loader
 • ስለ ጋራ ተገዳጆችና ስለ ዋሶች (የ፲፱፻፶፪ ዓ.ም. የንግድ ሕግ አዋጅ ፥ አንቀጽ ፪ ፥ ምዕራፍ ፭ ፥ ክፍል ፪።)

  @በህግ አምላክ   3 months ago
  ህግን አለማወቅ ከተጠያቂነት አያድንም!
 • loader Loading content ...
 • @በህግ አምላክ   3 months ago
  ህግን አለማወቅ ከተጠያቂነት አያድንም!

  የ፲፱፻፶፪ ዓ.ም. የንግድ ሕግ አዋጅ። የኪሣራና የመጠበቂያ ስምምነት። አንቀጽ ፪። ስለ መክሠር። ምዕራፍ ፭። የገንዘብ መጠየቂያ መብቶችን ስለ መመርመር። ክፍል ፪። ስለ ጋራ ተገዳጆችና ስለ ዋሶች።


  ቁጥር ሺ፶፭። ሳይከፋፈል ያንድነት አላፊነት የተጻፈባቸውን ሰነዶች ይዘው ስለሚቀርቡ ገንዘብ ጠያቂዎች።
  የከሠረው ሰውና መክፈላቸውን ያቋረጡ ሌሎች ሰዎች፤ ሳይከፋፈል ባንድነት ተገዳጆች በመሆን በጀርባው የፈረሙበትን ወይም አላፊ የሆኑባቸውን ሰነዶች የያዘ ገንዘብ ጠያቂ በሰነዱ ላይ በተጻፈው ዋጋ ልክ በኅብረቶቹ ሁሉ ውስጥ ለመግባትና በሚደረጉትም ክፍያዎች ሁሉ በሙሉ ገንዘቡን እሰኪያገኝ ድረስ ተካፋይ ለመሆን ይችላል።

  ቁጥር ሺ፶፮። ስለ ተከፈሉት ድርሻዎች በከሠሩ ሰዎች መካከል አቤቱታ ስለማቅረብ።
  በጋራ ተገዳጅ ሆነው ከከሠሩት ሰዎች አንዱ ባንዱ ላይ በቁጥር ሺ፶፭ መሠረት በተከፈሉት ድርሻዎች ምክንያት አቤቱታ ለማቅረብ የሚችለው፤ ከከሠሩት ሰዎች ንብረት የተከፈሉት ድርሻዎች ድምር፤ ከሚከፈለው ዋና ገንዘብና ከተጨማሪዎቹ በላይ የሆነ አንደ ሆነ ብቻ ነው። እንደዚህም በሆነ ጊዜ አልፎ የተከፈለው ገንዘብ የሚሰጠው፤ ሌሎቹ ተገዳጆች ዋስ ለሆኑላቸው የጋራ ተገዳጆችና ግዴታ በገቡበት ተራ ነው።

  ቁጥር ሺ፶፯። መክፈሉ ከመቋረጡ በፊት ከዕዳው ላይ ከፊሉን ስለተቀበለ ገንዘብ ጠያቂ።
  (፩) በከሠረው ሰውና በሌሎች የጋራ ተገዳጆች መካከል ሳይከፋፈል የአንድነት ኅላፊነት ያለባቸውን ሰነዶች የያዘ ገንዘብ ጠያቂ ከሚጠይቀው ገንዘብ ከፊሉን፤ መክፈሉ ከመቋረጡ በፊት የተቀበለ እንደ ሆነ፤ በኅብረቱ ውስጥ ገብቶ የሚታሰብለት ገንዘብ ከሚገባው ገንዘብ ላይ በከፊል የተሰጠው ገንዘብ ተቀንሶ ነው። ለሚቀረውም ገንዘብ በጋራ ተገዳጆቹ ወይም በዋሶቹ ላይ ያለውን መብቶች አንደ ያዘ ይቆያል።
  (፪) በከፊል የከፈለ የጋራ ተገዳጅ ወይም ዋስ፤ ስለባለዕዳው በከፈለው ገንዘብ መጠን በዚሁ ኅብረት ውስጥ ይገባል።

  ምንጭ:
  የ፲፱፻፶፪ ዓ.ም. የንግድ ሕግ
 • loader Loading content ...

Load more...