loader
 • የተለያዩ ሰዎች ቁጣቸውን (አለመስማማታቸውን) የሚገልፁባቸው መንገዶች። አብረናቸውም ለመኖር የሚረዱ ሙያዊ ምክሮች።

  @Miss Counselor   6 days ago
  ካጋጠሙኝ ፣ ካነበብኳቸው እና ከተማርኳቸው!
 • loader Loading content ...
 • @Miss Counselor   6 days ago
  ካጋጠሙኝ ፣ ካነበብኳቸው እና ከተማርኳቸው!


  ሰው ከሰው ጋር ሲኖር ግጭት መከሰቱ የማይቀር ነው። ሁላችንም ከሥራ ባልደረባዎቻችን፣ ከቤተሰብ አባል ወይም ከጓደኛችን ጋር ፍትሃዊ የሆኑ ክርክሮች እና ግጭቶችን እናስተናግዳለን። አንዳንድ ሰዎች ግጭትን ወይም አለመግባባትን በቀላሉ ተረድተው በጥበብ ነገሩን ማብረድ ሲችሉ ሌሎች ደግሞ ጭራሽ ትንሿን አለመግባባት አስፍተው ወደ ትልቅ ፀብ እንዲያመራ የማድረግ ባህሪይ አላቸው።

  አለመግባባትን ተረድቶ እንደየሁኔታው ተገቢውን ምላሽ ለመስጠት የሰዎችን ባህርይ መረዳት ከፍተኛ ድርሻ እንዳለው የስነ-ልቦና ተመራማሪዎች ይናገራሉ። ለዚህም እንዲረዳ ቁጣን እና አለመስማማትንም በሚገልፁባቸው መንገዶች ረገድ ሰዎችን በ 4 ዋና ዋና ክፍሎች ያስቀምጧቸዋል። እያንዳንዱንም ሰዎች በጭቅጭቅ ጊዜ እንዴት ጭንቅላታቸውን ማንበብ እንደምንችል እና ምላሻችን ምን መሆን እንዳለበት እንደሚከተለው ይነግሩናል።

   

  1. ነጭናጫ ሰዎች (Behavioral Anger)።

  እነዚህ ሰዎች ባልተጠበቀ ሁኔታ እና ሰዓት የምቆጡ ሰዎች ናቸው። ቁጣቸውንም በቃል ወይም አካላዊ በሆነ መልኩ ይገልፃሉ። ቁጣቸው በጣም አስፈሪ ብሎም እቃዎችን በመወርወር እና በመሳሰሉት ብስጭታቸውን ሊገለፅ ይችላል።

   

  ከእንደዚህ አይነት ሰዎችን ጋር እንዴት መኖር እንደሚቻል

  እነዚህ ሰዎች ብዙ ጊዜ በራሳቸው መተማመን ዙሪያ ክፍተት ያለባቸው፣ ስለነሱ መጥፎ ነገር ሲነገራቸው በቀላሉ የሚከፉ ሰዎች ናቸው። ምንም እንኩዋን ነገሮች ፈታኝ ቢሆኑም እራስዎ ተረጋግተው ነገሩን ለማረጋጋት ይሞክሩ እንጂ እሳትን በእሳት አይዋጉ። ምክንያቱም ቁጣቸውን የበለጠ ስለሚያባብስ። ተረጋግተው የተቆጡበትን ነገር እንዴት መፍትሄ እንደሚሰጡት ይጠይቁ። ጥፋተኛው ማን እንደሆነ፣ ትክክል ወይም ስህተት የሆነ ማን እንደሆነ ለማስረዳት አይሞክሩ ምክንያቱም ጭንቅላታቸው በጊዜው ምክንያታዊ በሆነ ሁኔታ ለመወያየት ዝግጁ ስላልሆኑ። ለወደፊቱም ምቾት የማይሰጣቸውን ነገርም በተቻለዎ መጠን አይነካኩባቸው።

  2. ኃይለ-ቃል ወርዋሪ፣ በነገር የሚጎሽሙ (Verbal Anger)።

  እነዚህ ሰዎች ቁጣቸውን የሚገልፁት ኃይለ-ቃሎችን በአሽሙር፣ በነቀፋ፣ እና መመሳሰሉት የቃላት ጦሮች በመወርወር ነው። አላማቸውም የሌሎችን ስሜት እና ስነ-ልቦና በመንካት ቁጣቸውን እና ቅሬታቸውን ለመግለፅ ነው ። ከተረጋጉ በኋላ ግን ብዙውን ጊዜ የሀፍረት እና የጸጸት ስሜት ይሰማቸዋል።

   

