loader

Topics (59)


 • @Tesfaw   1 year ago
  Sewasewer
  ብራማ ወይም ብራህማ፣ህንዶች እንደ አምላክ የሚያመልኩት ነው። የብራማ ካህናት ደግሞ እንደዚያው እንደ ሕጋቸው፣ከኃጢያት ሁሉ የራቁ ንፅሃን ናቸው ይባላሉ። ከብራሃማ ካህናቶች አንዱ ወደ ገቢያ ወጥቶ፣የፍየል ወጠጤ ገዝቶ በጫንቃው ተሸክሞ... Read more
 • loader Loading content ...
 • @Tesfaw   1 year ago
  Sewasewer
  በስዌድን ሀገር፣በመናገሻው ከተማ በስቶኮልም አንድ ውሻ ያለው ሰው ነበር። ፍቅር ማለት ከልማድ የተነሳነውና ውሻው ጌታውን በጣም ይወደው ነበረ። ጌታውም ለውሻው እንደ ልጁ ያስብለት ነበር። ነገር ግን እንኩአን የውሻ ፍቅር፣የሰውም ፍቅ... Read more
 • loader Loading content ...
 • @Tesfaw   1 year ago
  Sewasewer
  በመስኮብ ሀገር ሶስት ሴቶች ልጆች ያሉት አንድ ሽማግሌ ነበር። ከሶስቱ አንዲቷ በመልኩአና በጥበቧ እጅግ ስመ ጥሩ ናት። አንድ ቀን ወደ ገብያ ሲወጣ፣ለጆቼ ሆይ ከገበያ ምን ገዝቼላችሁ ልምጣ አላቸው። ሁለቱ ልጆች ጌጥ ገዝተህልን ና አ... Read more
 • loader Loading content ...
 • @Tesfaw   1 year ago
  Sewasewer
  የጀርመኑ ንጉስ፣ ታላቁ፣ ፍሬድሪክ፣ የሚባሉት ወደ ጦርነት ሲሄዱ፣ የሰፈሩበትን ቦታ ጠላቶቻቸው እንዳያዩት ብለው፣ አንድ ሰው እንኩዋን በድንኩአኑ ውስጥ፣ መብራት እያበራ ፣ የኔን ትእዛዝ አፍርሶ፣ መብራት አብርቶ የተገኘውን፣ የሞት ፍ... Read more
 • loader Loading content ...
 • @Tesfaw   1 year ago
  Sewasewer
  የእንግሊዙ ንጉስ ፫ኛ ጆርጅ፣ለሽርሽር ወደ ባላገር ሄደው ሳሉ፣ደርቆሽ የሚያጭዱና የሚሰበስቡ ሰዎች ሁሉ ሰራቸውን እየተዉ ንጉሱን ለማየት ወደ መንደር ሔዱ። ንጉሡ ግን አንደኛ ወታደር መስለው ድርቆሽ ከሚታጨድቤት ቢሄዱ ካንዲት ሴት በቀ... Read more
 • loader Loading content ...
 • @Tesfaw   1 year ago
  Sewasewer
  ሁለት ድመቶች ባንድነት ይኖሩ ነበር። አይጥ ለማደንም ቢሆን፣ምናምን ለመስረቅ ቢሆን፣አይለያዩም ነበር። አንድ ቀን ካንዱ ቤት ወደ አንዱ ቤት፣ሽርሽር ሲሉ፣መስኮቱ የተከፈተ ቤት አገኙ። በዚያን ጊዜ ድምፃቸውን አጥፍተው፣ቀስ እያሉ በመስ... Read more
 • loader Loading content ...
 • @Tesfaw   1 year ago
  Sewasewer
  ብዙ በጎች ያሉት አንድ ሰው ነበረ። እርሱም በጎቹን ስጠብቅ በብዙ ጥንቃቄ ነው። የለመለመ ሳር ይመግባቸዋል፣የጠራ ውሃ ያጠጣቸዋል ፣ወደ ተራራ ላይ ቢወጡ በጥንቃቄ ያወርዳቸዋል፣የደከሙትንም ይሽከማቸዋል፣ወደ ማሳ ውስጥ እየገቡ ሲለቅሙ ... Read more
 • loader Loading content ...
 • @Tesfaw   1 year ago
  Sewasewer
  ቀበሮ እና ፍየል ባልንጀራነት ገጥመው ባንድነት ሲውሉ፣አንድ ቀን የፀሐይ ሙቀት እጅግ ፅንቶ ነበርና ሁለቱንም ዉሃ ጥም ያዛቸው። እንዲሁ ዉሃ እየፈለጉ ካንዱ ስፍራ ወደ ሌላ ሰፍራ ሲሮጡ የጉድጉአድ ውሃ አገኙ። ሁለቱም አጅግ ተጠምተዋል... Read more
 • loader Loading content ...
 • @Tesfaw   1 year ago
  Sewasewer
  በቀድሞ ዘመን አንድ ንጉስ ነበር። እርሱም እግዚአብሔር የሰጠውን የመንግሥቱን ሰራ ትቶ ተረት የሚያውቅ ሰው እያስፈለገ ተረት ሲሰማ ይውል ነበር ። ተርት የሚያውቁ ብዙ ሰዎች እየመጡ ተረታቸው እያለቀባችው ይሄዳሉ። ንጉሡ ግን እያደር ... Read more
 • loader Loading content ...
 • @Tesfaw   1 year ago
  Sewasewer
  መልካም የገና በዓል አይተመኘሁ፣ የገና እና የጥምቀት በዓላት ሲደርሱ በምእመናኑ ዘወትር የሚጠየቁ ጥያቄዎች እና መልሶቻቸው የሚለውን የሚከተለውን ፀሁፍ እንድታነቡ እጋብዛለሁ። ጥያቄ ገና እና ጥምቀት ዓርብ እና ረቡዕ ቢውሉ ይበላባቸዋ... Read more
 • loader Loading content ...
  Load more...
loader Loading content ...

