loader
 • ሃገር።

  @እሸቱ አበበ   3 years ago
  Hard core sewasewer who believes in social learning!
 • loader Loading content ...
 • @እሸቱ አበበ   3 years ago
  Hard core sewasewer who believes in social learning!
  የሚቀጥለው ግጥም የሃገርን ትርጉም በደምብ የሚገልጽ ይመስለኛል። ተጻፈ በዶ/ር በድሉ ዋቅጅራ። 
  ---------------------

  ሀገር ማለት ልጄ፣ ሀገር ማለት፣
  እንዳይመስልሽ የተወለድሽበት ቦታ ፣ የተወለድሽበት አፈር፤
  እትብትሽ የተቀበረበት ፣ ቀድመሽ የተነፈሽው አየር፤
  ብቻ እንዳይመስልሽ።
  ሀገር ረቂቅ ነው ቃሉ፤
  አገር ውስብስብ ነው ውሉ።

  ሀገር ማለት ልጄ ፣
  ሀገር ማለት ምስል ነው ፣በህሊና የምታኖሪው፤
  ከማማ መህጸን ከወጣሽበት ቀን ጀምሮ ፤
  በጠባሽው ጡት፣ ወይም ጡጦ ፣
  በዳህሽበት ደጃፍ፣ በወደቅሽበት ፈፋ፤
  በተማርሽበት ትምህርት ቤት፣
  በተሻገርሽው ዥረት ፤
  በተሳልሽበት ታቦት ፣ወይ በተማፀንሽው ከራማ ፤
  በእውቀትሽና በህይወትሽ፣
  በእውነትሽና በስሜትሽ ፣
  የምትቀበይው ምስል ነው ፣ በህሊናሽ የምታኖሪው፤
  ስትወጅ ሰንደቅ ታደርጊው፡፡
  ቢያስጠላሽ የማትቀይሪው።

  ሀገር ማለት የኔ ልጅ ፣
  ሀገር ማለት ቋንቋ ነው በአንደበት አይናገሩት፤
  በጆሮ አያዳምጡት፤
  አማርኛ ኦሮሞኛ ፣ አፋርኛ ቅማንተኛ፤
  ጉራግኛ ወይ ትግርኛ፣ ብለው የማይፈርጁት ።

  የኔ ልጅ፣
  አማራውና አፋሩ፣ ኦሮሞው ሲዳማው ፣ ጉራጌኛሽን ባይሰማ፤
  ያለገባው እንዳይመስልሽ ፣ ሀዘን ደስታሽን ያልተጋራ።
  የየልቦናችንን ሀቅ፣ ፍንትው አድርጎ እያሳየ፤
  ህዝቦችን ከሰንደቃቸው፣ አስተሳስሮ ያቆየ፡፡
  ሀገር ቋንቋ ነው ልጄ፣ የሁለንተናሽ መስታወት፤
  ሲከፋሽ ትሽሽጊበት ፣ ሲደላሽ ትኳኳየዪበት ።

  የኔ ልጅ ፣
  አያት ቅም አያትሽ ፣ሰላም ሲሆን ከወልቂጤ አድማስ ማዶ ሸቅጦ፣
  ሲያቀና ወረቱን፤
  ለእኔና ለአንቺ መኖሪያ፣ ሲያቀና ቀዬና ቤቱን፤
  ሀገር ጠላት ሲደፍራትም፣ ጦሩን ሰብቆ እየፎከረ፤
  ከኦሮሞው ከትግሬው፣ ከአፋሩ ከወላይታው፣ . . . ከሁሉም የጦቢያ ልጆች ፣
  አጥንቱን እየማገረ፤
  ሀገር ይሉት መግባቢያ ፣ሰንደቅ ይሉት መለያ ፣ ሲያቆይልሽ፤
  በጉራግኛ ማትገልጭው፣ በጎጥ የማትገድቢው፣ ስንት አለ ታሪክ መሰለሽ!

  እና የእኔ ልጅ፣
  ለዚህ ነው ሀገር ይሉት ቋንቋ፣ ላንቺ የሚያስፈልግሽ፤
  ከወልቂጤ አድማስ ማዶ፣ ለተሳሰረ ታሪክሽ፤
  ከወልቂጤ አድማስ ማዶ ፣ ለተወጠነው እድገትሽ።
  እና ልብ በይ ልጄ ! ሀገር ማለት ቋንቋ ነው፣ ባንደበት አይናገሩት፤
  በጆሮ አያዳምጡት።

  ከሁሉም በላይ ልጄ ፣
  ተፈጥሮ ከቸረው በረከት ፣ የላቡን ፍሬ የሚበላ፤
  ሀገር ማለት ወገን ነው፣ የእኔ የምትይው ከለላ።
  ትመኪበት ጥሪት፣ ትደምቂበት ብርሃንሽ፤
  የሰብዕናሽ ግማሽ ውል ፣ወገን ነው ማሕተምሽ፡፡
  ዜጋው ነው ልጄ ሀገርሽ።

