loader

Topics (51)


 • @Alembrehan   10 months ago
  Sewasewer
  መሸልኝ ልተኛ ነገን አስባለሁ ነጋልኝ አልቀረም አዲስ ቀን አያልሁ አሁኔ ላይ ቆሜ ደሞ እዘረጋለሁ ምሶሶ ከንች ሆኖ የተቆላልፈው በረዶ ውሽንፍር ዶፍ የማይበግረው ተስፋ ነው ጉልበቴ ህይወቴን ያቆመው እሱን ያጣሁ ለታ አፍታም አታቆዩኝ!... Read more
 • loader Loading content ...
 • @Alembrehan   10 months ago
  Sewasewer
  ካብ ካብ አታርጉኝ ጭብጨባም ይቆየኝ ከፍ አርጋችሁ ከላይ ይቅር አትስቀሉኝ እንዳትቸገሩ ደሞ ስታወርዱኝ ምንጪ: ደረጄ መኩሪያ
 • loader Loading content ...
 • @Alembrehan   10 months ago
  Sewasewer
  ጨብጦ የያዘ ዘርግቶ ሲለቅቅ ደሞ ይቀበላል በተስፋ እሚጥብቅ ግና ያላወቅኽው የሆነብህ ሚስጥር አንተ ጋር የገባው እጅህ ያለው ነገር ባለተራ ሳለሁ እኔ ዘንድ ነበር…. ምንጪ: ደረጄ መኩሪያ
 • loader Loading content ...
 • @Alembrehan   1 year ago
  Sewasewer
  በልደታ በዓል ወይም በየወሩ መጀመርያ በተለይም በግንቦት ልደታ በዓመቱ በዓል በየጎጡ ፣በየደጃፉ ንፍሮ ይነፈራል ብዙም ድግስ ይደገሳል ፣ይህውም የሚነፈርው ንፍሮ እና የሚቀርበው ምግብ ሁሉ ስለቅድስት ማርያም  የልደት ክብር መታሰብያ ... Read more
 • loader Loading content ...
 • @Alembrehan   1 year ago
  Sewasewer
  ዕርጥባን ማልት እንደገና ማርጠብ ማለምለም ማልት ነው ። የኅዉም ማለት አንድ ሰው በልዩ ልዩ ምክንያት ችግር ሲገጥመው አደጋ ስውድቅበት ሕዝቡ ወይም ጎረቤቶቹ ተባብረው የሚያደርጉለት ዕርዳታ ወይም የሚሰጠው ስጦታ ነው ። መርጠብ ማለት... Read more
 • loader Loading content ...
 • @Alembrehan   1 year ago
  Sewasewer
  ዕድር  የሚለው ቃል ብዙ አይነት ፍቺ አለው ይኅውም ፣  ዘየ ወይም ልማድ ይሆናል፣ ለምሳሌ የእገሌ ሀገር ዕድር እንዲህ ነው ሲል ልማዱ ዘየው እንዲህ ነው ማለት ይሆናል ። ኅብረት፣ አንድንት ማለት ይሆናል ፣ይህንም የመሳስሉ ልዩ ልዩ... Read more
 • loader Loading content ...
 • @Alembrehan   2 years ago
  Sewasewer
  የግእዝ ቋንቁ ጥንታዊያን ከተሰኙ ቋንቋዎች መካከል አንዱ ሲሆን ኢትዮጵያውያን ሊቃውንት በቀን አቆጣጠርና በሥነ ጽሑፎቻቸው ሲጠቀሙበት ከትውልድ ወደ ትውልድ ሲተላለፍ ቆይቷል፡፡ ዛሬም የግእዝ ቁጥሮች በኢትዮጵያውያን ዘንድ ሰፊ ሥፍራ አ... Read more
 • loader Loading content ...
 • @Alembrehan   2 years ago
  Sewasewer
  የመጀመሪያው ኢትዮጲያዊ የቫዮሊን ተጫዋች ሲሆን ስልጠናውን የወሰዱት ከጣሊያን ጦርነት በፊት በሚኒሊክ  ት/ቤት ነበር። አሰልጣኛቸውም ኬቮርክ ናልባንዲያን የሚባሉ አርመናዊ ናቸው። በሻህ ከየካቲት ፩፱፬፪ እሰክ የካቲት ፩፱፮፬ ድረስ የ... Read more
 • loader Loading content ...
 • @Alembrehan   2 years ago
  Sewasewer
  ከብዙ አመታት በፊት በድሮ ጊዜ መንገደኞች በጉዞ ላይ ብዙ ቀናትን ያሳልፉ ነበር፡፡ እንዳሁኑ ዘመናዊ መጓጓዣ ስላልነበረ ለሶስት፣ ለአራት አንዳንዴም ለአንድና ለሁለት ሳምንታት ያህል ከቦታ ወደቦታ እየተዘዋወሩ በጉዞ ላይ ያሳልፉ ነበር... Read more
 • loader Loading content ...
 • @Alembrehan   2 years ago
  Sewasewer
  በደቡብ ኢትዮጵያ በየአምስትና አስር አመታት ፌንጣዎች አካባቢውን በመውረር በምድሪቱ ላይ ከፍተና ጥፋት ያደርሳሉ፡፡ ሰብሉን በሙሉ ሙልጭ አድርገው ከበሉ በኋላ ረሃብን ትተው ይጠፋሉ፡፡ ታዲያ በአንድ ወቅት እነዚሁ ፌንጣዎች አካባቢውን ... Read more
 • loader Loading content ...
  Load more...
loader Loading content ...

