loader

Topics (308)


loader Loading content ...

Explanations (269)


 • @Tesfaye Atew   2 months ago
  Member of Team Sewasew, and believes in social learning!

  ዶ/ር ጀምበር ተፈራ፣ የብርሃን ሶሻል ዴቨሎፕመንት ትሬኒንግ ኤንድ ኮንሰልቴሽን ሴንተር መሥራችና ዋና ሥራ አስኪያጅ

  ዶ/ር ጀምበር ተፈራ፣ በድህነት ቅነሳ በተለይም የደሃ ደሃ የሆኑ የኅብረተሰብ ክፍሎች ራሳቸውን ችለው እንዲቋቋሙ ለማድረግ የተመሠረተው የብርሃን ሶሻል ዴቨሎፕመንት ትሬኒንግ ኤንድ ኮንሰልቴሽን ሴንተር መሥራችና ዋና ሥራ አስኪያጅ ናቸው፡፡ በአዲስ አበባ ከተማ በተለይ በተወሰኑ አካባቢዎች የሚታየውን የከፋ ድህነት በመቅረፍ ረገድ ከሦስት አሠርታት በላይ ባከናወኑት ሠናይ ተግባር አንፃር በውጭ ጸሐፍት ዘንድ የኢትዮጵያዋ ‹‹ማዘር ቴሬዛ›› የሚል ቅፅል ስምንም አትርፈዋል፡፡ በ1935 ዓ.ም.የተወለዱት ዶ/ር ጀምበር፣ የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርታቸውን በኢትዮጵያ እስከ ስድስተኛ ክፍል በቀድሞው እቴጌ መነን፣ ከሰባት እስከ ስምንተኛ ክፍል ሐረር ወ/ሮ የሺመቤት ትምህርት ቤቶች ተምረዋል፤ ሁለተኛ ደረጃንም በብሪታኒያ አጠናቀዋል፡፡ በኢንግላንድ ተርንብሪጅ ዌልስ የነርሲንግ ትምህርት ቤት በ1957 ዓ.ም. በነርስነት (registered nurse) ሲመረቁ፣ ከጥቂት ዓመታት ቆይታ በኋላ ከማንቸስተር ዩኒቨርሲቲ በመጀመሪያ ደረጃ ጤና ክብካቤ (ፕራይመሪ ሄልዝ ኬር) የማስትሬት ዲግሪ፣ እንዲሁም ማስተርስ ኦፍ ፊሎሶፊ ሠርተዋል፡፡ በ1993 ዓ.ም. ከአሜሪካ ፊላዴልፊያ ኢስተርን ባፕቲስት ሴሚናሪ ዶክተር ኦፍ ዲቪኒቲ ዲግሪ አግኝተዋል፡፡ በዶክተራዊ የምርምር ሥራቸውም ከሁለገብ ተልዕኮ አንፃር ድህነትን መቀነስ የሚቻልበትን ሃንድቡክ አዘጋጅተዋል፡፡ ሲስተር/ዶክተር ጀምበር በዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ በከፋ ድህነት ውስጥ የሚኖሩ ወገኖችን አኗኗር ለማሻሻል በተቋማቸው በኩል ከፍ ያለ ጥረት በማድረግ በ52,000 ነዋሪዎች ላይ ለውጥ እንዲመጣ መረጃዎች ይጠቁማሉ፡፡ በኢትዮጵያ ንጉሠ ነገሥት መንግሥት ዘመን ከባሕር ማዶ ትምህርታቸው መልስ የመጀመሪያ አገልግሎት የሰጡት ክፍለ ሀገር አውቶቡስ ተራ በነበረው የመጀመሪያው ቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል ሲሆን፣ በመቀጠልም በኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ማኅበር አገልግለዋል፡፡ በወቅቱ ከሚጠቀስላቸው ሥራቸው አንዱ የመጀመሪያ ሕክምና እርዳታ መመርያ (ፈርስት ኤድ ማኑዋል) በአማርኛ ቋንቋ ማዘጋጀታቸው ነበር፡፡ የ1966ቱ አብዮት ተከትሎ በተፈጠረው የመንግሥት ለውጥ የቀዳማዊ ኃይለሥላሴ ዘመን የአዲስ አበባ ከንቲባ ከነበሩት ባለቤታቸው ነፍስ ኄር (the late) ዶ/ር ኃይለጊዮርጊስ ወርቅነህ ጋር በ1960ዎቹ መገባደጃና በ1970ዎቹ በደርግ ታስረው ነበር፡፡ ይህም ሆኖ ሲስተር ጀምበር የወህኒ ቤት ቆይታቸው ሥራቸውን ከማከናወን አልገታውም፡፡ በወህኒ ቤቱ የጤና ረዳት ትምህርት ቤት አቋቁመው ከእስረኞችና ከወህኒ ፖሊሶች የተውጣጡ 85 ግለሰቦችን አሠልጥነው በጤና ረዳትነት አስመርቀዋል፡፡ ዶ/ር ጀምበር ለዓመታት ላከናወኑት ማለፊያ ተግባር በአገር ውስጥና በውጭ ከሚገኙ የተለያዩ ተቋማት እውቅናና ሽልማት አግኝተዋል፡፡ ከነዚህም መካከል በአሜሪካ በኢትዮጵያውያን ዳያስፖራዎች የተመሠረተው ሲድ (SEED- Society of Ethiopians Established in The Diaspora) እና የአዲስ አበባው የሴቶች ቢዝነስ ማኅበር ኤውብ ይገኙበታል፡፡ ዶ/ር ጀምበር በሚመሩት ድርጅታቸው እንቅስቃሴና በተግባራቸው ዙሪያ ታደሰ ገብረማርያም አነጋግሯቸዋል፡፡


