
-
@በህግ አምላክ 3 months agoህግን አለማወቅ ከተጠያቂነት አያድንም!
-
@በህግ አምላክ 3 months agoህግን አለማወቅ ከተጠያቂነት አያድንም!
የ፲፱፻፶፪ ዓ.ም. የንግድ ሕግ አዋጅ። የኪሣራና የመጠበቂያ ስምምነት። አንቀጽ ፪። ስለ መክሠር። ምዕራፍ ፫። የአጠባበቅ ሥራዎች። ክፍል ፩። የአጠባበቅ ውሳኔዎች።
ቁጥር ሺ፬። የባለዕዳውን መዝገብች ስለ መዝጋት።
(፩) አስፈላጊም ሆኖ ሲገኝ በቁጥር ሺ፲፩ የተነገረው እንደ ተጠበቀ ሆኖ ንብረት ጠባቂዎቹ፤ ባለዕዳው ባለበት፤ መዝገቦቹን ለመዝጋትና ሒሳቡን ለማቆም ባለዕዳውን ይጠሩታል።
(፪) በዚሁ ጥሪ ባለዕዳው ያልቀረበ እንደ ሆነ፤ በአርባ ስምንት ሰዓት ውስጥ እንዲቀርብና መዝገቦችንም እንዲያቀርብ ደረሰኝ ባለው ሬኮማንዴ ደብዳቤ ይጠራል።
(፫) ለመቅረብ የማይችልበትን ምክንያቶች ያስረዳ እንደ ሆነና፤ መርማሪውም ዳኛ በቂ መሆናቸውን የተረዳ እንደ ሆነ፤ ባለዕዳው ስለእርሱ ሌላ ሰው ለመወከል ይችላል።
(፬) ራሱ ለመቅረብ ወይም ወኪል ለመላክ እንቢ ያለ እንደ ሆነ፤ ወይም የሸሸ እንደ ሆነና የማይገኝ እንደ ሆነ አስፈላጊውን ነገር እንዲያደርግ መርማሪው ዳኛ ለሕግ አስከባሪው ያስታውቃል።
ቁጥር ሺ፭። የባለዕዳውን መብቶች ስለ መጠበቅ።
(፩) ንብረት ጠባቂዎቹ ሥራቸውን እንደ ጀመሩ፤ ለባለዕዳው በራሱ ባለዕዳዎች ላይ ያሉትን መብቶች ለመጠበቅ አስፈላጊውን ተግባር ማድረግ አለበቸው።
(፪) ባለዕዳው ያላስመዘገበውን፤ በማይንቀሳቀስ ንብረት ላይ ያለውን የመያዣ መብት፤ ንብረት ጠባቂዎቹ ማስመዝገብ አለባቸው። ንብረት ጠባቂዎቹ ንብረት ጠባቂዎች መሆናቸውን አስረድተው፤ የመያዣውን መብት የሚያስመዘግቡት በኅብረቱ ስም ነው።
ቁጥር ሺ፮። የባለዕዳው በሆኑት የማይንቀሳቀሱ ንብረቶች ላይ የመያዣ መብትን ስለ ማስመዝገብ።
(፩) ንብረት ጠባቂዎቹ የባለዕዳው በሆኑትና ወደፊትም በሚያገኛቸው የማይንቀሳቀሱ ንብረቶች ላይ በኅብረቱ ስም የመያዣ መብትን ማስመዝገብ አለባቸው።
(፪) በስምምነት የመጨረሻውን ድርሻ ከከፈለ በኋላ ወይም ስምምነት ያልተደረገ እንደ ሆነ የሒሳቡ ማጣራት ሥራ በፍጹም ከተዘጋ በኋላ ባለዕዳው በሚያገኛቸው በማይንቀሳቀሱ ንብረቶች ላይ የመያዣ መብቶች አይመዘገቡም።
ቁጥር ሺ፯። በንግዱ ላይ የመያዣ መብትን ስለ ማስመዝገብ።
(፩) በዚህ ሕግ በሁለተኛው መጽሐፍ ቁጥር ፻፸፪ ንኡስ ቁ (፩) (ለ) በተመለከተው መሠረት ሕጋዊ የሆኑትን የመያዣ መብቶች በባለዕዳው ንግድ ወይም ንግዶች ላይ ንብረት ጠባቂዎቹ ማስመዝገብ አለባቸው።
(፪) መመዝገብ የሚገባው፤
(ለ) የባለዕዳው ስምና አድራሻ፤
(ለ) ባለዕዳው የከሠረ መሆኑ የተወሰነበት ፍርድ የተሰጠበት ቀን፤
(ሐ) ባለዕዳው የከሠረ መሆኑን የወሰነው ፍርድ ቤት ስም፤
(መ) የንግዱ ዐይነትና አድራሻ፤
(ሠ) መያዣ ያደረጉት የንግዱ ክፍሎች፤