Explanations (96)


 • @Alembrehan   10 months ago
  Sewasewer

  መሸልኝ ልተኛ ነገን አስባለሁ

  ነጋልኝ አልቀረም አዲስ ቀን አያልሁ

  አሁኔ ላይ ቆሜ ደሞ እዘረጋለሁ


  ምሶሶ ከንች ሆኖ የተቆላልፈው

  በረዶ ውሽንፍር ዶፍ የማይበግረው

  ተስፋ ነው ጉልበቴ ህይወቴን ያቆመው

  እሱን ያጣሁ ለታ አፍታም አታቆዩኝ!

  ባልሞትም ሞቻለሁ አደራ ቅበሩኝ !

  ምንጪ: ደረጄ መኩሪያ

 • loader Loading content ...
 • @Alembrehan   10 months ago
  Sewasewer

  ካብ ካብ አታርጉኝ

  ጭብጨባም ይቆየኝ

  ከፍ አርጋችሁ ከላይ ይቅር አትስቀሉኝ

  እንዳትቸገሩ ደሞ ስታወርዱኝ

  ምንጪ: ደረጄ መኩሪያ

 • loader Loading content ...
 • @Alembrehan   10 months ago
  Sewasewer

  ጨብጦ የያዘ ዘርግቶ ሲለቅቅ

  ደሞ ይቀበላል በተስፋ እሚጥብቅ

  ግና ያላወቅኽው የሆነብህ ሚስጥር

  አንተ ጋር የገባው እጅህ ያለው ነገር

  ባለተራ ሳለሁ እኔ ዘንድ ነበር….