  ሪፖርተር፡- የድርጅትዎ ተግባር በምን ዓይነት እንቅስቃሴ ላይ ያተኮረ ነው? ለማቋቋምስ ምን አነሳሳዎት?


  ዶ/ር ጀምበር፡- የድርጅቱ የትኩረት አቅጣጫ በድህነት ቅነሳ፣ በሥራ ዕድል ፈጠራ፣ በትምህርት፣ በጤና፣ በአረጋውያን እንክብካቤ ዙሪያና በሌሎች በርካታ ማኅበራዊ ዘርፎች ላይ ነው፡፡ ለትርፍ ያልቆመ፣ የፖለቲካ ወገንተኝነት የሌለው የደሃ ደሃ የሆኑ የኅብረተሰብ ክፍሎች ራሳቸውን ችለው እንዲቋቋሙ ለማድረግ ሲባል የተመሠረተ መንግሥታዊ ያልሆነ ድርጅት ነው፡፡ ይህ ዓይነቱን በጎ ተግባር ለማከናወን እንድነሳሳ ያደረገኝ እናቴ ለድሆች የነበራት ቀና አስተሳሰብ ነው፡፡ ይህም ማለት ግርማዊት እቴጌ መነን ትምህርት ቤት በተመላላሽነት በምማርበት ወቅት የአያታችን እንጨት ፈላጭ የነበረና ከጊዜ በኋላ ለዓይነ ስውርነት የተዳረገ ‹‹አቡሌ›› የተባለ ሰው ነበር፡፡ ይህ ሰው ቀን ቀን መንገድ ዳር ቁጭ ብሎ ሲለምን ይውልና አመሻሹ ላይ ወደ ማደሪያው ይገባል፡፡ ለልመና ሲሰማራ እጁን ይዤ መንገድ ዳር አስቀምጠው ነበር፡፡ ከትምህርት ቤት ለምሳ ወደ ቤት ስሄድ ስንት አገኘህ? እያልኩ እጠይቀው ነበር፡፡ ይህን ያህል አግኝቼያለሁ ሲለኝ በጣም ደስ ይለኛል፡፡ ሌላ ቀን ደግሞ እንደዚሁ ስጠይቀው ምንም አላገኘሁም ይለኛል፡፡ በዚህ ጊዜ በጣም አዝንና በእጄ የያዝኩትን የኪስ ገንዘብ እሰጠዋለሁ፡፡ ይህንን አድርጌ ወደ ቤት ስገባ እናቴ ‹‹ለመሆኑ የሰጠሁሽን የኪስ ገንዘብ የት ነው የምታውዪው?›› ወይም ‹‹ምን አደረግሽበት?›› ብላ ስትጠይቀኝ አይ! ለአቡሌ ሰጠሁት ያልኳት ቀን አቅፋ ትስመኝ ነበር፡፡ ይህም ሁኔታ ለእኔ የሰጠኝ ትምህርት ቢኖር ከረሜላ ገዛሁበት ከማለት ይልቅ እናቴን ለካ የሚያስደስታት ችግረኛን መርዳቴ ነው የሚል ነበር፡፡ ድህነት ምን እንደሆነ ከልጅነቴ ጀምሮ እንዲገባኝ አድርጋኛለች የሚል እምነት አለኝ፡፡ በዕድሜ ትንሽ ከፍ እያልኩ ስሄድ ግልጽ በሆነ መንገድ እግዚአብሔር ደሃን እንድረዳ በህልም ያሳየኝ ነበር፡፡


