የሳይንስ ክፍለ-ጊዜ ነው። መምህሩ ”ሰልፈሪክ አሲድ” ሰለሚባለው የአሲድ አይነት በማስተማር ላይ ናቸው።
"ልጆች፣ አሁን ይህን የወርቅ አንክብል እዚህ አሲድ ውስጥ ልከተው ነው። እና አሲዱ ወርቁን የሚያበላሸው ወይም የማያበላሽው መሆኑን ከናንተ መኻል አስቀድሞ ሊነግረኝ የሚችል አለ?"
"አያበላሸውም ቲቸር" አለ አንዱ ተማሪ ተሽቀዳድሞ።
«ለምን?»
"አሲዱ የሚያበላሸው ቢሆን ኖሮ፣ እርስዎ ቀድሞውኑ አሲድ ውስጥ አይከቱትማ!"
ምንጭ
ቀልዶች ከጋብሮቮ ምድር ፣ ትርጉም አረፈዓይኔ ሐጎስ።