  ምንጪ: ደረጄ መኩሪያ

 • loader Loading content ...
 • @Alembrehan   1 year ago
  Sewasewer

  በልደታ በዓል ወይም በየወሩ መጀመርያ በተለይም በግንቦት ልደታ በዓመቱ በዓል በየጎጡ ፣በየደጃፉ ንፍሮ ይነፈራል ብዙም ድግስ ይደገሳል ፣ይህውም የሚነፈርው ንፍሮ እና የሚቀርበው ምግብ ሁሉ ስለቅድስት ማርያም  የልደት ክብር መታሰብያ ነው ። ክርስቲያኑ ሕዝብ በተቻለው እና በመሰለው አቅሙም በፈቀደው መንገድ የሚገልጠው ክብር፣ የሚያሳየውም ፍቅር፣ የሚያደርገውም መታስቢያ፣ በዚህ መልክ ነው ። ሕዝብ በህብረት በየጊዜው አየተሰባሰበ ንፍሮ እያነፈረ ልዩ ልዩ አይነትም ድግስ አይደገሰ በአንድነት ይመገባል።  ይህም የልደታ በዓል ስለእመቤታችን የልደት ክብር እና ጥንታዊ ልማድ ከመሆኑ በተጨማሪ መቼ እና እንዴት እንደተጀመረ የሚጦቅም መረጃ ባይኖርም ምናልባትም ቅድስት ሐና ቅድስት ማርያምን ስትወልድ ወዳጆቿ ቅድስት ማርያምን በመውለድዋ እንደዚህ አድርገው ድግስ ደግሰው ሁሉም ተሰባስቦ ደስታቸውን አካፍለው ይሆናል የሚል ግምት እና እምነት ግን አለ።  

  ይህም የልደታ በዓል ትንሽ ትልቁ ወንዱ ሴቱ ሳይለያይ ሁሉም የሚሰባሰብበት የማህበራዊ አገልግሎት፣ የህብረት የስምምነት፣ የመልካም ኑሮ ወይም ጉርብትና መልክም አለው።  ኢትዮጵያውያን ላላቸውም ጠንካራ የማህበራዊ ኑሮ የልደታ በዓል አከባበር ትልቅ አስተዋፅኦ አለው ።

  ምንጭ : ማህበራዊ ኑሮ በኢትዮጵያ( በሊቀ ስልጣናት ሀብተ ማርያም ወርቅነህ)
 • loader Loading content ...
 • @Alembrehan   1 year ago
  Sewasewer

  ዕርጥባን ማልት እንደገና ማርጠብ ማለምለም ማልት ነው ። የኅዉም ማለት አንድ ሰው በልዩ ልዩ ምክንያት ችግር ሲገጥመው አደጋ ስውድቅበት ሕዝቡ ወይም ጎረቤቶቹ ተባብረው የሚያደርጉለት ዕርዳታ ወይም የሚሰጠው ስጦታ ነው ። መርጠብ ማለት እንደገና ማርጠብ ማለምለም እደገና ዕርጥብ ለምለም ማድረግ ማለት ነው ።

  ይህ ሰው መጀመርያ ዕርጥብ ወይም ለምለም ነበር ፣ማለት ባለፀጋ ሆኖ ይኖራል ማለት ነው። ይህም ማለት ለሰው ሸከም ሳይሆን ሰርቶ ባገኘው ሀብት ራሱን የሚረዳ ቤተስቡን የሚያስተዳድር ይሆናል። ይህ ሰው ግን የነበርውን ሀብት በልዩ ልዩ ምክንያት ስያጣው ከሰው እጅ ወድቆ እየለመነ ራሱንም ሰውንም እንዳያስችግር ወይም ሀገር ጥሎ ጎዙን ጠቅሎ እንዳይሰደድ በአለበት ሀገር ለማፅናት በማህበርም ለመርዳትና እንደገናም ለመትከል ራሱንም ችሎ እንዲተዳደር እንዲረጥብ፣እንዲለመልም በማለት ጎረቤቱ ወይም የሚያውቀው ሰው ሁሉ የቻለውን ያህል ይረዳዋል ፣ይረጥበዋል ይህም ቅዱስ ተግባር  ዕርጥባን ይባላል። ይህም ባህል በኢትዮጵያ የማህበራዊ ኑሮ ላይ ትልቅ አስተዋፅኦ አለው ።

  ምንጭ : ማህበራዊ ኑሮ በኢትዮጵያ( በሊቀ ስልጣናት ሀብተ ማርያም ወርቅነህ)
 • loader Loading content ...
 • @Alembrehan   1 year ago
  Sewasewer