  ከእንደዚህ አይነት ሰዎችን ጋር እንዴት መኖር እንደሚቻል

  የነዚህ ሰዎች አላማ ስሜትዎን እና ስነ-ልቦናዎን መጉዳት መሆኑን ተገንዝበው ለኃይለ-ቃላቸው ብዙም ቦታ እንዳይሰጡ ለራስዎ በደንብ ይንገሩት። ይህንም ሲያደርጉ አላማቸውን ማክሸፍ ይችላሉ።አንዳንዴም እንደሁኔታው እያዩ በወረወሩት ቃል ዙሪያ ቀልድን ፈጥረው ለመመለስ ይሞክሩ። ይህን ማድረግ በቃሉ አለመጎዳትዎን ያስገነዝባቸዋል፣ አንዳንዴም በመካከላችሁ ያለውን ውጥረት ለማርገብ ይረዳል። ቃላታቸው ጠንክሮ ግን መስመር ሲያልፍ፣ ክስ ባልተሞላበት ነገር ግን በሰከነ እና ፈርጠም ባለ መንገድ መስመር እንዳለፉ ይንገሯቸው። ሁሉም ካልሰራ ግን ዝምታን መርጠው በራሷቸው ጊዜ እንዲበርዱ ዕድልን ይስጧቸው።

   

  3. ምክንያታዊ በሆነ መልኩ እና ለውጥ ለማምጣት የሚቆጡ (Assertive anger)።

  እነዚህ ግለሰቦች ቁጣቸውን አወንታዊ ለውጦችን ለማምጣት ይጠቀሙበታል። ሁኔታውን በጥሩ ሁኔታ እና በንፅፅር እያደረጉ በረጋ እና በዘመናዊ መልኩ ከሌሎች ጋር ያላቸውን ችግሮች በግልጽ ይነጋገራሉ። ከዚያም ከሌሎች ወገኖች ጋር ችግሮችን እንዴት መፍታት እንደሚችሉ ይወያያሉ።

   

  ከእንደዚህ አይነት ሰዎችን ጋር እንዴት መኖር እንደሚቻል

  እነዚህ ሰዎች ቁጣቸውን የሚገልፁት ሆን ብለው እርስዎን መጉዳት ፈልገው ሳይሆን የነገሩን መለወጥ በመሻት ነው። ብዙ ጊዜም የሚፈልጉት ለውጥ አውንታዊ ለውጥ በመሆኑ ለመረዳት ይሞክሩ እና መረዳትዎን ይግለጹላቸው። ከእርስዎም የሚፈልጉትን ነገር ለመስጠት ይሞክሩ፣ ለውጡንም ለማምጣት አብረው ለመተባበር ይሞክሩ።

   

  ለምሳሌ በስራ ላይ ያለ ፕሮጀክትን እርስዎ እያጓተቱ መሆኑን አለቃዎ በምክንያት ቢገልፅልዎ፣ የነገሩን አሳሳቢነት መረዳትዎን እና እንዴት ማሻሻል እንደሚችሉ አብረው ይስሩ፣ ነገሩንም ለማሻሻል ቆራጥነትዎን ይግለፁላቸው።

  4. በአፍ መስማማትን እየገለፁ ግን በሚያደርጉት ተግባራቸውን አለመስማማትን የሚያሳዩ (Passive aggressiveness)።

  እነዚህ ሰዎች ያልተስማማቸው ነገር ሲኖር ፊት ለፊት መግለፅ (መጋፈጥ) አይወዱም። በቃላት ከመግለፅ ይልቅ መቃወማቸውን ቀስ እያሉ በድርጊታቸው መግለፅን ይመርጣሉ። ይህንም በማድረግ ሳይታወቅባቸው ሊያታልሉዎ ይሞክራሉ። አንድን ነገር በጋራ ለመስራት እቅድ ሲያዝ ባይስማሙበትም እሽታን ይገልፃሉ፣ ነገር ግን በሁዋላ እቅዱን ለማዳከም የሚረዷቸውን መንገዶችን ያፈላልጋሉ።

   

  ከእንደዚህ አይነት ሰዎችን ጋር እንዴት መኖር እንደሚቻል

  በነገሮች ላይ ከነዚህ ሰዎች ጋር ሲስማሙ፣ ፍርጥም እና ጠንከር ባለ መልኩ ውሳኔዎችን ለማስቀመጥ ይሞክሩ። ውሳኔዎችን ለማዳከምም የሚያደርጉዋቸውን እንቅስቃሴዎች በንቃት እያዩ ወደዉሳኔው ለማምጣት ይሞክሩ። አለበለዚያ ግን ግልፅ በሆነ መልኩ ድርጊታቸው እንደማይስማማዎት በግልፅ አፍረጥርጦ መንገር ያስፈልጋል።

   

 • loader Loading content ...