loader
 • በንግዱ መደብር ላይ መያዣ ያላቸው የገንዘብ ጠያቂዎች መብት (የ፲፱፻፶፪ ዓ.ም. የንግድ ሕግ አዋጅ ፥ አንቀጽ ፪ ፥ ምዕራፍ ፭ ፥ ክፍል ፭።)

  @በህግ አምላክ   3 months ago
  ህግን አለማወቅ ከተጠያቂነት አያድንም!
 • loader Loading content ...
 • @በህግ አምላክ   3 months ago
  ህግን አለማወቅ ከተጠያቂነት አያድንም!

  የ፲፱፻፶፪ ዓ.ም. የንግድ ሕግ አዋጅ። የኪሣራና የመጠበቂያ ስምምነት። አንቀጽ ፪። ስለ መክሠር። ምዕራፍ ፭። የገንዘብ መጠየቂያ መብቶችን ስለ መመርመር። ክፍል ፭። በንግዱ መደብር ላይ መያዣ ያላቸው የገንዘብ ጠያቂዎች መብት።


  ቁጥር ሺ፷፱። ከሌሎች ከሚንቀሳቀሱ ዕቃዎች ሽያጭ ዋጋ በፊት ስለ ተከፋፈለው የንግድ መደብር ሸያጭ ዋጋ።
  የንግዱ መደብር ሽያጭ ዋጋ ከመከፋፈሉ ተንቀሳቃሽ ንብረቶች ሽያጭ ዋጋ በፊት፤ ወይም አብሮ ክፍያው ተደርጎ እንደ ሆነ፤ ከመደብሩ ሽያጭ ዋጋ በሙሉ ዋጋቸውን ያልተቀበሉ የመያዣ ወይም ልዩ መብት ያላቸው ገንዘብ ጠያቂዎች፤ በቁጥር ሺ፵፩ እና በተከታዮቹ ውሳኔዎች መሠረት መብታቸው ተቀባይነት አግኝቶ እንደ ሆነ፤ ባልተከፈላቸው ገንዘብ መጠን ለኅብረቱ በሚከፈለው ገንዘብ ውስጥ ከተራ ገንዘብ ጠይቂዎች ጋራ ተካፋይ ይሆናል።
  ቁጥር ሺ፸። ከንግዱ መደብር ሽያጭ ዋጋ በፊት ስለ ተከፋፈለው የሌሎች ተንቀሳቃሽ ዕቃዎች ዋጋ።
  የንግዱ መደብር ሽያጭ ዋጋ ከመከፋፈሉ በፊት የሌሎች ተንቀሳቃሽ ንብረቶች ሽያጭ ዋጋ ተከፋፍሎ እንደ ሆነ፤ መያዣ ያላቸውና፤ መብታቸውም በደንብ ተቀባይነት ያገኘው ገንዘብ ጠያቂዎች፤ ከዚሁ ከሚከፋፈለው ገንዘብ፤ በሙሉ በሚጠይቁት ገንዘብ መጠን ተካፋይ ይሆናሉ። ስለ ሆነም፤ በቁጥር ሺ፷፯ የተደነገገው እንደ ተጠበቀ ሆኖ ነው።
  ቁጥር ሺ፸፩።መያዣ ካልሆነው ንብረት የሽያጭ ዋጋ የተከፈለውን ስለ መቀነስ።
  (፩) የንግዱ መደብር ከተሸጠና የሽያጩም ገንዘብ የሚከፋፈለበት አኳኋን ከተወሰነ በኋላ በንግድ መደብሩ ላይ ለሞላ ገንዘባቸው መያዣ ያላቸው ገንዘብ ጠያቂዎች ገንዘባቸውን ከንግዱ መደብር ሽያጭ ላይ የሚያገኙት፤ መያዣ ካልነበረው ንብረት የሽያጭ ዋጋ የተከፈላቸው ገንዘብ ተቀናሽ ሆኖ ነው።
  (፪) በንኡስ ቁጥር (፩) መሠረት የተቀነሰው ገንዘብ ከኪሣራው ላይ በኅብረት ገንዘብ ጠያቂ ለሆኑት ሰዎች ጥቅም መያዣ ወዳልሆነው ንብረት ተመላሽ ይሆናል።

  ቁጥር ሺ፸፪። በንግዱ መደብር ላይ የመያዣ መብት ያላቸው ገንዘብ ጠያቂዎች በከፊል ለመቀበል ተራ ስለ መጻፍ።
  ከንግድ መደብር ሽያጭ ዋጋ ላይ የመያዣ መብት ኑሮዋቸው በከፊል ብቻ የተከፈሉ ገንዘብ ጠይቂዎች ጉዳይ ከዚህ እንደሚቀጥለው ይሠራል፤
  (ሀ) ዋስትና በሌለው ንብረት ውስጥ ያላቸው መብት የሚወሰነው ከንግዱ መደብር ዋጋ ከተቀበሉት ገንዘብ በኋላ በሚቀራቸው ገንዘብ መጠን ነው።
  (ለ) ባለፈው መከፋፈል ውስጥ ከዚሁ ድርሻ በላይ የተቀበሏቸው ገንዘቦች፤ ለመቀበል ተራ ከተጻፉበት መያዣ ካለው ክፍያቸው ላይ ተይዘው ዋስትና ለሌለው ንብረት ተመላሽ ሆነው ይቆያሉ።

  ምንጭ:
  የ፲፱፻፶፪ ዓ.ም. የንግድ ሕግ
 • loader Loading content ...

Load more...