Explanations (104)


 • @Tesfaw   1 year ago
  Sewasewer

  ብራማ ወይም ብራህማ፣ህንዶች እንደ አምላክ የሚያመልኩት ነው። የብራማ ካህናት ደግሞ እንደዚያው እንደ ሕጋቸው፣ከኃጢያት ሁሉ የራቁ ንፅሃን ናቸው ይባላሉ።

  ከብራሃማ ካህናቶች አንዱ ወደ ገቢያ ወጥቶ፣የፍየል ወጠጤ ገዝቶ በጫንቃው ተሸክሞ ወደ ቤቱ ሲመለስ ሶስት አታላዮች አዩት። እነርሱም ይህን ካህን እናታለው ብለው ተማከሩና ቀደም ቀደም እያሉ ሂደው በሶስት ስፍራ ላይ እየተቀምጡ ቆዩት።

  በመጀመርያ አንደኛው አታላይ አገኘው፣የብራማ ካህን ሆይ እርስዎ ፣ቅዱስ፣ንፁህ ሆነው ሳሉ ስለምን ርኩስ ዉሻ በጫንቃዎ ተሽክመዋል አለው። ካህኑ መለሱ፣ወዳጄ ሆይ ፍየል ነው እንጂ ውሻ አይደለም አለው።

  ጥቂትም እንዳለፈ ሁለተኛው አታላይ አገኘው። የብራማ ካህን ሆይ እርስዎ ፣ቅዱስ፣ንፁህ ሆነው ሳሉ ስለምን ርኩስ ዉሻ በጫንቃዎ ተሽክመዋል አለው። ካህኑም ያንን ፍየል ከጫንቃው ላይ አውርዶ እንደገና እያገላበጠ ያይ ጀመረ። ካየም ቦኃላ ወዳጄ ሆይ ፍየል ነው እንጂ ውሻ አይደለም ብሎ ተሸክሞ ሄደ።

  ከዚያ ደግሞ ጥቂት እንዳለፈ ሶስተኛው አታላይ አገኘው። የብራማ ካህን ሆይ እርስዎ፣ ቅዱስ፣ንፁህ ሆነው ሳሉ ስለምን ርኩስ ዉሻ በጫንቃዎ ተሽክመዋል አለው።

  ከዚያ ቦሀላ ያ የብራማ ካህን ሶስተኛ ይህን ነገር በሰማ ጊዜ ያየው ሰው ሁሉ ውሻ ነው እያለ ሲመስክር እኔ ብቻዬን ፍየል ነው እላለሁ ብሎ ፣ከጫንቃው አውርዶ ወርውሮ ጥሎት ሄደ። እንዚያም አታላዮች ያንን ፍየል ይዘው ወደ ቤታቸው ወስደው አርደው በሉት።

  ልጆቼ ሆይ በምንም በምን ቢሆን ሰውን አታታሉ። እናንተም በምንም በምን ቢሆን አትታለሉ። አውቆ የሰሩት ሥራ ነው እንጂ ተታሎ የሰሩት ሥራ እንዳይጠቅም እወቁ።

  ምንጭ፣ የልጆች ማሳደጊያ በብላቴን ጌታ ኅሩይ ወልደ ሥላሴ   

 • loader Loading content ...
 • @Tesfaw   1 year ago
  Sewasewer

  በስዌድን ሀገር፣በመናገሻው ከተማ በስቶኮልም አንድ ውሻ ያለው ሰው ነበር። ፍቅር ማለት ከልማድ የተነሳነውና ውሻው ጌታውን በጣም ይወደው ነበረ። ጌታውም ለውሻው እንደ ልጁ ያስብለት ነበር። ነገር ግን እንኩአን የውሻ ፍቅር፣የሰውም ፍቅር ቢሆን ከሞት አያድንምና ፣ጌትየው ታመመና ሞተ። ዉሻውም ጌታው ከታመመ ጀምሮ እስኪሞት ድረስ ካልጋው ሰር አልተለየም። ከሞተም ቦሀላ ወደ ቤተክ ርስቲያን ሲወስዱት፣ሬሳውን ተከትሎ ሄደ። በዚያም መቃብር ቆፍረው ስቀብሩት አየ። ከተቀበረ ቦሀላ ግን፣ሰዎቹ ሁሉ ወደቤታቸው ሲገቡ እርሱ እዚያው በመቃብሩ አጠገብ ቆመ፣ ቢጠሩትም፣ ቢመቱትም፣ ዝም ብሎ ቀረ። ማታ ማታም በመቃብሩ ላይ እየተኛ ያድር ጀመረ።

  አንዲት ሴት ወይዘሮ ወሬውን ሰምታ ራትና ምሳውን ትሰጠው ጀመረ። እንዲሁ የቀን ሃሩር፣የለሊት ቁር ሳይፈራ ብዙ ቀን በመቃብሩ ላይ ኖረ። ሴቲቱም እንደገና አስባ የብረድ ልብስ ሰደደችለት።