  ዕድር  የሚለው ቃል ብዙ አይነት ፍቺ አለው ይኅውም ፣ 

  1. ዘየ ወይም ልማድ ይሆናል፣ ለምሳሌ የእገሌ ሀገር ዕድር እንዲህ ነው ሲል ልማዱ ዘየው እንዲህ ነው ማለት ይሆናል ።
  2. ኅብረት፣ አንድንት ማለት ይሆናል ፣ይህንም የመሳስሉ ልዩ ልዩ ትርጉሞች አሉት ግን አሁን በዚህ ዘመን የሚታየው የስራው አፈፃፀም የሚያመለክተው ሁለተኛውን ቁጥር የመሰለ ሆኖ እናገኘዋለን።

  ስለዚህ ዕድር ማለት አሁን ለቀብር ጊዜ የሚያገለግል ዉል ፣የቀብሩን ስረዓት የሚመለክት ገንዘብ የሚዋጣበት አገልግሎት ነው። ይህም ማለት አንድ ሰው ኃዘን ሳይደርስበት አስቀድሞ ገንዘብ ያዋጣል የተለያየ ሃሳብም ይለዋወጣል ፣ እንደዚሁ አድርገው የሚያዋጡት ገንዘብ ይህም የሚወስኑት ውሳኔ ማህበሩም በጠቅላላ የሥራውም አፈፃፀም ነው ።

  ዕድር መልኩን ለውጦ ነው እንጂ እዝን ከምንለው ጋር በጣም ይመሳስላል እንዲያዉም እርሱን አሻሽሉት መልኩን ለወጡት ለማለት ይቻላል ፣ ምክንያቱም እዝን በዚያው በአደጋው ዕለት የሚያዋጡት ወይም የሚሰጡት ነገር ሲሆን ዕድር ግን አስቀድሞ የተወሰነ ገንዘብ ሲያዋጡ ቆይተው ቦሀላ በሀዘኑ ፣ በችግሩ ጊዜ የሚረዱት ወይም እርዳታ የሚሰጡበት አገልግሎት ነው ።

  ምንጭ : ማህበራዊ ኑሮ በኢትዮጵያ( በሊቀ ስልጣናት ሀብተ ማርያም ወርቅነህ) 

 • loader Loading content ...
 • @Alembrehan   2 years ago
  Sewasewer

  የግእዝ ቋንቁ ጥንታዊያን ከተሰኙ ቋንቋዎች መካከል አንዱ ሲሆን ኢትዮጵያውያን ሊቃውንት በቀን አቆጣጠርና በሥነ ጽሑፎቻቸው ሲጠቀሙበት ከትውልድ ወደ ትውልድ ሲተላለፍ ቆይቷል፡፡ ዛሬም የግእዝ ቁጥሮች በኢትዮጵያውያን ዘንድ ሰፊ ሥፍራ አላቸው፡፡ የግእዝ ቋንቋ እንደ ማንኛውም ቋንቋ እራሱን የቻለ የቁጥር አጻጻፍ ስልቶች አሉት፡- እነዚህ ቁጥሮች እኛ በተለምዶ አጠራር የአማርኛ ቁጥሮች ብለን እንጠራቸዋለን፡፡ ይሁን እንጂ ትክክለኛውን አካሄድ ስንመለከት በአጠቃላይ የአማርኛ ብቻ ሳይሆኑ ልክ እንደ አማርኛ ፊደሎች ሁሉ ቁጥሮቹም መነሻቸው ግእዝ መሆኑን እንረዳለን፡፡

  የግእዙም ሆነ አሁን እኛ የምንጠቀምበት ቁጥር ማለትም ከዐ/ዜሮ/ ጀምረን የምንጽፈው የአማርኛ ቁጥር ሳይሆን ስያሜው ከየት እንደመጣ ትክክለኛ መረጃዎች ባይኖሩም 0፣ 1፣ 2፣ 3….. እየተባሉ የሚዘረዘሩት ቁጥሮች የዐረብኛ ቁጥሮች ተብለው እንደሚጠሩ በተለያዩ መጻሕፍት ተጽፈው እናገኛለን፡፡