  ሪፖርተር፡- ድሆችንና አቅመ ደካማ አረጋውያንን ጭምር በተደራጀ መልኩ መርዳት የጀመሩት ከመቼ ጀምሮ ነው?


  ዶ/ር ጀምበር፡- እንደ አጋጣሚ ሆኖ የዓለም ባንክ በአዲስ አበባ ከተማ በ1970 ዓ.ም. አንድ ጥናት አካሂዶ ነበር፡፡ ጥናቱም በተክለ ሃይማኖት አካባቢ ስምንት የመጨረሻ ደሃ ቀበሌዎች መኖራቸውን የሚያሳይ ነበር፡፡ ከእነዚህም ቀበሌዎች መካከል በቀድሞው ከፍተኛ ሦስት ቀበሌ 41 ውስጥ የኖርዌይ ሕፃናት መርጃ በድህንነት ቅነሳና በጤና፣ በትምህርትና በሌሎችም ማኅበራዊ ዘርፎች ትኩረት ያደረገ የተቀናጀ ሥራ ለአምስት ዓመት ያህል ለማከናወን ከመንግሥት ጋር ተስማምቶ ወደ እንቅስቃሴ ገብቶ ነበር፡፡ አራት ሺሕ ሕዝብ በሚኖርበት በዚሁ ቀበሌ ይህንኑ ተግባር ለማከናወን ድርጅቱ የማኅበራዊ ኑሮ ባለሙያ፣ መሐንዲስ፣ የጤና ሙያተኛና ድጋፍ ሰጪ ሠራተኛ ቀጠረ፡፡ እኔ በጤና ሙያተኝነት ተቀጠርኩ፡፡ በሙሉ አቅማችን ሥራውን ከመጀመራችን በፊት ዓለም ባንክ ካወጣው መረጃ በተጨማሪ የራሳችን የዳሰሳ ጥናት ማካሄድ ስለነበረብን የእያንዳንዱን አባወራ ወይም ቤተሰብ መኖሪያ ቤት እያንኳኳን ምን ትፈልጋለህ? እያልን መጠየቁን ተያያዝነው፡፡ ከሁሉም አባወራ ያገኘነው መልስ የቤት፣ የማኅበራዊና የጤና ችግሮች፣ የሥራ አለማግኘት፣ የሕፃናት መማር አለመቻላቸው፣ የመሳሰሉ ይገኙባቸዋል፡፡ ከቀረቡት ችግሮች በመነሳት ሳይጠገኑ ለረጅም ዓመታት የቆዩ፣ በጊዜ ብዛት የተነሳ ሊፈራርሱ የተቃረቡና ለሰው ልጅ መኖሪያ ከማይሆኑ የቀበሌ ቤቶች መካከል መጠነኛ ጉዳት የደረሰባቸው እንዲጠገኑ፣ የከፋ ጉዳት ያለባቸው ደግሞ ፈርሰው እንደገና በአዲስ መልክ እንዲገነቡ ተደርገዋል፡፡ ለልጆች ትምህርት ቤት፣ ለእናቶች ደግሞ የገቢ ምንጭ በመፍጠር እንዲቋቋሙ ሲደረግ በጤናው ዘርፍም በእናቶችና ሕፃናት ጤና ክብካቤ ዙሪያ ትርጉም ያለው ሥራ ተሠርቷል፡፡ በሽታን በመከላከል ረገድም ውጤት ተገኝቶበታል፡፡


  ሪፖርተር፡- ድርጅቱ ይህን ሥራ ሲያከናውን ከመንግሥት ጋር የነበረው ስምምነት ምን ይመስል ነበር?