  ከብዙ ቀን ቦሀላ ራትና ምሳውን የምትሰድለት ወይዘሮ በድንገት ታመመችና ውሻውን የሚጠይቀው ሌላ ሰው ጠፋ።ውሻው ግን ይህን ሁሉ መከራና ችጋር ታግሶ እዚያው በጌታው መቃብር ላይ ሞተ።

  ሴቲቱም ከበሽታዋ ስትድን ትዝ አላትና፣ ሰው ልካ ብታሳየው፣ሞቶ ተገኘ። ከዚህ ቦሀላ እርሷ ራሷ ሄዳ በብዙ ሃዘን በዚያው በጌታው መቃብር አጠገብ አስቀበረችው።

  ልጆቼ ሆይ። እንኩአን ሰው እንስሳም ቢሆን ከወደዱት መውደዱ አይቀርምና፣ሁሉን ውደዱ። ወዳጃችሁንም በፍፁም ልባቹ ከውደዳችሁት በመከራችሁ ቀን አይለያችሁም።   

  ምንጭ፣ የልጆች ማሳደጊያ በብላቴን ጌታ ኅሩይ ወልደ ሥላሴ   
 • loader Loading content ...
 • @Tesfaw   1 year ago
  Sewasewer

  በመስኮብ ሀገር ሶስት ሴቶች ልጆች ያሉት አንድ ሽማግሌ ነበር። ከሶስቱ አንዲቷ በመልኩአና በጥበቧ እጅግ ስመ ጥሩ ናት። አንድ ቀን ወደ ገብያ ሲወጣ፣ለጆቼ ሆይ ከገበያ ምን ገዝቼላችሁ ልምጣ አላቸው። ሁለቱ ልጆች ጌጥ ገዝተህልን ና አሉት። አንዲቱ ግን እኔ ምንም አልፍልግም፣ነገር ግን የምመክርህን ምክር ስማኝ አለችው። ለግዜው ነገሩ ከበደው ነገር ግን ልጁ እጅግ ብልህ መሆኗን ያዋቃልና ይሁን ንገሪኝ አላት። ወይንማውን በሬ ወደ ገብያ አውጥተህ ስትሸጥ፣ ዋጋ ንገር ያሉህ እንደሆነ የንጉሱን ግራ አይኑን አምጡና ውሰዱ በላቸው አለችው። እርሱም በገብያ ተቀመጠና የበሬውን ዋጋ ንገር ሲሉት፣ ልጁ እንደመከረችው፣የንጉሱን ግራ አይኑን አምጡና ውሰዱ ይል ጀመረ።

  ይህንም ወሬ ንጉሡ ሰምቶ እጁን ይዛቹ አምጡልኝ ብሎ አዘዘ። ሽማግሌውም በቀረበ ጊዜ፣ንጉስ ሆይ እንደዚህ ያደረገችኝ ልጄ ናትና ማረኝ እያለ ይለምን ጀመረ። ንጉሱም ይህን በሰማ ጊዜ ሔደህ ልጅህን አምጣትና እምርሃለው አለው። ሽማግሌውም እያዘነና እየተንቀጠከጠ፣ሄዶ ልጁን ይዞ ወደ ንጉስ ቀረበ። ንጉሱም ልጅቱን ባያት ጊዜ ለበሬው ዋጋ የንጉሱን ግራ አይን አምጡና ውሰዱ በላቸው ብለሽ ለአባትሽ የመከርሽው ስለምን ነው አላት።

  ንጉስ ሆይ አልቀጣሽም ብለህ ማልልኝና እነግርሀለው አለችው። አልቀጣሽም ብሎ ማለላት። ንጉስ ሆይ ድሃና፣ ጌታ፣ተጣልተው ወዳንተ የመጡ እንደሆነ በቀኝ የቆመውን ጌታዉን ብቻ ታያለህ እንጂ፣በግራ የቆመውን ድሃውን አታይም ስለዚህ መቸም ግራ አይንህ ሥራ ካልያዘልህ ብዬ ነው አለችው ።

  ንጉሱም የልጅቱን ንግገር ሰምቶ እጅግ አድንቆ ወዲያዉም ወንድ ልጁን ጠርቶ፣ልጄ ሆይ፣በመልክና፣በእውቀት ከርሷ የምትሻል ሴት የለችምና እርሷን አግብተህ መንግስቴን ይዘህ ኑር አለው። ልጁም እርሷን አግብቶ እርሱ ንጉስ አርሷ ደግሞ ንግስት ተብለው ኖሩ።

  ልጆቼ ሆይ መልካም ንግግርና ጥበብ፣ስውን ታከብራለችና፣ንግግራችሁ ሁሉ በመልካምነትና ብጥበብ ይሁን። የጥበብ መጀመርያም እግዚአብሔርን መፍራት ነው።  

  ምንጭ፣ የልጆች ማሳደጊያ በብላቴን ጌታ ኅሩይ ወልደ ሥላሴ
 • loader Loading content ...
 • @Tesfaw   1 year ago
  Sewasewer

  የጀርመኑ ንጉስ፣ ታላቁ፣ ፍሬድሪክ፣ የሚባሉት ወደ ጦርነት ሲሄዱ፣ የሰፈሩበትን ቦታ ጠላቶቻቸው እንዳያዩት ብለው፣ አንድ ሰው እንኩዋን በድንኩአኑ ውስጥ፣ መብራት እያበራ ፣ የኔን ትእዛዝ አፍርሶ፣ መብራት አብርቶ የተገኘውን፣ የሞት ፍርድ እፈርድበታለሁ ብለው አዋጅ ነገሩ ።

