loader
 • ደርግ ሁለተኛው የኢትዮጵያ ፓትርያርክ አቡነ ቴዎፍሎስ ላይ ያቀረበባቸውና ለስቅላታቸው እንደምክንያት የተሰነዘረው ክስ ምን ነበር?

  @ሊ/ትጉሃን እምሩ   2 years ago
  Sewasewer
 • loader Loading content ...
 • @ሊ/ትጉሃን እምሩ   2 years ago
  Sewasewer
  ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ቴዎፍሎስ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስትያን ሁለተኛው (ከ1963 እስከ 1969 ዓም)   ፓትርያርክ የነበሩና በአጠቃላይ  በዘመናቸው ቤተክርስትያኗን በልዩ ልዩ ቦታዎች ለ28 አመታት ያገለገሉ አባት ናቸው  ( http://www.sewasew.com/phrases/1204?withDetails=1 ) ።   አቡነ ቴዎፍሎስ በግብፅ የጵጵስና ማእረግ ከተሰጣቸው የመጀመሪያዎቹ አምስት ኢትዮጵያውያን አባቶች ውስጥ አንዱ ሲሆኑ የፓትርያርክ ሹመታቸውን ከማግኘታቸው በፊት ካገለገሉባቸው ዋና ዋና ቦታዎች ዉስጥ የሚከተሉት በዋናነት ይጠቀሳሉ:

  1) የመጀመሪያው ፓትርያርክ (አቡነ ባስሊዮስ) እንደራሴ (ምክትል ፓትርያርክ) በመሆን
  2) የሐረር ግዛት ጳጳስ በመሆን
  3)   በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ   ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ላይ ለዘመናት ተጭኖ የኖረው የግብፅ    ቤተ ክርስቲደን የግዞት ቀንበር ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ ተሰብሮ  እንዲወድቅ በተደረገው ትግል ልዑክ በመሆን
  4) የቅድስት ስላሴ መንፈሳዊ ት/ቤት (አሁን ኮሌጁ) ዳይሬክተር እና አስተማሪ በመሆን
  5) የመንበረ ፀባኦት ቅድስት ስላሴ ካተድራል ሊቀ ስልጣናት ሆነው ቤተክርስትያኑን በመምራት
  የንጉሡ  ዘውዳዊ መንግሥት በጊዜያዊ ወታደራዊ አስተዳደር ደርግ መንግ ሥት ከተተካ ከጥቂት አመታት በሇላ የካቲት 9 1968 ዓም  ከመንበረ ፓትርያርክነታቸው ወርደው ለእስር ተዳርገው  በስር ቤት ስቃይ ለ 28 ወራት ከእራት ቀን  በመሪር ኀዘንና ጸሎት ከቆዩ በኋላ ሐምሌ 7 ቀን  1971 ዓም  በስሜን አዲስ አበባ ወረዳ 17 ቀበሌ 22 ተወስደው የልዑል ራስ  ዓሥራት ካሳ ቤት ተወስደው በሚያሳቅቅ ሁኔታ በገመድ ታንቀው እንደተገደሉ ይነገራል ፡፡ 

  ለቅዱስነታቸው አሰቃቂ የስቅላት ዋና መንስኤ ለደርግ ወታደራዊ አገዛዝ መሳሪያ ላለመሆን ባላቸው ግልፅ አቇም እና ተቃውሞ እንደሆነ ይነገራል። ለስርዓቱም ያላቸው ግልፅ ተቃውሞ ይሚከተሉት እንደ ምሳሌ ይጠቀሳሉ:
  • 1) በ1966 ዓም የ62ቱ የመንግስት ባለሥልጣናት ሲገደሉ በህዝብ ፊት ድጋፋቸውን እንዲሠጡ በደርግ መንግስት አመራሮች ሲጠየቁ በምላሹ 'የመንፈሳዊ አባት ኀላፊነት አንድ ሰው ያለወንጀሉ እንዳይገደል መምከር እና ማስተማር ነው' ብለው መልስ ሰጥተዋል።

  • 2) በ1966 ዓም 'አዲስ ኅይወት' በተሰኘችው የቤትክርስትያን መፅሄት በፃፉት ፅሁፋቸው ወታደራዊ አገዛዝን ብቻ ያማከለ ስርዐት ለሐገሪቷ የሚፈለገውን የህግ የበላይነት ሊያመጣ እንደማይችል፤ የልቁንም አመራሩ ወታደራዊ መሪዎችን ብቻ ሳይሆን ሁሉንም የማህበረሰብ ክፍሎች የወከለ ስብጥር ሊኖረው እንደሚገባ ፅፈዋል።

  • 3) በዚሁ መፅሄት ደርግ የቤተክርስትያንን ሃብቶች መውረሱ ተገቢ እንዳልነበር እና የእግዚብሔርንም እንደሚያሥቆጣ ፅፈዋል። ከዚሁም በተያያዘ ለአገዛዙ ይህ ድርጊት የቤተክርስትያኗን መብት የጣሠ መሆኑን የሚያስረዳ ደብዳቤ ለአመራሩ ልከዋል።