  ዶ/ር ጀምበር፡- ድርጅቱ ከመንግሥት ጋር የነበረው ስምምነት፣ የማቋቋሙን ሥራ ካከናወነ ከአምስት ዓመት በኋላ ለመንግሥት አስረክቦ ለመሄድ ነበር፡፡ ነገር ግን ይህ ስምምነት በመንግሥት በኩል አልተከበረም ነበር፡፡ በዚህም የተነሳ መንግሥት ቃሉን ስላላከበረ ወይም ፕሮጀክቱን ለመረከብ ፈቃደኛ ሆኖ ስላልተገኘ ድርጅቱ ሥራውን ለማቆም ተገደደ፡፡ ሥራውም የቆመው በ1979 ዓ.ም. ነበር፡፡ ድርጅቱ ሥራውን ሲያቆም እኛም እየተበተንን ነበር፡፡ ሆኖም ከጥቂት ዓመታት በኋላ እኔ ፕሮጀክቱን ተረክቤ የማቋቋሙን ሥራ ቀጠልኩበት፡፡ በፊት ከነበረው ቀበሌ በተጨማሪ ቀበሌ 30፣ ቀበሌ 42 እና ቀበሌ 43 የፕሮጀክቱ ተጠቃሚ እንዲሆኑ አደረግኩ፡፡ በዚህም ብቻ ሳልወሰን በቂርቆስ ክፍለ ከተማ የሚገኙ ሁለት ቀበሌዎችም በፕሮጀክቱ እንዲታቀፉ በማድረግ አገልግሎቱን አስፋፋሁ፡፡ በዚህም የተነሳ በተክለሃይማኖት አካባቢ በአራት ቀበሌዎች፣ እንዲሁም በቂርቆስ ክፍለ ከተማ በሁለት ቀበሌዎች ለሚገኙ ችግረኛ ወገኖች መዋለ ሕፃናትና የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ተቋቁሞላቸዋል፡፡ ልጆቹ ከአሥረኛ ክፍል በኋላ ጥሩ ውጤት ሲያመጡ መሰናዶ ትምህርት ቤትና ዩኒቨርሲቲ እንዲቀጥሉ ሲደረግ፣ ውጤት ያልመጣላቸው ደግሞ በቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ሥልጠና ገብተው እንደ የሙያ ዝንባሌያቸው እንዲሠለጥኑ ተደርጓል፡፡ በዚህ ዓይነት አካሄድ በርካታ ችግረኞችና ጎዳና ተዳዳሪ የነበሩ ታዳጊ ወጣቶች ራሳቸውን እንዲችሉ ተደርጓል፡፡ ልጆቹ ከመዋለ ሕፃናት እስከ ሁለተኛ ደረጃና ከዛም ዩኒቨርሲቲ ገብተው እስከሚመረቁ ድረስ ወጪያቸውን የሚችለው ድርጅቱ ነው፡፡ ወጪያቸውም ዩኒፎርምና የትምህርት መሣሪያዎች ግዥና የምግብ አቅርቦት ናቸው፡፡ ትልልቆቹ በቀን አንድ ጊዜ ምሳ፣ ትንንሾቹ ደግሞ በቀን ሁለቴ ምሳና መክሰስ በነፃ ይመገባሉ፡፡ ለዚህም የሚውሉ የመመገቢያ ጣቢያዎች ተቋቁመዋል፡፡ ይህ ዓይነቱ ፕሮጀክት ታዳጊ ወጣቶችን ከመርዳት አልፎ ከ300 በላይ ለሚሆኑ አቅመ ደካማ አረጋውያንም እንክብካቤ የሚያደርግላቸው ሲሆን፣ ምግብም ይቀርብላቸዋል፡፡ መንቀሳቀስ የሚችሉ አረጋውያን መመገቢያ ጣቢያ እየሄዱ ሲመገቡ፣ መንቀሳቀስ የማይችሉና ቤት ለዋሉ አረጋውያን ደግሞ ቤታቸው ድረስ ይሄድላቸዋል፡፡ ልጆቹና አረጋውያኑ በመመገቢያ ጣቢያው የሚገለገሉት በፈረቃ ነው፡፡ ለዚህ ሁሉ የሚያስፈልገውን ወጪ የሚሸፍኑት ጀርመን፣ ሆላንድ፣ እንግሊዝ፣ በጥቂቱ አሜሪካ የሚገኙ በጎ አድራጊ ድርጅቶችና ግለሰቦች ናቸው፡፡


