loader
 • ውልን ለዋስትና መያዣነት ስለ ማስተላለፍ (የ፲፱፻፶፪ ዓ.ም. የፍትሐ ብሔር ሕግ ፥ አንቀጽ ፲፱ ፥ ምዕራፍ ፫ ፥ ክፍል ፭)

  @በህግ አምላክ   3 months ago
  ህግን አለማወቅ ከተጠያቂነት አያድንም!
 • loader Loading content ...
 • @በህግ አምላክ   3 months ago
  ህግን አለማወቅ ከተጠያቂነት አያድንም!

  የ፲፱፻፶፪ ዓ.ም. የፍትሐ ብሔር ሕግ። አንቀጽ ፲፱። የአስተዳደር ክፍል መሥሪያ ቤቶች (አድሚኒስትራሲዮኖች) የሚያደርጓቸው ውሎች። ምዕራፍ ፫። የመንግሥት ሥራዎችን የመቋረጥ ውል። ክፍል ፭። ውልን ለዋስትና መያዣነት ስለ ማስተላለፍ።


  ቁጥር ፫ሺ፪፻፺፫። የመንግሥት ሥራ የተቋረጠበትን ውል በዋስትና ስለ ማስያዝ።
  ሥራ ተቋራጩ ወይም መሥሪያ ቤቱ ያወቃቸው ከዋናው ተቋራጭ ውስጥ ሁለተኛ ተቋራጮች የሆኑት የመንግሥትን ሥራ የተቋረጡባቸውን ውሎች ለዕዳ መያዣ ሊሰጧቸው ይችላሉ።

  ቁጥር ፫ሺ፪፻፺፬። የመንግሥትን የሥራ ውል ስለ ማስተላለፍ።
  የመንግሥት ሥራ ውል በደንብ መሠረት እንዲተላለፍ ተደርጎ እንደሆነ ዋጋውን ለመቀበል መብት ያለው አስተላላፊው ብቻ ነው።

  ቁጥር ፫ሺ፪፻፺፭። ከዋናው ተቋራጭ ውስጥ ተቋራጭ የሆነው ሰው መብቶች።
  (፩) በአስተዳደር መሥሪያ ቤት የታወቀ ከዋና ተቋራጭ ውስጥ ሁለተኛ ተቋራጭ የሆነ ሰው ስለፈጸማቸው ሥራዎች ዋጋውን በቀጥታ ከመሥሪያ ቤቱ ለመቀበል ይችላል ይህም ዋናው ተቋራጭ የፈቀደለት ሲሆንና በውሉም ሁለተኛው ሥራ ተቋራጩ የሚሠራው የሥራ ዐይነትና የሥራውም ዋጋ በግልጽ የተመለከተ በሆነ ጊዜ ነው።
  (፪) ሁለተኛው ሥራ ተቋራጭ የፈጸማቸውን ሥራዎች የሚያስረዱ የዝርዝር ማስታወቂያዎቹን የውሉ ባለቤት እንዲቀበላቸው አስፈላጊ ነው።
  (፫) ከሁለተኛው ሥራ ተቋራጭ ጋራ በቀጥታ ለመተሳሰብ የሚይቻል የሚሆነው ዋናው ተቋራጭ ውሉን በመያዣነት በሰጠው ጊዜ ነው።

  ቁጥር ፫ሺ፪፻፺፮። ከሒሳብ አስቀድሞ የሚከፈል ገንዘብን መከልከል።
  ሁለተኛ ሥራ ተቋራጭ የሆነው በማናቸውም አኳኋን ቢሆን ከሒሳብ አስቀድሞ የሚከፈል ገንዘብ ለመቀበል አይችልም።

  ምንጭ:
  የኢትዮጵያ የ፲፱፻፶፪ ዓ.ም. የፍትሐ ብሔር ሕግ (፲፱፻፶፪)
 • loader Loading content ...

Load more...