  • 4) የግርማዊ ቀዳማዊ ኃይለሥላሴ ሞት በመንግስት አካላት ይፋ ሲደረግ ከሁለት ሌሎች ጳጳሳት ጋር በመሆን የደርግ ፅፈት ቤት ድረስ በመሄድ የአፄ ኃይለ ስላሴን አስከሬን በቤተክርስትያን ህግ እና ስርዐት መሰረት የፍትሃት እና ቀብር ስነስርዐት እንዲፈፀምለት ጠይቀዋል። ነገር ግን በአገዛዙ እንደተከለከሉ ይነገራል።

  ከእነዚህ ክስተቶች በሇላ በተፈጠረ አንድ የቤተክርስትያን ክስተት ነበር እንግዲህ የደርግ አገዛዝ በቤተክርስትያን አመራሮች ላይ ቀጥተኛ እርምጃ መውሰድ የጀመረው። ይሀውም ክስተት ብፁዕ አቡነ ቴዎፍሎስ የቤተክርስትያኗ መዋቅሮች እየሰፉ በመሆኑ ይህን መዋቅር ሊያስተዳድሩ የሚችሉ ተጨማሪ ጳጳሳት እንደሚያስፈልግ በመግለፅ ሶስት እጩዎችን ለሲኖዶሱ በማቅረብ በ1968 ዓም የጵጵስና ሹመትን ያሰጣሉ። በዚህ ጊዜ ነበር የደርግ አመራሮች በቤተክርስትያን ጉዳይ ጣልቃ በመግባት የተሾሙትን ሦስት ጳጳሳት ያሰሩት። ከጥቂት ቀናት በሇላም አቡነ ቴዎፍሎስን ወደ እስርቤት እንዲገቡ ተደረገ።

  ደርግ ከእስሩ በሇላ ነገሩን የሚያጣራ ኮሚቴ በማቇቇም ክስ እንዲመሰረትባቸው አደረገ። የዚህ ኮሚቴ አባላት ከፓትርያርኩ ጋር በስልጣን ሽሚያ እና በዘር ምክንያት የማይጣጣሙ የቤተክርስትያን አባላትን የያዘ እንደነበርም ይነገራል። በፓትርያርኩ አቡነ ቴዎፍሎስ ከተመሰረቱባቸው ክሶችም ውስጥ ዋና ዋናዎቹ የሚከተሉት ናቸው።

  1) አቡነ ቴዎፍሎስ በብቃታቸው ሳይሆን ከአፄ ኃይለ ስላሴ ጋር በነበራቸው የቀረበ ወዳጅነት ምክንያት የፓትርያርክ ማዕረጉ ለእሳቸው ተሰቷል።

  2) የካፒታሊስት ስርዐት አመለካከት አላቸው። ለዚህም እንደምስክርነት ትላልቅ ቤቶችን አሰርተው እንደሚያከራዩ ተተቅሷል። 

  3) በስማቸው ሃያ የባንክ ሂሳብ መኖሩ እና በጏደኞቻቸው እና ዘመዶቻቸው ስም ተጨማሪ ሂሳቦች መኖራቸው፤ በእነዚህ የባንክ ሂሳብ ውስጥም በአጠቃላይ 4,029,350 ብር አከማችተዋል
  ብፁዕ እቡነ ቴዎፍሎስ በፅሁፍ ባስቀመጡት የኑዛዜ ቃላቸው የተመሰረተባቸው ክስ የውሸት ክስ እንደነበር ገልፀው፣ የባንክ ብድር ወስደው ትልቅ የሚከራይ ቤት እንደሰሩና ገቢውንም ላደጉበት ለደብረ ኤልያስ ቤተ ክርስትያን እና ለጎፋ ገብርኤል ቤተክርስትያን ማሰሪያ እና ማሣደሻ እንደሆነ ገልፀዋል። የኑዛዜ ቃላቸውም የወደፊት ገቢውን ሁለቱ ቤተክርስትያኖች ገቢውን ለሁለት እንዲካፈሉት ገልፀዋል።

  ባንክ አካውንቶችንም በተመለከተ፣ ሲታሰሩ እጃቸው ላይ የተገኘ ግን በስማቸው ያልሆነ (በተቇማት ስም የተከፈቱ) አምስት ብቻ የባንክ ደብተሮች ብቻ እንደነበሩ ለመረዳት ተችሏል። እነዚህም ደብተሮች ሲታሰሩ ለሚመለከታቸው ተቇማት ማናጅመንቱን እንዲረከቡት ተሰቷቸዋል። እነኝህ የባንክ ደብቶሮች በሚከተሉት ተቇማት ስም የተከፈቱ እንደነበር ለማወቅ ተችሏል።
  1) በኬንያ በሚሰራ ቤተክርስትያን ስም የተከፈተ ሂሳብ
  2) ጎፋ ገብርኤል ማሰሪያ የተከፈተ ሂሳብ
  3) ለቲዎሎጅ ኮሌጅ ገቢ ማሰባሰቢያ የተከፈተ ሂሳብ
  4) የቤተ ክርስትያኗ አጠቃላይ ገቢ ሂሳብ
  5) የሐረር አካባቢ ቤተክርስትያኖች ገቢ ሂሳብ
  እነኝህንም የባንክ ሂሳቦች በበላይነት ይከታተሉ እንደነበር ታውቇል።

  ምንጭ:-
         1) http://www.dacb.org/stories/ethiopia/tewoflos2.html
         2)  ዜና ጳጳሳት ኢትዮጵያውያን (ዲ/ን መርሻ አለሀኝ)
 • loader Loading content ...