loader

Topics (7)


 • @Teferi Mihiret   1 year ago
  "i am what i am & that is all that i a am."
  #አለቃ_አያሌው_ታምሩ!  #ድማኅ /ዲማ/ ቅዱስ ጊዮርጊስ ! ወያኔ በጠመንጃ ሃይል ካስቀመጣቸው ጳጳስ ከአባ ገ/መድህን የቅዱስ ሲኖዶስ ተጠሪነቱ ለፓትሪያርኩ ይሁን በሚል አባ ገ/መድህን ሲወስኑ አለቃ አያሌው በበኩላቸው ቅዱስ ሲኖዶስ ... Read more
 • loader Loading content ...
 • @Teferi Mihiret   1 year ago
  "i am what i am & that is all that i a am."
  ፕሮፌሰር ሃይሌ ገሪማን በጨረፍታ (የዘመን አቆጣጠሩ ሁሉ እንደ አውሮፓውያን ነው )  ከአሥር ልጆች አራተኛ በመሆን የተወለደው ኃይሌ ገሪማ መጋቢት 1946 ላይ ነው ይችን አለም የተቀላቀለው ፡፡ እናቱ የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርት ቤት ... Read more
 • loader Loading content ...
 • @Teferi Mihiret   1 year ago
  "i am what i am & that is all that i a am."
  የአድዋ ጦርነት በየካቲት ፳፫ ቀን ፲፰፻፹፰ ዓ.ም. በኢትዮጵያና ኢጣሊያ መካከል የተካሄደ ውጊያ ሲሆን የአንደኛው የኢትዮጵያና ጣሊያን ጦርነት ክፍል ነው። በ ኢትዮጵያ አሸናፊነት የጣልያን የቀኝ ግዛት ማስፋፋት ተኮላሸ። ምኒሊክ ተወል... Read more
 • loader Loading content ...
 • @Teferi Mihiret   1 year ago
  "i am what i am & that is all that i a am."
  ፊት አዉራሪ አየለ ተሰማ(አባ ጓዴ) #በጎንደር ከጓንግ ወንዝ እስከ መተማ የፋሽስት ጣሊያን መንግስት ሃገራችን በግፍ በወረረበት ወቅት ሃገራችን ብዙ ስመጥር ጅግኖችን አፍርታለች። በዚህ ወረራ ወቅት በጎንደር ከጓንግ ወንዝ እስከ መተማ... Read more
 • loader Loading content ...
 • @Teferi Mihiret   1 year ago
  "i am what i am & that is all that i a am."
  አርበኛ ሸዋረገድ ገድሌ  "የምታስፎክር ሰንጋ ገለሌ በጦር መካከል ሳይሆኑ አያሌ በጥይት ገዳይነጭ ብርገድሌ የሴት ወንድናት ሸዋረገድ ገድሌ"ተብሎ የተገጠመላቸውን፣ በአምስት ዓመቱ የጠላት ወረራ ጊዜም አኩሪ ጀብዱየፈጸሙትን የአርበኛዋን... Read more
 • loader Loading content ...
 • @Teferi Mihiret   1 year ago
  "i am what i am & that is all that i a am."
  የፋሽስት ጣሊያን መንግስት ሃገራችን በግፍ በወረረበት ወቅት ሃገራችን ብዙ ስመጥር ጅግኖችን አፍርታለች። በዚህ ወረራ ወቅት በጎንደር ከጓንግ ወንዝ እስከ መተማ ድረስ በጀግንነት ሃገሩን ከወረራ ነፃ ካደረጉት መካከል ጀግናዉ አርበኛ ፊ... Read more
 • loader Loading content ...
 • @Teferi Mihiret   1 year ago
  "i am what i am & that is all that i a am."
  ትውልድና እድገቷ ሰሜን ጐንደር ቆላ ድባ ከተማ ነው::ተመልካችን በእጅጉ በሚማርከው ፈገግታዋ መድረክ ላይ ወጥታእንደ እንዝርት ስትሾር የታዳሚውን ቀልብ ትገዛለች:: ባላት ልዩ የውዝዋዜ ተሰጥኦም በአብዛኞቹ መድረኮች ኢትዮጵያን ትወክላ... Read more
 • loader Loading content ...
loader Loading content ...

Explanations (7)


 • @Teferi Mihiret   1 year ago
  "i am what i am & that is all that i a am."

  #አለቃ_አያሌው_ታምሩ
  #ድማኅ /ዲማ/ ቅዱስ ጊዮርጊስ !
  ወያኔ በጠመንጃ ሃይል ካስቀመጣቸው ጳጳስ ከአባ ገ/መድህን የቅዱስ ሲኖዶስ ተጠሪነቱ ለፓትሪያርኩ ይሁን በሚል አባ ገ/መድህን ሲወስኑ አለቃ አያሌው በበኩላቸው ቅዱስ ሲኖዶስ መመራት ያለበት በመንፈስ ቅዱስ ነው፡፡ ጰጳሳቱ በእኩል ተቀምጠው በመግባባት በእኩልነት ነው ሊወስኑ የሚገባቸው በቅዱስ ሲናዶስ ማንም የበላይ ሊሆን አይገባም፡፡ ኃይማኖቱም የሚያዘው ይህንኑ ነው በማለት የተከራከሩ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተ-ክርስትያን የሊቆች ሊቅ የነበሩት አለቃ አያሌው ታምሩ ናቸዉ !


  እኚህ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተ-ክርስትያን የሊቆች ሊቅ የነበሩት አለቃ አያሌው ታምሩ የተወለዱት መጋቢት 23 ቀን 1915 ዓ.ም ሲሆን ቦታውም በምስራቅ ጐጃም ዞን፣ እነማይ ወረዳ በታላቁ ደብረ ድማኅ /ዲማ/ ቅዱስ ጊዮርጊስ ቤተ-ክርስትያን፣ ልዩ ስሙ ቤተ-ንጉስ በተሰኘ ቦታ ነበር። የአለቃ አባት አቶ ታምሩ የተመኝ ሲባሉ እናታቸው ደግሞ ወ/ሮ አሞኘሽ አምባዬ ይባላሉ።

