ ታስሮ በቤት ውስጥ ተቆልፎበት በእሣት ተቃጥሎ እንዲሞት ተደረገ፣ ከነነፍሱ ገደል ውስጥ ተወረወረ፣ ሴቶች ተደፈሩእያሉ በድርጅታቸው አማካኝነት አቤቱታ በሚያቀርቡ ጊዜ ሁለት አይነት ቅሥቀሳ ተከፍቶባቸው ነበር:: አንደኛው ወገን "ትምክህተኛ፣ ነፍጠኛ፣ ጦረኛና የድሮ ሥርዓት ናፍቂ" የሚል ቅጥያ ሰጥቶ የማጥላላት ዘመቻ ከፈተባቸው:: ሌላው ወገን በተለይም ደግሞ "ተማርን ባይእና መስሎ ማደር ይቻላ" የሚሉ የአማራ ተወላጆች የረባ ጐጆ የሌለው፣ ከደበሎ ለባሽነት ያልወጣ፣ ዓለም ለደረሰበት ስልጣኔ በእጅጉ ባይተዋር የሆነው የአማራ ህዝብ የጐ ጥላቻ ባደረባቸው ፖለቲከኞች ቁም ስቅሉን እያየ መሆኑን አይተው እንዳላየ ሰምተው እንዳልሰማ በመምሰል ኖረው አሁን "አስራት የወያኔን አላማ ለማስፈፀም በጐሳ ላይ የተመሰረተ የፖለቲካ ድርጅት አቋቋመእያሉ እንደትልቅ ኃጢያት በመቁጠር የውግዘት ቅስቀሳ ማድረግን ቀጠሉ:: በሁለቱ ኃይሎች ግፊት ሲደረግባቸው ከቆዩ በኋላ 1986 .. ደብረብርሃን ላይ የመዐህድ አባላትና ደጋፊዎች በተሰበሰቡበት ለጦርነት የሚያነሳሳ ንግግር አድርገዋል የሚል ክስ ቀርቦባቸው ሰኔ 10 ቀን 1986 .. የእስራት ቅጣት ተፈረደባቸው:: በጥቅምት ወር 1989 .. ታትሞ የወጣው "ኢትዮጵ" ጋዜጣ ከአቀረበው ዘገባ ለመረዳት እንደሚቻለው ፕሮፌሰር አስራት ከታሰሩበት ከሰኔ 10 ቀን 1986 እስከ 1989 .. ድረስ ባለው ጊዜ ውስጥ 150 ጊዜ ፍርድ ቤት እንዲቀርቡ ተደርገዋል:: ፕሮፌሰር አስራት ከታሰሩ ጊዜ በፊትና በኋላም ቀጥለው የተዘረዘሩት የድርጅቱ የአመራር አባላት የእስራት ቅጣት አጋጥሟቸዋል ::

  1. ሻለቃ ጌታቸው መንግሥቴ (ዋና ፀሐፊ)

  2. አቶ ወንድአየሁ ካሣ (የአዲስ አበባ መዐህድ ሰብባቢ)

  3. ኩሎኔል ጌታሁን እጅጉ (የህዝብ ግንኙነት ሃላፊ )

  4. አቶ ዓሊ እንድሪስ (የአስተዳደር ዘርፍ ሃላፊ)

   5. አቶ ግርማ ዕንቁሥላሴ (የሂሣብ ሹም) ነበሩ::

  ፕሮፌሰር አሰራት ለአምስት አመታት ያህል በእስር ቤት እንደቆዩ በጠና በመታመማቸው የመላ ዐማራ ህዝብ ድርጅት፣ የአለም ሰብአዊ መብት ተከራካሪዎችና ህዝቡም ባቀረቡት ተደጋጋሚ ጥያቄና ባሳደሩት ጫና እንደታሰሩ ከሚታከሙበት ሆስፒታል ተፈተው ለከፍተኛ ህክምና ወደ አሜሪካን አገር ሄዱ:: ፕሮፌሰር አስራት ወደ አሜሪካን በሚጓዙ ጊዜ የጤንነታቸው ችግር ተባብሶ ስለነበር በአውሮፕላን ላይ እርዳታ የሚሰጧቸው የህክምና ያተኞች አብረዋቸው ተጉዘዋል:: ፕሮፌሰር አስራት 1991 .. አሜሪካን አገር በህክምና ላይ እንዳሉ አርፈው አስከሬናቸው ወደኢትዮጵያ መጥቶ ቅድስት ሥላሴ ጐን በሚገኘው በባለወልድ ቤተ-ክርስቲያን ቅጥር ግቢ ውስጥ እንዲያርፍ ተደረገ:: ፕሮፌሰር አስራት ወልደየስ የሁለት ወንዶች ልጆች አባት እንደሆኑ መረጃዎች ይጠቁማሉ::

   ምንጭ:- ታሪካዊ መዝገበ-ሰብ  

   

 • loader Loading content ...
 • @አማን   3 weeks ago
  Stop waiting for the perfect moment. Take the moment you've and make it perfect.