  ሪፖርተር፡- የተላከው ዕርዳታ ለተጠቃሚዎቹ በቀጥታ መድረሱን ድርጅቶቹና ግለሰቦቹ እንዲያውቁ የሚደረግበት አካሄድ አለ?


  ዶ/ር ጀምበር፡- ለምሳሌ ያህል በትምህርት ዘርፍ የሚደረገውን ወጪ ብንመለከት እያንዳንዱ ዕርዳታ ሰጪ ስንት ልጆች እንደሚያስተምር ኮታ ተሰጥቶታል፡፡ በዚህም መሠረት የሚያስተምራቸው ልጆች የትምህርት ውጤታቸውና የደረሱበት የክፍል ደረጃ፣ ለዩኒፎርም፣ ለትምህርት መሣሪያ መግዣዎችና ለምግባቸው የወጣው ሁሉ በየዓመቱ ከደረሰኝ ጋር ተያይዞ እንዲቀርብለት ይደረጋል፡፡ ይህንንም ያመዛዝንና ለቀጣዩ ዓመት የሚውል በጀት ይልካል፡፡


  ሪፖርተር፡- ፕሮጀክቱ በተክለሃይማኖት አካባቢና በቂርቆስ ክፍለ ከተማ ባቀፋቸው ቀበሌዎች ቤትን በተመለከተ ያከናወነው ተግባር ምንድን ነው?


  ዶ/ር ጀምበር፡- በተክለ ሃይማኖት አካባቢ በሚገኙ አራት ቀበሌዎች ውስጥ አምስት ሺሕ ቤቶች ተሠርተዋል፡፡ ከእነዚህም ውስጥ ሦስት ሺሕ ያህሉ ሙሉ ለሙሉ አዲስ የተሠሩ ሲሆኑ፣ 1,500 የሚሆኑት ደግሞ ከባድ ጥገና የቀሩት ግን ቀላል ጥገና የተደረገላቸው ናቸው፡፡ በቂርቆስ ክፍለ ከተማ በሁለት ቀበሌዎች ለሚገኙ 80 ቤተሰቦች ባለአራት ፎቅ የጋራ መኖሪያ ቤቶች ተሠርቶላቸዋል፡፡ የጋራ መኖሪያ ቤቶቹ ባለአንድ የመኝታ ክፍልና ስቱዲዮ ናቸው፡፡ ለሦስት ቤተሰብ አንድ ወጥ ቤትና አንድ መፀዳጃ ቤት ተሠርቶላቸዋል፡፡ በተጠቀሱት ቀበሌዎች የሚገኙ እነዚሁ የቀበሌ ቤቶች በመጠገናቸው ወይም አዲስ በመገንባታቸው የተነሳ የኪራይ ጭማሪ አልተደረገም፡፡


  ሪፖርተር፡- በተክለሃይማኖት አካባቢ በአራቱም ቀበሌዎች በአዲስ መልክ የተሠሩትና ጥገና የተደረገላቸው ቤቶች ለልማት በሚል ምክንያት አልፈረሱም?