  ዕድሜአቸው ለትምህርት ሳይደርስ ገና የሦስት ዓመት ተኩል ሕፃን ሳሉ በፈንጣጣ ሕመም ምክንያት የዐይናቸውን ብርሃን አጥተዋል። የስምንት ዓመት ዕድሜ ልጅ ሳሉ በዓለ ተክለ አልፋን
  ለማክበር ከአባታቸው ጋር ወደ ዲማ እንደ ሄዱ በዚያው ትምህርታቸውን ለመቀጠል
  ቀሩ። ከዚህ ጊዜ ጀምሮም በቅርብ ቤተ ዘመድ እየተረዱ ለአንድ ዓመት ያህል ሲማሩ
  ከቈዩ በኋላ አባታቸው ስላረፉ ኑሮአቸው በትምህርት ቤት ብቻ ስለ ተወሰነ ከቤተ ሰብእ
  ጋር የነበራቸው ግንኙነት እየቀነሰ መጣ። ይህም ሁኔታ የሚፈልጉትን ትምህርት በአንድ
  ልብ ለመቀጠል ግድ ሆኖባቸዋል።
  በዚሁ መሠረት በ፲፭ ዓመት ዕድሜአቸው የቅኔ መምህር ለመሆን በቅተዋል። ስለ
  ዐይናቸው ብርሃንና ስለ ትምህርታቸው፤ «ምልጃ ዕርቅና ሰላም፤» በተባለው
  መጽሐፋቸው ገጽ ፬ ላይ እንዲህ ሲሉ ገለጸዋል። «ይህ ሁሉ የተገኘው ገና በልጅነት
  ዕድሜዬ፤ በቅዱስ ሐዋርያ ያዕቆብ እንደ ተነገረው የምመራበት፣ የምኖረበት
  በወሰድከው በዐይኔ ፈንታ ዕውቀት ስጠኝ ብዬ የለመንኩት አምላኬ፤ «ለምኑ
  ይሰጣችኋል፤ ሹ ታገኛላችሁ፤ በር ምቱ ይከፈትላችኋል፤ ለሚወደኝ እኔ ራሴን
  እገልጥለታለሁ፤» ሲል በሰጠው ተስፋና በለገሰኝ የአእምሮ ምጽዋት መሆኑን
  ስለምረዳ ነው፤» ብለዋል።
  ክቡር አለቃ አያሌው ታምሩ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ
  ክርስቲያን እምነት፥ ትምህርት፥ ሥርዐትና አስተዳደር ከጊዜ ወደ ጊዜ እየተለወጠና
  እየተበላሸ መሄዱ በእጅጉ ያሳዝናቸው ስለ ነበር፤ የቤተ ክርስቲያኒቱ የሊቃውንት ጉባኤ
  ዋና ሰብሳቢ እንደ መሆናቸው መጠን፤ ጥፋቱ እንዲታረም ብዙ አቤቱታና ተማጽኖ
  ጉዳዩ ወደሚመለከተው ወደ ቤተ ክርስቲያኒቱ ቅዱስ ሲኖዶስ፤ ሲኖዶሱን በመሠረተና
  በሚመራው በመንፈስ ቅዱስ ስም ተማጽነው ቢያቀርቡም ሲኖዶሱ ጉዳዩን ለማፈን
  ከመሞከር በስተቀር ምንም እርምጃ ሳይወስድ ቀርቷል። እሳቸውም ያቀረቡት ጥያቄ
  መፍትሔ ባለማግኘቱ ጉዳዩን ለሚመለከተው ለኢተዮጵያ ሕዝበ ክርስቲያን
  ለማሳወቅና፤ በቤተ ክርስቲያን ላይ ዐመፅ የሚፈጽሙትን ፓትርያርኩንና የእሳቸው
  ተባባሪ የሆኑ ጳጳሳትን ባላቸው ከፍተኛ ኀላፊነተና ሥልጣነ ክህነት በሥልጣነ አብ
  ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ፥ በሥልጣነ ጴጥሮስ ወጳውሎስ ለማውገዝ ተገደዋል።
  ከዚህም በተጨማሪ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ካህናት በጸሎተ
  ቅዳሴ ጊዜ የዐመፀኛውን ፓትርያርክ ስም እንዳይጠሩ ውግዘት አስተላልፈዋል።
  ምእመናንም ከዐመፀኞች ካህናት ምንም ዐይነት አገልገሎት ማገኘት የማይችሉ
  መሆናቸውን ተገንዝበው ሕይወታቸውን በጥንቃቄ እንዲመሩ አሳስበዋል። በዚህም
  ምክንያት ከ፶ ዓመት በላይ ካገለገሉበት የቤተ ክርስቲያን አገልግሎት በሐሰት ክስና
  የእምነት ክሕደት ቃላቸውን ባልሰጡበት ሁኔታ ያለ ምንም ጡረታ ከሥራ ገበታቸው
  ላይ በግፍ እንዲነሡ በመደረጉ ከሚያዝያ ወር ፲፱፻፹፰ ዓመተ ምሕረት ጀምሮ እስከ
  ዕለተ ዕረፍታቸው በመኖሪያ ቤታቸው ተወስነው ኖረዋል። በነዚህ ዓመታትም በየዕለቱ
  ለጸሎት ባዘጋጇት አነስተኛ ክፍል በመገኘት ወደ ልዑል እግዚአብሔር በመጸለይና
  በማልቀስ ይተጉ ነበር። ምእመናንም በተኲላ እንዳይነጠቁ በተለያዩ ጋዜጦች
  ትምህርትና ማበረታቻ ሲሰጡ ኖረዋል።
  የክቡር አለቃ አያሌው ታምሩ የቀብር ሥነ ሥርዐት ነሐሴ ፲፯ ቀን ፲፱፻፺፱ ዓመተ
  ምሕረት ብዙ ዘመን ባገለገሉበት የአዲስ አበባው ደብረ አሚን ተክለ ኃይማኖት ቤተ
  ክርስቲያን ብዙ ሕዝብ በተገኘበት ተፈጽሟል።
  ክቡር አለቃ አያሌው ታምሩ በቤተ ክርስቲያን ሥርዐት መሠረት በሥርዐተ ተክሊል
  ከወይዘሮ ርብቃ ልሳነ ወርቅ ጋር ሚያዝያ ፲፪ ቀን ፲፱፻፶ ዓመተ ምሕረት ጋብቻ ፈጽመው
  ፲፬ ልጆችና ፲፪ የልጅ ልጆች ለማፍራት ታድለዋል።
  መንፈሳዊ አገልግሎትና አስተዳደር።
  ወደ አዲስ አበባ ከመጡ በኋላ ዛሬ የክቡር ዐፅማቸው ማረፊያ በሆነው ደብረ
  አሚን ተክለ ኃይማኖት ቤተ ክርስቲያን የቅኔ መምህርነት አገልግሎታቸውን በ፲፱፻፴፱
  ዓመተ ምሕረት ጀመሩ። በመቀጠልም በዚሁ ደብር፤ መጀመሪያ የሊቀ ጠበብትነት
  ማዕረግ አግኝተው ያገለገሉ ሲሆን ኋላም የዚሁ ደብር አስተዳዳሪ በመሆን ሰፊ
  አገልግሎት አበርክተዋል።
  በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ጠቅላይ ቤተ ክህነት የሊቃውንት
  ጉባኤ ተመርጠው ከሰኔ ወር ፲፱፻፵፰ ዓመተ ምሕረት ጀምሮ የስብከተ ወንጌል ክፍል
  አባል ሆነው አገልግለዋል።  በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የሊቃውንት ጉባኤ አባልና ዋና
  ሰብሳቢ ሆነው ሠርተዋል። በዚህም የሥራ ዘመናቸው፤ የቤተ ክርስቲያን የወንጌል
  ትምህርት በመሆኑ ይህ አገልግሎት ሳይበረዝና ሳይከለስ እምነቱም፣ ትምህርቱም፣
  ሥርዐቱም ተጠብቆ ከትውልድ ወደ ትውልድ እንዲተላለፍ ለማድረግ
  የሚያስችለውን መንገድ ለመቀየስ በተሰጣቸው ኀላፊነት ደከመኝ ሰለቸኝ ሳይሉ ሌት
  ተቀን ሠርተዋል።
  አልፎ አልፎም ከውስጥም ሆነ ከውጪ ለሚነሡት መናፍቃን መልስ በመስጠት፣
  በቤተ ክርስቲያኒቱ በየጊዜው የሚታተሙትን መጻሕፍት በማረምና ለኅትመት
  እንዲበቁ በማድረግ፤ ስለ ቤተ ክርስቲያንም ሆነ ስለ ቅድስት ሀገራችን ኢትዮጵያ
  ለሚጠየቁ ጥያቄዎች መልስ በመስጠት፤ በበዓላትም ሆነ በሌሎች አጋጣሚዎች
  በራዲዮ፥ በቴሌቪዥን፥ በመጽሔቶችና በጋዜጦች ትምህርትና ምክር በማስተላለፍ
  ሀገራዊና ሃይማኖታዊ ኃላፊነታቸውን ተወጥተዋል።
  ሐዲስ ኪዳንን በግእዝና በአማርኛ ፥ መጽሐፈ ግጻዌ፥ ሃይማኖተ አበው የተባሉትን
  መጻሕፍት ከሌሎች የጉባኤው አባላት ጋር ተርጉመው እንዲታተሙ አድርገዋል።
  በቀዳማዊ ኀይለ ሥላሴ ዩኒቨርሲቲ መንፈሳዊ ኰሌጅ ከ፲፱፻፶፬ እስከ ፲፱፻፷፬ ዓመተ
  ምሕረት፤ እንዲሁም በተግባረ እድ ትምህርት ቤትና በቅዱስ ጳውሎስ ከፍተኛ
  መንፈሳዊ ትምህርት ቤት መንፈሳዊ ትምህርት አስተምረዋል።
  ከኢትዮጵያ ዓይነ ሥውራን ማኅበር መሥራቾች አንዱ ሲሆኑ፤ መጀመሪያ የማኅበሩ
  ምክትል ፕሬዚዳንት ኋላም የቦርድ ሊቀ መንበር በመሆን አገልግለዋል።
  የአለቃ አያሌው መጻሕፍት
  በመጽሐፍ ጥራዝ አዘጋጅተውና አሳትመው ለትውልድ ያስተላለፏቸው መጻሕፍት ዘጠኝ
  ሲሆኑ በይዘታቸው በሁለት የተከፈሉ ናቸው። በአንደኛው ክፍል ያሉት የቤተ
  ክርስቲያንንና የኢተዮጵያን ማንነት ለኢትዮጵያውያን ለማስተማር የተዘጋጁ ሲሆኑ፤
  በሁለተኛው ክፍል ያሉት ደግሞ ከቤተ ክርስቲያን ውስጥም ሆነ ከቤተ ክርስቲያን
  ውጪ ለተነሡና ለሚነሡ መናፍቃን መልስ በመስጠት የምእመናንን ልቦና ለማጽናት
  የሚያስችል መልእክት የሚያስተላልፉ ናቸው። ከነዚህ መጻሕፍት ውስጥ ዐምስቱ
  በቤተ ክህነት አገልገሎት ላይ የተዘጋጁ ሲሆኑ፤ አራቱ ደግሞ ከቤተ ክርስቲያን
  አገልግሎት በግፍ ከታገዱበት ከ፲፱፻፹፰ ዓመተ ምሕረት በኋላ የተዘጋጁ ናቸው።
  በቤተ ክህነት አገልገሎት ላይ በነበሩበት ጊዜ ያዘጋጇቸው፤
  «መች ተለመደና ከተኲላ ዝምድና»፥
  «የኢትዮጵያ እምነት በሦስቱ ሕግጋት»፥
  «የኑሮ መሠረት ለሕፃናት»፥
  «ወላዲተ አምላክ በኢትዮጵያ»፥
  «የጽድቅ በር»
  የተባሉት መጻሕፍት ሲሆኑ፣ ከሥራ ገበታ ከታገዱ በኋላ በመኖሪያ ቤታቸው ሆነው
  ያዘጋጇቸው፤
  «ምልጃ፥ ዕርቅና ሰላም»፥
  «ተአምርና መጽሐፍ ቅዱስ»፥
  «መልእክተ መንፈስ ቅዱስ»፥
  «ዜና ሕይወት ዘቅድስተ ቅዱሳን እመ አምላክ»
  የተባሉት ናቸው። 
  ነፍሳቸውን በቅዱሳን እቅፍ ያድርግልን።
  "እመቤታችን የተፈጠረችው ለአባቷና ለእናቷ ብቻ አይደለም፣ለሰው ዘር ሁሉ የሕይወት መሠረተ ሆና ነው።
  ስለዚህ ክብሩዋ፣ልዕልናዋ ከሰዎች ታሪክ ጋር አይደረደርም፣መንገዱም መሥመሩም ልዩ ነው፣"
  ( ሊቁ አለቃ አያሌው ታምሩ)
  ከድዕረ ገፅ 
  #TEFERI_MIHIRET!

 • loader Loading content ...
 • @Teferi Mihiret   1 year ago
  "i am what i am & that is all that i a am."

  ፕሮፌሰር ሃይሌ ገሪማን በጨረፍታ
  (የዘመን አቆጣጠሩ ሁሉ እንደ አውሮፓውያን ነው ) 
  ከአሥር ልጆች አራተኛ በመሆን የተወለደው ኃይሌ ገሪማ መጋቢት 1946 ላይ ነው ይችን አለም የተቀላቀለው ፡፡ እናቱ የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርት ቤት አስተማሪ ሲሆኑ አባቱ, አቶ ገሪማ ተፊካ ደግሞ የተውኔት እና የቴአትር አዘጋጅ ነበሩ፡ እንደ ሳንኮፋ ድረገጽ ከሆነ ፕሮፌሰር ሃይሌ ገሪማ ገና በወጣትነት ዘመኑ የአባቱን ፈለግ በመከተል በአባቱ ቲያትሮች ይለማመድ ነበር ፡፡ ሃይሌ እና እህቱ ዘመናዊ ትምህርት ቤት በመሄድ በቤተሰባቸው ውስጥ የመጀመሪያዎቹ እንደሆኑ ድረገጹ ጠቅሶ የሃገሩን ባህል እና ሥርዓተ ትምህርት በማስተማር እና ለአሜሪካ የሰላም ጓድ አባላት እንዴት ፊደል መጻፍ እንደሚቻል በማስተማር እንዲሁም ባህሉን በማስተዋወቅ የድርሻውን ተወጥቷል ፡፡  ፕሮፌሰር ሃይሌ. "ቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ ዩኒቨርሲቲ በፈጠራ ጥበብ ማዕከል ውስጥ አጭር ቆይታ ካደረገ በኋላ, ድራማ ለማጥናት ወደ አሜሪካ አቅንቷል፡፡እዚያም ሸሪኪያና ከተባለች ሴት ጋር በትዳር ተጣምሮ አምስት ልጆችን አፍርቷል፡፡
  በሎስ አንጀለሰ ከተማ ካሊፎርኒያ ዩኒቨርሲቲ ከ1976 ጀምሮ የፊልም ጥበብን በማስተማር ስራ ላይ ተሰማርቶ ይገኛል ፡፡
  የፊልም ጥበብ ቀማሪው ፕሮፌሰር ሃይሌ ገሪማ ከሰራቸው ፊልሞች መካከል አወር ግላሰ ፣ ቻይልድ ኦፍ ሬንሰንስ ፣ ቡሽ ማማ የተባሉ ስራዎችን በ1975 የሰራ ሲሆን ስሪ ታውዘንድ የተሰኘ ፊልም በ1976 ፣ዊልምግተን ፣ቴን ዩ ኤስ ኤ ቴን ታውዘንድ የተሰኘን ፊልም በ1977 አሽስ ኤንድ ኢምበርስ በ1982 ፣ አፍተር ዊንተር ስተርሊን ብሮውን በ1985 ፣ሳንኮፋ በ1993 አድዋ አን አፍሪካን ቪክትሪ በ2000 የሰራ ሲሆን በዩኒቨርሲቲው ተሸላሚም ነው፡፡ የፓን አፍሪካን የፊልም አዘጋጆች ፌዴሬሽን እና የአፍሪካን የፊልም አዘጋጆች ኮሚቴ አባልም ነው ፕሮፌሰር ሃይሌ ገሪማ፡፡

  ከሰራቸው ፊልሞች መካከል:-
  • 1972 - Hour Glass Hour Glass
  • 1972 - Child of Resistance
  • 1976 - Bush Mama
  • 1976 - Mirt Sost Shi Amit (also known as Harvest: 3,000 Years)
  • 1978 - Wilmington 10 -- U.S.A. 10,000
  • 1982 - Ashes and Embers
  • 1985 - After Winter: Sterling Brown
  • 1993 - Sankofa
  • 1994 - Imperfect Journey
  • 1999 - Adwa - An African Victory
  • 2009 - Teza