  / ባፈና የአፄ ምኒልክ ሁለተኛ ባለቤት ናቸው:: ይህም ከወ/ አልጣሽ ቴዎድሮስ በኋሏ ከእቴጌ ጣይቱ በፊት ያገቧቸው በእድሜ ብዙ የሚበልጧቸው ነበሩ:: / ባፈና ትውልዳቸው ሰሜን ሸዋ ውስጥ በመርሐቤቴ አውራጃ ነው:: አፄ ምኒልክን ከማግባታቸው በፊት ካገቧቸው ከመጀመሪያ ባለቤታቸው ብዙ ልጆችን ወልደው ድረው ነበር:: / ባፈና ልጆቻቸውን ከትልቅ የሥልጣን ደረጃ የማድረስ ህልም ስለነበራቸው ብዙዎቹን የዳሯቸው ለትልልቅ መኳንንት ነበር:: ለምሣሌ አንደኛዋ ልጃቸውን የአፄ ምኒልክ የአጐት ልጅ ለሆኑት ለደጃዝማች መሸሻ ሰይፉ ሲድሩ፣ ሌላዋን ደግሞ ለወሎው ገዥ ለራስ (በኋላ ንጉሥ) ሚካኤል ድረዋል:: / ባፈና የአፄ ምኒልክ ባለቤት ይሁኑ እንጂ በፖለቲካዊ አስተሣሰብ ግን ምንጊዜም ከንጉሠ-ነገሥቱ በተቃራኒ ይቆመው እንደነበር በታሪክ ተፅፏል:: ተክለፃዲቅ መኩሪያ ከአፄ ቴዎድሮስ እስከ ቀዳማዊ ኃይለሥላሴ በሚለው መፅሃፍ የወ/ ባፈናንና የአፄ ምኒልክን ቅራኔ እንዲህ ሲሉ ገልፀውታል:: « .... / ባፈና ከአፄ ምኒልክ ከተጋቡ በኋላ እንደሌሎቹ ሴቶች ለባላቸው ክብር ከመቅናትና ባላቸውን በማገልገል ፈንታ ብዙ ጊዜ ከአፄ ምኒልክ ባላንጦች ከነደጃዝማች ሰይፉ ከአማቻቸው ይማም መሃመድ ጋራ ውስጥ ውስጡን እየተላላኩ በባለቤታቸው በአፄ ምኒልክ ላይ አድማ ይሠሩባቸው ነበር:: እንደዚሁም በአፄ ዮሐንስ ግጭት በመጣ ጊዜ አሳባቸውን ወደ አፄ ዮሐንስ እያደረጉ ይስማሙ ነበር ይባላል:: ይሁን እንጂ አፄ ምኒልክ ይኸንንም ቢያውቁ ፍቅር የማያሸንፈው ነገር አይገኝምና ክህደታቸውንና አድማቸውን በፍቅር ምክንያት እየታገ አብረው ይኖሩ ነበር:: በኋላ ግን / ባፈና ይኸንኑ ያድማ ነገር እየቀጠሉ ስለሄዱ 1875 .. በጭራሽ ፈቷቸው» ብለዋል:: የውጭ የታሪክ ፀሐፊዎች እንደገለፁት / ባፈና 1869 .. በአፄ ምኒልክ ላይ ተቀስቅሶባቸው በነበረው አመፅ ላይ ተካፋይ ነበሩ:: ፍላጐታቸው ሁሉ የልጃቸው ባለቤት ደጃዝማች መሸሻ ሰይፉ ሥልጣኑን ጠቅልለው እንዲይዙ ነበር:: / ባፈና አፄ ምኒልክ ከፈቷቸው በኋላ ተፈቅዶላቸው በቤተ-መንግሥቱ ቅጥር ግቢ ይኖሩ ነበር:: እቴጌ ጣይቱን በሃይማኖታዊ ሥርዓት እንዳገቡ ከቤተመንግሥት ወጥተው ሲኖሩ ሳለ 1889 .. በድንገት ታመው ሞቱና በደብረሊባኖስ ገዳም ሥርዓተ-ቀብራቸው ተፈፀመ::   

  ምንጭ:- ታሪካዊ መዝገበ-ሰብ 

 • loader Loading content ...
 • @አማን   3 weeks ago
  Stop waiting for the perfect moment. Take the moment you've and make it perfect.

