loader
 • ስለ ማኅበሮች መክሠርና የመጠበቂያ ስምምነቶች የሚጸኑ ልዩ ውሳኔዎች (የ፲፱፻፶፪ ዓ.ም. የንግድ ሕግ አዋጅ ፥ አንቀጽ ፬።)

  @በህግ አምላክ   3 months ago
  ህግን አለማወቅ ከተጠያቂነት አያድንም!
 • loader Loading content ...
 • @በህግ አምላክ   3 months ago
  ህግን አለማወቅ ከተጠያቂነት አያድንም!


  የ፲፱፻፶፪ ዓ.ም. የንግድ ሕግ አዋጅ። የኪሣራና የመጠበቂያ ስምምነት። አንቀጽ ፬። ስለ ማኅበሮች መክሠርና የመጠበቂያ ስምምነቶች የሚጸኑ ልዩ ውሳኔዎች።


  ቁጥር ሺ፻፶፬። የጠቅላላ ደንቦች ተፈጻሚነት።

  ከዚህ በፊት ባሉት አንቀጾች የተነገሩት ደንቦት ሳይነኩ ማኅበሮች በዚህ አንቀጽ ውሳኔዎች ይመራሉ።


  ቁጥር ሺ፻፶፭። የመክሠር ማስታወቂያ ፍርድ ሊሰጥባቸው የሚችሉ ማኅበሮች።

  (፩) ከእሽሙር ማኅበሮች፤ በቀር ማቸውም የንግድ ማኅበሮች ሁሉ የመክሠር ማስታቅያ ፍርድ ሊሰጥባቸው ወይም የመጠበቂያ ስምምነት ለማግኘት ሊፈቀድላቸው የሚችሉ ናቸው።

  (፪) ሒሳቡን በማጣራት ያለ ማኅበር የመክሠር ማስታወቂ ፍርድ ሊሰጥበት ይችላል።

  (፫) ማኅበሩ በመሥራት ላይ መኖሩ ከተረጋገጠ፤ በሕግ ፈራሽነቱ በተገለጸ ማኅበር ላይ እነዚህ ውሳኔዎች ተፈጻሚዎች ይሆናሉ።


  ቁጥር ሺ፻፶፮። የመክፈልን መቋረጥ ስለ ማስታወቅ።

  በቁጥር ፱፻፸፪ መሠረት ያንድ ማኅበርን መክፈል ማቋረጥ የሚያስታውቀው፤ ሕጋዊ ከሆኑ እንደራሴዎች አንዱ ነው። ማኅበሩ ሒሳቡን በማጣራት ላይ የሆነ እንደ ሆነ፤ ይህን ማስታወቂያ ማድረግ ግዴታ ያለበት ሒሳብ አጣሪው ነው።


  ቁጥር ሺ፻፶፯። ስለ ፍርድ ቤት ሥልጣን።

  (፩) የሥርው ዋና ጽሕፈት ቤት ባለበት ቦታ ባለሥልጣን የሆነው ፍርድ ቤት በመክሠር ረገድ የሚቀርበውን ክስና ሥርዐት ለማየት ሥልጣን አለው።

  (፪) የኢንተርናሲዮናል ስምምነቶች እንደ ተጠበቁ ሆነው፤ የሥራው ዋና ጽሕፈት ቤት እውጭ አገር በመሆኑ የመክሠሩን ጉዳይ የውጨ አገር ፍርድ ቤት ያየውም ቢሆን፤ የኢትዮጵያ ፍርድ ቤት የመከሠሩን ጉዳይ ለማየት ሥልጣን አለው።


  ቁጥር ሺ፻፶፰። ሳይከፋፈል የአንድነትና ወሰን የሌለው አላፊነት ያላቸው ማኅበረተኞችስላሉበት ማኅበር መክሠር።

  (፩) የኅብረት የሽርክና ማኅበር ሲሆን፤ ማኅበረተኞች ሁሉ፤ ሁት ዐየነት ኅላፊነት ያለበት የሸርክና ማኅበር ሲሆን፤ ያልተወሰነ ኅላፊነት ያለባቸው ማኅበረተኞች ሁሉ እነርሱን ለሚመለከቱ ጉዳዮች በቁጥር ሺ፻፶፮ የተመለከተውን ማስታወቂያ፤ ማኅበሩ መክፈሉን ካቋረጠ በሐያ ቀን ውስጥ፤ መስጠት አለባቸው።