  ዶ/ር ጀምበር፡- ቤቶቹን ለማፍረስ በ1992 ዓ.ም. እና በ1996 ዓ.ም. ሁለት ጊዜ ሙከራ ተደርጐ በእግዚአብሔር ቸርነትና ቦብ ጊልዶፍ በተባለው ታዋቂ የሙዚቃ ባለሙያ አማላጅነት እንዳይፈርስ ተደርጓል፡፡ እስካሁንም ድረስ ምንም አልሆኑም፡፡ የወደፊቱንም እግዚአብሔር ያውቃል፡፡


  ሪፖርተር፡- ድርጅትዎ በጤናው ዘርፍ ያበረከተውን ጉልህ አስተዋጽኦ ቢያብራሩልን፤


  ዶ/ር ጀምበር፡- በተለይ በእናቶችና ሕፃናት ጤንነት ላይ ነው ትኩረት ያደረገው፡፡ ነፍሰ ጡር እናቶች እስከሚወልዱ ድረስ የሕክምና ክትትል ይደረግላቸዋል፡፡ ከወለዱም በኋላ ሕፃኑ አምስት ዓመት እስከሚሞላው ድረስ አስፈላጊ ክትባት እንዲያገኝ፣ በሦስት ዓመት ደግሞ መዋለ ሕፃናት እንዲገባ ይደረጋል፡፡ ለዕድገቱና ለጤንነቱ ተስማሚ የሆነ ምግብም ይሰጠዋል፡፡ በአጠቃላይ ፕራይመሪ ሔልዝ ኬር እንዲተገበር በማድረግና በንጽህና አጠባበቅ ዙሪያ ውጤት ተገኝቷል፡፡


  ሪፖርተር፡- ትምህርትዎን በውጭ አገር አጠናቀው ወደ አገር ቤት ከተመለሱ በኋላ መጀመሪያ አገልግሎት የሰጡት በቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል ነበር፡፡ በዚህ ዙሪያ ማብራሪያ ቢሰጡን፤


  ዶ/ር ጀምበር፡- የቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል የተቋቋመው ለድሆች የሕክምና አገልግሎት በነፃ እንዲሰጥ ለማድረግ ነበር፡፡ እኔም ጥሪዬ ለድሆች ነው፤ በዚህም የተነሳ ከውጭ አገር እንደመጣሁ ሥራ የጀመርኩት በዚሁ ሆስፒታል ነበር፡፡ በመጀመሪያ የአንድ ዋርድ ኃላፊ አደረጉኝ፡፡ ከዛም በኋላ የሐኪም ቤቱ ኃላፊ ሆኜ ተመደብኩ፡፡ በዚህ መልኩ ለሦስት ዓመታት ያህል አገልግያለሁ፡፡ ሆስፒታሉ ቀድሞ ከነበረበት የክፍለ ሀገር አውቶቡስ ተራ ተነስቶ አሁን ወዳለበትና አዲስ ወደ ሠራው ሕንፃ ሲዛወር፣ አገልግሎቱን ሙሉ ለሙሉ በድሃ ላይ ባለማተኮሩ የተነሳ ለቀቅኩና ኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ማኅበር ገባሁ፡፡ ማኅበሩም የጤናና ማኅበራዊ የሚባል አዲስ ክፍል ከፈተልኝ፡፡ በጤናው በኩል የአምቡላንስ፣ የክሊኒክና የመጀመሪያ ዕርዳታ ሥራ፣ በማኅበራዊ ዘርፍ ደግሞ የሥጋ ደዌ ተጠቂ ለሆኑትና ለሌሎችም ችግረኞች የሙያ ሥልጠና በመስጠት የማቋቋም ሥራ እንዲከናወን ተደረገ፡፡ ይህን መሰል ሰብአዊ አገልግሎት በመስጠት ላይ እያለሁ የፖለቲካ እስረኛ ሆኜ ወህኒ ገባሁ፡፡


  ሪፖርተር፡- በምን ምክንያት ነው ለእስር የተዳረጉት?