  አንድ ቀን ማታ፣ በሰፈር መካከል፣ ብቻቸውን ሲመላለሱ ፣ አንዱ የወታደር አለቃ፣ አልታይም ብሎ፣ በድንኩዋን ዉስጥ፣ መብራት አብርቶ፣ ደብዳቤ ፅፎ ፣ማኅተም ለማተም ሲዘጋጅ በድንገት ደረሱበት ።

  አንተ ትዛዜን ማፍረሰህ ስለምን ነው አሉት ፣ጃንሆይ ፣አይቆጡኝ ለሚስቴ ደብዳቤ እፅፋለው ብዬ ነው አላቸው፣ እንግዲያውስ አንዲት ቃል ጨምረህ ፃፍ አሉት ፣እንዴት ብዬ አላቸው ።

  ይህ ደብዳቤ ሲደርስሽ፣ እኔ የንጉሥ ትዛዝ በማፍረሴ፣ ተፈርዶብኘ መሞቴን እወቂው፣ ብለህ ፃፍ አሉት። እርሱም ይህን ፅፎ አትሞ ላከ ፣ ንጉሱም በማግስቱ አስፈርደው ገደሉት።

  ልጆቼ ሆይ ፣ንጉስ እምቢተኞችን ሁሉ፣ ለመቅጣት ከእግዚአብሔር ሰይፍ ተቀብሏልና፣ የንጉስን ትእዛዝ ጠብቁ።

  ምንጭ፣ የልጆች ማሳደጊያ በብላቴን ጌታ ኅሩይ ወልደ ሥላሴ
 • loader Loading content ...
 • @Tesfaw   1 year ago
  Sewasewer

  የእንግሊዙ ንጉስ ፫ኛ ጆርጅ፣ለሽርሽር ወደ ባላገር ሄደው ሳሉ፣ደርቆሽ የሚያጭዱና የሚሰበስቡ ሰዎች ሁሉ ሰራቸውን እየተዉ ንጉሱን ለማየት ወደ መንደር ሔዱ። ንጉሡ ግን አንደኛ ወታደር መስለው ድርቆሽ ከሚታጨድቤት ቢሄዱ ካንዲት ሴት በቀር አንድ እንክዋን ሳያገኙ ቀሩ። ባልንጀሮችሽ ሁሉ የት ሄዱ ብለው ሴቲቱን ጠየቁዋት። ሴቲቱም መለሰች፣ንጉስ ወደባላገር መጥቶዋል ተብሎ ተወርቶ ነበርና እርሳቸውን ለማየት ሄዱ አለቻቸው።

  አንቺ ምነው ሳትሄጂ ቀረሽ አሏት፣ ንጉስ ወዳለበት ሲገባ ገንዘብ እየተከፈለ ነው፣እኔ ግን ደሃ ነኝና፣በዚያ የምከፍለው ገንዘብ የለኝም ፣ደግሞ አምስት ልጆች አሉኝና ለነዚያ ምግብ ስል ሰራ መፍታት አልወድም፣ ሰራም ካልሰራው ገንዘብ አይገኝም ብላ መለሰች። ይህንም ሁላ ስትናገር ንጉስ ጆርጅ መሆናቸውን አላወቀችም ነበር። ንጉሡ ግን የሶስት መቶ ብር ወርቅ ከኪሳቸው አውጥተው ሰጧት፣ወዲያውም ባልንጀሮችሽ ሲመጡ ንጉሡ እናንተን ለማየት መጥቶ፣እናንተ ሰራችሁን ትታችሁ ወደ ንጉስ ለምን ሄዳቹ፣እዚሁ በሰራችሁ ፀንታችሁ በቆያችሁ፣አሁን ንጉሡ መጥቶ ሳለ፣ሶስት ሶስት መቶ ብር ታገኙ ነበረ ብለሽ ንገሪያቸው ብለዋት እየጋለቡ ተመልሰው ሄዱ። እነዚያም ሰራተኞች ስራቸውን ሳይሰሩ፣ንጉሡንም ሳይዩ፣ገንዘብም ሳያገኙ፣እንዲያው በከንቱ ደክመው ቀሩ።

  ሌጆቼ ሆይ፣ በታዘዛቹበት ሥራ ፀንታችሁ ብትኖሩ፣ እግዚአብሔር፣ድካማችሁን ሁላ አይቶ የምትጠቀሙበትን ነገር ያዝላችዋል።   

  ምንጭ፣ የልጆች ማሳደጊያ በብላቴን ጌታ ኅሩይ ወልደ ሥላሴ
 • loader Loading content ...
 • @Tesfaw   1 year ago
  Sewasewer

  ሁለት ድመቶች ባንድነት ይኖሩ ነበር። አይጥ ለማደንም ቢሆን፣ምናምን ለመስረቅ ቢሆን፣አይለያዩም ነበር። አንድ ቀን ካንዱ ቤት ወደ አንዱ ቤት፣ሽርሽር ሲሉ፣መስኮቱ የተከፈተ ቤት አገኙ። በዚያን ጊዜ ድምፃቸውን አጥፍተው፣ቀስ እያሉ በመስኮቱ ዘለው ገቡ። በዚያም በእንቁላልና በስኩዋር በሌላም በሚጣፍጥ ነገር የተሰናዳ ምግብ በጠረቤዛ ላይ አዩ። በጉዋዳው አንድ ሰው እንክዋ፣ አለመኖርን አይተዋልና ባንድነት ዘለው ያንን የጣፈጠ ምግብ አፋቸው እንደቻለላቸው ይዘው በመስኮት እየሾለኩ ወጡ፣ከወጡም ቦሀላ በአታክልት ዉስጥ ተደብቀው ለመብላት ሁለቱም የያዙትን ቀላቅለው አስቀምጠው ስው እንዳያያቸው ግራ እና ቀኝ፣ይመለከቱ ጀመር። ለመብለም በቀረቡ ጊዜ አንዱ ክፍል ምግብ ካንዱ በልጦ አዩት በዚህም ምክንያት ትልቁ የኔ ነው፣የኔ ነው በማለት ሁለቱ ድመቶች ተጣሉ፣ምግቡንም ትተው እርስ በራሳቸው ይሞጫጨሩ ጀመሩ።   

