loader
 • አስናቀች ወርቁ - ”የክራሯ ንግሥት” (Asnaketch Worku)

  @ሰላም   3 months ago
  Live a life you are proud of.
 • loader Loading content ...
 • @ሰላም   3 months ago
  Live a life you are proud of.

  አስናቀች ወርቁ የኢትዮጵያ ታዋቂ ዘፋኝ ስትሆን ብዙ ባህላዊ የሙዚቃ ስራወችን በማቅረብ ትታወቃለች። በአዲስ አበባ ከተማ ስድስት ኪሎ አካባቢ ተወልዳ በከተማ አካባቢ ነበር ያደገችው። ወላጆቿዋ ከተወለደች በኋላ ብዙም ሳይቆዩ በመለያየታቸው አባቷን አላገኘቻቸውም። እናቷ በሦስት አመቷ ከሞተች በኋላም አስናቀች ያደገችው ብዙም ፍቅች ከሌላት ከክርስትና እናቷ ጋር ነበር። በኋላ ላይ ከታላቅ እህቷ እልፍነሽ ማረፊያ ጋር መኖር የጀመረች ሲሆን ሁለቱም ወደ ትያትርና ኮንሰርቶች መሄድ ያስደስታቸው ነበር። አስናቀች የመጀመሪያዋን ክራር በ25 ሳንቲም ገዝታ እንዴት መጫወት እንዳለባት ራሷን አስተምራ በትንሽ መጠጥ ቤት እና የምሽት መዝናኛ ቤት መዝፈን እና መስራት ጀምራለች። ይሁን እንጂ በአነስተኛ ደመወዝ እና የወሲብ ትንኮሳ ምክንያት ስራዋን ቸርችል ጎዳና ላይ ይገኝ ከነበረው መጠጥ ቤት አቁማለች። አስናቀች አፍቅራ ተቀባይነት ባለማግኘቷ፣ በጭንቀት ተውጣ እና ለሦስት ቀናት መመገብ አቆመች እና ለአጭር ግዜ መኝታ አልጋዋ ጋር ተቆራኝታ ነበር።

  በ1952 እ.ኤ.አ. አስናቀች የመጀመሪያዋ ተዋናይት በመሆን በመዘጋጃ የቲያትር አዳራሽ በ "የፍቅር ጮራ" (Rays of Love) ተጫውታለች። መጀመሪያ ለመተወን ፈቃደኛ አልነበረችም፤ ነገር ግን በጓደኞቿ እና በኢጣሊያዊው ባለቤቷ ምክር በኋላ ተቀብላለች። እ.ኤ.አ. በ1955 ከFranz Zelwecker የድምጽ ትምህርት ወስዳለች። የተውኔት ደራሲ ተስፋዬ ገሰሰ እንደሚገልጻት "የመድረክ ዕንቁ"፣ ብዙውን ጊዜ የጭካኔ በሃሪ ያለባቸውን ገጸ ባሕርያት ተጫውታለች። በ1950 ዎቹ ውስጥ አስናቀች በውበቷ እና የፍቅር ድራማዎች አጨዋወቷ አወዛጋቢ ምስል ነበረች። የረዥም ጊዜ እና የተሳካለት የመድረክ ሥራ ባሻገር፣ አስናቀች በመጀመሪያ የምትታወቀው ከተዋናይነት ይልቅ፣ በክራር ችሎታዋ እና ፈጣን አእምሮ እና ተመስጦ ማሻሻያዎች ነበር። የሙዚቀኛነት ስራዋ በትክክለኛ የጀመረው እ.ኤ.አ. በ1963 በኦቴሎ ትያትር ዴዝዴሞናን ሆና ከጫነች በኋላ ብዙም ሳይቆይ ነበር። እ.ኤ.አ. ሚያዝያ 1974 የመጀመሪያ አልበሙአን “ክራር ዘፈኖች በአስናቀች ወርቁ” በሚል ፊሊፕስ-ኢትዮጵያ የተሰኘው ሌብል ተለቀቀ። መጠነኛ ስኬት ብታገኝበትን፤ ነገር ግን አብዮቱ ከተጀመረ በኋላ ከገበያው ታግዷል። በ1970 ዎቹ ውስጥ የእርሷ ዘፈኖች በሬዲዮ ተደማጭ እና ታዋቂ ነበሩ። አስናቀች እ.ኤ.አ በ 1987 የወታደራዊ መንግስትን ወክላ በረሃብ ወቅት የውጭ ሀገሮች ላደረጉት እርዳታ ለማመስገን በአውሮፓ እና አሜሪካን የ16 ሳምንታት ጉብኝት አድርጋለች። አስናቀች በ1990ዎቹ ውስጥ ተመልሳ መስራት ብትቀጥልም በ1989 ወደ ጡረታ ከመሄዷ በፊት በብሔራዊ ቲያትር ውስጥ ለ30 ዓመታት ሰርታለች። በወቅቱ የንጉሠ ነገሥት ቀዳማዊ ኃይለሥላሴ ምስሎች ያሉበት ጉትቻዎችን በማድረግ የታወቀች ነበረች።

  እ.ኤ.አ. በ1990ዎቹ መጀመሪያ ላይ በአውሮፓ ብዙ ጊዜ ጎብኝት አድርጋለች። እ.ኤ.አ በ1995 አስናቀች “እንደ ኢየሩሳሌም” የሚለውን ሲዲ የአኩስቲክ ሙዚቃ በጀርመን ከበገና ተጫዋች እለሙ አጋ ጋር አሳትማለች፤ የመጨረሻ ስራዋም ነበር። እ.ኤ.አ. በ1998 ዓ.ም ከኢትዮጵያ ሥነ ጥበብ እና የመገናኛ ብዙሃን የህይወት ዘመን ሽልማትን አሸናፊ ሆናለች። እ.ኤ.አ. በ2003 የቡድሃ ሙዚቃ “ኢቲዮፒስ 16” “ሴትዬዋ ከክራር ጋር” በሚባል መልኩ እ.ኤ.አ. በ1970ዎቹ አጋማሽ የአስናቀችን ቅጂዎች አሰባሰበው ጠቅለል ያለ ሲዴ ለቀዋል። በዚሁ ጊዜ የአስናቀች የሕይወትም ታሪክ ታትሞ ወጣ።

  እ.ኤ.አ በመስከረም 14 ቀን 2011 በአዲስ አበባ ቤተዛታ ሆስፒታል ውስጥ ከዚህ አለም በሞት ተለየች። የቀብር ሥነ ሥርዓቱ በአዲስ አበባ በሚገኘው ቅድስት ስላሴ ካቴድራል ውስጥ ተከናውኗል። “አስኒ፦ ድፍረት፣ ፍላጎት፣ እና ግርማሞገስ” በሚል ርዕስ ጥናታዊ ዘጋቢ ፊልም እ.ኤ.አ. በ2013 የአስናቀችን ሰለሙዚቃዋ ያደረገችውን ቃለምልልስ በማካተት ለእይታ ቀርቧል። ፊልሙ የተመራው በራሄል ሳሙኤል ሲሆን፣ ራሄል አስናቀችን የምትጠራት "Ethiopia's Edith Piaf" በማለት ነው።

  

  ምንጭ፦ ከዊኪፒዲያ የተተረጎመ

 • loader Loading content ...

Load more...