  (፪) ሳይከፈል የአንድነትና ያልተወሰነ ኅላፊነት ያለባቸው ማኅበረተኞች ያሉበት ማኅበር መክሠር፤ ወዲያውኑ የነዚህን ማኅበረተኞች መክሠር ያስከትላል።


  ቁጥር ሺ፻፶፱። ስለ አላፊነት የሚደረግ ክስ።

  በቁጥር ፫፻፷፭ እና ፫፻፷፮ መሠረት በመርማሪዎች፤ በዋና ሥራ አስኪያጆችና በሒሳብ አጣሪዎች ላይ በአላፊነት የሚቀርበውን ክስ፤ በመርማሪው ዳኛ ፈቃድ የገንዘብ ጠያቂዎቹን ኮሚቴ ሐሳብ ሰምቶ ንብረት ጠባቂው ይፈጽመዋል።


  ቁጥር ሺ፻፷። የጋራ መክሠርን ስለ ማስታወቅ።

  (፩) የአክሲዮን ማኅበር ወይም አላፊነቱ የተወሰነ የግል ማኅበር የከሠረ እንደ ሆነ፤ በዚህ ማኅበር ውስጥ ተግባሮቹን በመሸፈን ለራሱ ጥቅም የንግድ ሥራዎችን ሠርቶ በማኅበሩም ገንዘብ እንደ የግል ገንዘቡ አድርጎ የተጠቀመ ማናቸውም ሰው ሁሉ፤ በማኅበሩ ላይ የተሰጠው የመከሠር ፍርድ በርሱም ላይ በጋራ እንዲጻናበት ሊደረግ ይቻላል።

  (፪) በንኡስ ቁ (፩) የተመለከተው ውሳኔ፤ ሁለት ዐየነት ኅላፊት ያለበት የሸርክግ ማኅበር አስተዳደር ውስጥ በገቡት የተወሰነ ኅላፊነት ባለባቸው ማኅበረተኞች ላይ ይፈጸማል።


  ቁጥር ሺ፻፷፩። ሥራውን የተወ በአንድነት ሳይከፋፈል አላፊ ስለ ሆነ ማኅበረተኛ።

  (፩) ማኅበሩ መክፈሉን ያቁረጠው፤ ማኅበረተኛው ከመሰረዙ በፊት የሆነ አንደ ሆነ፤ ማኅበረተኛው ከንግድ መዝገብ ከተሰረዘበት ጊዜ አንሥቶ እስከ አንድ ዓመት ድረስ ሳይከፋፈል የአንድነት አላፊነት ያለበት ማኅበረተኛ መክሠር እንዲገለጽ ለመጠየቅ ይቻላል።

  (፪) ሳይከፋፈል በአንድነት አላፊ የሆነው ማኅበረተኛ በንግድ መዝገብ ያልተመዘገበ የሆነ እንደ ሆነ፤ ሥራውን ከተወ በኋላ በማናቸውም ጊዜ መክሠሩ እንዲገለጽ ለመጠየቅ ይቻላል።


  ቁጥር ሺ፻፷፪። በማኅበሩ የውስጥ ደንብ ለመክፈል ከተወሰነው ጊዜ በፊት መዋጮዎቹ እንደገቡ ስለ መጠየቅ።

  በማናቸውም ማኅበር በማኅበሩ የውስጠ ደንብ ለመክፈያ ከተወሰነው ጊዜ በፊት ቢሆንም እንኳን፤ ንብረት ጠባቂው ያልተገቡት መዋጮዎች እንዲገቡ ለማስገደድ ይችላል።


  ቁጥር ሺ፻፷፫። ሳይከፋፈል በአንድነት ኅላፊነት ስለ አለባቸው ማኅበረተኞች መክሠር ሥነ ሥርዐት።

  (፩) የማኅበሩንና ሳይከፋፈል በአንድነት ኅላፊዎች የሆኑትን ማኅበረተኞች መክሠር ፍርድ ቤቱ በአንድ ፍርድ ይገልጻል። እንደ ደንቡም አንድ መርማሪ ዳኛና አንድ የንብረት ጠባቂ የሾማል። ነገር ግን የማኅበሩ ንብረት ከማኅበረተኞቹ ንብረት እንደ ተለየ የቆያል። የያንዳንዱም መክሠር ኅብረት በተለይ ይቋቋማል።