  ነጋድራስ ተሰማ እሸቴ ከአባታቸው ከአቶ እሸቴ ጉቤ እና ከእናታቸው ከወ/ሮ ወለተያስ ሀብቱ ሐምሌ 20 ቀን 1869 ዓ.. ሰሜን ሸዋ ውስጥ በምንጃር ወረዳ ልዩ ስሙ ቀርሾ አጥር በሚባል ሥፍራ ተወለዱ:: አባታቸው አቶ እሸቴ ጉቤ ከጎጃም እና ከወሎ አማራ ሣይንት ይወለዳሉ:: እናታቸው ወ/ሮ ወለተያስ ሀብቱ ደግሞ ቡልጋ ውስጥ የመስኖ ማርያም አካባቢ ተወላጅ ናቸው:: የነጋድራስ ተሰማ አባት የቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ ኦባት የልዑል ራስ መከንን ወልደሚካኤል ጭፍራ ነበሩ:: አፄ ምኒልክ 1879 .. ሀረርን ከውጭ ወራሪዎች ተከላክለው ከተማዋን ለመቆጣጠር በሚል የጦር አለቆቻቸውን ይዘው ወደ ሥፍራው በሄዱ ጊዜ ልዑል ራስ መኰንን በቡልጋና አካባቢዋ የሚገኙ የሠራዊት አባላትን ይዘው ተጓዙ:: ልዑል ራስ መኰንንን ተከትለው ከሄዱት አንዱ የነጋድራስ ተሰማ አባት እሸቴ ጉቤ ነበሩ:: አካባቢው ከተረጋጋ በኋላ ቤተሰባቸውን ወደዚያው ስለወሰዱ ነጋድራስ ተስማ 10 አመት እድሜያቸው አንስቶ ያደጉት በሀረር ከተማ ነው:: ብዙም ሳይቆዩ አባታቸው አቶ እሸቴ ሀረር ላይ እንዳሉ በመሞታቸው ነጋድራስ ተሰማ አፄ ምኒልክን ተከትለው ወደአዲስ አበባ በመምጣት በንጉሠ-ነገሥቱ ቤተ-መንግሥት እየተማሩ መኖር ቀጠሉ:: በቤተ-መንግሥት እድገታቸውና ኑሯቸው ከሙዚቃ በተጨማሪ የሥዕል ያንም አጥንተው ስለነበር በሚሰሩት ሥራ ሁሉ በአፄ ምኒልክ ዘንድ ተወዳጅነትን ለማትረፍ ቻሉ:: ሰምና ወርቁ ተሰማ እሸቴ በሚለው መፅሃፍ እንደተብራራው 1900 .. ወደውጭ አገር ሄደው የመማር እድል አጋጠማቸው:: ሆልስ የተባለ ጀርመናዊ በኢትዮጵያ የሚያደርገውን ቆይታ ጨርሶ ወደአገሩ ሲመለስ ለስንብት ከአፄ ምኒልክ ፊት በቀረበ ጊዜ ወደአገሩ ወስዶ የሚያስተምራቸው ሶስት ወጣቶች እንዲሰጡት ጠየቀ:: አፄ ምኒልክም ነጋድራስ ተሰማ እሸቴን በጥሩ ሰዓሊነታቸው ያመሰግኗቸው ነበርና « ተሰማ እሸቴ እጀ ብልህና ነውና መኪና መንዳትና መጠገን እንዲማር እሱ ይሂድ» ብለው ፈቀዱላቸው:: ነጋድራስ ተሰማም ወደጀርመን አገር ሄደው የአውቶሞቢልን አሠራር አጠኑ:: በዋናነት የሜካኒክነትና የሾፌርነት ቢያጠኑም በሙዚቃም ብዙ ስራ ለመሥራት ቻሉ:: ነጋድራስ ተሰማ መሰንቆ መምታትና ዜማ አወጣጥን ከአባታቸው ተምረው ስለነበር ጀርመን አገር ሄደው በቆዩበት ጊዜ "ሂስ ማስተር ቮይስ ̈ ከሚባለው ኩባንያ ጋር በመዋዋል 17,000 የጀርመን ማርክ ተከፍሏቸው በዘለኛና በመዲና ላይ ያተኮሩ 17 ዲስኮችን ለማስቀረፅ ቻሉ:: በህይወት ታሪካቸው ላይ ከተፃፈው ለመረዳት እንደሚቻለው እነፈረደ ጐላ፣ ንጋቷ ከልካይና ተሻሰ መንግሥቱ 1925 .. ዲስኮችን ለማስቀረፅ እስከቻሉ ድረስ 20 ዓመታት የአማርኛ ዲስኮች በአዲስ አበባና በሌሎች ትልልቅ ከተሞችም ይደመጡ የነበሩት የነጋድራስ ተሰማ እሸቴ ብቻ ነበሩ:: ከሙዚቃ ችሉታቸው እኩል ነጋድራስ ተስማ እሽቴ በግጥም ችሎታቸው እጅግ የተደነቁ ናቸው :: ብዙዎቹ ግጥሞቻቸው የሰምና የወርቅ ፍችዎችያሏቸው፣ የሚያስተላልፉት መልዕክት ንካራ እና በአፃፃፍ ቴክኒካቸ የተዋጠላቸው ኛቸው:: ብዙዎቹ የነጋድራስ ተሰማ እሸቱ ጥሞች በወቅታዊ ማህበራዊና ፖለቲካዊ ጉዳዮች ላይ የተመሰረቱ ሲሆኑ የተነት ባህሪ ይንፀባረቅባቸዋል። ቀጥለው የተጠቀሱት ስት ምሣሌዎ የነጋድራስን የግጥም ርዕሠ-ጉዳዮችና የግጥሞቹን ደረጃዎች ሊያመለክቱ ይችላሉ፡፡

  1. የአገሬ ወንዞች መጥኔውን ይስጣችሁ፣

  ክረምት ሲመጣ እየጨነቃችሁ፣

  ዋጋ አትቀበሉ አስታዋሽ የላችሁ፣

  ከአዳም ጀምሮ እስከአሁን እድሜያችሁ፣

  ሰውንም ከብቱንም እቃ እንዳጋዛችሁ፣

  የማትታመኑ በዋል ፈሰስ ናችሁ፣

  ለውቂያኖስ ዓሣ እያስረከባችሁ፣

  አንድ እንኳ አታመጡ ወዲህ መልሳችሁ ::

  2. አገሬ ታውቂያለሽ እንደምንወድሽ፣

  በታመምሽ ጊዜ ተዘግቶ ጆሮሽ፣

  በነፃነት ፀጋ እስክትፈወሽ፣

  በአራቱ ማእዘን ዓለም ሲጠራሽ፣

  ያምላክ ውለታ ምነው ማጥፋትሽ፣

  አትናገሪም ወይ ተሰማ ብለሽ?