  ዶ/ር ጀምበር፡- እነሱ ያውቃሉ፡፡ ለነገሩ ባለቤቴ ባለሥልጣን ስለነበር እኔን ጨምሮ ብዙ የባለሥልጣን ሚስቶች ታስረው ነበር፡፡ ወህኒ መግባቴ ግን ብዙ በጎ ተግባራትን ለማከናወን ጥሩ አጋጣሚ ፈጥሮልኛል፡፡ በዚህም የተነሳ ግቢው ውስጥ ክሊኒክ አሠራሁ፡፡ የምክር (ካውንስሊንግ) አገልግሎት ለሚያስፈልጋቸው የሕግ እስረኞች የምክር፣ ለወላዶች የወሊድ አገልግሎቶችን አበረክት ነበር፡፡ ከዚህም ሌላ በግቢው ውስጥ የጤና ረዳት ኮርስ አቋቁሜ ወደ 87 የሚጠጉ የወህኒ ፖሊሶችና የሕግ ታራሚዎች (እስረኞች) በጤና ረዳትነት እንዲሠለጥኑ አድርጌያለሁ፡፡ መዋለ ሕፃናትም አቋቁሜያለሁ፡፡


  ምንጭ፦ ሪፖርተር

 • loader Loading content ...
 • @Tesfaye Atew   4 months ago
  Member of Team Sewasew, and believes in social learning!

  ልጅዎ የሚከተለውን ከሆነ

  • በረቂቅ የሚያስቡ ከሆነ ማለትም የላቀ የሒሳብ እና የቋንቋ ጽንሰ-ሃሳቦች የሚረዱ ከሆነ እና ሰለ እምነት እና ሃይማኖት የመሳሰሉ ውስብስብ ጉዳዮችን ማውራት ከቻሉ።
  • የሒሳብ ስሌቶችን በእአምሮዋቸው የሚሰሩ ከሆነ ወይም በትምህርት ቤት ውስጥ ከመማራቸው  በፊት እንደ ማባዛትን የመሳሰሉ ጽንሰ-ሀሳቦችን መረዳት የሚችሉ ከሆነ።
  • ለረጅም ጊዜ በአንድ እንቅስቃሴ ላይ በትኩረት መቆየት የሚችሉ ከሆነ።
  • ብዛት ያለው የቃላት ዝርዝር ካወቁ እና ከእኩዮቻቸው በላይ ቃላት ካወቁ።
  • አብዛኛውን ጊዜ ቡድኖች ማዋቀር እና መምራት የሚችሉ፣ ለምሳሌ ጨዋታዎችን እና የቡድን እንቅስቃሴዎችን የሚያደራጅ መሪ ከሆኑ።
  • ባከናወኗቸው ስኬቶች እና ሀሳቦች ላይ እርግጠኛነት ካላቸው።
  • በትምህርታቸው ጥሩ ውጤት የሚያመጡ ከሆነ።
  • የፈጠራ ችሎታ ካለቸው እና ታሪኮችን መናገር፣ መሳብ ወይም ዘፈኖችን መፃፍ የሚችሉ ከሆነ።
  • ተጫዋች እና የብዙዎችን ስሜት የሚያገናዝብ ከሆነ።
  • ከትላልቅ ህጻናትና ጎልማሶች ጋር ጊዜ ለመውሰድ የሚመርጥ ከሆነ።
  • ከክፍል ደረጃቸው የላቀ ትምህርታዊ ስራ ያከናውናል።
  • ለሌሎች ሰዎች ስሜት የሚጠነቀቁ
  • በቀላሉ እውነታዎችን ማስታወስ እና በተገቢው ጊዜ መጠቀም መቻል።


  ምንጭ: ብሄራዊ ማህበር ተሰጥኦ ላላቸው ልጆች


 • loader Loading content ...
 • @Tesfaye Atew   11 months ago
  Member of Team Sewasew, and believes in social learning!