  አንድ ጦጣም በአታክልቱ ዉስጥ ሁኖ የመለከታቸው ኖሮ በቶሎ እየሮጠ መጥቶ እርስ በራሳቹ ምን ያጣላቹዋል፣አሁን በአመጣቹት ምግብ ተጣልታቹ እንደ ሆነ የአታክልቱ ዉስጥ ዳኛ እኔ ነኝ እና ወደ ሸንጎ ቀርባቹ፣በዳኛ ፊት ነገራችሁን መጨረስ ነው አላቸው።

  ድመቶቹም ፣ይሁን ደግ ነው አሉ። እንግዲያውስ ኑ አለና ወደ ዛፍ ሰር ሄዶ በጥላው ውስጥ አስቻለ። ከዚህም ቦኃላ ፍርዱን ጀመረ፣ ይህን ምግብ ሁለታችሁም ባንድነት አይታችሁ አንስታችሁ የለምን አላቸው። አዎን ስንገባም ባንድነት፣ስናየውም ባንደነት ስናነሳውም ባንድነት ነው አሉ። እንግዲያዉስ ትክክል ተካፈሉ ነገር ግን ትክክል ለመካፈል ሚዛን ያስፍልጋልና፣ ሚዛን አምጥታችሁ ላካፍላችሁ አላቸው። ይሁን ብለው ሚዛን አመጡ።

  ቢመዝነው በእውነትም አንዱ ክፍል ትልቅ ኑሮ ሚዛኑ ደፋ። ዳኛዉም፣አንዱ መብለጡን አይቶ፣ልክ ላግባላቹ ብሎ ከሚዛኑ ላይ አነሳና አንድ ጊዜ ጎመጠለት። መልሶ ብመዝነው ደግሞ ያ ትንሽ የነበረው በዛና ሚዛኑ ዳፋ፣ድግሞ ያንን አንድ ጊዜ ጎመጠና መልሶ ቢመዝነው ፣የፊተኛው ሚዛን ደፋ፣ሦስተኛ አንስቶ እገምጣለው ሲል፣ድመቶቹ ነገሩን አዩና ዳኛ ሆይ፣ተወው፣ተወው እኛው ተስማምተን እንካፈለዋለን ስጠን አሉት።

  ዳኛው ጦጣ መለሰ ፣እመቤቶቼ ሆይ፣እናንተ እንዲህ ብትሉ መቸ ይሆናል፣ ያኔ ስራ አይደለምን፣ሳላስተካክል ብሰጣችሁ ፍርድ መጉደሉ አይደለምን አለና ደግሞ አንድ ጊዜ ጎመጠለት። እንደዚሁ ከዝያም፣ ከዝያም እየጎመጠ ጨረሰና ጥቂት ሲቀረው ቢመዝነው ትክክል ሆነ ፣እነሆ አሁን ትክክል ሆነላችሁ አላቸው። እንግድያውስ ሰጠን አሉት።

  ጦጣ መለሰ፣ቆዩ አላቸው፣እናንት ነገሩ ሁሉ በመቸኮል የሚሆን ይመስላቹዋል፣እኔ ስራዬን ሁሉ ትቼ እስካሁን ድረስ በናንተ ነገር ደክሜ፣ደክሜ እንዲያው ልቀር ነውን፣ ይህስ የዳኝነቴ ነው፣አለና ያንኑ የተረፈውን ወደ አፉ አድርጎ ችሎት ተመለሰ።

  ድመቶቹም እያዘኑ ወደ ስፈራቸው ሄዱ።

  ልጆቼ ሆይ፣ከባልንጀራችሁ ጋራ በተጣላችሁ ጊዜ፣ቢቻላችሁ፣ነገሩን ትታችሁ ተቀመጡ። ባይቻላችሁ ግን በዘመድ እና በወዳጅ ተዋቅሳችሁ ታረቁ እንጂ ወደ ዳኛ ለመሄድ አትቸኩሉ።

  ምንጭ፣ የልጆች ማሳደጊያ በብላቴን ጌታ ኅሩይ ወልደ ሥላሴ።

 • loader Loading content ...
 • @Tesfaw   1 year ago
  Sewasewer

  ብዙ በጎች ያሉት አንድ ሰው ነበረ። እርሱም በጎቹን ስጠብቅ በብዙ ጥንቃቄ ነው። የለመለመ ሳር ይመግባቸዋል፣የጠራ ውሃ ያጠጣቸዋል ፣ወደ ተራራ ላይ ቢወጡ በጥንቃቄ ያወርዳቸዋል፣የደከሙትንም ይሽከማቸዋል፣ወደ ማሳ ውስጥ እየገቡ ሲለቅሙ ባጠገባቸው ተቀምጦ ዋሽንት ይነፋላቸዋል፣በጎቹም ዋሽንቱን እየሰሙ እጅግ ደስ ይላቸዋል።

