loader
 • ስለ ሃሳብ...

  @Gosa   1 year ago
  ጎሳ ሰው ነው።
 • loader Loading content ...
 • @Gosa   1 year ago
  ጎሳ ሰው ነው።
  ራስ ካሳ ኃይሉ ፍኖተ አዕምሮ በተሰኘው መፅሐፋቸው ላይ፣ ሰው ምኞቱ ሳይለወጥ በሃሳቡ ብቻ እንደሚጎዳ እና እንደሚጠቀም እንደዚህ ያብራራሉ:

  የሰው መጠቀሚያው እና የመጎጃው መሰረት አሳቡ ነው እንጂ በስራው አለመሆኑን ብዙ የሚያስረዳ ነገር አለልህና አስተውል።

  ሰው በፅድቁ መሰረት ኃጢያትን ይሰራል። አንዱን ሥራ የስራውን አይነት ሳይለውጥ ባሳቡ መለወጥ ብቻ ፅድቅና ኃጢያት የሚሆኑትንም አስተውል።

  ለእግዚአብሄር ምስጋና የታዘዘውን ፀሎት ሰው አውቆለት እንዲያበላውና እንዲያከብረው ቢያደርግ ለእግዚአብሄር የሚገባውን ገንዘብ ለሱ ጥቅም ሸጦለጣልና ኃጢያት ይሆንበታል። ለሱ ጥቅም ባይሸጠው ግን ፅድቅ ይሆንለታል። ስራው ሳይለወጥ ባሳቡ መለወጥ ብቻ ይጎዳልና በዚህ አስተውል።

  ምፅዋትንም መስጠት አንድ ሆኖ ሲሰጥ ምስጋና መሻትን አስቦ ሲሆን ከንቱ ይሆንበታል፤ መመስገንን ሸሽቶ ሲሰጥ ለፅድቅ ይሆንለታል።

  አለባበስም እንደዚሁ ሁሉ ስራው አንድ ሆኖ ባሳብ ብቻ መለወጥ ያስፈርዳል። አለባበስም ኢስተጎፍሮሙ ለነዳያነ በበይነ ትፍስሕትከ ያለውን አስቦ እንደሱ ባለመልበሳቸው የሚያዝኑ ሰዎች ኑረው እነሱን ላለማሳፈር ራሱንም በልብሱ ላለማኩራት ፍትወቱን በማጎበቡ ደስ ለማሰኘት ስል ዝቅተኛ ቢለብስ የሚያምር ምግብ መተው ፆም ሆኖ እንደሚጠቅም የሚያምረውንም ልብስ ስለዚህ ሃሳብ ስል ቢተው ባለባበሱ ፅድቅ ይሰራል፤ ንቆ ኮርቶ ቀንቶ አኩርፎ እያለው ወራዳ ቢለብስ ኃጢያት ይሰራል። ከቤቱ ያለውን የሱን ልብስ የለበሱትን ሁሉ መናቁ ነውና ሳይቸግረው ኃጢያት ይሰራል።

  አነጋገርም ቃሉም ሳይለወጥ በድምፅ ስልት ብቻ እየጎተተ ስናገረው የንቀት፣ እያጠበቀ ስናገረው የድፍረት፣ እየጮሀ ስናገረው የእብደት ሆኖ ሰው የሚያስቀይም ኃጢያት ይሆናል። እየከፈለ ሲያወጣው፣ እየመጠነ ሲናገረው የእውቀትና ለሰው የሚጠቅም አፅዳቂ ቃል ይሆናል። ራሱም እምቃልከ ትፀድቅ የተባለውን ያገኛል። እያሳዘነ በቀስታ በፍራት ስናገረው ሰውን እያሳዘነው ራሱን የሚጠቅምበትን ያገኛል። የፊደሉ ስም፣ ያንደበቱ አነጋገር ሳይለወጥ መጎጃውና መጠቀሚያው በድምፁ ስልት ብቻ መሆኑን አስተውል። አይነቱም ... ድኅናም አይደለህ ማለት ሲነሳ ስድብ ስለዝብ ደግሞ ጥያቄ መሆኑን አስተውል።

  አስተያየትም የቅንድቡ አገላለጥ አንድ ሲሆን ሲያጨነቅረው የሰው ንቀት፣ ሲያስፈጥጠው ቶሎ ቶሎ ሲያዛውረው የቁጣ፣ የእብደት ሆኖበት ይጎዳበታል። መጥኖ ረግቶ ሲገልጠው የእውቀት እና የፍቅር ሆኖ ይጠቀምበታል።

  ስለዚህ ሥራ ያሳብ ታዛዥ ነውና ሰው የሚጎዳበትም የሚጠቀምበትም እንደ አሳቡ አይነት መሆኑን እውቅና የምትሰራው ሁሉ ምክንያቱን ለእግዚአብሄር መሆኑን ወይም ለስምና ለሰውም እንደሆነ ለነፍስህም እንደሆነ ወይም ስለ ስጋህ ምኞት እንደሆነ ከስራህ በፊት የምትሰራበትን ምክንያት ልቡናህን መርምረህ የምትሰራለትን ባለቤቱን የምትሰራበትን ምክንያቱን እያወቅከው ሥራ እንጂ እንደ እንስሳ በልማድህ ብቻ አትስራ።

  ምንጭ:
  ፍኖተ አዕምሮ
  ራስ ካሳ ኃይሉ 
 • loader Loading content ...
 • @መርሻ   1 year ago
  Interested in just about everything!
  እናመሰግናለን ጎሳ! እውነት ነው፤ ተመሳሳይ ቃል በዓነጋገር ስልት ወይም በሰውነት ሁኔታ ብቻ በሰዎች ዘንድ የተለየ አስተያየት ሊያስከትል ይችላል።
 • @ቀዮ   1 year ago
  ብልህ እያንዳንዱን አጋጣሚ ከሌሎች ለመማር ይጠቀምበታል!
  የሆነ ወቅት ላይ ይህንን መፅሃፍ በከፊል ለማንበብ ችዬ ነበር። ራስ ካሳ በጊዜያቸው ከነበረው አስተሳሰብ ትንሽ ወጣ የማለት ዝንባሌ ነበራቸው  ለማለት ያስደፍረኛል። ምን ያህሉን ፍልስፍናቸውን በራሳቸው ህይወት ላይ ኖረውታል የሚለውን ባላውቅም።

Load more...