  Over the course of his career, Gerima has received numerous awards and distinctions in film festivals:-
  • 1976 - Grand prize / Silver Leopard for Harvest: 3,000 Years- Locarno
  • 1982 - Grand Prix Award for Ashes and Embers-Lisbon International Film Festival
  • 1983 - FIPRESCI Film Critics Award for Ashes and Embers-Berlin International Film Festival
  • Outstanding Production Ashes and Embers - London Film Festival
  • 1984 - Tribute Festival De la Rochelle, France
  • 1987 - Long Metrage De Fiction-Prix de la Ville de Alger for Ashes and Embers
  • 1993 - Best Cinematography Award for Sankofa, FESPACO, Burkina Faso
  • 2003 - Lifetime Achievement Award, 4th Annual Independence Film Festival, Washington D.C.
  • 2006 - Festival De Cannes Selection Official Cannes Classic -Harvest: 3,000 Years
  • 2008 - Venice Film Festival Special Jury Prize and Best Screen Play Award - Teza
  • 2009 - Jury Award at the 18th International Film Festival Innsbruck/Austria - Teza
  • 2009 - Golden Stallion of Yennenga at the FESPACO African Film Festival - Teza http://www.rfi.fr/actuen/articles/111/article_3102.asp
  • 2009 - Dioraphte Award Hubert Bals film in highest audience regard at the Rotterdam Film Festival
  • 2009 - Golden Tanit/Best Film Award for its "modesty and genius," Best Music (Jorga Mesfin Vijay Ayers), Best Cinematography (Mario Massini), Best Screenplay (Haile Gerima), Best Supporting Actor Abeye Tedla at the Carthage/Tunisia Film Festival for Teza
  • 2009 - Golden Unicorn and Best Feature Film at the Amiens/France International Film Festival France for Teza
  • 2009 -The Human Value's Award at the Thessaloniki Film Festival in Greece for Teza
  • 2009 - Official Selection at the Toronto Film Festival for Teza
  ፕሮፌሰር ሃይሌ ገሪማ በሚሰራቸው የፊልም ጥበቦች ሃገሩን በማሰተዋወቅ ባለውለታ እንደሆነ ብዙዎች ይመሰክሩለታል፡፡ ወደፊትም በሚያበረክታቸው የፊልም ስራዎቹ ውስጥ ለሃገሩ ልዩ ቦታ እንደሚሰጥ ተናግሯል፡፡
  #TEFERI_MIHIRET

 • loader Loading content ...
 • @Teferi Mihiret   1 year ago
  "i am what i am & that is all that i a am."
  የአድዋ ጦርነት በየካቲት ፳፫ ቀን ፲፰፻፹፰ ዓ.ም. በኢትዮጵያና ኢጣሊያ መካከል የተካሄደ ውጊያ ሲሆን የአንደኛው የኢትዮጵያና ጣሊያን ጦርነት ክፍል ነው። በ ኢትዮጵያ አሸናፊነት የጣልያን የቀኝ ግዛት ማስፋፋት ተኮላሸ።
  ምኒሊክ ተወልዶ ባያነሣ ጋሻ
  ግብሩ እንቀላል ነበር ይሄን ጊዜ አበሻ፤
  ***
  ገበየሁ ቢሞት ተተካ ባልቻ
  መድፍ አገላባጭ ብቻለብቻ፤
  ***
  የአድዋ ሥላሴን ጠላት አረከሰው
  ገበየሁ በሞቴ ግባና ቀድሰው፤


  የአድዋ ድል የኢትዮጵያ ብሔራዊ ክብር ማኅተም፤ የጥቁር ህዝቦች የነፃነት ተጋድሎ ቀንዲል ነው፡፡ የመላው ዓለም ተፈጥሮአዊ ግብር እና ሰብአዊ ክብር የታደሠው፤ በእውነትና በፍትህ ህልውናና ምልዓት ላይ የተሰካ ትልቅ ጥርስ የተነቀለው … በአድዋ የታላቅ ህዝቦች ታላቅ ድል ነው፡፡
  ከአዲስ አበባ ወደ ሰሜን ኢትዮጵያ ስንሄድ 1066 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ ታላቁ ጦርነት የተደረገበትና ታላቁ ድል የተገኘበት ሥፍራ አድዋ ከተማና የከተማው ግድም ገመገሞች ይገኛሉ፡፡ በኢትዮጵያውያን አቡሻኽር (Julian calendar) የካቲት 23 ቀን 1888 ዓ.ም፤ ወይም በአውሮጳውያን የዘመን አቆጣጠር (Gregorian Calendar) February (የካቲት) መጨረሻ እና March (መጋቢት) መጀመሪያ ላይ 1896. ለጦርነቱ መነሻ የሆነው ውል የተፈፀመው በዚሁ ዘመን ከአዲስ አበባ በስተሰሜን 468 ኪሎ ሜትር ርቀት ግድም ከውጫሌ ከተማ ግርጌ ከአምባሰል ተራራ ሥር ወሎ ውስጥ ንጉሥ ይስማ እየተባለ በሚጠራ ሥፍራ ነው፡፡
  ሸልዶ ተራራ ወይም (ሶሎዳ ተራራ)፤ ማርያም ሸዊቶ፤ አዲ ተቡን፤ ረቢ አርእየኒ (እግዚሃር አሳየኝ)… በመሠኘት የሚታወቁት እነዚህ ገመገሞችና ተራራማ ሥፍራዎች ዋነኞቹ የጦር ግንባሮች ናቸው፡፡ በመቶ ሺህ የሚሠላ የኢትዮጵያ ገበሬ ሠራዊት ከአንድ ቀን ባልበለጠ ጊዜ ውስጥ የአውሮጳ ቅኝ ገዢ ወራሪዎችን ድባቅ ከመታና ረግጦ ካስወጣ በኋላ ከምሽቱ አራት ሰዓት ግድም (የካቲት 23 ቀን) እንዳማርያም ላይ ተሰባስቦ በአንድ እግሩ ቆሞ ቀኙን (ድሉን) ለሰጠው አምላክ ምሥጋና አቅርቧል፡፡ አባት ሆይ፤ ንቀውን የመጡ የአገራችንን ድንበርና ልዕልና የደፈሩ የአውሮጳ ኮሎኒያሊስት ወራሪዎችን እንድናሸንፍ (ድል እንድናደርግ) ስለረዳኸን እናመሰግንሃለን ...
  ሃያ ዘጠኝ ሺህ ፈረሰኞችን ጨምሮ ከመቶ ሺህ እስከ መቶ ሃያ ሺህ የሚገመት አንድ ሺህ ኪሎ ሜትር በባዶ እግሩ የተጓዘ የኢትዮጵያ የገበሬ ሠራዊት በወታደራዊ አካዳሚ የሠለጠነውን የአውሮጳ ወራሪ ጦር የካቲት 23 ማለዳ አሥራ አንድ ሰዓት ግድም ገጥሞ ከረፋዱ አራት ሰዓት ላይ ማሸነፉን አረጋግጧል ይለናል የታሪክ ተመራማሪው ጆርጅ በርክሌይ የአድዋ ጦርነትና ዳግማዊ አፄ ምኒሊክ በተሰኘና ዳኘው ኃይለሥላሴ ወደ አማርኛ በተረጐሙት መጽሐፉ ላይ፡፡ የኢትዮጵያ ገበሬ ሠራዊት ፈረሱ ላይ ሆኖ የጋሻውን እምብርት መሬት ላይ እያጠቀሰ ጐራዴውን አየር ውስጥ እየቀዘፈ ባበደ መንፈስ (በተቆጣና በቆረጠ መንፈሥ) በጀግንነት ተዋግቷል፡፡
  ጦርነቱ በተጀመረ ከአምስት ሰዓት ባልበለጠ ጊዜ ውስጥ ሃምሣ ስድስቱም የኢጣሊያ መድፎች ሙሉ ለሙሉ ተማርከዋል፤ የቅኝ ገዢውን ወራሪ ሠራዊት ከመሩት ጀኔራሎች ጄኔራል አልቤርቶኒ ሲማረክ የሠራዊቱ ዋና አዛዥ ጄኔራል ባራቴሪ ከጥቂት አጃቢዎቹና በሽንፈት ከተበታተኑ የኢጣሊያ ወታደሮች ጋር ሸሽቷል፡፡
  በዚህ ድብልቅልቅ ያለ ውጊያ ከሃምሣ ስድስቱ የኢጣሊያ መድፎች በተጨማሪ ብዙ ሺህ ቀላልና ከባድ መትረየሶች እንዲሁም የነፍስ ወከፍ ጠመንጃዎች በአሥር ሺሆችና በመቶ ሺዎች ከሚቆጠሩ መሰል ጥይቶቻቸው ጋር ተማርከዋል፡፡ በአጠቃላይ ምርኮው ወደ አዲስ አበባ የተጓጓዘው በአምስት መቶ አጋሰሶች ተጭኖ ነው፡፡
  በማግስቱ የካቲት 24 ቀን 1888 ዓ.ም ከጠዋቱ አራት ሰዓት ላይ የኢጣሊያ ምርኮኞች በምኒሊክ ድንኳን ፊት ሲያልፉ የኢትዮጵያ ጀግና የገበሬ ሠራዊት እየፎከረ እየሸለለ አሳልፉዋቸዋል፡፡ ጄኔራል አልቤርቶኒ በምርኮኛነት ኢትዮጵያ ውስጥ ቆይቶ አገሩ ከተመለሰ በኋላ በፃፈው መጽሐፍ ላይ ከሚፎክሩት ጥቁር የነፃነት ተዋጊዎች መሃከል አንዱ እንደ እኛው ነጭ አውሮጳዊ ነው ብሎአል፡፡ ይህ ሰው ከፈረንሣይ አገር ወደ ኢትዮጵያ ለጦር መሣሪያ ጥገና የመጣ ካፒቴን ኦርዲናንስ ሲሆን፤ አሁን ጊዜው የጦርነት ስለሆነ ወደ አገርህ ተመለስ ቢባል ቢሠራ አሻፈረኝ ብሎ ከእኛ ጋር አድዋ ድረስ የዘመተ ነው፡፡
  ኢትዮጵያ በአድዋ ጦርነት ላይ ከተዋጋችባቸው የጦር መሣሪያዎች ሠማንያ ሺህ የሚሆኑት አሮጌ ጠመንጃዎች የተገዙት ከፈረንሳይ አገር በምሥጢር ነው፡፡ ጠመንጃዎቹን ገዝተው ወደ ኢትዮጵያ ያስገቡት ለመጀመሪያ ጊዜ መኪና ወደ ኢትዮጵያ ያስገቡት በሥጋ በደምና በትውልድ አርመናዊ በነፍስና በመንፈስ በዜግነትና በልብ ፍቅር ኢትዮጵያዊ የሆኑት የኢትዮጵያ የልብ ወዳጅ ሰርኪስ ቴሪዝያን ናቸው፡፡
  አሁን በመዲናችን የሚገኘው የአርሾ ላቦራቶሪ ባለቤትና በዓለም ላይ ኢትዮጵያን የመሰለ ውብ አገር የለም ያሉኝ ዶክተር አርሻቪር ቴሪዝያን ኢትዮጵያ ውስጥ አርመናዊ ትውልድ ኖሮት ኢትዮጵያዊ ዜግነት የሌለው (ኢትዮጵያዊ ያልሆነ) አርመን ያለመኖሩን ያጫወቱኝ ከአሥራ አምስት ዓመታት በፊት ነው፡፡ የሠማንያ ሺህ ጠመንጃዎቹን አገዛዝ ሁናቴ የሚያውቁት ደግሞ ከአርሾ ቀደም የሚሉትና ከአሥራ ስድስት ዓመታት በፊት ለሪፖርተር ጋዜጣ ይሄንኑ በአንደበታቸው የገለፁት አቬዲስ ቴሪዝያን ናቸው፡፡ ሠርኪስ ቴሪዝያን ጠመንጃዎቹን ከገዙ በኋላ ወደ ኢትዮጵያ ያስገቡት በጅቡቲ በኩል ነፋስ ባህሩን ሲያነሳና እንደ ግድግዳ ሲያቆም በዚያ ተፈጥሮአዊ ክንውን በመጠቀም ደብቀውና ሸሽገው ነው፡፡