  3. የወዲያ ሰዎች ክፋታቸው፣

  እሬሳ አጋድመው መብላታቸው፣

  የሸዋ ሰው መልካም፣

  ወዳጁን ሳይቀብር አይበላም::

  ነጋድራስ ተሰማ እሸቴ በአፄ ምኒልክ፣ በልጅ ኢያሱ፣ በንግሥት ዘውዲቱና በቀዳማዊ ኃይለሥላሴ መንግሥታት ሲኖሩ በመኪና መካኒክነት፣ ሹፌርነት፣ በሥዕል፣ በሙዚቃና በሌሎችም ተጓዳኝ ያዎች የሚታወቁትን ያህል በቀልድ አዋቂነታቸውም የተደነቁ ነበሩ:: ነጋድራስ ተሰማ እሸቴን በቅርብ እናውቃለን ከሚሉ ወገኖች አስተያየት ለመረዳት እንደሚቻለው ከወቅታዊ ሁኔታ የሚያመነቸው ቀልዶች ከአለቃ ገብረሃና ቀልዶች ጋር ተመሳሳይነት አላቸው:: ነጋድራስ ተሰማ በህይወት ዘመናቸው ከቀለዷቸውና ሰምና ወርቁ ተሰማ እሸቴ በሚባለው መፅሃፋቸው ውስጥ ከታተሙት አሽሙሮች መካከል ሁለቱን ቀጥሎ እንመልከታቸውና ምላተ- ድለታቸውን እንመርምር።

  1. ነጋድራስ ተሰማ አንድ ጊዜ ከመኳንንት ጋር ቁጭ ብለው ሲጫወቱ «አሁን ሁላችሁም በሆዳችሁ የምታስቡትን አውቃለሁ» በማለት ተናገሩ:: መኳንንቱም አያውቁም ሲሉ ተከራከሯቸው። ከመኳንንቱ አንዱ «አያውቁም» ሲሉ በመቶ ብር ተወራረዷቸው:: እሳቸውም «ሁላችሁም ለንጉሡ ነው የምታስቡት በሆዳችሁ ያለው ይህ ነው» ብለው ተናገሩ:: በዚህ ጊዜ ደፍሮ  ̈አይደለም ̈ ብሎ የሚከራከር በመጥፋቱ ውርርዱን ረቱ።

  2. ንጉ ባሉበት የኢላማ ተኩስ ሲደረግ እልፍኝ አስከልካዩ በመጀመሪያ ጥይት ተኩሶ ዒላማውን መታ:: በዚህ ጊዜ ነጋድራስ ቀስ ብለው «ባንዴ ቡን አደረጋት» ሲሉ ተናገሩ:: የእልፍ አስኮልካዩ በጠላት ዘመን ባንዳ ስለነበረ ያንን ለመንካት ሲሉ የተናገሩት ጣምራ ትርጉም ያለው ንግግር ነበር::

  ነጋድራስ ተሰማ እሸቴ በልጅ ኢያሱ ዘመን ጉልህ ፖለቲካዊ ተሣትፎ ነበራቸው:: አብዛኛው በአዲስ አበባ ከተማ የነበረው የመሃል አገሩ መኳንንት ልጅ ኢያ ከሥልጣን ለማውረድ በተሰለ ጊዜ ሁሉ ነጋድራስ ተሰማ የልጅ ኢያሱ ታማኝ ባለሟል ሆነው እስከ መጨረሻው ዘልቀዋል:: ልጅ ኢያሱ ከሥልጣን ወርደው ደጋፊዎቻቸውም በየጦር ሜዳው ድል ከሆኑ 1909 እስከ 1916 .. ለሰባት አመታት ጅማ ውስጥ በግዞት ተቀምጠው ቆዩ:: ከግዞት ሲመለሱ አዲስ አበባ ውስጥ ራስ መኰንን ድልድይ አጠገብ ካለው ቤትና ቦታቸው በቀር ያለው ንብረታቸው ሳይመለስላቸው እንደ ተወረሰ ቀረ:: ከውጭ አገር በልጅ ኢያሱ ፈቃድ ጠበንጃና ጥይት እያስመጡ ይነግዱ ስለነበር በታሰሩ ጊዜ የጉምሩክ መሥሪያ ቤትና አንድ ግሪክ ነጋዴ ቤት ያስቀመጡትን ግምቱ 300,000 ብር የሚያወጣ ጠበንጃና ጥይትም ሳይመለስላቸው ቀረ:: በጣሊያን የወረራ ዘመን በተለይም ከየካቲት 12 ቀን 1929 .. አንስቶ በአዲስ አበባ ሲኖሩ ቆይተዋል:: ጣሊያን እሳቸው የልጅ ኢያሱ ደጋፊና የቀዳማዊ ኃይለሥላሴ ተቃዋሚ ናቸው ብሎ ስላሰበ አልተቃወማቸውም ነገር ግን በመጨረሻ ጣሊያን በሰሜን ሸዋ ከሚንቀሳቀሱት ከነራስ አበበ አረጋይ ጋር እንዲያስታርቁት ሽምግልና ልኳቸው ነበር ግን አርበኛውን የሚጠቅምና ጠላትን የሚጐዳ ድርድር አድርገው መመለሳቸው ስለታወቀ ለተወሰነ ጊዜ በግዞት እንዲቆዩ አደረጋቸው:: ነጋድራስ ተሰማ እሸቴ በዚህ ጊዜ ጠላትን የሚቃወሙ ብዙ ግጥሞችን ገጥመዋል:: ቀጥሎ ያለው ግጥም ለምሣሌ በትረመንግሥቱን የጨበጠውን ጣሊያንን የማይገባ ምግባር የሚተች ነው::