  በኢትዮጵያ የቀን አቆጣጠር /የቀን መቁጠሪያ/ ላይ የምናገኛቸውን በየወቅቱ የሚከበሩተን ሃይማኖታዊ በዓላትንና ብሔራዊ በዓላትን ለማክበር የምጠቀመው የቀን አቆጣጠር የግእዝ ቁጥር /ኢትዮጵያዊ/ ቁጥር እንደሆኑ በግልጹ ልንረዳውና ተገቢውን ስያሜ አውቀን በስሙ ልንጠራው ይገባናል፡፡

  የግእዝ ቁጥሮችን ከብዙ በጥቂቱ ይህን ይመሰላሉ፣

  የግእዝ ቁጥሮች በአኀዝ..... የግእዝ ቁጥሮች በፊደል.... የዐረብኛ ቁጥር
  -      አልቦ     0
  ፩     አሐዱ     1
  ፪     ክልኤቱ     2
  ፫     ሠለስቱ     3
  ፬     አርባዕቱ    4
  ፭     ሐምስቱ    5
  ፮     ስድስቱ     6
  ፯     ስብዓቱ     7
  ፰     ስመንቱ    8
  ፱     ተሰዓቱ     9
  ፲     አሠርቱ     10
  ፲፩     አሠርቱ ወአሐዱ   11
  ፲፪     አሠርቱ ወክልኤቱ   12
  ፲፫     አሠርቱ ወሠለስቱ   13
  ፲፬     አሠርቱ ወአርባዕቱ   14
  ፲፭     አሠርቱ ወሐምስቱ   15
  ፲፮     አሠርቱ ወስድስቱ   16
  ፲፯     አሠርቱ ወሰብዓቱ   17
  ፲፰     አሠርቱ ወስመንቱ   18
  ፲፱     አሠርቱ ወተሰዓቱ   19
  ፳     እስራ     20
  ፳፩     እስራ ወአሐዱ    21
  ፳፪     እስራ ወክልኤቱ   22
  ፳፫     እስራ ወሠለስቱ   23
  ፳፬     እስራ ወአርባዕቱ   24
  ፳፭     እስራ ወሐምስቱ   25
  ፳፮     እስራ ወስድስቱ   26
  ፳፯     እስራ ወሰብዓቱ   27
  ፳፰     እስራ ወሰመንቱ   28
  ፳፱     እስራ ወተሰዓቱ   29
  ፴     ሠላሳ     30
  ፴፩     ሠላሳ ወአሐዱ    31
  ፴፪     ሠላሳ ወክልኤቱ   32
  ፴፫     ሠላሳ ወሠለስቱ   33
  ፴፬     ሠላሳ ወአርባዕቱ   34
  ፴፭     ሠላሳ ወሐምስቱ   35
  ፴፮     ሠላሳ ወስድስቱ   36
  ፴፯     ሠላሳ ወሰብዓቱ   37
  ፴፰     ሠላሳ ወሰመንቱ   38
  ፴፱     ሠላሳ ወተሰዓቱ   39
  ፵     አርብዓ     40
  ፶     ሃምሳ     50
  ፷     ስድሳ     60
  ፸     ሰብዓ     70
  ፹     ሰማንያ     80
  ፺     ተሰዓ     90
  ፻     ምዕት     100
  ፻፩     ምዕት ወአሐዱ   101
  ፻፪     ምዕት ወክልኤቱ   102
  ፻፫     ምዕት ወሠለስቱ   103
  ፻፬     ምዕት ወአርባዕቱ   104
  ፻፭     መዕት ወሐምስቱ   105
  ፻፮     ምዕት ወስድስቱ   106
  ፻፯     ምዕት ወሰብዓቱ   107
  ፻፰     ምዕት ወስመንቱ   108
  ፻፱     ምዕት ወተሰዓቱ   109
  ፻፲     ምዕት ወአሠርቱ   110
  ፻፲ወ፩     ምዕት አሠርቱ ወአሐዱ  111
  ፻፲ወ፪     ምዕት አሠርቱ ወክልኤቱ  112
  ፻፲ወ፫     ምዕት አሠርቱ ወሠለስቱ  113
  ፻፲ወ፬     ምዕት አሠርቱ ወአርባዕቱ  114
  ፻፲ወ፭     ምዕት አሠርቱ ወሐምስቱ  115
  ፻፲ወ፮     ምዕት አሠርቱ ወስድስቱ  116
  ፻፲ወ፯     ምዕት አሠርቱ ወሰብዓቱ  117
  ፻፲ወ፰     ምዕት አሠርቱ ወስመንቱ  118
  ፻፲ወ፱     ምዕት አሠርቱ ወተሰዓቱ  119
  ፻፳     ምዕት ወእስራ    120
  ፻፴     ምዕት ወሠላሳ    130
  ፻፵     ምዕት ወአርብዓ   140
  ፻፶     ምዕት ወሃምሳ   150
  ፻፷     ምዕት ወስድሳ    160
  ፻፸     ምዕት ወሰብዓ   170