  ሲመሽም እንዳይበርዳቸው ወደ መልካሙ ጉረኖዋቸው አግብቶ ያጉራቸዋል። አውሬም እንዳያስደንግጣቸው ውሾች በውጭ ሆነው ይጮውላቸዋል። ካንዱ ግልገል በቀር ሁሉም ጠባቂያቸውን ይወዳሉ። ያ አንዱ ግልገል ግን ጠባቂውን አይወድም ነበርና ማታ ማታም ወደ ጉረኖው መግባት አይወድም ነበር። አንድ ቀን ወደ እናቱ ቀርቦ እናቴ ሆይ እኛ ማታ ማታ ለምን ይዘጋብናል እንሆ ውሾች ሳይዘጋባቸው በደህና ያድራሉ፣አሁንም ማታ እናንት ስትገቡ እኔ ተደብቄ ቀርቼ በጨረቃ ብረሃን ከወዲያ ወዲህ እየሮጥሁ ደስ ሲለኝ ልደር አላት ።

  እናትቱ መለሰች ፣ ልጄ ሆይ አርፈህ ተቀመጥ፣ጠባቂያችን እጅግ መልካም ሰው ነው፣እርሱ እንዳዘዘን ውለን ብንገባ ይሻላል፣ እምብ ያልህ እንደሆነ ግን በራስ ላይ ጥፋትን ታመጣለህ አለችው።

  ግልገሉም ይህን በሰማ ጊዜ እናቴ ሆይ ፣መልካም ምክር አልመከርሽኝም እኔስ ያሰብሁትን ሳላረገው አልቀርም አላት።

  ከዚህ ቦኃላ ጠባቂያቸው ማታ በጎቹን ሁሉ ነድቶ ወደ ቤቱ ሲመልስ ያ ግልገል ወደ ጉረኖው የገባ መስሎ ባጥር ውስጥ ምናምኑን ከለላ ሰጥቶ ቀረ። ጠባቂውም ግልገሉ ቀደም ብሎ የገባ መስሎት አጉሮባቸው ወደ ቤቱ ገባ።

  ጊዜው ሲጨልም እና በጎቹ ሁሉ ለጥ ብለው ሲተኙ እርሱ ከተደበቀበት ስፍራ ተነስቶ እየሮጠ ወደ ዱር ተመለሰ። በዚያም ወዲያ እና ወዲህ እየሮጠ ሲጫወት አንድ ተኩላ አይቶት ኑሮ በድንገት ደረሰበት ወደ ጉረኖውም ለመሮጥ ቢያስብ ሩቅ ነበርና የማይሆንለት ሆነ ፣ከዚህ ቦሀላ ተኩላው ታቅፎ ወስዶ ጉድግዋድ ውስጥ አግብቶ ገነጣጥሎት በላው።

  ልጆቼ ሆይ ፣ያባትና የናታቸውን ምከር የማይሰሙ ልጆች እንደዚህ ይሆናሉና፣የቤተስብን ምክር እንዳትንቁ ተጠንቀቁ።

  ምንጭ፣ የልጆች ማሳደጊያ በብላቴን ጌታ ኅሩይ ወልደ ሥላሴ።

 • loader Loading content ...
 • @Tesfaw   1 year ago
  Sewasewer

  ቀበሮ እና ፍየል ባልንጀራነት ገጥመው ባንድነት ሲውሉ፣አንድ ቀን የፀሐይ ሙቀት እጅግ ፅንቶ ነበርና ሁለቱንም ዉሃ ጥም ያዛቸው። እንዲሁ ዉሃ እየፈለጉ ካንዱ ስፍራ ወደ ሌላ ሰፍራ ሲሮጡ የጉድጉአድ ውሃ አገኙ።

  ሁለቱም አጅግ ተጠምተዋልና የኃላ መውጫቸውን ሳያስቡ ባንድ ጊዜ ዘለው ወደ ጉድጉአድ ውስጥ ገቡ። ዉሃዉንም እንደጠገቡ ከጠጡ ቦሀላ የመውጫቸው ነገር ትዝ አላቸውና ያስቡ ጀመሩ፣ ብዙም ልዩ ልዩ አሳብ አሰቡ ግን አልሆነላቸውም። ከዚያ ቦሀላ መቸም ቀበሮ ተንኮለኛ ነውና ወዳጄ ፍየል ሆይ እኔ አንድ መልካም አሳብ አገኘው አለው፣ እንግዲህ አንተ በጣም ጠንክረህ ቦኃላ እግረህ ቁም በፊት እግርህም ግራና ቀኝ አንፈራጠህ በቀንድህ እና በግንባርህ የጉድጉአዱን መሬት ተደግፈህ ቁም ፣ እኔ በጀርባህ ላይ ተንጠላጥዬ ከወጣሁ ቦሀላ ቀንድህን ይዤ ሽቅብ አየጎተትሁ አወጣሃለው አለው። ሞኙ ፈየል ሆይ እውነት መሰለውና ቀበሮ እንደነገረው አደረገ። ቀበሮም በፈየል ጀርባ ላይ ተንጠላጥሎ ወጣ። ከዚህ ቦሀላ ፈየል ራሱን ቀና አደረገና በል እንግዲህ ሽቅብ ጎትተህ አውጣኝ አለው። 

  ቀበሮ መለሰ ፣ ፈየል ሆይ አንተ ሽማግሌ ነህ ፣ ጢምም አውጥተሃል ፣ በእውቀት ግን ገና ሕፃን ነህ። እኔስ አንድ ጊዜ ከውጣው ቦሀላ አንተን ጎትቼ አወጣለሁ ብዬ ሁለተኛ ሰውነቴን አላጠፋም። የሆነ ሆኖ ባልንጀራዬ ነህና አንድ ምክር ልምከርህ ፣ ከእንግዲህ ወዲህ መውጫህን ሳታስብ ወደ ጉድጉአድ ዘለህ አትግባ ብሎ ጥሎት ሄደ።

