loader
 • ስራዎ ላይ ቀልጣፋ መሆን ከፈልጉ በአንድ ጊዜ ብዙ ስራዎችን እያገላበጡ ማከናዎንን (Multitasking) ያስወግዱ።

  @Miss Counselor   6 days ago
  ካጋጠሙኝ ፣ ካነበብኳቸው እና ከተማርኳቸው!
 • loader Loading content ...
 • @Miss Counselor   6 days ago
  ካጋጠሙኝ ፣ ካነበብኳቸው እና ከተማርኳቸው!


  ብዙ ስራዎች በአንዴ ለማከናዎን መሞከር ከጥቅሙ ጉዳቱ እንደሚያመዝ ጥናቶች ያሳያሉ ። ትኩረታችንን በመበታተን  በጣም ቀላል የሆኑ ስራዎችን እንኳ በቀላሉ እና በፍጥነት እንዳናከናውን ያረገናል። የስራዎቻችን ጥራትም በእጅጉ ይቀንሳል። የምንሰራቸው ስራዎች መጠንም እንደዚሁ።

  ጥናቶች እንደሚያሳዩት ጭንቅላታችን ከአንድ ተግባር ወደ ሌላ ተግባር በሚሸጋገርበት ጊዜ በጣም ብዙ የሰውነት ኃይልን ይጠቀማል። በመሆኑም ብዙ ስራዎችን በአንዴ በምናገላብጥበት ጊዜ ሰውነታችን ቶሎ ይደክማል። ለረጅም ሰዓትም ስራዎችን መስራት ይከብደናል።

  ምንም እንኳ በዚህ ዘመን ብዙ ቀልባችንን የሚፈልጉ ነገሮች ቢኖሩም፣ ጊዜያችንን እና ጉልበታችንን በአግባቡ ለመጠቀም እና ጥራት ያለው ብዙ ሥራ ለመስራት በአንድ ጊዜ አንድ ሥራ ላይ ብቻ አተኩረን መስራት ያስልፈልጋል። ይህንም እንዴት ማድረግ  እንደምንችል የሚከተሉት ጥናታዊ ምክሮች ይጠቁማሉ።

   

  1. በቂ እረፍት ያግኙ

  በቂ እረፍት ስናገኝ እና በቀናችን ውስጥ ተደጋጋሚ አጫጫር እረፍቶችን ስንወስድ አእምሯችን ማተኮር እና በጣም አስፈላጊ የሆኑ ስራዎች ላይ ብቻ መጠመድ ይችላል። በአንፃሩ፣ አእምሯችን ሲደክም፣ ቀልባችን  ምንም አስፈላጊ ባልሆኑ ስራዎች እንኩዋን በቀላሉ ይወሰዳል። በቂ እረፍት ማገኘት ሲባል በቀናችን ውስጥ ተደጋጋሚ አጫጫር እረፍቶችን መውሰድ ብቻ ሳይሆን ማታም በቂ እንቅልፍ ማገኘትን ይጠይቃል።

   

  2. የቀን ዕቅድዎን ያውጡ

  የሚከተሉት የቀን ዕቅድ ከሌለዎት፣ የቀን ክስተቶች ቀንዎትን ባልፈለጉት አቅጣጫ ይመሩታል። የቀን ዕቅድ ሲኖርዎት ግን፣ ጭንቅላትዎ ምን ላይ ማተኮር እንዳለበት በአግባቡ ያውቃል። በመሆኑም ከውጭ የሚመጡ ነገሮች ቀንዎን አይቆጣጠሩብዎትም፣ እናም በሚያስፈልገው ሥራ ላይ ይበልጥ በተሻለ ሁኔታ ላይ ያተኩራሉ።

   

  3. እየሰሩበት ካለው ነገር ውጭ ያሉ ነገሮችን ከሥራ ጠረጴዛዎ ላይ ያስወግዱ።

  የስራ አካባቢያችን ቀልባችንን በሚዎስዱ ነገሮች ሲሞላ፣ አእምሯችን በአስፈላጊው ነገር ላይ ማተኮር ይከብደዋል። በያዝነው ሥራ መካከልም ሌላ መስራት ስላለብን ነገር ያሳስበንና ወደ ልሎች ስራዎች እንሸጋገራለን።  በአንፃሩ፣ የስራ ጠረጴዛችን ባዶና የምንሰራውን ነገር ብቻ ሲይዝ አእምሯችን አስፈላጊው ሥራ ላይ ብቻ ማተኮር ይችላል።

   

  4. የስራ ቦታዎ ላይ ሥራዎን ብቻ ያከናውኑ።

  የስራ ቦታችን ላይ ከስራችን በተጨማሪ ሌላ ነገር የምንሰራ ከሆነ፣ ለመሳሌ፣ ጋዜጣ ማንበብ፣ ሶሻል ሜድያ ገፆቻችን መጎብኘት እና የመሳሰሉትን ነገሮች የምናከናውን ከሆነ በአስፈላጊው ስራችን ላይ መካከል ቀልባችን ወደነዚሁ ነገሮች ይሳባል። ማድረግ የሌለብንን ነገሮች ለማድረግም ሁልጊዜ ፈተናዎች ይኖሩብናል። እነዚህን ነገሮች የሚያደርጉበት የተለየ ቦታ ይኑርዎ፣ ለምሳሌ ከስራ መልስ ቤትዎ ውስጥ። ይህን ሲያደርጉ፣ ሥራ ቦታ እያሉ አእምሮዎ ሥራዎ ላይ ብቻ እንዲያተኩር ይለማመዳል።

   

  5. አላስፈላጊ የሆነ የስራ ጫና ወደርስዎ ሲገፋ “አይሆንም” ማለትን ይልመዱ።

  አላስፈላጊ የሆኑና ጠቃሚ የሆነውን ስራዎትን የሚጋፋ ሥራ ሲመጣ ትህትና በተሞላበት እና ምክንያታዊ በሆነ መልኩ “አይሆንም” ማለትን ይልመዱ። የቀልብ መከፋፈል ችግር የሚጀምረው ያለበወትን የስራ ጫና ሳያገናዝቡ ለሚመጡ ስራዎች “እሺ” ብለው ሲቀበሉ ነው።  “እሺ” ወይም “አዎ” ከማለት ይልቅ “ላስብበት” ወይም “ጊዜየን አይይቼ በሁዋላ ላሳውቅ” በማለት ጊዜዎትን ወስደው ማሰብ እና እንዴት ምክንያታዊ በሆነ መልኩ ምላሽ እንደሚሰጡ መዘጋጀት ይችላሉ።

   

  6. ለመጨረስ እጅግ አስፈላጊ የሆኑ ሥራዎን ለማከናወን ጸጥ ያለ ቦታ ያግኙ።

  ለመጨረስ በጣም አስፈላጊ የሆኑ ሥራዎች ካለዎት፣ ፀጥ ያሉ ክፍሎች ውስጥ በመግባት ያከናውኑ። ይህ ትኩረት የሚጠይቁትን ሌሎች አስፈላጊ ያልሆኑ ስራዎችን ለማስወገድ እና በአንድ ስራ ላይ ብቻ ለማተኮር ይረዳዎታል።.

 • loader Loading content ...