  መሬትማ የእኔ ልጅ፣
  በእምነትሽና እውቀትሽ፣ ከልለሽ ካላበጀሽው፤
  ለእድገትሽ ውጥን ካልሆነ ፣ለተስፋሽ ካልተመገብሽው፤
  መሬትማ ባዳ ነው፣ ላለማው የሚለማ፤
  ለተስማማው የሚስማማ።
  ዥረቱም ግድ የለውም ፣ ቦይ ለማሰለት ይፈሳል
  ተራራውም ደንቆሮ ነው ፣ ለቦረቦረው ይበሳል።
  መሬቱ አደለም የኔ ልጅ፣ እድርተኛው ነው ሃገርሽ፤
  ስትቸገሪ ታድጎ፣ ስትታመሚ አስታሞ፣ ስትሞቺ አፈር ሚያለብስሽ።
  በእጅሽ ያለ ብሩህ ጽጌ ፣ ሰው ነው ልጄ ሀገርሽ፤
  ወገን ነው ልጄ ሀገርሽ።

  እና የኔ ልጅ፣
  ሀገር ረቂቅ ነው ቃሉ፤
  ሀገር ውስብስብ ነው ውሉ።


 • loader Loading content ...
 • @ሊ/ትጉሃን እምሩ   2 years ago
  Sewasewer
  ከበደ ሚካኤል ደግሞ ሀገር የሚለውን እንደሚከተለው ገልፀውታል።

  " አገር በታሪክ፣ በቋንቋ፣ በሃይማኖት፣ በልማድ፣ በተስፋ፣ በደስታና በመከራ ተሳስሮ የሚኖር አንድ ወገን የሆነ ሕዝብ የሚኖርበት የዓለም ከፍል ነው።

  አገር ማለት አያት ቅድመ አያት የተወለዱበት ፤ አድገውም በጀግንነት ከውጪ ጠላት እየተከላከሉ ለሕዝብና ለመንግሥት የሚጠቅም ሥራ ሠርተው ዕድሜያቸው ሲደርስም ልጆቻቸውን ተከተው የተቀበሩበት ጕድጓድ ነው።

  በመወለድ አትብት፤ በመሞት አካለ ከአፈሩ ጋራ ስለሚዋሐድ የአገሩ አፈር ሕዝቡ በላዩ የሚኖሩበት ማለት ነው።

  እግዚአብሔር ከምድሯ ፍሬ ሕይወት እንዲገኝባት በማድረጉ አገር እያጠባች የምታሳድግ ፍቅሯ በአጥንት በስጋ ገብቶ የማይደመሰስ የሆነች እናት ማለት ነው።

  ከልጅነት ጀምሮ ወንዙን ተራራውን ሜዳውን ቆላውንና ደጋውን በማየት ስለ ማደግ አባቶች በይህወትና በሞት የሰሩበት፣ ደግ ስራ በአእምሮ ታትሞ ስለቀረ በአገር አስካሉ ሲታይ፤ በስደት ሲሆኑ ሲታሰብ ፍቅርና ናፍቆት የሚያሳድር አገር ነው።

  አገር አባት፣ እናት፣ ዘመድ፣ ምግብ፣ ጌጥና ሃብት በመሆኑ ድህነትና ጥቃት በመጣ ቁጥር እስከ ሞት ድረስ እንዲሰራበት ከአያት ከቅድመ አያትና ከአባቶች በጥብቅ አደራ የተሠጠ ገንዘብ ነው።"

  ምንጭ
  • ታሪክና ምሳሌ (ከበደ ሚካኤል)

 • loader Loading content ...
 • @Abigel   1 year ago
  Sewasewer
  በጣም እናመሰግናለን@እሸቱ፣ መልእክት ያለው  ጥሩ ግጥም ነው !
 • @Adugna   1 year ago
  Sewasewer
  Thank you እሸቱ for such an inspiring poem!
 • @Tesfaw   1 year ago
  Sewasewer
  መሳጭ ግጥም!
 • @Tola (ቶላ)   1 year ago
  ከተኛ አንበሳ ዞር ዞር ያለ ቀበሮ ይሻላል!
  ከዶክተር በድሉ ዋቅጅራ ግጥሞች ውስጥ በጣም የምወደው ግጥም ነው! እዚህ ስላመጣህልን እናመሰግናለን እሸቱ!!
 • @ቀዮ   1 year ago
  ብልህ እያንዳንዱን አጋጣሚ ከሌሎች ለመማር ይጠቀምበታል!
  Great poem by Dr. Bedilu! Thanks for bringing it to sewasew, እሸቱ! I also like the explanation by Hon. Dr. Kebede Michael!
 • @Demoze   1 year ago
  Sewasewer
  አንጀት አርስ ግጥም! አንጀት አርስ አገላለፅ! እናመሰግናለን።
 • @Mesfin   1 year ago
  Sewasewer
  እንደዚህ ልብ ዘልቆ የሚገባ ግጥም ካነበብኩ ቆይቻለሁ! ማንኛውም ኢትዮጵያዊ ሊያነበው የሚገባ! እናመሰግናለን ገጣሚውንና ፖስት ያረጉትን!
 • @Biruk   1 year ago
  Sewasewer
  Wow! Thanks a lot!

Load more...