  ለጆቼ ሆይ ፣ ቃሉን አፍርሶ በተንኮል ከዳነው ቀበሮ ይልቅ ፣ በቃሉ ፀንቶ በጉድጉአድ ዉስጥ የሞተው ፈየል ይሻላል። ስለዚህ ባልንጀራችሁም የሚጠቀምበተን ሰራ ሰሩ አንጂ እናንተ ብቻ የምትጠቀሙበትን ሥራ አትስሩ።    

  ምንጭ፣ የልጆች ማሳደጊያ በብላቴን ጌታ ኅሩይ ወልደ ሥላሴ

 • loader Loading content ...
 • @Tesfaw   1 year ago
  Sewasewer

  በቀድሞ ዘመን አንድ ንጉስ ነበር። እርሱም እግዚአብሔር የሰጠውን የመንግሥቱን ሰራ ትቶ ተረት የሚያውቅ ሰው እያስፈለገ ተረት ሲሰማ ይውል ነበር ። ተርት የሚያውቁ ብዙ ሰዎች እየመጡ ተረታቸው እያለቀባችው ይሄዳሉ። ንጉሡ ግን እያደር የተርት ፍቅር እየፅናበት ይሄድ ጀመረ። ከእለታት አንድ ቀን ወረቀቱንና ቀለሙን አቅርቦ እኔ በቃኝ እስክል ድረስ አዲስ አዲስ ተርት የምነግረኘ ሰው የተገኘ እንደሆነ ልጄን አጋብቼ መንግስቴን አወርሰዋለው ብሎ ፅፎ ማኅተሙን አተመ። እንዲህ ማለቱ ግን መቸም ብዙ ተርት የሚያውቅ ሰው አይገኘም ብሎ ነበር።

  ከዚያም ቦሃላ ይሄ ወሬ በያገሩ ደረሰና አንድ ብልህ ሰው መጥቶ እኔ ለንጉሡ በቃኝ እስኪል ድረስ ተርት እንግራቸዋለሁና ንገሩልኝ አለ። ንጉሱም በሰማ ጊዜ እጅግ ደስ አለው። የውሉንም ወረቀት ሰጠው። ከዚህም ቦሀላ ተረቱን ሊነግር ጀመረ።

  ንጉስ ሆይ አንድ ባለጠጋ ሰው አዝመራውና መከሩ አማረለት እንደ አማረለትም ካየ ቦሀላ ስንዴውን የሚያኖርበት ታላቅና ሰፊ ጎተራ ሰራ ፣የጎተራውም ርዝመቱ ሰላሳ ክንድ ወርዱ ሃያ ክንድ ቁመቱ አስር ክንድ ነበር ።

  በመክርም ወራት ስንዴውን ወቅቶ በጎተራው ሞልቶ አስቀመጠ። ነገር ግን በሙቀቱ ምክንያት እንዳይነቅዝ ብሎ ለንፋስ መግብያ ትንሽ መስኮት አውጥቶለት ነበርና አንዲት ገብረ ጉንዳን በዚያ ገብታ አንዲት ቅንጣት ሰንዴ ይዛ ወጣች ብሎ ነገርው። ንጉሱም እሀ አለው። ደግሞ ሌላዋ ገብረ ጉንዳን ገባችና አንድ ቅንጣት ስንዴ ይዛ ወጣች አለው። ከዚያስ ወድያ አለው። ደግሞ ሌላይቱ ገብረ ጉንዳን ገባችና አንዲት ቅንጣት ስንዴ ይዛ ወጣች አለው። ከዚያ ቦሀላ ንጉሡ ተንስቶ ዛሬ ይበቃናል ነገ ደግሞ እንጨዋወታለን አለው ።

  በማግስቱም በማለዳ ንጉሡ መጥቶ ወደ መጫወቻቸው ቤት ገብቶ ተቀመጠ። ሰውዬውም ቀረበ፣ ንጉሱም እህ አለው። ደግሞ ሌላይቱ ገብረ ጉንዳን ገባችና አንዲት ቅንጣት ስንዴ ይዛ ወጣች አለው። ይህንማ ትናንትና ነግረህኝ የለምን አለው። ሰውዬው መለሰ። ንጉስ ሆይ ጎተራው እኮ ሰፊ ነው ፣ ስንዴው አላለቀም አለው። ንጉሱም ተቆጣና ተነስቶ ወደ ቤቱ ገባ።

  በማግስቱም በማለዳ መጥቶ ወደ መጫወቻው ቤት ገባ ሰውዬውም ቀረበ ንጉሡም እህ አለው። ደግሞ ሌላይቱ ገብረ ጉንዳን ገባችና አንድ ቅንጣት ስንዴ ይዛ ወጣች አለው። ንጉሱም ይህን በሰማ ጊዜ ይህንስ ትናንትና ነግረህኛል ሌላ ተርት የለህምን አለው። ተረተስ ሞልቶኛል አለው። ነገር ግን ስንዴው መቼ አለቀ። ጎተራው እኮ ሰፊ ነው አለው። እንዲህ እያለ አስራ አምስት ቀን ሙሉ አሰለቸው። በመጨረሻም ንጉሡ እንደ ልማዱ በመጫወቻው ቤት ገብቶ ተቀመጠ ሰውየውም ቀረበ ንጉሱም እህ አለው። ደግሞ ሌላይቱ ገብረ ጉንዳን ገባችና አንድ ቅንጣት ስንዴ ይዛ ወጣች አለው።