  የአድዋ ድል ለመጀመሪያ ጊዜ የተከበረው በሠባተኛ ዓመቱ በ1895 ዓ.ም (እ.ኤ.አ በ1903) ከአንድ መቶ ዘጠኝ ዓመታት በፊት አሁን ጊዮርጊስ ቤተክርስቲያን ያለበት ሥፍራ ምኒሊክ አደባባይ ነው፡፡ በክብረ በዓሉ (በድል በዓሉ) ላይ ዲፕሎማቶችና የውጪ አገር መንግሥታት ተወካዮች አርበኞች የመንግስት ባለሥልጣኖች ብዙ ሺህ ፈረሰኞችና ሥፍር ቁጥር (ወፈ ሠማይ የሆኑ) ኢትዮጵያውያን ከሊቅ እስከ ደቂቅ መገኘታቸውን፤ ከፈረሰኞቹ ብዛት የተነሳ ፀሐይ በአቧራ እስከመጋረድ መድረሷን ጳውሎስ ኞኞ የኢጣሊያና የኢትዮጵያ ጦርነት በተሰኘ መጽሐፉ ላይ ጽፎአል፡፡ እንዲሁም ተክለፃዲቅ መኩሪያን የመሳሰሉ ኢትዮጵያውያን የታሪክ ተመራማሪዎችና የውጪ አገር ዜግነት ያላቸው ፀሐፍትና ተመራማሪዎች በተለያዩ መፃሕፍቶቻቸው ይሄንን አሣምረው ጽፈውታል፡፡
  ታላቁ የጥቁር ህዝቦች ድል (የአድዋ ድል) በመላው ዓለም ፖለቲካ ላይ ከፍተኛና ዋነኛ ለውጦች አምጥቶአል፡፡ የእንግሊዝ ጋዜጦች በአድዋ ድል ማግስት የዓለም ታሪክ ተገለበጠ ታላቅ የትውልድ ኃይል በአፍሪቃ ተቀሰቀሰ … ብለው ፃፉ፡፡ በኢንሳይክሎፒዲያ ብሪታኒካ፡- ዘመናዊት ኢትዮጵያን የፈጠረ የተባሉት ዳግማዊ ዓፄ ምኒሊክ በሌሉበት (እርሳቸው በአካል ባልተገኙበት የነፃነት ተጋድሎ መሪዎች ጉባኤ) የአፍሪቃና የመላው ዓለም ጥቁር ህዝቦች የነፃነት ተጋድሎ መሪ ተደርገው ተመረጡ፡፡
  ጦርነቱ ከመደረጉ በፊት እ.ኤ.አ በ1880ዎቹ መጀመሪያ ጀርመን አገር በርሊን ከተማ ላይ በተደረገው የአውሮጳ ቅኝ ገዢ (ኮሎኒያሊስት) መንግስታት ሥልጣናትና ልሂቃን የጦር ጄኔራሎችና ሊቃውንት ስብሰባ ላይ ጥቁር ትልቅ ትል ነው ቅንቡርስ ነው እንጂ ነፍስ ያለው ሰው አይደለም ብለው የነበሩ አፈሩ፤ እውነትና ፍትህ ኢትዮጵያና አፍሪቃ ከበሩ፡፡ ከሲግመንድ ፍሮይድ የሳይኮ አናላይሲስ ጥናትና ምርምር በፊት፡- ጥቁር ህዝብ ትልቅ ትል ላይሆን ነፍስ ያለው ሰው ከሰውም ሰው ጀግና መሆኑን በተጨባጭ ያስመሰከረ የኢትዮጵያ ገበሬ ሠራዊት ነው፡፡
  ከፈረንጅ የአውሮጳ መንግሥታት ሩሲያና ፈረንሳይ የአድዋን ድል ከልብ ደገፉ፡፡ ጀኔራል ባራቴሪ በአገሩ በኢጣሊያ ጦር ፍርድ ቤት ቀርቦ ማዕረጉ ተገፈፈ፡፡ የአገሪቱ ጠቅላይ ሚኒስትር ሲኞር ክሪስፒ በፈቃዳቸው ሥልጣናቸውን ለቀቁ፡፡
  የኢጣሊያዊው ንጉሥ አማኑኤል ኡምቤርቶ የልደት ቀን የሀዘን ቀን እንዲሆን ተወሰነ፡፡ ሮማ (ሮም)ን ፍሎሬንስን ሚላኖ (ሚላን)ን ቬነስን…የመሳሰሉ የኢጣሊያ ከተሞች ምኒሊክ ለዘላለም ይኑር በሚሉ የተቆጡ አውሮጳውያን ትዕይንተ ህዝብ አድራጊዎች ተጥለቀለቁ፡፡ ኢትዮጵያ በአድዋ ጦርነት ወቅት በዋናው የጦር ግንባር ገጥማ በፍልሚያ ድል ማድረግ ብቻ ሳይሆን በአጠቃላይ በአራት መስክ ሠለጠነች በምትባለው አውሮጳዊት አገር ኢጣሊያ ላይ ድል ተቀዳጅታለች፡፡ ይኸውም፡- በጦርነት እና በወታደራዊ መረጃ (Military Security intellegence)፤ በዲፕሎማሲና በፖለቲካ ጥበብ ነው፡፡
  በፖለቲካ ጥበብ በኢጣሊያ ቅኝ ገዢ ብልጣብልጥ የመንግሥት ሥልጣን ላይ ድል የተቀዳጀችው ገና ጦርነቱ ሳይጀመር ለጦርነቱ መጀመር መነሻ የሆነው የውጫሌ ውል በተደረገበት ሥፍራ ነው፡፡
  የውጫሌ ውል አንቀጽ አሥራ ሰባት የጣሊያንኛው፡- ኢትዮጵያ ከአውሮጳ መንግሥታት ጋር ማድረግ የምትፈልገውን ግንኙነት በኢጣሊያ መንግስት በኩል ማድረግ አለባት ሲል፤ አማርኛው ደግሞ ኢትዮጵያ ከአውሮጳ መንግሥታት ጋር ማድረግ የምትፈልገውን ግንኙነት በኢጣሊያ መንግሥት በኩል ማድረግ ትችላለች ይላል፡፡
  የአማርኛው የኢትዮጵያን ሉአላዊነትና ልዕልና ያከብራል፤ የጣሊያንኛው የኢትዮጵያን ሉአላዊነትና ልዕልና መድፈር ብቻ ሳይሆን ብሔራዊ ክብሯንና ጥቅሟን ይነካል፡፡ ይሄን የተገነዘቡት የኢትዮጵያ መሪዎች የውሉ አንቀጽ አሥራ ሰባት የጣሊያንኛ ትርጓሜ የኢትዮጵያን ክብርና ጥቅም በማይነካና ሉአላዊነቷን በሚያከብር መልኩ እንዲስተካከል በተደጋጋሚ ወተወቱ፡፡ መወትወቱ ውጤት ሳያመጣ ቢቀር፤ ምኒሊክ፡- መዘግየት አደገኛ ነው ጣይቱ አሉ፤ ስለዚህ ጉዞ ወደ ወሳኙ ጦርነት (ማድረግ) የግድ ነበር፡፡
  የኢትዮጵያን አገራዊ ክብርና ጥቅም ህልውናና ልዕልና ሲሆን ሲሆን በውድ ካልሆነ ደግሞ ሳይወድ በግድ ማስከበርና ማስጠበቅ የአንድ አገር መንግሥት ዋነኛ ግዴታና ኃላፊነት ነው፡፡
  ስለዚህ አባቶቻችን (የጥንት ወላጆቻችን) ውትወታቸው አልሰማ ቢል ጦር እንግጠም አሉ፡፡
  ይሄ የፖለቲካ ጥበብ ብልጫ ወይም ድል ነው፡፡
  በወታደራዊ መረጃ (Military Security intellegence) ብልጫ የኢንቲጮ ተወላጅ በሆኑት ባሻዬ አውአሎም ሀረጐት አማካይነት ኢትዮጵያ ሠለጠነ የተባለውን የአውሮጳ ኃይል አሸንፋ ጣሊያኖች ባልፈለጉት ቦታና ባልመረጡት ጊዜ ወደ ጦርነት እንዲገቡ አድርጋለች፡፡
  በወታደራዊ ሣይንስ (Military Science) አገባብ ለጦርነት የተንቀሳቀሰ አንድ ሠራዊት ወዲያውኑ ወደ ጦር ግንባር መግባት አለበት፡- ይሄ አንድ ነጥብ ነው፡፡ ሌላው ነጥብ አንድ ለግዳጅ የተንቀሣቀሠ ሠራዊት ለመሰናዶም ሆነ ለመከላከል ውጊያ በአንድ የመከላከያ ወረዳ ከሠፈረ በዚያ መከላከያ ወረዳ ከስድስት ወራት በላይ መቆየት የለበትም፡፡ በአንድ ቦታ ላይ ከስድስት ወራት በላይ ከቆየ ሊደርስ የሚችል የወታደራዊ ሥነልቦና (Military Psychology) ጉዳት አለ፡፡ የመሸገበትን የመከላከያ ወረዳ እየተለመማመደ ሲሄድ ስለሚዘናጋና የውጊያ ስሜቱ እየቀነሰ (እየቀዘቀዘ) ስለሚመጣ ጉዳት አለው፡፡ ከሎጂስቲክ አኳያ የውጊያ ዝግጁነቱም አደጋ ላይ ስለሚወድቅ (በሌላ አነጋገር ስንቅ እየጨረሰ ስለሚሄድ) በነዚህ ምክንያቶች በአፋጣኝ ወደ ጦርነት መግባት ለሠራዊቱ ድል አድራጊነት ትልቅ ጥቅም አለው፡፡
  የኢትዮጵያ በሠላም ጊዜ ገበሬ በጦርነት ጊዜ ጀግና ተዋጊ እንጂ ዘመናዊ ወታደራዊ መሠረት ያለው Professional Army ባልነበራት በዚያ ዘመን ለአንድ መቶ ሃያ ሺህ ሠራዊት የሎጂስቲክ አገልግሎት እየሰጡ ለረጅም ጊዜ መቆየት አስቸጋሪ ነው፡፡ ስለዚህ የጀግንነት ግለት ሳይበርድ የሎጂስቲክ (ስንቅ ትጥቅ መድሃኒት) አቅም ሳይዳከም በፍጥነት ጦር መግጠም እጅግ አስፈላጊ ነበር፡፡ የኢትዮጵያ ሠራዊት ጦርነቱን ፈጥኖ ለመግጠም ጣሊያኖች ወደ አድዋ መምጣት አለባቸው፤ ወይም ደግሞ የእኛ ሠራዊት ጣሊያኖች ወደመሸጉበት የኤርትራ ከፍተኛ ቦታዎች መሄድ አለበት፡፡ ከነዚህ ሁለት ሁኔታዎች የአንደኛው መሆን የግድ ነበር፡፡ ወደ ጣሊያኖች መሄድ ከፖለቲካ ሁኔታዎች ባሻገር ከወታደራዊ ሳይንስ አንፃር የሚመረጥ አይደለም፡፡ በምሽግ ውስጥ ሆኖ የሚከላከል ሠራዊትና ከምሽግ ወጥቶ የሚያጠቃ ሠራዊት መስዋዕትነት የመክፈል ዕድሉ እኩል አይደለም፤ ለሚከላከል አንድ ወታደር ሶስት የሚያጠቃ ወታደር ነው የሚያስፈልገው፡፡
  ስለዚህ ጣሊያኖች ወደ አድዋ እንዲመጡ ማድረግ የግድ ሆነና የአድዋ ድል ቁልፍ የምላቸው የአርባ ዓመቱ ጐልማሣ ባሻዬ አውአሎም ሀረጐት ተጠሩና ለአንድ ታላቅ አገራዊ ኃላፊነት እንዲሠናዱ ተደረገ፡፡ ይሄ ሁሉ በምሥጢር ነው የተከወነው፡፡ በሚቀጥሉት ቀናት አውአሎም ለኢጣሊያ ኮሎኒያሊስት ወራሪዎች ከሚሠልሉ የአገር ተወላጆች (ፌርማቶሪዎች) ጋር ወደ ባራቴሪ ተላኩ፡፡ ከመሄዳቸው በፊት ስንቅ ማለቁና ተስቦ በሽታ በሠራዊቱ ውስጥ መግባቱ ፌርማቶሪዎች ባሉበት ተለፈፈ፡፡ አውአሎምና ፌርማቶሪዎቹ ወደ ኤርትራ ዘልቀው ለጄነራል ባራቴሪ ይሄንኑ ነገሩት፡፡
  ባራቴሪ ጊዜው አሁን ነው አለና የካቲት 22 አመሻሽ ላይ በአውአሎም መሪነት ሠራዊቱን ይዞ ወደ አድዋ ተመመ፡፡ የካቲት 21 እንዳይነሣ ዝናብ ስለያዘው እንጂ ታላቁ ጦርነት የካቲት 22 ሊደረግ ይችል ነበር፡፡ ስለዚህ ጄነራል ባራቴሪ በዝናብ በመያዙ ምክንያት ዘመቻውን በማግሥቱ አደረገና የካቲት 22 ቀን 1888 ዓ.ም ሌሊቱን ሙሉ ሲጓዝ አድሮ ሊነጋ ሲል የካቲት 23 ቀን 1888 ዓ.ም አድዋ ጦር ግንባር ደረሠ፡፡ አውአሎም ከፊት ለፊታቸው የጀግናው የቱርክ ፓሻ የአፍሪቃ ጀኔራል አሉላ አባነጋ የገበሬ ሠራዊት ምሽግ እንደታያቸው መሮጥ ጀመሩ፡፡ ባራቴሪ፡- አውአሎም አውአሎም ብሎ ተጣራ፡፡ እስሀ ዝዋአልካዮ አያውለና ብለውት ዘለው አሉላ ምሽግ ውስጥ ገቡ፡፡ ዛሬ አንተን አያድርገኝ ማለታቸው ነው በአማርኛ፡- እስሀ ዝዋአልካዮ አያውለና፡፡
  ከጥቂት ደቂቆች በኋላ ምድር ቁና የሆነችበት ድብልቅልቅ ያለው ጦርነት ተጀመረ፡፡ የኢትዮጵያ ጀግና የገበሬ ሠራዊት ከጠዋቱ አራት ሠዓት ግድም ታላቁን የአድዋ ድል መቀዳጀቱን አረጋገጠ ፡፡ ብዙ ሺህ የኢጣሊያ ወታደሮች በጦር ሜዳ ተገደሉ፡፡ ብዙ ሺዎች ደግሞ ቁስለኛና ምርኮ ሆኑ፡፡ የተቀረውንና ድል ተመትቶ የተበታተነውን የኢጣሊያ ወታደር እያሣደደና እያባረረ አፍሪቃዊው ኃይል ፈጀው ብሎ ፅፎአል ጆርጅ በርክሌይ፡፡ ከሚሸሹት መሃከል አንዱ የአውሮጳዊው ወራሪ ሠራዊት ዋና አዛዥ ጄኔራል ባራቴሪ ነው፡፡
  ይሄ (በአውአሎም ብስለትና ሥልጡንነት መስዋዕትነትና ኢትዮጵያዊ ፍቅር የተገኘው) ሰለጠነ በሚባለው የአውሮጳ ኃይል ላይ አልሰለጠነም በሚባለው አፍሪቃዊ ኃይል የተጨበጠ ትልቅ የወታደራዊ መረጃ (Military Security intelligence) ብልጫ ወይም ድል ነው፡፡
  በወታደራዊ ሣይንስ ደግሞ ወታደራዊ መረጃ ለወታደራዊ ግጃጅ አፈፃፀም ዋነኛና ወሣኝ ጠቀሜታ አለው፡፡ በዚህች ዓለም ላይ ከተደረጉ አብዛኞቹ ጦርነቶች ድል ያደረጉት የወታደራዊ መረጃ ብልጫ የነበራቸውና ፍትህና እውነትን ፖለቲካዊ መሠረት ያደረጉት ናቸው፡፡ እኛ ሁለቱንም ነበረን፤ ዓላማችን የአገራችንን ጥቅምና ክብር ህልውናና ልዕልና ማስከበር ነፃነታችንን ማስጠበቅ ሲሆን፡- ይህም የፍትህና የእውነት ነፍሥ ነው፡፡ በአገር ወዳዱ ባሻዬ አውአሎም ሀረጐት አማካይነት ደግሞ በአውሮጳ ላይ የወታደራዊ መረጃ ብልጫን ተቀዳጀን፡፡ ኢትዮጵያ በረጅም ዘመን ታሪኳ ከውጪ ወራሪዎች ጋር ባደረገቻቸው ጦርነቶች ሁሉ፡- እውነትና ፍትህን መሠረት አድርጋለች፡፡
  የዲፕሎማሲያዊ ድሉን የተቀዳጀችው ኢትዮጵያ፡- አውሮጳ ውስጥ ባስቀመጠቻቸው የቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ ወላጅ አባት ራስ መኮንንና ግራዝማች ዮሴፍ በተሰኙ ዲፕሎማቶቿ አማካይነት ነው፡፡ ጣሊያኖች ኢትዮጵያውያን ያልሰለጠኑ በመሆናቸው በምርኮኞች ላይ ሠብአዊነት የጐደለው ድርጊት ይፈፅማሉ ብለው ያስወራሉ፡፡ ግራዝማች ዮሴፍ በተለያዩ ቋንቋዎች እየፃፈ ለአውሮጳ ጋዜጦች ይሄን ያስተባብላሉ፡፡ ከጥቂት ጊዜያት በኋላ ደግሞ ኢትዮጵያ ልክ ዲፕሎማቶቿ እንዳሉት ምርኮኞችን ግብር አብልታ አካላቸዉም ምቾታቸውም ሳይጓደል ወደ አገራቸው ሰደደች፡፡
  በዚህም ዲፕሎማሲያዊ ሥልጣኔዋን ለመላው አውሮጳ እና ለመላው ዓለም በተጨባጭ አሳየች፡፡ ከመቶ ዓመታት በላይ ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት ያላት ብቸኛ አፍሪቃዊት አገር፡- ኢትዮጵያ ነች፡፡ የአብዛኞቹ የአፍሪቃ አገሮች ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት ረጅም ዕድሜ ከስድሣ ዓመት አይዘልም፡፡ ኢትዮጵያ፡- ከኢጣሊያና ከፈረንሣይ ከአሜሪካ (USA) እና ከእንግሊዝ ከሩሢያና ከጀርመን (ከስድስት አገራት) ጋር ከመቶ ዓመታት ለሚበልጥ ጊዜ ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነትን አዳብራ እና አፅንታ ቆይታለች፡፡
  በአድዋ ድል፡-
  ዋነኛው ድል በጦር ግንባር ፍልሚያ የተገኘው ድል ነው፤ ታላቁ የአድዋ ድል፡፡
  የአድዋ ጦርነት የተደረገው በሁዳዴ ፆም ውስጥ ነው፡፡ ከዚያ በፊት በአፄ ቴዎድሮስ ዘመነ መንግሥት የተደረገው የመቅደላ ጦርነትም በሁዳዴ ፆም ውስጥ ነው የተካሄደው፡፡ በአድዋ ጦርነት ፆምና ውጊያ አብሮ ስለማይሄድ ግብፃዊውን ጳጳስ ሠራዊቱን ይፍቱትና እንደ ልቡ ይዋጋ ቢባሉም ባለመፍታታቸው ከኢትዮጵያ የገበሬ ሠራዊት ጿሚ የሆነው እየፆመ ለመዋጋት ተገዶአል፡፡ በመቅደላ ውጊያ ዓፄ ቴዎድሮስ [ካሣ ኃይሉ ወልደጊዮርጊስ (አባ ታጠቅ ካሣ) (መዩሣው ካሣ) (ወሬሣው ካሣ)] ሊወጋቸው ለመጣው እንግሊዛዊው ጄኔራል ናፒዬርና ሠራዊቱ ፆምህን ፈትተህ ከእኔ ጋር ውጊያ ግጠም ብለው አንድ ሺህ በጐች ልከውለታል፡፡
  ከአድዋ ጦርነት በፊት ባሉት ጥቂት ወራትና ሣምንታት መቀሌና አምባላጌ ላይ የተደረጉ ጦርነቶች አሉ፡፡ የመቀሌን ከተማ በኢጣሊያዊው ኮሎኔል ጋሊያኖ ከሚመራው አውሮጳዊ ሠራዊት ለማስለቀቅ መስዋዕትነቱ የበዛ በመሆኑ፡- መቀሌ የተለቀቀችው በፈረንጆች ሚሊኒየም BBC (British Broadcasting Corporation) የሚሊኒየሙ ምርጥ ሠብዕና ብሎ ከአህጉር አፍሪቃ ባጫቸው ከጐንደር ኦሮሞ ቤተሠብ በሚወለዱት እቴጌ ጣይቱ ብጡል ሥልጡን ወታደራዊ መላ ነው፡፡