  እገበያ መሀል ፈስ እያንዛረጡ፣

  አውራ ጐዳና ላይ ዳቦ እየገመጡ፣

  ቤተ-ክርስቲያን ውስጥ ትምባሆ እየጠጡ፣

  እንዲህ ነው ወይ ጣልያን አልጋ ላይ ሲወጡ። 

  መጋቢት 28 ቀን 1933 ዓም. የኢትዮጵያ አርበኞችና የእንግሊዝ ወታደሮች በቅንጅት ተዋግተው አዲስ አበባን ከጣልያን ይዞታ እንለቀቁ የእንግሊዝ ጦር አዛዥ ነጋድራስ ተሰማ እሸቴንና ባላምባራስ ግርማ ያየህይራድን የኢትዮጵያን ባንዲራ ይዘው ከደጃዝማች ገረሱ ዱኪ ዘንድ ሄደው የሚማረኩት ጣሊያኖች ሁሉ በጦር ምርኮኞች ሥርዓት እንዲይዙ የሚል መልእክት እንዲያደርሱ ላኳቸው:: ደጃዝማች ገረሱ ዱኪ ግን እነነጋድራስ ተሰማ እሸቴን ከጣሊያን ጋር ኖራችኋል በማለት አሠሯቸው፡፡ ወር ባልሞላ ጊዜ ውስጥ ባላምባራስ ርማ ሲፈቱ ነጋድራስ ተሰማ ወሊሶ ውስጥ ስድስት አመታት በግዞት እንዲቀመጡ ተደረጉ። ከግዞት ነፃ ከወጡ በኋላ ልዩ ልዩ ሥራዎችን ሲሠሩ ኖሩ:: 1952 .. የአየር ኃይል ፓይለት የነበረው ልጃቸው መቶ አለቃ ኤልያስ ተሰማ በአውሮፕላን አደጋ በአሥመራና በምፅዋ መካከል በሞተ ጊዜ በድንጋጤ በአንጐላቸው ውስጥ ደም በመፍሰሱ የልሣን ማዕከላቸው ጉዳት ሊደርስበት በቃ:: ለአምስት አመታት ያህል በህክምና ሲረዱ ቆይተው ጥቅምት 3 ቀን 1957 .. በተወለዱ 87 ዓመታቸው ከዚህ አለም በሞት ተለዩ:: የጋብቻ ህይወታቸውን በተመለከተ ነጋ ድራስ ተሰማ እሸቴ የመጀመሪያ ጋብቻቸውን የፈፀሙት የአፄ ምኒልክ የአጐት ልጅ ከሆኑት / ላቷ ገብረሥላሴ ጋር ሲሆን ታዋቂውን የእስፖርት ሰው ይድነቃቸው ተሰማን ጨምሮ ሰባት ልጆችን አፍርተዋል:: ከውጭ የወለዱትን ጨምሮ የነጋድራስ ተሰማ እሸቴ ልጆች የሚከተሉት ናቸው።

  1. አይናቸው ተሰማ               5. ይድነቃቸው ተሰማ

  2. ታምሩ ተሰማ                   6. አዘነች ተሰማ

  3. መታሰቢያ ተሰማ              7. ኤልያስ ተሰማ

  4. የምሥራች ተሰማ              8. ማሚቴ ተሰማ ናቸው ::

  ነጋድራስ ተሰማ እሸቴ ከአፍ መፍቻ ቋንቋቸው ከአማርኛ ሌላ ከአገር ውስጥ ኦሮምኛና አደርኛን፤ ከአገር ውጭ ፈረንሣይኛን፣ ጣሊያንኛን፣ ጀርመንኛንና አረብኛ ቋንቋዎችን አጣርተው ይናገሩ እንደ ነበር ታሪካቸው ያስረዳል::


   ምንጭ:- ታሪካዊ መዝገበ-ሰብ 

 • loader Loading content ...
 • @አማን   3 weeks ago
  Stop waiting for the perfect moment. Take the moment you've and make it perfect.

