loader
 • የሊ/መ ቴዎድሮስ ዮሴፍ “እኔ እራሴን ካልጣልኩ“ መዝሙር  ግጥም

  @ምስጋና   1 week ago
  ሲመሽም ሲነጋ ምስጋና ለፈጠረን ጌታ፡፡
 • loader Loading content ...
 • @ምስጋና   1 week ago
  ሲመሽም ሲነጋ ምስጋና ለፈጠረን ጌታ፡፡

  እኔ እራሴን ካልጣልኩ

  አታውቅም ጥለኸኝ

  እኔ እራሴን ካልጣልኩ

  አታውቅም ጥለኸኝ

  ፍቅር ነህ ጌታዬ በፍቅር የምታየኝ

  ፍቅር ነህ አባቴ በፍቅር የምታየኝ


  እኔ እራሴን ካልጣልኩ

  አታውቅም ጥለኸኝ

  እኔ እራሴን ካልጣልኩ

  አታውቅም ጥለኸኝ

  ፍቅር ነህ ጌታዬ በፍቅር የምታየኝ

  ፍቅር ነህ አባቴ በፍቅር የምታየኝ


  ሐጥያቴ ነው እንጂ ከአንተ የሚያሸሸኝ

  በደሌ በዝቶ እንጂ አንገት የሚያስደፋኝ

  አምላኬ ይዞኛል ሰፊው መዳፍህ

  በበዛው ቸርነት ምሕረት ይቅርታህ


  እኔ እራሴን ካልጣልኩ

  አታውቅም ጥለኸኝ

  እኔ እራሴን ካልጣልኩ

  አታውቅም ጥለኸኝ

  ፍቅር ነህ ጌታዬ በፍቅር የምታየኝ

  ፍቅር ነህ አባቴ

  በፍቅር የምታየኝ


  ዛሬ ይቅር ብለኽኝ ዛሬ እንኳን ባጠፋ

  አምላኬ በእኔ ላይ አትቆርጥም ተስፋ

  እኔ እየሸሸው ትከተለኛለህ

  ጀርባዬን ስሰትህ ልጄ ትለኛለህ


  እኔ እራሴን ካልጣልኩ

  አታውቅም ጥለኸኝ

  እኔ እራሴን ካልጣልኩ

  አታውቅም ጥለኸኝ

  ፍቅር ነህ ጌታዬ በፍቅር የምታየኝ

  ፍቅር ነህ አባቴ

  በፍቅር የምታየኝ


  መመለሴን እንጂ ስለማትወድ ሞቴን

  መጣህልኝ ብለህ አቀፍከኝ አንገቴን

  በአንተ ተጀምሮ ስለማያልቅ በሰው

  አምላኬ በአንተ ላይ ተስፋዬ ብዙ ነው


  እኔ እራሴን ካልጣልኩ

  አታውቅም ጥለኸኝ

  እኔ እራሴን ካልጣልኩ

  አታውቅም ጥለኸኝ

  ፍቅር ነህ ጌታዬ በፍቅር የምታየኝ

  ፍቅር ነህ አባቴ በፍቅር የምታየኝ


  እኔ እያጠፋሁኝ እኔው ስበድልህ

  ፍሪዳውን ማረድ አንተ ግን ነው ልምድህ

  የጠፋው ተገኝቷል ተነስቷል የሞተው

  ትላለህ አምላኬ ማዳንህ ድንቅ ነው


  እኔ እራሴን ካልጣልኩ

  አታውቅም ጥለኸኝ

  እኔ እራሴን ካልጣልኩ

  አታውቅም ጥለኸኝ

  ፍቅር ነህ ጌታዬ በፍቅር የምታየኝ

  ፍቅር ነህ አባቴ በፍቅር የምታየኝ


  በአስለመድከኝ ምሕረት በአስለመድከኝ ፍቅር

  ከእኔ ጋር ነህና ተመስገን እግዚአብሔር

  ስለሆንከኝ አንተ መጠጊያ ከለላ

  ክፉውን አልፈራም መሄድ በሞት ጥላ


  እኔ እራሴን ካልጣልኩ

  አታውቅም ጥለኸኝ

  እኔ እራሴን ካልጣልኩ

  አታውቅም ጥለኸኝ

  ፍቅር ነህ ጌታዬ በፍቅር የምታየኝ

  ፍቅር ነህ አጋቴ በፍቅር የምታየኝ

  እኔ እራሴን ካልጣልኩ

  አታውቅም ጥለኸኝ

  እኔ እራሴን ካልጣልኩ

  አታውቅም ጥለኸኝ

  ፍቅር ነህ ጌታዬ በፍቅር የምታየኝ

  ፍቅር ነህ አባቴ በፍቅር የምታየኝ

 • loader Loading content ...

Load more...