  ዝርዝሩን እዚህ አላወሣውም እንጂ መቀሌ በጣይቱ ልዩ ወታደራዊ ብቃት መያዝዋን መግለፅ ይጠቅማል፡፡ በኋላ ላይ ኮሎኔል ጋሊያኖ በአድዋ ጦርነት ተማርኮ፡- የምንሊክን ፊት ከማይ ግደሉኝ ብሎአል፡፡ በአምባላጌው ጦርነት ሊቀ መኳስ አባተ መድፍ ተኩሠው በጣሊያን መድፍ አፍ ውስጥ እስከ መክተት የዘለቀ አነጣጣሪነታቸውን አሣይተዋል፡፡ የኢትዮጵያ መንግሥት ሥልጣናት፡- ማዕከል ወሎ ውጫሌ በነበረበት ሁናቴ፤ ዳግማዊ ዓፄ ምኒሊክ (አባ ዳኘው) ለህዝባቸው የክተት ጥሪ ካደረጉ በኋላ ከዳር እስከ ዳር የተንቀሣቀሠው የተቆጣ ኢትዮጵያዊ ሠራዊት ሢተም፤ ሲገባኝ ከሠሜን ኢትዮጵያ ከጐንደር ከጐጃም ከወሎና ከትግራይ … የተንቀሳቀሰው አትንኩኝ ያለ ኢትዮጵያዊ ጀግና ከሚተምመው ሠራዊት የተገናኘው በትውልድ አቅራቢያው ሆኖ ነው፡፡
  መጓጓዣ በሌለበት ዘመን የሠሜኑን የኢትዮጵያ ጀግና የገበሬ ሠራዊት ወደ ሰሜን ለማዝመት ሲባል በመሀል አገር ማሰባሰብ የሚያስፈልግበት ሁኔታ አልነበረም፡፡
  ዘላለማዊ ክብር ለጀግኖች አባቶቻችን ይገባቸዋል!
 • loader Loading content ...
 • @Teferi Mihiret   1 year ago
  "i am what i am & that is all that i a am."