  እቴጌ ምንትዋብ የአፄ በካፋ ባለቤት እና የአፄ ኢያሱ ዳግማዊ (የቋረኛ ኢያሱ) እናት ናቸው:: እቴጌ ምንትዋብ 1700 .. አካባቢ ቋራ ውስጥ ከአባታቸው ከደጃዝማች መንበሩ ከእናታቸው ከወ/ እንኮዬ ተወለዱ:: በታሪክ ፀሐፊዎች እንደሚወሳው ከሆነ እቴጌ ምንትዋብ ወለተጊዮርጊስ በሚለው የክርስትና ሥማቸውና ብርሃን ሞገሳ በሚለው የክብር ስሞቻቸውም ይታወቃሉ:: አፄ ኢያሱ ዳግማዊ ወይም ብርሃን ሰገድ ኢያሱ በሚሉ ስመ-መንግሥቶች የሚታወቁት ልጃቸው በነገ ጊዜ እናታቸው እቴጌ ምንትዋብን በቀኝ እጃቸው ዙፋን ላይ አስቀምጠው የወርቅ ዘውድ አደረጉላቸው:: ባለቤታቸው አፄ በካፋ መስከረም 11 ቀን 1723 .. በድንገት ከዚህ ዓለም በሞት ሲለዩ ታዳጊው ልጃቸው ኢያሱ ዳግማዊ (የቋረኛ ኢያሱ) ነገ:: በዚህ ጊዜ እውቀትና በህዝቡም ዘንድ ተደማጭነት የነበራቸው እቴጌ ምንትዋብ ንግሥት ተብለው ከልጃቸው ጐን ተቀመጡ:: ንግሥት በተባሉበት ቀን የወርቅ አክሊል ደፍተው እና የወርቅ ጫማ ተጫምተው «ጐማ» በሚል መጠሪያ በሚታወቀው በቅሏቸው ላይ ተቀምጠው ወደአደባባይ በወጡ ጊዜ ህዝቡ የሚከተለው ዘፈን በመዝፈን የደስታቸው ተካፋይ ሆነላቸው ::

  አሁን ወጣች ጀምበር፣ ወጣች ጀምበር፣

  ተሸሽጋ ነበር ::

  አሁን ወጣች ጨረቃ፣ ወጣች ጨረቃ፣

  የምትለን ፍርድ ይብቃ::

  ደስ ይበልህ ዘመድ፣ ይበልህ ዘመድ፣

  ከነገሠች በዘውድ::

  ደስ ይበልህ ባለጌ፣ ይበልህ ባለጌ፣

  ከነገሠች እቴጌ::

  ደስ ይበልህ ንደር፣ ይበልህ ንደር፣

  ቀድሞ ከፍቶህ ነበር ::

  ዘውዱን ይጫኑ እንጂ ቅብዓ-ዘይቱን ግን እንዳልተቀቡ በዘመኑ የነበሩ የውጭ የታሪክ ሰዎች የመዘገቡት ታሪክ ያስረዳል:: ልጃቸው አፄ ኢያሱ "ቋረኛ ኢያሱ" የሚለውን መጠሪያ ያገኙት የእናታቸውን የእቴጌ ምንትዋብን የትውልድ ሥፍራ በሥልጣኑ ዙሪያ የነበሩትን ከቋራ የመጡ ዘመዶቻቸውን ለማስታወስ መሆኑ ይነገራል:: የአፄ ኢያሱ ዳግማዊ መንግሥት 24 ዓመታት በቆየበት ጊዜ የእቴጌ ምንትዋብ ተፅዕኖ እጅግ የላቀ እንደነበር የታሪክ ሰነዶች ያረጋግጣሉ:: እቴጌ ምንትዋብ በማዕከላዊ መንግሥት የሥልጣን ይዞታ ጠንካራ ይሁኑ እንጂ በምዕራብና በሰሜን በኩል ያለው የኢትዮጵያ ድንበር ግን በባዕዳን ወረራ ችግር ውስጥ የገባበት አጋጣሚ ነበር:: ይህም የታሪክ ክፍለ-ጊዜ ኢትዮጵያ ወደ ዘመነ መሣፍንት ትጓዝ የነበረበት ጊዜ ነው:: 

  በእቴጌ ምንትዋብ ዘመን የሴት ውበትና የአዕምሮ ብልህነት ተጣምረው ይገኙ ነበር የተባለበት ምክንያት በልጃቸው በኢያሱ ዳግማዊ ስም የመንግሥቱን ጉዳይ በሞግዚትነት ሲያካሂዱ በመቆየታቸው ነው:: በእቴጌ ምንትዋብ ልጅ (በቋረኛ ኢያሱ ዘመን) ራስ ሥሁል ሚካኤል የተባሉ በፖለቲካና በውትድርና ዝነኛ የሆኑ ሰው በትግራይ ተነስተው ነበር:: እኒህን መስፍን ህይወታቸውን በአደጋ በተረፈላቸው ዘዴ ከአልጋ ጋር እንዲቆራኙ አደረጉ። ራስ ሥሁል ሚካኤል ለመጀመ ሪያ ጊዜ በእምቢተኝነት ተከሰው ነበር:: በዚህ ጊዜ አፄ ኢያሱ በዘመቱባቸው ጊዜ ሰማያት በተባለው ከትልቁ አምባ ላይ ተከበው እጃቸውን ሰጡ:: በመጨረሻም ከዚያ የነበረውን ሀብት ሁሉ ለንጉ አስረከቡ:: አንዳንድ ፀሐፊዎች ሲፅፉ ደግሞ ከነበራቸው ሁብት ግማሹን ብቻ እንዳስረከቡ ገልፀዋል:: አድሮ ችግር እንደሚፈጠር የተረዱት እቴጌ ምንትዋብ ግን ልጃቸውን አስቴርን ለራስ ሥሁል ሚካኤል በመዳር ከልጃቸው ከአፄ ኢያሱ ጋር የነበረውን ቅራኔ ንዲሽር በማድረግ ከአልጋው ጋር ቁርኝት እንዲኖራቸው አደረጉ:: አንድ ጊዜ በንጉሡ በአፄ ኢያሱ ዳግማዊ ግቢ ግብዣ ተደርጐ ራስ ሥሁል ሚካኤል በብርሌ ሲጠጡ ያዩአቸው የእቴጌ ምንትዋብ ወንድም እና የሰሜን አገረ-ገዥ የሆኑት ራስ ወልደ ልዑል «ጌታዬ ምነው እንደማዕረገዎ በወርቅ ፅዋ የማይጠጡ» ይሏቸዋል:: የራስ ሚካኤልም መልስ «የኔ ወርቅ በሰማያት ነው» የሚል ነበር:: ሰማያት ራስ ሥሁል ሚካኤልና አፄ ኢያሱ ዳግማዊ የተጋጩበት ቦታ ነው:: ሁኔታውን እንዲያለዝቡ በእቴጌ ምንትዋብ የተመከሩት አፄ ኢያሱም አንድ የወርቅ ሲልኩላቸው በመያ ላይ «ሀብታቸውን በሰማያት የሚያከማቹ ብፁአን ናቸው» የሚል ፅሁፍ አፃፉበት:: ራስ ሚካኤል ደግሞ ከወርቁ ላይ ይህንኑ ፅሁፍ በሌላው ዋው ጐን አስቀረፁት:: ይህን ፅዋ ባለቤታቸው / አስቴር ትግራይ ውስጥ ለሚገኘው ለቅዱስ ሚካኤል ቤተ-ክርስቲያን እንደሰጡት የፃፉ የታሪክ ሰዎች አሉ::