  ፻፹     ምዕት ወሰማንያ   180
  ፻፺     ምዕት ወተሰዓ    190
  ፪፻     ክልኤቱ ምዕት    200
  ፪፻ወ፩     ክልኤቱ ምዕት ወአሐዱ  201
  ፪፻ወ፪     ክልኤቱ ምዕት ወክልኤቱ  202
  ፪፻ወ፫     ክልኤቱ ምዕት ወሠለስቱ  203
  ፪፻ወ፬     ክልኤቱ ምዕት ወአርባዕቱ  204
  ፪፻ወ፭     ክልኤቱ ምዕት ወሐምስቱ  205
  ፪፻ወ፮     ክልኤቱ ምዕት ወስድስቱ  206
  ፪፻ወ፯     ክልኤቱ ምዕት ወሰብዓቱ  207
  ፪፻ወ፰     ክለኤቱ ምዕት ወስመንቱ  208
  ፪፻ወ፱     ክልኤቱ ምዕት ወተሰዓቱ  209
  ፪፻ወ፲     ክልኤቱ ምዕት ወአሠርቱ  210
  ፪፻፲ወ፩     ክልኤቱ ምዕት አሠርቱ ወአሐዱ 211
  ፪፻፲ወ፪     ክልኤቱ ምዕት አሠርቱ ወክልኤቱ 212
  ፪፻፲ወ፫     ክልኤቱ ምዕት አሠርቱ ወሠልስቱ 213
  ፪፻፲ወ፬     ክልኤቱ ምዕት አሠርቱ ወአርባቱ 214
  ፪፻፲ወ፭     ክልኤቱ ምዕት አሠርቱ ወሐምስቱ 215
  ፪፻፲ወ፮     ክልኤቱ ምዕት አሠርቱ ወስድስቱ 216
  ፪፻፲ወ፯     ክልኤቱ ምዕት አሠርቱ ወሰብዓቱ 217
  ፪፻፲ወ፰    ክልኤቱ ምዕት አሠርቱ ወሰመንቱ 218
  ፪፻፲ወ፱     ክልኤቱ ምዕት አሠርቱ ወተሰዓቱ 219
  ፪፻፳     ክልኤቱ ምዕት ወእስራ  220
  ፪፻፴     ክልኤቱ ምሪዕት ወሠላሳ  230
  ፪፻፵     ክልኤቱ ምዕት ወአርብዓ  240
  ፪፻፶     ክልኤቱ ምዕት ወሃምሳ  250
  ፪፻፷     ክልኤቱ ምዕት ወስድሳ  260
  ፪፻፸     ክልኤቱ ምዕት ወሰብዓ  270
  ፪፻፹     ክልኤቱ ምዕት ወሰማንያ  280
  ፪፻፺     ክልኤቱ ምዕት ወተሰዓ  290
  ፫፻     ሠለስቱ ምዕት    300 
  ፬፻     አርባዕቱ ምዕት   400
  ፭፻     ሐምስቱ ምዕት   500
  ፮፻     ስድስቱ ምዕት    600
  ፯፻     ስብዓቱ ምዕት    700
  ፰፻     ስመንቱ ምዕት   800
  ፱፻     ተሰዓቱ ምዕት    900
  ፲፻     አሠርቱ ምዕት    1000
  ፳፻     እስራ ምዕት    2000
  ፴፻     ሠላሳ ምዕት    3000
  ፵፻     አርብዓ ምዕት    4000
  ፶፻     ሃምሳ ምዕት    5000
  ፷፻     ሳድስ ምዕት    6000
  ፸፻     ሰብዓ ምዕት    7000
  ፹፻     ሰማንያ ምዕት    8000
  ፺፻     ተሰዓ ምዕት    9000
  ፻፻     እልፍ     10,000
  ፪፻፻     ክልኤቱ እልፍ    20,000
  ፫፻፻     ሠለስቱ እልፍ    30,000
  ፬፻፻     አርባዕቱ እልፍ    40,000
  ፭፻፻     ሐምስቱ እልፍ    50,000
  ፮፻፻     ስድስቱ እልፍ    60,000
  ፯፻፻     ሰብዓቱ እልፍ    70,000
  ፰፻፻     ስመንቱ እልፍ    80,000
  ፱፻፻     ተሰዓቱ እልፍ    90,000
  ፲፻፻     አሠርቱ እልፍ    100,000
  ፳፻፻     እስራ እልፍ    200,000
  ፴፻፻     ሠላሳ እልፍ    300,000
  ፵፻፻     አርብዓ እልፍ    400,000
  ፶፻፻     ሃምሳ እልፍ    500,000
  ፷፻፻     ስድሳ እልፍ    600,000
  ፸፻፻     ሰብዓ እልፍ    700,000
  ፹፻፻     ሰማንያ እልፍ    800,000
  ፺፻፻     ተሰዓ እልፍ    900,000
  ፻፻፻     አእላፋት    1,000,000
  ፲፻፻፻     ትእልፊት    10,000,000
  ፻፻፻፻     ትልፊታት    100,000,000
  ፲፻፻፻፻     ምእልፊት    1,000,000,000