  (፪) በማኅበሩ መክሠር ውስጥ የገንዘብ መጠየቂያ መብታቸውን ያቀረቡ ገንዘብ ጠያቂዎች በሚገባቸው ገንዘብ ልክ በየአንዳንዱ ማኅበረተኛ መክሠር ውስጥ መብታቸው እንዲታወቅላቸው እንዳቀረቡ የቆጠራሉ።

  (፫) መክፈል ከሚገባቸው በላይ ስለ ከፈሉት ገንዘብ የያንዳንዱ ማኅበረተኛ መክሠር በሌላው ማኅበረተኛ መክሠር ላይ ክስ ለማቅረብ የተሰጠው መብት ሳይነካ፤ ከማኅበሩ ላይ ገንዘብ ጠያቂ የሆነው ሰው፤ ገንዘቡ በሙሉ እስኪከፈለው ድረስ፤ በሚደረጉት ክፍያዎች ሁሉ ተካፋይ ለመሆን መበት አለው።

  (፬) ከማኅበረተኞቹ ላይ የግል ገንዘብ ጠያቂ የሆኑት ሰዎች በብታቸው ሊሠሩበት የሚችሉት፤ ባለዕዳ በሆናቸው ማኅበረተኛ መክሠር ውስጥ ብቻ ነው።

  (፭) እያንዳንዱ ገንዘብ ጠያቂ፤ በእርሱ ጋራ ተካፋይ የሆኑትን ገንዘብ ጠያቂዎች መብት ለመቃወም ይችላል።


  ቁጥር ሺ፻፷፬። የስምምነት ሐሳብ ስለ ማቅረብ።

  (፩) በመክሠር ላይ ላለው ማኅበር የስምምነቱን ጥያቄ የሚፈርሙት የማኅበሩ ሕጋዊ እንደራሴዎች ናቸው።

  (፪) የኅብረት የሽርክና፤ ወይም ሁለት ዐይነት ኅላፊነት ያለበት የሽርክና ማኅበር በሆነ ጊዜ፤ የስምምነቱን ሐሳብና ሁኔታዎች ከማኅበሩ ዋና ገንዘብ ውስጥ ፍጹም የድምፅ ብልጫ ያላቸው ማኅበረተኞች እንዲቀበሉት አስፈላጊ ነው።

  (፫) የአክሲዮን ማኅበር ወይም ኅላፊነቱ የተወሰነ የግል ማኅበር በሆነ ጊዜ፤ ስምምነቱን የማጽደቁ ሥልጣን ለአስተዳዳሪዎቹ ካልተሰጠ በቀር፤ ለስምምነቱ የቀረበውን ሐሳብ ድንገተኛው ጠቅላላ ጉባኤ እንዲያጸድቀው አስፈላጊ ነው።


  ቁጥር ሺ፻፷፭። በአንድነት ሳይከፋፈል ኅላፊ የሆኑ ማኅበረተኞች ስላሉበት ማኅበር የሚደረግ ስምምነት።

  (፩) በአንድነትና ሳይከፋፈል ያልተወሰነ ኅላፊነት ያለባቸው ማኅበረተኞች ያሉበት ማኅበር ስምምነት በጠየቀ ጊዜ፤ ገንዘብ ጠያቂዎቹ ስምምነቱን ላንዱ ወይም ለብዙዎቹ ማኅበረተኞች ብቻ ሊፈቅዱላቸው ይችላሉ።

  (፪) እንዲሁም በሆነ ጊዜ፤ በጠቅላላው የማኅበሩ ንብረት የግዴታ ማጣራት አሠራር ይፈጸምበታል። ስምምነቱ የተፈቀደላቸውም ማኅበረተኞች የግለ ንብረት ከማጣራቱ ውጭ ይሆናል። በስምምነቱም የማኅበሩ ንብረት ባልሆነ ነገር ላይ ካልሆነ በቀር የድርሻ መክፈል ግዴታ ሊኖርበት አይችልም።

  (፫) የግል ስምምነት የተፈቀደለት ማኅበረተኛ ካንድነት አላፊነት ነጻ ይሆናል።


  ምንጭ:

  የ፲፱፻፶፪ ዓ.ም. የንግድ ሕግ

 • loader Loading content ...

Load more...