  ፊት አዉራሪ አየለ ተሰማ(አባ ጓዴ)
  #በጎንደር ከጓንግ ወንዝ እስከ መተማ


  የፋሽስት ጣሊያን መንግስት ሃገራችን በግፍ በወረረበት ወቅት ሃገራችን ብዙ ስመጥር ጅግኖችን አፍርታለች። በዚህ ወረራ ወቅት በጎንደር ከጓንግ ወንዝ እስከ መተማ ድረስ በጀግንነት ሃገሩን ከወረራ ነፃ ካደረጉት መካከል ጀግናዉ አርበኛ ፊት አዉራሪ አየለ ተሰማ አባ ጓዴ አንዱ ነበሩ። በአንድ ወቅት ፊት አዉራሪ አየለ ተሰማ ሰባስጌ በተባለ የፋሽስት የጦር ካምፕ ቦታ ላይ ከትንሽ ተከታዩቻቸዉ ጋር ጥቃት ፈፅመዉ 3 ወታደር ገድለዉና ብዛት ያለቸዉን በማቁሰላቸዉ፤ የፋሽስት ጣሊያን ባለስልጣናት በፊት አዉራሪ አየለ ላይ የተጠናከረ ዘመቻ በማድረግ አሳድደዉ ለመግደል ያላደረጉት ጥረት አልነበረም። ነገር ግን እሱን መያዝ ቢቸግራቸዉ ቤተሰቦቹን አባቱን ቀኝ አዝማች ተሰማን ፤ ወንድሞቹን ልጅ ታደሰ እና ረዳን በመያዝ በጎንደር አርበኞች በሚታጎሩበት እስር ቤት አሰሯቸዉ። ነገር ግን በወቅቱ በእስር ቤቱ በተነሳዉ የታይፎይድ በሽታ ብዙ አርበኞች ሲሞቱ ልጅ ታደሰ የገፈቱ ተቃማሽ ነበር። ይሁን እንጅ የቀሪዎች ህይወት ለማትረፍ በተደረገዉ ጥረት ወ/ሮ አቻሽማን ተሰማ ሽማግሌዉ አባቷን ቀኝ አዝማች ተሰማ እና ወንድሟን ረዳን ለማስፈታት ባደረገችዉ ጥረትና በዚህ ወቅትም ብዙ የጎንደር አርበኞች በጣሊያን ባለስልጣናት ምህረት ተደርጎላቸዉ ከስር ተፈተዋል። ይሁን እንጅ ቀኝ አዝማች ተሰማ በወቅቱ በታመሙት የታይፎይድ በሽታ በተፈቱ በሳምንታት ዉስጥ ለሞት አበቃቸዉ። ታዲያ ለዚህ ሁሉ የቤተሰብ ችግር አምጭ ተደርጎ የታየዉ ፊት አዉራሪ አየለ ተሰማ ነበር። ለፊት አዉራሪ ግን የእነሱ ሞት ለነፃነታቸዉ እንደ መሰዋዕትነት አድረጎ ነዉ የቆጠረዉ። በዚህ ልዩ የቁጭት አርበኝነትና ሃገር ወዳድነት ስሜት ጀግናዉ አርበኛ ፊት አዉራሪ አየለ ተሰማ አባ ጓዴ ከወንድሙ ከግራዝማች ረዳና ከልጅ አበራ ጋር በመሆን በሜጀር ባንቲ ቸኮ ሴንታታ የሚመራዉን የጣሊያንን ጦር በመተማ አካባቢ ነጋዴ ባህር አማኒት ተብሎ በሚጠራዉ ቦታ በሰኔ 29 ቀን 1938 ዓ.ም በመሄድ አስደናቂ ጀብድ በመስራት የፋሽስትን ጦር በመደምሰስ አኩሪ ታሪክ ሰሩ። ይህ ጀብዳቸዉም እስከ ስደተኛዉ ንጉስ ቀዳማዊ ሃይለ ስላሴ ድረስ በመሰማቱ ጃንሆይም የአድንቆት ደብዳቤና በግራዝማች ራዳ አማካኝት 300 ጠበንጃ፤ 3000 ጥይትና 1000 ብር ልከዋል። በአባባ ገሪማ ታፈረ "ጎንደሬ በጋሻዉ" እና በሕይዎት ህዳሩ የቀ.ኃ.ስ መልክተኛ "ያች ቀን ተረሳች" መፃህፎች ስለጀግናዉ አርበኛ ፊት አዉራሪ አየለ ተሰማ እና ወንድማቸዉ ግራዝማች ረዳ ተገልፆል። በዚህ የአማኒት ጦርነት ድል መሰረት ለጀግናዉ አርበኛ ፊት አዉራሪ አየለ ተሰማ በህዝብ እንዲህ በፉከራና በቀረርቶ ተገጠመላቸዉ፡፡

  አባት አስገዳይ ወንደም አስገዳይ ብለዉ ሲያሙት
  ነጭ ሰዉ ገዳይ ወርዶ አማኒት
  ገዳይ አማኒት
  እንደ አራስ ነብር ተጉዞ ሌሊት
  ገዳይ ኩመር በር
  በለዉ እያለ ከቀስቅስ ጋር፡፡
  የአባቱን ጠላት የተሰማን
  የታዴን ጠላት የወንድሙን
  በቁሙ ጠጣዉ በሳንጃ አልቢን
  አርዶ በካር ጠጣዉ ደሙን፡፡
  ፊት አዉራሪ አየለ ተሰማ ‹‹ ባልንጀራዬ! ፤ ባልደረባዬ! ፤ የኔ ቢጤ! ›› ሚለዉ ቢኖር ‹‹ አባ ጓንዴ! ነዉ ፈረሱ! ›› አንድ ቀን አሉ አየለ እና ፈረሱ ፋሺስት ጣሊያን ሲያሳዳቸዉ ቢያድር በመንገድ ላይ ሳሉ እራባቸዉ በዚህን ግዜ አባ አየለ ከፈረሱ ጋር ወደ መንደር ወጠዉ ካንድ ባዶ ቤት የሚበላ ሲያዩ በስርቆት ማለት ነዉ ህሊናቸዉን ወቀሳቸዉ እና ለፈረሳቸዉ ‹‹ የማናውቀውን ፡ ሌብነት፣ ልንሰርቅ ፡ ገብተን ፡ ከሰው : ቤት፣ ይቅርብን ፡ ጓዴ ፡ እንውጣ፣ የሚጠብቀን : መጣ! ›› ብለዉ ፈረሳቸዉን በቃለ ሰብአዊ አወሩት ፡፡ ይህን ነገር የሰማ ያአገሩ ኗሪም ‹‹ ለፈረስ ፡ ለበቅሎ ፡ ይተርፍ ፡ የነበረ፣ ዛሬስ ፡ ለሰው ፡ ያኽል ፡ ይቸግር ፡ ጀመረ! ›› ብሎ አነባ፡፡ እሳቸዉ እራሳቸዉም ይባላል ለሰዉ ሲመክሩ ‹‹ ሌሊት ፡ ከጭቃ ፡ ላይ ፡ ፈረስ ፡ ቢጥልህ፣ ወንድሜ ፡ አትናደድ ፡ ማንም ፡ አላየህ፣ ይልቁን ፡ ተጠንቀቅ ፡ ቀን ፡ እንዳይጥልህ! ›› ነዉ ሚሉ አሉ፡፡ እና አንድ ቀን ፊት አዉራሪ አየለ ተሰማ ሰባስጌ በተባለ የፋሽስት የጦር ካምፕ ቦታ ላይ ከትንሽ ተከታዩቻቸዉ ጋር ጥቃት ፈፅመዉ ሶስት ወታደር ገድለዉና ብዛት ያለቸዉን በማቁሰላቸዉ፤ የፋሽስት ጣሊያን ባለስልጣናት ‹‹ ምን? ፡ ቀረኝ ፡ በሎ ፡ ነዉ ፡ ይሄን ፡ ሚያረገዉ! ›› ብለዉ አጠገብ ባሉ ባንዳወች ቢያፈጡ ‹‹ ተሰማ ፡ ሳይቀጣው ፡ በልጅነት ፡ ቀርቶ፣ ገና ፡ ራስ ፡ ይመታል ፡ እንኳን ፡ ባት ፡ አግኝቶ! ›› ብለዋል፡፡

  በዚህን ግዜ የፋሽስት ጣሊያን ጦር እሱን ለመያዝ ቢቸግራቸዉ ቤተሰቦቹን አባቱን ቀኝ አዝማች ተሰማን ፤ ወንድሞቹን ልጅ ታደሰ እና ረዳን በመያዝ በጎንደር አርበኞች በሚታሰሩበት እስር ቤት አጎሯቸዉ፡፡ በእሰር ቤቱም በተነሳዉ የታይፎይድ ወረርሽኝ ብዙ አርበኞች ሲያልቁ ወንድማቸዉ ልጅ ታደሰም የዚህ ገፈት ቀማሽ ሆኑ፡፡ እህታቸዉም ወ/ሮ አቻም የለሽ ተሰማ ሽማግሌዉ አባቷን ቀኝ አዝማች ተሰማ እና ወንድሟን ረዳን ለማስፈታት ባደረገችዉ ጥረት እንዲሁም ፋሺስት ጣሊያ ‹‹ ሎሌ ፡ ለሰህተት ፡ ጌታ ፡ ለምህረት! ›› እንደ ተፈጠረ ይታወቅላቸዉ ዘንድ ጥቂት አርበኞችን በምህረት ፈቱ፡፡ አባታቸዉ ግን ቀኝ አዝማች ተሰማ ከእስር እንደ ወጡ በሳምንቱ ሞቱ፡፡
  ፊት አዉራሪ አየለም ተሰማም ከአባታቸዉ ሞት በዉሃላ በከፍተኛ ቁጭት እና የአርበኝነት ስሜት ከወንድሙ ከግራዝማች ረዳና ከልጅ አበራ ጋር በመሆን ‹‹ በሜጀር ፡ ባንቲ : ቸኮ : ሴንታታ! ›› የሚመራዉን የጣሊያንን ጦር በመተማ አካባቢ ነጋዴ ባህር ‹‹ አማኒት ›› ተብሎ በሚጠራዉ ቦታ ሰኔ ሃያ ዘጠኝ ቀን 1938 ዓ.ም አስደናቂ ጀብድ በመስራት የፋሽስትን ጦር በመደምሰስ አኩሪ ታሪክ ሰሩ። በዚህን ግዜ ሜጀር ፡ ባንቲ : ቸኮ : ሴንታታ!

  ‹‹ የዕድሌ ፡ ክፋቱ ፡ ፈተና ፡ አብዝቶብኝ፣
  አየለ ፡ አየለና ፡ ኀይሌን ፡ ወሰደብኝ! ›› ብሎ አነባ፡፡ 
  ይህን ያየና የሰማ የሀገሩ ኗሪ እና ጉብል 
  ‹‹ አባት ፡ አስገዳይ ፡
  ወንደም : አስገዳይ : ብለዉ : ሲያሙት
  ነጭ : ሰዉ : ገዳይ ፡ ወርዶ : አማኒት
  ገዳይ ፡ አማኒት
  እንደ ፡ አራስ : ነብር : ተጉዞ ፡ ሌሊት
  ገዳይ ፡ ኩመር ፡ በር
  በለዉ : እያለ : ከቀስቅስ : ጋር
  የአባቱን ፡ ጠላት : የተሰማን
  የታዴን : ጠላት : የወንድሙን
  በቁሙ ፡ ጠጣዉ : በሳንጃ : አልቢን
  አርዶ : በካር : ጠጣዉ : ደሙን፡፡ ›› እያለ ሲሸልል እና ሲፎክር 
  አንዲት የጎንደር ጉበል እርጉዝ ሁኗ ኑሯ ‹‹ ሰጋ አማረኝ! ›› አለች አገሬዉ
  ‹‹ ሥጋ ፡ አማረኝ : አለች :የቀለቤሰ ፡ እናት፣ መተማ ፡ አትሄድም ፡ ወይ ፡ ከታረደበት! ›› ብለዉ መለሱላት ፡፡
  ይህን አኩሪ ደል የሰሙትም ስደተኛዉ ንጉስ ቀዳማዊ ሃይለ ስላሴ በግራዝማች ራዳ አማካኝት ‹‹ ያባይ ፡ ምልክቱ ፡ አንደበቱ ፡ የገዳይ : ምልክቱ : ሽልማቱ! ›› ብለዉ የአድንቆት ደብዳቤና 300 ጠበንጃ፤ 3000 ጥይትና 1000 ብር ላኩ። 
  #ዘላለማዊ ክብርና ሞገስ ለምንግዜም ሃገር ወዳድ የነፃነት ጀግኖች አባቶቻችና እናቶቻችን!! 
  #አሹ ዋሴ

 • loader Loading content ...
 • @Teferi Mihiret   1 year ago
  "i am what i am & that is all that i a am."
  አርበኛ ሸዋረገድ ገድሌ 

