loader
 • አለቃ ኪዳነ ወልድ ክፍሌ

  @Haset   2 years ago
  Sewasewer
 • loader Loading content ...
 • @Haset   2 years ago
  Sewasewer
  አለቃ ኪዳነወልድ ክፍሌ በሸዋ ክፍለ ሀገር በይፋትና ጥሙጋ አውራጃ በ1862 ዓ.ም. ተወለዱ። ለትምህርት ሲደርሱ በአካባቢያቸው የነበረውን የአገራቸውን ትምህርት ተማሩ። በኋላም ወደ ጎንደር ተጉዘው የመጻሕፍትን ትርጓሜ አጠኑ። በጊዜው የነበራቸው የቀለም አቀባበል፣ የሚስጥር መመራመርና መራቀቅ በጉባኤው ላይ «የቀለም ቀንድ» የሚል ቅጽል  አሰጥቷቸውም ነበር ።

  አለቃ ኪዳነወልድ ከግዕዝና አማርኛ ሌላ አረብኛ፣ ዕብራይስጥኛ እና ላቲን ቋንቋዎችን  አጠናቅቀው ያውቁ ነበር። በ1882 ዓ.ም. ወደ እየሩሳሌም ሄደው እዛ ይኖሩ ነበር ፣ በዚያም ቆይታቸው ብሉይና ሀዲስ ኪዳንን  በሦስት ቋንቋ አመሳክረው ተርጉመዋል።

  በ1912 ዓ.ም. የኢትዮጵያ  መንግሥት አልጋወራሽ ተፈሪ  መኮንን (ቀዳማዊ ኃይለሥላሴ)  ትችል አንደሆን መጥተህ ሕዝቅኤልን ተርጉምልኝ የሚል ደብዳቤ ፀፈውላችው ስለነበረ ነው ተመልሰው ወደ ሀገራቸው ወደ ኢትዮጵያ የመጡት። ሕዝቅኤልንም ንባቡን ከነ ሙሉ ትርጓሜው ጋር አሳትመው ካስረከቡ ቦሀላ በቅድስት አየሩሳሌም የወጠኑትን ይህን መፅሐፈ ሰዋሰው ወግስ ወመዝገበ ቃላት ሐዲስ የተባለውን የግዕዝና የአማርኛ መዝገበ ቃላት ድሬደዋ ላይ ተቀምጠው ማዘጋጀት ጀመሩ ። 

  ሞልቬር "ብላክ ላይንስ " በተባለው መፅሐፋቸው አንደጠቀሱት የግዕዝና የአማርኛ መዝገበ ቃላቱን የጀመሩት መምህር ክፍለጎዮርጊስ የተባሉት የራሳቸው  የአለቃ ኪዳነ ወልድ ክፍሌ መምህር ናቸው። ይህን የጀመሩትን መፅሐፍ ለመፍፀም የበቃ ዘመን እንደሌላቸው በተረዱ ጊዜ ሃሳቡን ከፍፃሜ እንዲያደርሱት ለአለቃ ኪዳነ ወልድ ክፍሌ አደራውን ይሰጧችዋል። አለቃ ኪዳነ ወልድ ክፍሌ በ 1929 ዓ.ም.  የወራሪውን  የፋሺስት የጭካኔ ተግባር በይፋ በመቃወማቸው  በጭለማ እስር ቤት ውስጥ ያስሩዋቸዋል። በጭለማ ክፍል ለረጅም ግዜ በመታሰራቸዉም የአይን ብረሃናቸውን ያጣሉ። እሳቸውም በተራቸው አደራዉን ለደስታ ተክለወልድ በመስጠት በ 1936 ዓ.ም. ሰኔ 24 ቀን አርፈው ደብረሊባኖስ ተቀበሩ ። ደስታ ተክለወልድ ጅምሩን ከፍፃሜ በማድረስ  መፅሐፈ ሰዋሰው ወግስ ወመዝገበ ቃላት ሐዲስ የተባለውን  በግዕዝና በአማርኛ ተፅፎ በ866 ገፅ የተዘጋጀውን መዝገበ ቃላት በ1948 ዓ.ም.  በአርቲስቲክ ማተሚያ ቤት አሳትመው አወጡት። በዚህ መዝገበ ቃላት መግቢያ ላይ የሶስቱን ምሁራን ተሳትፎ በተመለከተ  " መፅሐፈ ሰዋሰው ወግስ ወመዝገበ ቃላት ሐዲስ፣ በክፍለጎዮርጊስ ተጀምሮ በኪዳነ ወልድ ክፍሌ የዳበረውን ደስታ ተክለዎልድ አሳተመው " ተብሎ ተፅፎበት ይገኛል ። አለቃ ኪዳነ ወልድ ክፍሌ የግእዝና የአማርኛ መዝገበ ቃላት ከመጀመራቸው በፊት የሁለቱን ቋንቋዎች ታሪክዊነት በተመለከተ የገጠሙት እና ደስታ  ተክለዎልድ በኋላ "ሀዲስ የአማርኛ መዝገበ ቃላት" በተባለው የመዝገበ-ቃላት መፃፋቸው ላይ አሳትመው ያወጡት ግጥማቸው እንዲህ ይነበባል።
  እናንተ እንጂ ናችሁ የአፍሪካ ራስ ቅል ፣
  ባለዘውድ ቋንቋ ባለነፃ አክሊል ፣
  ግእዝና አማርኛ ሁለቱ ቋንቋዎች ፣
  ታላቅ እና ታናሽ  የአፍሪካ ወንዞች ፣
  ከአፍሪካ አልፈው ተርፈው በባህር በየብስ ፣
  ገና ይሰፋሉ እንደእግዜር መንፈስ ፣
  ሰለአማርኛ እና ስለግእዝ ክብር ፣
  ዋዜማ ጠቁሟል በብዙ አህጉር ።

  የደስታ  ተክለዎልድ መዝገበ ቃላት አሁን ድረስ እጅግ ተፈላጊ ቢሆንም በየግዜው የሚያስተመውና የሚያሰራጨው ድርጅት ወይም ግለሰብ ባለመገኘቱ በገብያ ላይ ለማግኘት በጣም አስቸጋሪ ነው።

  አለቃ ኪዳነወልድ ክፍሌ የኢትዮጵያ ፊደል አመጣጡንና ባህሉን በውል አስተባብረው በማቅረባቸውም በጊዜው ተቋቁመው ለነበሩት ትምህርት ቤቶች መመሪያና መማሪያ ለመሆን በቅተዋል። ቀጥለውም ትንሽ አማርኛ ፊደል ከአረብና ከዕብራይስጥ አቆራኝተው አሳትመዋል


  ምንጭ፣
  •  ኪዳነ ወልድ ክፍሌ፤ "መጽሐፈ ሰዋስው ወግስ ወመዝገበ ቃላት ሓዲስ"
  • አዲስ አድማስ ጋዜጣ • loader Loading content ...
 • @Adugna   1 year ago
  Sewasewer
  በጣም ትልቅ ስራ የሰሩ አባት ናቸው!thanks for sharing Haset!
 • @Bilen(ብሌን)   1 year ago
  Sewasewer
  Inspiring story, thank you Haset for sharing!

Load more...