   ምንጭ
  የግእዝ ቁጥሮች አጻጻፍ በመ/ት ኑኀሚን ዋቅጅራ

 • loader Loading content ...
 • @Alembrehan   2 years ago
  Sewasewer
  አለማየሁ እሸቴ የኢትዮጲያን ዘመናዊ ሙዚቃ ከፍ ወዳለ ደረጃ ካደረሱት ድምፃዊያን መሃል አንዱ ነው።
  "ኢትዮጵያዊው ጀምስ ብራውን" ወይም "ሀበሻው ኤልቪስ"  የሚባሉ ቅጽል ስሞችም  ነበሩት። "አዲስ አበባ ቤቴ" ፤ "የወይን ሃረጊቱ" ፤ "የሰው ቤት የሰው ነው"፣  "ደንየው ደነባ"፤ "ትማርኪያለሽ"፣ "ወልደሽ ተኪ እናቴ"  የሚባሉት ከመጀመሪያ ዘፈኖቹ  መሃል ናቸው።

 • loader Loading content ...
 • @Alembrehan   2 years ago
  Sewasewer
  Beshah was the first violin player in Ethiopia. Trained at Menilik School under Kevork Nalbadian, he served as head of musical section at the Hager Fikir from Feb 1942 to Feb 1964.
 • loader Loading content ...
 • @Alembrehan   2 years ago
  Sewasewer
  የመጀመሪያው ኢትዮጲያዊ የቫዮሊን ተጫዋች ሲሆን ስልጠናውን የወሰዱት ከጣሊያን ጦርነት በፊት በሚኒሊክ  ት/ቤት ነበር።
  አሰልጣኛቸውም ኬቮርክ ናልባንዲያን የሚባሉ አርመናዊ ናቸው።
  በሻህ ከየካቲት ፩፱፬፪ እሰክ የካቲት ፩፱፮፬ ድረስ የሀገር ፍቅር ማህበር የኪነት ክፍል ሃላፊም ነበሩ ።


 • loader Loading content ...
  Load more...
loader Loading content ...

Comments (24)


loader Loading content ...