(ረ) ያለም እንደ ሆነ፤ መያዣ የሆነው ቅርንጫፍና ውክልና ነው።
(፫) በዚህ ቁጥር መሠረት መያዣ ስለሚደረግ ነገር ሁሉ በዚህ ሕግ አንደኛ መጽሐፍ ከቁጥር ፻፸፱ እስከ ፻፺፫ ያሉት ድንግጌዎች ተፈጻሚዎች ይሆናሉ።
ቁጥር ሺ፰። ለመርማሪው ዳኛ የሚደረግ መግለጫ።
(፩) ሥራቸውን በጀመሩ በወሩ ወስጥ ንብረት ጠባቂዎቹ የባለዕዳውን ጉዳይ ሁኔታና ለዚሁም ሁኔታ መነሻ የሆኑትን ምክንያቶች ጭምር የሚያስረዳ መግለጫ ለመርማሪው ዳኛ ይልካሉ።
(፪) መርማሪውም ዳኛ ሐሳቡን ጨምሮ ይህን መግለጫ ወዲያውኑ ለሕግ አስከባሪው ያስተላልፋል። መግለጫውም በታዘዘው ጊዜ ውስጥ ያልተሰጠ እንደ ሆነ፤ የዘገየበትን ምክንያቶች አስረድቶ ለሕግ አስከባሪው ማስታወቅ አለበት።
ምንጭ:
የ፲፱፻፶፪ ዓ.ም. የንግድ ሕግ


Similar topics
የመጠበቂያ ስምምነት (የ፲፱፻፶፪ ዓ.ም. የንግድ ሕግ አዋጅ ፥ አንቀጽ ፫።)
የኪሣራና የመጠበቂያ ስምምነት ፤ አጭር ሥነ ሥርዐት (የ፲፱፻፶፪ ዓ.ም. የንግድ ሕግ አዋጅ ፥ አንቀጽ ፭።...
ስለ ንግድ ቤት ሠራተኞች (የ፲፱፻፶፪ ዓ.ም. የንግድ ሕግ አዋጅ ፥ አንቀጽ ፪ ፥ ምዕራፍ ፩።)
በግዴታ የሚሆን የንብረት ማጣራት (የ፲፱፻፶፪ ዓ.ም. የንግድ ሕግ አዋጅ ፥ አንቀጽ ፪ ፥ ምዕራፍ ፭ ፥ ም...
ስለ ማኅበሮች መክሠርና የመጠበቂያ ስምምነቶች የሚጸኑ ልዩ ውሳኔዎች (የ፲፱፻፶፪ ዓ.ም. የንግድ ሕግ አዋጅ...
በመፋለም የመጠየቅ መብት (የ፲፱፻፶፪ ዓ.ም. የንግድ ሕግ አዋጅ ፥ አንቀጽ ፪ ፥ ምዕራፍ ፭ ፥ ክፍል ፮።...
ስለኪሣራው አሠራር የሚደረግ ዘዴ ፤ ስምምነት (የ፲፱፻፶፪ ዓ.ም. የንግድ ሕግ አዋጅ ፥ አንቀጽ ፪ ፥ ምዕ...
በማይንቀሳቀሱ ንብረቶች ላይ የመያዣና ልዩ መብት ያላቸው ገንዘብ ጠያቂዎች (የ፲፱፻፶፪ ዓ.ም. የንግድ ሕግ...
ስለ ቼክ አጻጻፍና ሥርዐት (ፎርም) (የ፲፱፻፶፪ ዓ.ም. የንግድ ሕግ አዋጅ ፥ አንቀጽ ፪ ፥ ምዕራፍ ፬ ፥...
የመክሠሩ ሥራ መዘጋት (የ፲፱፻፶፪ ዓ.ም. የንግድ ሕግ አዋጅ ፥ አንቀጽ ፪ ፥ ምዕራፍ ፭ ፥ ምዕራፍ ፯።)

Popular topics
የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስትያን የፓትርያርክ ስልጣኗን ለማግኘት ከግብፅ ቤተክርስትያን ጋር ያረ...
የመጀመሪያው የቀዳማዊ ኃይለስላሴ ኦፊሴላዊ የአሜሪካን ጉብኝት (State visit) ምን ይመስል ነበር?
የኢትዮጵያው ንጉስ አፄ ካሌብ (st. Elesbaan)
የመጀምሪያዋ ዘመናዊ የኢትዮጵያ የጦር መርከብ ማን ትባላለች?
የአድዋን ጦርነት የመሩት ዋና ዋና የሁለቱም አገራት የጦር አበጋዞች እነማን ናቸው?
የ፲፱፻፶፫ መፈንቅለ መንግስት በኢትዮጵያ በፍጥነት ታቅዶ በፍጥነት የተከወነ ነው ይባላል። ለዚህ አባባል እ...
የላሊበላ ውቅር አብያተክርሥትያናት ሥንት ቤተ ክርሥትያኖችን የያዘ ነው?