  "የምታስፎክር ሰንጋ ገለሌ
  በጦር መካከል ሳይሆኑ አያሌ
  በጥይት ገዳይነጭ ብርገድሌ
  የሴት ወንድናት ሸዋረገድ ገድሌ"ተብሎ የተገጠመላቸውን፣ በአምስት ዓመቱ የጠላት ወረራ ጊዜም አኩሪ ጀብዱየፈጸሙትን የአርበኛዋን የሸዋረገድ ገድሌን ታሪክ የሚተርክ መጽሐፍ ሰሞኑን ቀርቧል፡፡ ‹ሸዋ ረገድ ገድሌ፣ የአኩሪ ገድላት ባለቤት› ይሰኛል፡፡ ሺበሺ ለማ ጽፎት ዶክተር ክፍሌ ማርቆስ ገድሌ አሳትመውታል፡፡ በአምስት ዓመቱ የፋሽስት ወረራጊዜ ለሀገራቸው አኩሪ ገድል በመፈጸምና ለነጻነታችን ዋጋ በመክፈል ስማቸው ከሚነሡ ሴቶች ሸዋረገድ ገድሌ ግንባር ቀደም ናቸው፡፡በ1878 ዓም የተወለዱት ወ/ሮ ሸዋ ረገድ ገድሌ ሁለገብ እንደነበሩ ታሪካቸው ያሳያል፡፡ የቤተ ክህነቱን ትምህርት ተምረዋል፡፡ትዳርን አልፈልግም ብለው ምናኔን መርጠው ኢየሩሳሌም ድረስ ተጉዘዋል፡፡ ከመጀመሪያዎቹ የባንክ ተጠቃሚዎች፣ የአክሲዮን ገዥዎች፣የፋብሪካ ተካዮች መካከል አንዷ ነበሩ፡፡ የጉለሌ ቅዱስ ገብርኤልንም ያስተከሉት እርሳቸው ነበሩ፡፡
  የሸዋረገድን ስም ይበልጥ ከፍ አድርጎያስጠራው አርበኛነታቸው ነው፡፡ የኢጣልያ ጦር ሊጎርሰን ማሰፍሰፉ ሲሰማ በአዲስ አበባ ከተማ በሀገር ተቆርቋሪ ዜጎች በተቋቋመውየሀገር ፍቅር ማኅበር አባልነት መጀመሪያ ከተመዘገቡት ጥቂት ሴቶች መካከል አንዷ እርሳቸው ነበሩ፡፡ ወራሪው ፋሽስት አዲስ አበባሲገባና የኢትዮጵያ ሰንደቅ ዓላማ ወርዶ የኢጣልያ ባንዴራ ሲተካ ወ/ሮ ሸዋረገድ ገድሌ ስቅስቅ ብለው አለቀሱ፡፡ በዚህ ምክያትምበኋላ ‹የኢትዮጵያ ሰንደቅ ዓላማ ወርዶ የገናናው የኢጣልያ ሰንደቅዓላማ ሲውለበለብ በማየትሽ አልቅሰሻል›› በሚል ተከሰው ነበር፡፡ ሸዋረገድም ያለምንም ፍርሃት ‹አዎ አልቅሻለሁ፤ ያገሬን መወረርናመዋረድ ያወቅሁት የኛ ሰንደቅ ዓላማ ወርዶ የናንተ ሲውለበለብ በመታየቱ ነው፡፡ ሰው ለእናት ሀገሩ ቢያለቅስ ነውሩ የት ላይ ነው?››ብለው ነበር የመለሱት፡፡
  ወ/ሮ ሸዋረገድ ለአርበኞች ስንቅበማቀበል፣ መሣሪያ በመግዛት፣ መረጃ በማሰባሰብ፣ መድኃኒት በመላክና ሞራል በመስጠት አምስቱን ዓመት በተጋድሎ ነው ያሳለፉት፡፡በዚህ ምክንያት በተከሰሱ ጊዜም ‹‹ለአርበኞች ስንቅ ማቀበሌ እውነት ነው፤ይህንንም ያደረግኩት ለሀገሬ ክብር ብዬ ነው፡፡ ሰው እንኳንለሀገሩ የእናንተ ወይዛዝርት ሀገራቸው ያልሆነቺው ኢትዮጵያን ለመውረር የጣታቸውን ቀለበት ሳይቀር መስጠታቸውን ትናገራላችሁ፡፡ እኔምለሀገሬ የሠራሁት ሲያንሰኝ እንጂ አይበዛብኝም›› ነበር ያሉት፡፡ ወ/ሮ ሸዋረገድ ከሚጠቀሱላቸው ሥራዎቻቸውአንዱ ለቀይ መስቀል ማኅበር የነበራቸው ድጋፍ ነው፡፡ በጦርነቱ ዋዜማ ሐምሌ 1 ቀን 1927 ዓም ለተቋቋመው የኢትዮጵያ ቀይ መስቀልማኅበር ንብረታቸውን ሸጠው አስረክበዋል፡፡ እሥር ቤት በገቡ ጊዜ ከተከሰሱበት ወንጀል አንዱም ‹ቀይ መስቀልን ትረጃለሺ› የሚልነበር፡፡ ሸዋረገድ ቀይ መስቀልን ከመርዳትም ባሻገር ኢትዮጵያውያን ወይዛዝርት እራፊ ጨርቅ እንዲያሰባስቡ በማድረግ ለአርበኞች ቁስልማሸጊያ ይልኩላቸው ነበር፡፡
  ሸዋረገድ ከርዳታው ጎን ለጎን ለአርበኞቹየመረጃ ምንጭም ነበሩ፡፡ በከተማው የሚገኙ የጠላት መረጃዎችን በማሰባሰብና ወደ አርበኞች በምሥጢር በመላክ አርበኞች እንዲጠቀሙባቸውአድርገዋል፡፡ በዚህና በሌሎች ገድሎቻቸው ምክንያትም የሞት ፍርድ ተፈርዶባቸው ነበር፡፡ በፈጣሪ ቸርነት ግን ሳይፈጸምባቸው ቀርቷል፡፡የሞት ፍርዱ ባይፈጸምባቸውም የኢጣልያን እሥር ቤት ከሚያዘወትሩት አንዱ ሸዋረገድ ሆነዋል፡፡ በየጊዜው ይታሠራሉ፤ ይፈታሉ፡፡ በመጨረሻግን አዚናራ ወደምትባል ከሰርዲኒያ ሰሜናዊ ምዕራብ ወደምትገኝ ደሴት ታሥረው ተልከዋል፡፡ እዚያም ቢሆን ጽናታቸው አልተሰበረም፤ወኔያቸውም አልተሰለበም፡፡ የሚያደርጉት ቢያጡ በእሥር ቤት የሚቀርብላቸውን የተበላሸ ምግብ በአሣሪዎቻቸው ፊት በመድፋትና ጦማቸውንበመዋል ፋሽስትን ይቃወሙ ነበር፡፡ በዚህ ሁኔታም ለአንድ ዓመት ከመንፈቅ ታሥረው ተፈቱ፡፡ አዲስ አበባ ሲገቡ ግን ትግላቸውን ቀጠሉእንጂ አላቆሙም፡፡ ሕዝቡም የዘበኛ ሱሪካኪና ገምባሌ እንኳን ደኅናመጣሺ ሸዋረገድ ገድሌ ብሎ ተቀበላቸው፡፡
  በተለይም በጅቡቲ የነበረ አንድኢትዮጵያዊ የሰጣቸውን ‹የይሁዳ አንበሳ› የሚል ጽሑፍና ዓርማ ያለበትን ወረቀት ከንጉሡ የተላከ የሚመስል መልእክት እየጻፉ ወደበረሐ በመላክ አርበኞችን አበረታተውበታል፡፡ የአዲስ ዓለም የጣልያን ምሽግ ኅዳር 5 ቀን 1933 ዓም በአርበኞች ሲሰበር ዋናውንመረጃ የሰበሰቡትና ዐቅድ የነደፉት ሸዋረገድ ነበሩ፡፡ ከምሽጉ ሰበራ በኋላም ደጀን መሆኑን ትተው ራሳቸው ወደ ውጊያ ዐውድማ ገቡ፡፡በተለይም መቂ አካባቢ ከሻለቃ በቀለ ወያ ጦር መካከል ተሰልፈው ተዋግተዋል፡፡ በኋላም ጅማ አካባቢ ከነበረው ከገረሱ ዱኪ ጦር ጋርለመገናኘት ተጓዙ፡፡ በዚያ እያሉም ጠላት ድንገተኛ አደጋ ጥሎ ገጠማቸው፡፡ ለአራት ሰዓት ያህልም ተዋግተው ተማረኩ፡፡ ወደ እሥርቤት ተወስደውም የፊጥኝ ታሠሩ፡፡ በ1933 ዓም ሀገሪቱ ከፋሽስትኢጣልያ ወረራ ነጻ ስትወጣ ሸዋረገድ ገድሌ አርበኞችን ወደመርዳትና የበጎ አድራጎት ሥራን ወደ መሥራት ገቡ፡፡ በንግዱም መስክ ተራመዱ፡፡ሀገራቸውን እስኪበቃቸው አገልግለው፤ ግሼን ማርያም ሄደው ሥጋወደሙን ተቀብለው፤ ከዚያም ወደ ላሊበላ ተጉዘውና ተሳልመው፤ የመጨረሻቸውመሆኑን እየተናገሩ ጥቅምት 22 ቀን 1942 ዓም ዐረፉ፡፡ ሕዝቡም
  እናንት ወጥቤቶች በርበሬ ቀንጥሱ
  እናንት ሥጋቤቶች ሰንጋውን ምረጡ
  ሸዋረገድ ገድሌ ለገና ሲመጡ፡፡
  ቤተሰቧ ሰፊ ገናና ጥምቀት
  ሸዋረገድ ገድሌ እንደምን ትሙት
  ብሎ ገጠመላቸው፡፡ ሰፊ ነው ታሪካቸው፡፡ ልብ የሚያሞቅ፤ወኔ ቀስቃሽ፤ አስደማሚ፤ ከዐለት የበረታ ጽናት፤ ከእቶን የጋለ አርበኝነት፤ ከትንታግ የተንቀለቀለ የሀገር ፍቅር ታገኙበታላችሁ፡፡ምናለ አደባባዮቻችን በንግድ ኩባንያዎች ስም ከሚጠሩ በነ ሸዋረገድ ገድሌ ስም ቢሰየሙ ብላችሁም ትቆጫላችሁ፡፡
  (ከዳንኤል ክብረት)
 • loader Loading content ...
 • @Teferi Mihiret   1 year ago
  "i am what i am & that is all that i a am."