  እቴጌ ምንትዋብ ከሰሜናዊ ኢትዮጵያ በኩል የአስተዳደሩን ሰላም በዚህ መልኩ ሲያስጠብቁት ከደቡባዊ ምሥራቅ በኩል ደግሞ ልጃቸው አፄ ኢያሱን ከነገደ ኤጃው ከተወለደችው ውቢት ከተባለች ወጣት ልጃገረድ ጋር አጋቧቸው:: የወጣቷን ክርስትና ስምም ቤርሳብህ አሏት:: በዚያም ጋብቻ ልጃቸው አፄ ኢዮአስ ስመ-መንግሥታቸውን አዲያም-ሰገድ ሣልሣዊ ተብለው አልጋውን ወረሱ:: በኒህ በልጅ ልጃቸው ዘመነ-መንግሥትም የእቴጌ ምንትዋብ ሥልጣን ትልቅ ተፅዕኖ ነበረው:: በአፄ ኢዮአስ ዘመን ራስ ማርያም ባርያ ጦርነት አስነስተው የአፄ ኢዮአስን ወታደሮች ድል ባደረጉ ጊዜ በእቴጌ ምንትዋብ ምክር ራስ ሥሁል ሚካኤል የአፄ ኢዮአስን ወገን በመደገፍ ራስ ማርያም ባርያን በውጊያ አሸንፈው ማረኳቸው:: አፄ ኢዮአስ ከሞቱም በኋላ እቴጌ ምንትዋብ አላረፉም:: ከኃይለኛው አማቻቸው ከራስ ሥሁል ሚካኤል ጋር ለመወዳደር ሞከሩ:: ከአፄ ኢዩአስ ሞት በኋላ ራስ ሥሁል ሚካኤል በአንድ ወገናቸው የአፄ ዮሐንስ ልጅ የሆኑትን አፄ ተክሃይማኖትን አንግሠው ወደ አክሱም ይዘዋቸው በሄዱ ጊዜ እቴጌ ምንትዋብም በፈንታቸው የኢዮአስን ልጅ ለማንገሥና በሥልጣን ለመቆየት ሞክረዋል:: 

  ሥርገው ሐብለሥላሴ በፃፉት የአማርኛ የቤተ-ክርስቲያን መዝገበ ቃላት በተባለው መፅሃፍ እንደተብራራው እቴጌ ምንትዋብ ብዙ አብያተ-ክርስቲያናትን አሠርተዋል:: ካሠሯቸው አብያተ-ክርስቲያን አንዱ የጐንደር ቁስቋምን በሺ ወቄት ወርቅ እንዳሰሩት ታሪካቸው ያስረዳል። በዚሁ በጐንደር ከተማ የሚገኘውን መጥምቁ ዮሐንስንና በጣና ሃይቅ በደቅ ደሴት ላይ ያለውን ናግራ ሥላሴን ያሰሩ እቴጌ ምንትዋብ ናቸው። ከዚያው ጣና ሃይቅ የሚገኘውን የደጋ እጢፋኖስ ቤተ-ክርስቲያንንም በዘመናቸው እድሳት እንዲያገኝ አድርገዋል:: በሃይማኖታዊ ተግባራቸው አንዳንድ ፀሐፊዎች ዳግማዊት እቴጌ እሌኒ በማለት ያመሰግኗቸዋል። የመጨረሻውን ህይወታቸውን ያሳለፉት በፆም በፀሎት ሲሆን የፅጌ ፆምም በእሳቸው ዘመን እንደተጀመረ ተፅፏል። እቴጌ ምንትዋብ በኢትዮጵያውያን የዘመን አቆጣጠር በ1767 ዓ.ም. ከዚህ ዓለም በሞት እንደተለዩ በዘመናቸው ካሠሯቸው ቤተ-ክርስቲያን አንዱ በሆነችው በቁስቋም ማርያም ተቀበሩ:: የእቴጌ ምንትዋብ ድባብ በህገወጥ መንገድ ከኢትዮጵያ ወጥቶ እንግሊዝ አገር ለንደን ከተማ በጨረታ ሊሸጥ ቀርቦ በኢትዮጵያ ኤምባሲ በኩል ተገዝቶ ወደኢትዮጵያ የተመለሰ ሲሆን አሁን አዲስ አበባ በብሄራዊ ሙዚየም ውስጥ ይገኛል።

