loader
 • ፕሮፌሰር ገቢሳ እጀታ ማን ነው?

  @አማን   2 years ago
  Stop waiting for the perfect moment. Take the moment you've and make it perfect.
 • loader Loading content ...
 • @አማን   2 years ago
  Stop waiting for the perfect moment. Take the moment you've and make it perfect.

  ፕሮፌሰር ገቢሳ እጀታ (Gebisa Ejeta) በ1950 ዓ.ም. በኦሎንኮሚ ከተማ ተወለዱ:: በወቅቱ በትምርታቸው የላቀ ውጤት በማምጣት የሚታወቁት ፕሮፌሰር ገቢሳ እስከ 7ኛ ክፍል የተማሩት እዛው ኦሎንኮሚ ሲሆን የዘመናዊ ትምህርት ባካባቢው ባለመኖሩ ቤት ተከራይተው በክፍያ ከሚያስተምሩ ትምህርት ቤት ነበር የተማሩት:: ቤተሰባቸው በመለያየታቸው ምክንያት ሙሉ በሙሉ የማሳደጉ ሃላፊለት የወደቀባቸው እናታቸው ወ/ሮ ሙሉ አያነው ምንም እንኳን ኑሯቸው ከእጅ ወደአፍ ቢሆንም የልጃቸው የትምህርት ጉጉት እና ከእኩዮቹም እንዳይለይባትም በማሰብ ጠላ እየሸጡ ያስተምሯቸው ነበር::  የ8ኛ ክፍል ትምህርታቸውን ደግሞ ከኦሎንኮሚ 20 ኪ.. ርቀት ላይ በምትገኘው አዲስ አለም ከተማ ዘመድ ጋር በመቀመጥ ቀለባቸውን በየሳመንቱ እየተመላለሱ በመውሰድ አጠናቀቁ:: የሁለተኛ ደረጃ ትምህርታቸውን በወቅቱ ከአክላሆማ ዩኒቨርስቲ ጋር በትብብር በተከፈተው የጅማ የእርሻ የቴክኒክ ትምህርት ቤት ገብተው በከፍተኛ ማዕረግ በማጠናቀቅ የሃረማያ ዩኒቨርስቲን በ1973 ዓ.ም. ተቀላቀሉ::  በፕላንት ሳይንስ በከፍተኛ ማዕረግ ከተመረቁ በኋላ  ከፐርዱ ዩኒቨርስቲ ለሁለተኛ ዲግሪያቸው  ስኮላርሺፕ አግኝተው  በ1976 ዓ.ም. አጠናቀቁ:: በመቀጠልም በፕላንት ብሪዲንግ እና በጄኔቲክስ የፒ.ኤች.ዲ ዲግሪያቸውን አግኝተዋል::

  በመቀጠልም ከፊል በረሃማ በሆኑ የትሮፒካል አካባቢዎች ከአለም አቀፍ የአዝዕርት ምርምር ተቋማት ጋር ማሽላ ላይ በማተኮር ወደ አፍሪካ በመሄድ ምርምር ማድረጉን ተያያዙት:: ለአምስት ዓመታት ምርምሩን ካከናወነ በኋላ “ሃጂን ዶሮዋን” የተባለ የሱዳንን በረሃ የሚቋቋም እና ውጢቱም በ150% የላቀ ምርት የሚሰጠውን የተዳቀለ ማሽላን አገኙ:: ከዮ.ኤስ.ኤድ ጋር በመተባበርም ይህን ምርጥ ዘር በማምረት ለብዙ ገበሬዎች እንዲዳረስ የዘር ኢንደስትሪ እንቅስቃሴ አስጀመሩ::

  ተመራማሪ ገቢሳ በተጓዳኝም Striga ወይም “ሟርተኛው አረም” ተበሎ  የሚጠራውን የማሽላ ጠንቀኛ ጠላት ለማጥፋት ወደ ፐርዱ ዩኒቨርሲቲ በመመለስ ከተመራማሪ ጓደኛው ጋር በመሆን ጥናታቸውን ቀጠሉ::  Striga ወይም “ሟርተኛው አረም” 500,000 ዘሮችን የመበተን  እና ዘሩም ከ10 - 20 ዓመት በአፈር ውስጥ የሚቆይ እና የዋናውን ተክል ዘር ሙሉ በሙሉ ወሮ ከጥቅም ውጭ የሚያደርግ አደገኛ አረም ነው:: በምርምራቸውም የዚህን አደገኛ አረም እና  የማሽላን ኬሚካላዊ ትስስር በመለያየት ለመታደግ የቻሉ ታላቅ ሰው ናቸው::

  ፕሮፌሰር  ገቢሳ በዚህ ታላቅ ውጤታቸው ከታላላቅ ተቋማት ጋር  የሰሩ ሲሆን ለመጥቀስም ያህል  .ኤስ.ኤድ፣ ሮክፌለር እና ጌትስ ፋውንዴሽን እንዲሁም አባል በመሆንም ከምግብና  የእርሻ  ድርጅት (ፋኦ)፣ የሳይንስ ካውንስል፣ የሳሳካዎ ግሎባል የቦርድ አባል እና የአሊያንስ ግሪን ሪቮሉሽን የክብር አባል በመሆን አገልግለዋል::

  በርካታ  ሽልማቶችን እና ሜዳሊያዎችን ያገኙ ሲሆን በ2009  የወርልድ ፉድ ፕራይዝ ተሸላሚ የአለም ሎሬት ገቢሳ እንዲሁም ከቀድሞው የኢትዮጵያ ፕሬዝዳንት ግርማ ወ/ጊዮርጊስ የብሄራዊ ጀግና የሚል ሽልማት አግኝተዋል::  2011 ዓ.ም. የጅማ ዩኒቨርስቲ የሳይንስ የክብር ዶክትሬት ተሸላሚም ናቸው:: በ2013 ዓ.ም. የዩ.ኤን. ዋና ጸሃፍ ባን ኪሙን በሳይንስ ዘርፍ ሾሞዋቸዋል:: በቅርቡም 2015 ዓ.ም. የቀድሞ ትምህርት ቤታቸው የሃረማያ ዩኒቨርሲቲ የክብር ዶክትሬት ተሸላሚ ሆለዋል::

 • loader Loading content ...
 • @መርሻ   1 year ago
  Interested in just about everything!
  እናመሰግናለን አማን!
 • @Demoze   1 year ago
  Sewasewer
  Thanks አማን! We should have more of such personalities on sewasew for generations to learn from them!