  የፋሽስት ጣሊያን መንግስት ሃገራችን በግፍ በወረረበት ወቅት ሃገራችን ብዙ ስመጥር ጅግኖችን አፍርታለች። በዚህ ወረራ ወቅት በጎንደር ከጓንግ ወንዝ እስከ መተማ ድረስ በጀግንነት ሃገሩን ከወረራ ነፃ ካደረጉት መካከል ጀግናዉ አርበኛ ፊት አዉራሪ አየለ ተሰማ አባ ጓዴ አንዱ ነበሩ። በአንድ ወቅት ፊት አዉራሪ አየለ ተሰማ ሰባስጌ በተባለ የፋሽስት የጦር ካምፕ ቦታ ላይ ከትንሽ ተከታዩቻቸዉ ጋር ጥቃት ፈፅመዉ 3 ወታደር ገድለዉና ብዛት ያለቸዉን በማቁሰላቸዉ፤ የፋሽስት ጣሊያን ባለስልጣናት በፊት አዉራሪ አየለ ላይ የተጠናከረ ዘመቻ በማድረግ አሳድደዉ ለመግደል ያላደረጉት ጥረት አልነበረም። ነገር ግን እሱን መያዝ ቢቸግራቸዉ ቤተሰቦቹን አባቱን ቀኝ አዝማች ተሰማን ፤ ወንድሞቹን ልጅ ታደሰ እና ረዳን በመያዝ በጎንደር አርበኞች በሚታጎሩበት እስር ቤት አሰሯቸዉ። ነገር ግን በወቅቱ በእስር ቤቱ በተነሳዉ የታይፎይድ በሽታ ብዙ አርበኞች ሲሞቱ ልጅ ታደሰ የገፈቱ ተቃማሽ ነበር። ይሁን እንጅ የቀሪዎች ህይወት ለማትረፍ በተደረገዉ ጥረት ወ/ሮ አቻሽማን ተሰማ ሽማግሌዉ አባቷን ቀኝ አዝማች ተሰማ እና ወንድሟን ረዳን ለማስፈታት ባደረገችዉ ጥረትና በዚህ ወቅትም ብዙ የጎንደር አርበኞች በጣሊያን ባለስልጣናት ምህረት ተደርጎላቸዉ ከስር ተፈተዋል። ይሁን እንጅ ቀኝ አዝማች ተሰማ በወቅቱ በታመሙት የታይፎይድ በሽታ በተፈቱ በሳምንታት ዉስጥ ለሞት አበቃቸዉ። ታዲያ ለዚህ ሁሉ የቤተሰብ ችግር አምጭ ተደርጎ የታየዉ ፊት አዉራሪ አየለ ተሰማ ነበር። ለፊት አዉራሪ ግን የእነሱ ሞት ለነፃነታቸዉ እንደ መሰዋዕትነት አድረጎ ነዉ የቆጠረዉ። በዚህ ልዩ የቁጭት አርበኝነትና ሃገር ወዳድነት ስሜት ጀግናዉ አርበኛ ፊት አዉራሪ አየለ ተሰማ አባ ጓዴ ከወንድሙ ከግራዝማች ረዳና ከልጅ አበራ ጋር በመሆን በሜጀር ባንቲ ቸኮ ሴንታታ የሚመራዉን የጣሊያንን ጦር በመተማ አካባቢ ነጋዴ ባህር አማኒት ተብሎ በሚጠራዉ ቦታ በሰኔ 29 ቀን 1938 ዓ.ም በመሄድ አስደናቂ ጀብድ በመስራት የፋሽስትን ጦር በመደምሰስ አኩሪ ታሪክ ሰሩ። ይህ ጀብዳቸዉም እስከ ስደተኛዉ ንጉስ ቀዳማዊ ሃይለ ስላሴ ድረስ በመሰማቱ ጃንሆይም የአድንቆት ደብዳቤና በግራዝማች ራዳ አማካኝት 300 ጠበንጃ፤ 3000 ጥይትና 1000 ብር ልከዋል። በአባባ ገሪማ ታፈረ "ጎንደሬ በጋሻዉ" እና በሕይዎት ህዳሩ የቀ.ኃ.ስ መልክተኛ "ያች ቀን ተረሳች" መፃህፎች ስለጀግናዉ አርበኛ ፊት አዉራሪ አየለ ተሰማ እና ወንድማቸዉ ግራዝማች ረዳ ተገልፆል። በዚህ የአማኒት ጦርነት ድል መሰረት ለጀግናዉ አርበኛ ፊት አዉራሪ አየለ ተሰማ በህዝብ እንዲህ በፉከራና በቀረርቶ ተገጠመላቸዉ፡፡

  አባት አስገዳይ ወንደም አስገዳይ ብለዉ ሲያሙት
  ነጭ ሰዉ ገዳይ ወርዶ አማኒት
  ገዳይ አማኒት
  እንደ አራስ ነብር ተጉዞ ሌሊት
  ገዳይ ኩመር በር
  በለዉ እያለ ከቀስቅስ ጋር፡፡
  የአባቱን ጠላት የተሰማን
  የታዴን ጠላት የወንድሙን
  በቁሙ ጠጣዉ በሳንጃ አልቢን
  አርዶ በካር ጠጣዉ ደሙን፡፡
  ፊት አዉራሪ አየለ ተሰማ ‹‹ ባልንጀራዬ! ፤ ባልደረባዬ! ፤ የኔ ቢጤ! ›› ሚለዉ ቢኖር ‹‹ አባ ጓንዴ! ነዉ ፈረሱ! ›› አንድ ቀን አሉ አየለ እና ፈረሱ ፋሺስት ጣሊያን ሲያሳዳቸዉ ቢያድር በመንገድ ላይ ሳሉ እራባቸዉ በዚህን ግዜ አባ አየለ ከፈረሱ ጋር ወደ መንደር ወጠዉ ካንድ ባዶ ቤት የሚበላ ሲያዩ በስርቆት ማለት ነዉ ህሊናቸዉን ወቀሳቸዉ እና ለፈረሳቸዉ ‹‹ የማናውቀውን ፡ ሌብነት፣ ልንሰርቅ ፡ ገብተን ፡ ከሰው : ቤት፣ ይቅርብን ፡ ጓዴ ፡ እንውጣ፣ የሚጠብቀን : መጣ! ›› ብለዉ ፈረሳቸዉን በቃለ ሰብአዊ አወሩት ፡፡ ይህን ነገር የሰማ ያአገሩ ኗሪም ‹‹ ለፈረስ ፡ ለበቅሎ ፡ ይተርፍ ፡ የነበረ፣ ዛሬስ ፡ ለሰው ፡ ያኽል ፡ ይቸግር ፡ ጀመረ! ›› ብሎ አነባ፡፡ እሳቸዉ እራሳቸዉም ይባላል ለሰዉ ሲመክሩ ‹‹ ሌሊት ፡ ከጭቃ ፡ ላይ ፡ ፈረስ ፡ ቢጥልህ፣ ወንድሜ ፡ አትናደድ ፡ ማንም ፡ አላየህ፣ ይልቁን ፡ ተጠንቀቅ ፡ ቀን ፡ እንዳይጥልህ! ›› ነዉ ሚሉ አሉ፡፡ እና አንድ ቀን ፊት አዉራሪ አየለ ተሰማ ሰባስጌ በተባለ የፋሽስት የጦር ካምፕ ቦታ ላይ ከትንሽ ተከታዩቻቸዉ ጋር ጥቃት ፈፅመዉ ሶስት ወታደር ገድለዉና ብዛት ያለቸዉን በማቁሰላቸዉ፤ የፋሽስት ጣሊያን ባለስልጣናት ‹‹ ምን? ፡ ቀረኝ ፡ በሎ ፡ ነዉ ፡ ይሄን ፡ ሚያረገዉ! ›› ብለዉ አጠገብ ባሉ ባንዳወች ቢያፈጡ ‹‹ ተሰማ ፡ ሳይቀጣው ፡ በልጅነት ፡ ቀርቶ፣ ገና ፡ ራስ ፡ ይመታል ፡ እንኳን ፡ ባት ፡ አግኝቶ! ›› ብለዋል፡፡

  በዚህን ግዜ የፋሽስት ጣሊያን ጦር እሱን ለመያዝ ቢቸግራቸዉ ቤተሰቦቹን አባቱን ቀኝ አዝማች ተሰማን ፤ ወንድሞቹን ልጅ ታደሰ እና ረዳን በመያዝ በጎንደር አርበኞች በሚታሰሩበት እስር ቤት አጎሯቸዉ፡፡ በእሰር ቤቱም በተነሳዉ የታይፎይድ ወረርሽኝ ብዙ አርበኞች ሲያልቁ ወንድማቸዉ ልጅ ታደሰም የዚህ ገፈት ቀማሽ ሆኑ፡፡ እህታቸዉም ወ/ሮ አቻም የለሽ ተሰማ ሽማግሌዉ አባቷን ቀኝ አዝማች ተሰማ እና ወንድሟን ረዳን ለማስፈታት ባደረገችዉ ጥረት እንዲሁም ፋሺስት ጣሊያ ‹‹ ሎሌ ፡ ለሰህተት ፡ ጌታ ፡ ለምህረት! ›› እንደ ተፈጠረ ይታወቅላቸዉ ዘንድ ጥቂት አርበኞችን በምህረት ፈቱ፡፡ አባታቸዉ ግን ቀኝ አዝማች ተሰማ ከእስር እንደ ወጡ በሳምንቱ ሞቱ፡፡
  ፊት አዉራሪ አየለም ተሰማም ከአባታቸዉ ሞት በዉሃላ በከፍተኛ ቁጭት እና የአርበኝነት ስሜት ከወንድሙ ከግራዝማች ረዳና ከልጅ አበራ ጋር በመሆን ‹‹ በሜጀር ፡ ባንቲ : ቸኮ : ሴንታታ! ›› የሚመራዉን የጣሊያንን ጦር በመተማ አካባቢ ነጋዴ ባህር ‹‹ አማኒት ›› ተብሎ በሚጠራዉ ቦታ ሰኔ ሃያ ዘጠኝ ቀን 1938 ዓ.ም አስደናቂ ጀብድ በመስራት የፋሽስትን ጦር በመደምሰስ አኩሪ ታሪክ ሰሩ። በዚህን ግዜ ሜጀር ፡ ባንቲ : ቸኮ : ሴንታታ!

  ‹‹ የዕድሌ ፡ ክፋቱ ፡ ፈተና ፡ አብዝቶብኝ፣
  አየለ ፡ አየለና ፡ ኀይሌን ፡ ወሰደብኝ! ›› ብሎ አነባ፡፡ 
  ይህን ያየና የሰማ የሀገሩ ኗሪ እና ጉብል 
  ‹‹ አባት ፡ አስገዳይ ፡
  ወንደም : አስገዳይ : ብለዉ : ሲያሙት
  ነጭ : ሰዉ : ገዳይ ፡ ወርዶ : አማኒት
  ገዳይ ፡ አማኒት
  እንደ ፡ አራስ : ነብር : ተጉዞ ፡ ሌሊት
  ገዳይ ፡ ኩመር ፡ በር
  በለዉ : እያለ : ከቀስቅስ : ጋር
  የአባቱን ፡ ጠላት : የተሰማን
  የታዴን : ጠላት : የወንድሙን
  በቁሙ ፡ ጠጣዉ : በሳንጃ : አልቢን
  አርዶ : በካር : ጠጣዉ : ደሙን፡፡ ›› እያለ ሲሸልል እና ሲፎክር 
  አንዲት የጎንደር ጉበል እርጉዝ ሁኗ ኑሯ ‹‹ ሰጋ አማረኝ! ›› አለች አገሬዉ
  ‹‹ ሥጋ ፡ አማረኝ : አለች :የቀለቤሰ ፡ እናት፣ መተማ ፡ አትሄድም ፡ ወይ ፡ ከታረደበት! ›› ብለዉ መለሱላት ፡፡
  ይህን አኩሪ ደል የሰሙትም ስደተኛዉ ንጉስ ቀዳማዊ ሃይለ ስላሴ በግራዝማች ራዳ አማካኝት ‹‹ ያባይ ፡ ምልክቱ ፡ አንደበቱ ፡ የገዳይ : ምልክቱ : ሽልማቱ! ›› ብለዉ የአድንቆት ደብዳቤና 300 ጠበንጃ፤ 3000 ጥይትና 1000 ብር ላኩ። 
  #ዘላለማዊ ክብርና ሞገስ ለምንግዜም ሃገር ወዳድ የነፃነት ጀግኖች አባቶቻችና እናቶቻችን!! 
  #አሹ ዋሴ


 • loader Loading content ...
 • @Teferi Mihiret   1 year ago
  "i am what i am & that is all that i a am."  ትውልድና እድገቷ ሰሜን ጐንደር ቆላ ድባ ከተማ ነው::ተመልካችን በእጅጉ በሚማርከው ፈገግታዋ መድረክ ላይ ወጥታእንደ እንዝርት ስትሾር የታዳሚውን ቀልብ ትገዛለች:: ባላት

  ልዩ   የውዝዋዜ   ተሰጥኦም   በአብዛኞቹ   መድረኮች   ኢትዮጵያን   ትወክላለች -   አርቲስት   እንዬ   ታከለ ::   የኢትዮጵያን   ውብ   ባህላዊ   ውዝዋዜም   በዓለም   አቀፍ   ደረጃ   በማስተዋወቅ   በኪነ   ጥበቡ   ዘርፍ   ዘመን   ተሻጋሪ   ስም   አስቀምጣለች ::  

 • loader Loading content ...
loader Loading content ...

Comments (0)


  This user has no comment yet.