   

  ምንጭ:- ታሪካዊ መዝገበ-ሰብ 

 • loader Loading content ...
 • @አማን   2 years ago
  Stop waiting for the perfect moment. Take the moment you've and make it perfect.

  ሳላይሽ የጦር መሣሪያ ግምጃ ቤት በ1890 ዓ..  ከአድዋ ድል በኋላ የተሰራ የአጼ ምኒሊክ የጦር መሣሪያ ግምጃ ቤቶች ስብስብ ነው:: የሚገኘውም ከደብረ ብርሃን ወደ አዲስ አበባ ባለው  መንገድ 54 ኪ. ሜትር ርቀት ላይ በምትገኝ ቦታ ልዩ ስሟ ኮረማሽ ከተማ ላይ ነው::  ግምጃ ቤቶቹ ባጠቃላይ 14 ሲሆኑ እንቁላላማ ቅርጽ ይዘዋል::

  ይህ ግምጃ ቤት በድሮ ጊዜ ለሚቀጡ ባለስልጣናት በእስር ቤትነት አገልግሏል:: ለመጥቀስም ያህል ልጅ እያሱ በዚህ ማዕከል ታስረዋል:: 

  ምንጭ፦ የአማራ ክልል የቱሪስት መስህብ ሃብቶች

 • loader Loading content ...
 • @አማን   2 years ago
  Stop waiting for the perfect moment. Take the moment you've and make it perfect.

  የጐዜ መስጊድ በሸዋ ሮቢት ከተማ የሚገኝ ሲሆን ከ500 ዓመታት በላይ ዕድሜ ያለው ነው:: መስጊዱ ግድግዳውም ጣሪያውም ከድንጋይ በ15ኛው ክፍለ ዘመን በይፋት ሥርወ መንግስት የተገነባ ነው::  የጐዜ መስጊድ ኮረብታ ላይ የሚገኝ ሲሆን የአርጎባ ማህበረሰብም ባካባቢው ስለሚኖር እምነታቸውን የሚያከናውኑበት ቦታ ነው::

  የጐዜ መስጊድ ዙሪያ ጥንታዊ የመቃብር ቦታ፣የቀድሞ ነዋሪዎች የውሃ ጉድጓድ እና የሃይማኖቱ መሪዎች የጦር መሳሪያ ሳይቀር ይገኛል::                    

                                       ምንጭ፦ የአማራ ክልል የቱሪስት መስህብ ሃብቶች

 • loader Loading content ...
 • @አማን   2 years ago
  Stop waiting for the perfect moment. Take the moment you've and make it perfect.

  ጋብቻ በሰዎች መካከል የሚፈጠር ማህበራዊ የአንድነት ሥርዓት ወይም ህጋዊ ስምምነት ነው። ስርዓቱ የሚመሠረተው በሰርግ ስነስርአት ወይም በሌላ ዝግጅት ሊሆን ይችላል። የዚህ ተቋም አወቃቀር እንደየ ባህሉ፣ እንደየ ሃይማኖቱ እና እንደየ ጊዜው ይለያያል። በወንድ እና በሴ መካከል ለሚፈጠር ጋብቻ ወንዱ ባል የሚባል ሲሆን ሴቷ ደግሞ ሚስት ትባላለች።

  በተሻሻለው የቤተሰብ ህጋችን ውስጥ በዋነኝነት በሶስት አይነት የጋብቻ ማስፈፃሚያ ስርዓቶች እውቅና ሰጥቷል፡፡ እነዚህም፡-

  1.       በክብር መዝገብ ሹም ፊት የሚፈጸም ጋብቻ፣

  2.       በሀይማኖት ስርዓት መሠረት የሚፈጸም ጋብቻ እና

  3.       በባህል ስርዓት መሠረት የሚፈጸም ጋብቻ ናቸው፡፡ (በተሻሻለው የቤተሰብ ሕግ አንቀጽ 1 - 4)

  በውጭ ሀገር የተፈጸመ ጋብቻ በዛ ሀገር ጋብቻ አፈፃፀም ሕግ መሠረት የተፈጸም ከሆነ እና የዚህን ሀገር (ኢትጵያ) ህዝብ ሞራል እስቃልተቃረነ ድረስ በተሻሻለው የቤተሰብ ሕግ መሠረት ከላይ በተገለጸው ሶስት አይነት ስርዓቶች ከተፈጸሙ ጋብቻዎች ጋር እኩል እውቅናና ተቀባይነት አለው፡፡

 • loader Loading content ...
  Load more...
loader Loading content ...

Comments (0)


  This user has no comment yet.