loader
 • አስቴር አወቀ

  @Yared   2 years ago
  Sewasewer
 • loader Loading content ...
 • @Yared   2 years ago
  Sewasewer
  አስቴር አወቀ ጎንደር ውስጥ ተወልዳ አዲስ አበባ ውስጥ ያደገችና ላለፉት  30   አመታ ት ገደማ  ዝነኛ  ሆና  የዘለቀች  ድምፃዊት  ናት።  የዘፈን  ሙያዋን  የጀመረችው  በሀገር  ቅር  ቲያትር  በድምፃዊነት  እና  በተወዛዋዝነት  በመቀጠር ሲሆን   በመጀመሪያዎቹ  ውዝዋዜ  እና  የዘፈን  ስራዎቿ ጊዜ  የብዙነሽ  በቀለ ፣  ሂሩት  በቀለ  እና  የሙሉቀን  መለሰን ስራዎች  በመጫዎት  እንደጀመረች  ትናገራለች ። በዚህ ረጅምና ስኬታማ የሙያ ጊዜየዋ  ውስን   ዘፈኖች  የሚይዙትን  ሽክ ላ  አልበሞችን   ጨም ሮ  ሃያ  በላይ   አልበሞችን  አሳትማለች


   
   

  አስቴር በትምህርቷ ጎበዝ እንደነበረች እና የቤተሰቦቿ ፍላጎትም ዘፈን ሳይሆን በትምህርቷ እንድትቀጥልና ብሎም ከፍተኛ ደረጃ እንድትደርስ ነበርና የተወሰኑ አልበሞቿን እንደሰራች በዚሁ በቤተሰቦቿ ግፊት እና እሷም የዘፈን ህይወት ይህን የመሰለ ውጤትን እንደሚያመጣ በወቅቱ እርግጠኛ ባለመሆን የዘፈኑን ሙያ ወደጎን በማለት በፈረንጆቹ አቆጣጠር በ1981 ለትምህርት ወደ አሜሪካን አገር፣ ሳን ፍራንሲስኮ  (San Francisco)  ከተማ እንደተጏዘች ሸገር ላይ በሰጠችው ቃለ ምልልስ ገልፃለች። ሆኖም ግን ሳን ፍራንሲስኮ አካባቢ ለሁለት አመታት ከኖረች በሇላ  ኑሮው ከበድ እንዳላት እና ደስታን እንደፈለገችው ባለማግኘቷ ዋሽንግተን ዲሲ ያሉ ኢትዮጵያውያን ያቀርቡላት የነበረውን ግብዣ ተቀብላ ወደዛው ተጉዛ ስራ መስራት እንደጀመረች ትናገራለች።

  አስቴር በስራዋ የሀገሯን ሰዎች ብቻ ሳይሆን የውጭ ሀገር ሰዎችን ጆሮዎችም የሳበች ሲሆን ከሲቢኤስ  (CBS)  ኮርፖ ሬሽን ጋር የሰባት አመት ኮንትራት እንደነበራት ተገልፇል። በተመሳሳይም ከሌላ ከእንግሊዝ ሀገር ካምፓኒ ጋር ሌላ ኮንትራት ተዋውላ ስራዎቿን አበርክታለች። ተዋቂው ታይም (TIME) መፅሄትም ላይ አዲስ አይነት የሙዚቃ ስልት ዘርፍ ላይ ትልቅ አድናቆትን ተሰቷታል። ከዚህም ባሻገር "ካቡ" የተሰኘው አልበሟ በፈረንጆች አቆጣጠር በ1990 በ" CMJ New Music Charts " ላይ ለአራት ሳምንታት ከፍተኛ ቦታ (top  position) ላይ እንዲሁም በ" Billboard's World Music Charts " ላይ ለአስር ሳምንታት አስሩ ዝነኛ ዘፈኖች (top ten of  Billboard's World Music Charts ) ሆኖ ቆይቷል።

  አስቴር ወደ ኢትዮጵያ መጥታ ትልልቅ የሙዚቃ ዝግጅቶችን በጃንሜዳ፣ አዲስ አበባ ስታድየም፣ ሸራተን አዲስና ሚሊኒየም አዳራሽ አድርጋለች። ከዚህ ባሻገር በተደጋጋሚ እየደረሰ ያለውን የረሃብ አደጋ ሰለባዎች ለመርዳት በተደረገው ጥረት "ለወገን ደራሽ ወገን ነው" የሚለውን መሪ መፈክር ተቀብላ ወደሃገሯ በመምጣት በሙያዋ አስተዋፅኦ አድርጋለች። 
   
  የራስሽን ዘፈን ስትሰሚ ምን ይሠማሻል ተብላ ተጠይቃ "ተለዋዋጭ ነው፣ በወጣትነት ጊዜየ በጣም አፍር ነበር፤ የኔን ዘፈን ካዘፈንሽ ያንቺ መኪና ውስጥ አልገባም ነበር፣ የኔን ዘፈን ካዘፈንሽ እቤትሽ አልመጣም ነበር። ምክንያቱን ሁሌም በሰማሁ ቁጥር ይህን እንዲህ ማድረግ ነበረብኝ የምላቸው ስሜቶች ይሰሙኝ ነበር። አሁን ግን ዘፈኖቸን በሰማሇቸው ቁጥር በጊዜው የነበሩትን ነገሮች ቁልጭ አድርገው ስለሚያስታውሱኝ ደስ ይለኛል" ብላለች።

  አስቴር በምኒልክ መፅሄት በተደረገላት ቃለ መጠይቅ ላይ ደግሞ እራሷን በራሷ እንድትገልፅ ተጠይቃ "አስቴር አወቀ በጣም ደግ፣ ስስ ቆዳ ያላትና ትልቅ ለመሆን የምትፈልግ ሴት ናት። መፈቀርም ማፍቀርም የምትፈልግ ናት። ሌላ ትርጉም ሊሰጣት አይገባም ከተፈቀረች ይበቃታል። ሌላ ነገር አትፈልግም" ብላለች።


  አስቴር  አወቀ  ንድ  ሴት  ልጅ ያላት ሲሆን    የግል ህይወቷን ከሰው ሸሸግ አድርጋ የምትኖር እና ከ   አደባባይ  ይ  ልቅ  የግል    ሰው እንደሆነች  ትልቅ  የሆነም  የመድረክ  ፍርሃት እንዳለባት ትናገራለች።

  ምንጭ
  • የሸገር ኤፍኤም፣ የጨዋታ እንግዳ ዝግጅት ቃለ ምልልስ (ማዕዛ ብሩ)
  • ታሪካዊ መዝገበ ሰብ (ፋንታሁን እንግዳ)
  • ምኒልክ መፅሄት
  • http://www.billboard.com/artist/280125/aster-aweke/biography

 • loader Loading content ...

Load more...