  ንጉሱም ተቆጣና ይህንማ ስትነግረኝ ሰነበትህ የለምን፣ ሌላ ተረት እንዳለህ  አምጣ አለው። ንጉስ ሆይ ተረትስ ሞልቶኛል ነገር ግን  የተጀመረውን ሳልጨርስ ሌላ መጀመር አይገባኝም። ጎተራው እጅግ ትልቅ ነው፣ ስንዴውም ብዙ ነው አለው።

  በዚያ ጊዜ ንጉሱም እጅግ ተናደደና ፣ሁለተኛ ይህን ተረት አትንገረኝ እጅግ ሰለቸኝ። ልጄንም ሰጥቼሃለው መንግስቴንም አውርሼሃለው አለው።

  ሰውዬውም የንጉሱን ልጅ አግብቶ መንግስቱን ወርሶ በዙፋኑ ተቀመጠ።

  ልጆቼ ሆይ የሚረባዉን ነገር ትታችሁ የማይረባዉን ነገር አትፈልጉ ። ቀልድና ጨዋታም አብዝታችሁ አትውደዱ።        

  ምንጭ፣ የልጆች ማሳደጊያ በብላቴን ጌታ ኅሩይ ወልደ ሥላሴ።

 • loader Loading content ...
 • @Tesfaw   1 year ago
  Sewasewer

  መልካም የገና በዓል አይተመኘሁ፣ የገና እና የጥምቀት በዓላት ሲደርሱ በምእመናኑ ዘወትር የሚጠየቁ ጥያቄዎች እና መልሶቻቸው የሚለውን የሚከተለውን ፀሁፍ እንድታነቡ እጋብዛለሁ።

  ጥያቄ

  ገና እና ጥምቀት ዓርብ እና ረቡዕ ቢውሉ ይበላባቸዋል ወይስ ይጾማሉ?

  መልስ 

  ፍትሐ ነገሥት ዳግመኛ በየሳምንቱ ዓርብ እና ረቡዕን መጾም ነው፡፡ በዓለ ሃምሳ፣ የልደት እና የጥምቀት በዓል የተባበሩባቸው ጊዜ ካልሆነ በቀር /ዐንቀጽ 15፣ ቁ566/

  የዓርብን እና የረቡዕን ጾም ግን ከልደት፣ከጥምቀት እና ከበዓለ ሃምሳ በቀር ዘወትር ይጹሙ /ዐንቀጽ 15፣ቁ 603/

  ******

  ጥያቄ

  የገና እና የጥምቀት ቅዳሴ ስንት ሰዓት ነው?

  ፍትሐ ነገሥት፡ ስለ ልደት እና ጥምቀት ግን በዚያ ዘመን በኒቂያ የተሰበሰቡ ሊቃውንት ቅዳሴው በሌሊት ይሆን ዘንድ አዘዙ /ዐንቀጽ 15፣ ቁ 595/

  ******

  ጥያቄ

  ልደት ጋድ አለው?

  መልስ 

  ፍትሐ ነገሥት፡ የልደት እና የጥምቀት በዓላት ጋድ አላቸው /ዐንቀጽ 15፣ ቁ 566/

  ትንታኔ፡ የገና ጾም 44 ቀናትን ይይዛል፡፡

  •  40 ጾመ ነቢያት
  •  3 ጾመ አብርሃም ሶርያዊ
  •  1 ጋድ

      ድምር 44

  የገና ጋድ ከጾሙ ተያይዞ የተቀመጠ እንጂ ለብቻው የተቀመጠ አይደለም፡፡ ለምሳሌ ሰሙነ ሕማማት ለብቻው የሚቆጠር ጾም ነው፡፡ /ዐንቀጽ 15፣ቁ 565/ ነገር ግን አንድ ሰው ዐቢይ ጾምን ሳይጾም ከርሞ ሕማማትን ለብቻው መጾም አይችልም፡፡ የገናም ጋድ እንዲሁ ነው፡፡

  ******

  ጥያቄ

  ይህንን ጋድ የልደትን ጾም የማይጾሙ ሰዎች እንዲጾሙት የተሠራ ነውን?

  መልስ

  በቤተ ክርስቲያን ላልተጠመቁ፣ ለማይቆርቡ፣ ንስሐ ለማይገቡ፣ ለማያስቀድሱ፣ ለማይጾሙ ሰዎች ተብሎ የተሠራ ልዩ ሥርዓት የለም። በፍትሐ ነገሥት ዐንቀጽ 15፣ ቁ 565 እንደተገለጠው ሰባቱ አጽዋማት «ለክርስቲያን ሁሉ» የታዘዙ ናቸው። ስለዚህም የገናን ጾም ክርስቲያን ሁሉ ጾመው በበዓለ ልደት ሊገድፉ ይገባቸዋል። ፍትሐ ነገሥት ስለ ገና ጾም ሲገልጥ «መጀመርያው የኅዳር እኩሌታ ፋሲካው የልደት በዓል ነው» ይላል /ዐንቀጽ 15፣ ቁ 568/። ይህም ከገና ጾም ተሸርፎ የሚጾም ነገር እንደሌለው ያሳያል።  ምንጭ፣ የዳንኤል ክብረት እይታዎች

 • loader Loading content ...
  Load more...
loader Loading content ...

Comments (9)


loader Loading content ...