  የለበትም መድሎ በገንዘብ ተታሎ

  ከተደበቀበት ሐሽሹን ፈልፍሎ

  ብቅ ይላል ቡችዬ ባፉ አንጠልጥሎ

  የለም በቡቺ ዘንድ ዝምድና ትስስር

  ታማኝ ነው ለስራው ቡቺ ችሎ ማደር

  ለተሰማራበት ለተሰጠው ተግባር

  አያውቅም ሰለቸኝ ደከምኩ ብሎ ነገር


  ጊደር ካህያ ጋር ውላ ስትመጣ

  አጉል ልማድ ቀስማ ስታበዛ ጣጣ

  ቡቺ ግን ከሰው ጋር እየዋለ ሲያድር

  አልተማረም ውሸት ቅጥፈት ብሎ ነገር


  ቡቺ ችሎ ማደር በኛውማ ዘንዳ እርኩስ ነው ተብሎ

  ቤተስኪያን አይገባም <<ቅዱሱን>> ጌታውን ሰውን ተከትሎ

  እንኩዋን ከቤተስኪያን በስሕተት ቢገባ ገረገራው ግቤ

  በድንጋይ እሩምታ ተባርሮ ይወጣል መከረኛው ቦቢ


  ሰው ለቤቱ ውሻ ችሎ ማደር ብሎ ስሙን ያወጣለት

  ለማሰተማር ነበር ሰው ከሰው ጋር መኖር መቻል እነዳለበት

  ነገር ግን ለቡቺ ስሙ ተስማምቶታል

  አብሮ ኖርዋልና ችሎ የኛን አመል


  ቡችዬ ብትሰማ ይህንን ቅኔዬን

  ታወዛውዝ ነበር ያችኑ ጭራህን

  ከደስታህ ብዛት አብዝተህ ቡረቃ

  ልብሴን እየቀባህ አቡዋራና ጭቃ


  ይቅር ባትሰማ ምን ያረግልሃል

  በውዳሴ ከንቱ አጉል በመታለል

  ድንገት ዘው ብለህ ከኛው አጉል ባህል

  እኔን እጠቅም ብለህ ሌላ እንዳትበድል


  ምንጭ: ግጥም በ ቦጋለ ዳኜ

 • loader Loading content ...
 • @Tesfaye Atew   1 year ago
  Member of Team Sewasew, and believes in social learning!

  Here is a note from my reading as how he described it and what to do to lead a happy life.

  “Don’t simply believe whatever you are told, or whatever has been handed down from past generation, or what is common opinion, or whatever the scripture says. Don’t accept something as true merely by deduction or inference or by considering outward appearance or by partiality for a certain view, or because of its plausibility or because your teacher tells you it is so. But when you yourselves directly know, “These principles are unwholesome, blameworthy, condemned by the wise; when adopted and carried out they lead to harm and suffering." then you should abandon them. And when you yourselves directly know, “these principles are wholesome, blameless, praised by the wise, when adopted and carried out they lead to welfare and happiness then you should accept and practice them.”

  By the way, in all his teachings he gave the highest importance to the direct experience of truth which he believes is a solid ground on which to take a stand and he also calls it "Dhamma" or the law of nature.

  Reference: The Art of living by S.N Goenka

 • loader Loading content ...
 • @Tesfaye Atew   1 year ago
  Member of Team Sewasew, and believes in social learning!

  Abba Salama, the Coptic Patriarch of the Ethiopian Church: an engraving based on one of the earliest photographs ever taken in Ethiopia, by the missionary Henry Stern, in the early 1860s


  Reference:Ethiopia Photographed: Historic Photographs of the Country and its People Taken Between 1867 and 1935 by Richard Pankhurst
 • loader Loading content ...
 • @Tesfaye Atew   1 year ago
  Member of Team Sewasew, and believes in social learning!
  "አፈር ፈጭተን" ከጎደኝነት ጋር በተያያዝ ሲነገር፣ ከሕፃንነት አንስቶ ያለዉን ጥብቅ የሆነ የአብሮ አደግ ግንኙነት ወይም አንድነት ለመግለፅ ይመሰለኛል ፣ በእርግጥም ልጆች እህልን ማስፍጨት ወይም መፍጨትን ለማስመሰል አፍርን በመፍጨት ይጫወቱም ነበር።
 • loader Loading content ...
 • @Tesfaye Atew   3 years ago
  Member of Team Sewasew, and believes in social learning!
  ዕንደራ
 • loader Loading content ...
 • @Tesfaye Atew   3 years ago
  Member of Team Sewasew, and believes in social learning!
  ረብሓ
 • loader Loading content ...
 • @Tesfaye Atew   3 years ago
  Member of Team Sewasew, and believes in social learning!
  ቅድሚት
 • loader Loading content ...
 • @Tesfaye Atew   3 years ago
  Member of Team Sewasew, and believes in social learning!
  ኣምለኸ፣ምድናቕ፣ምድማጽ
 • loader Loading content ...
  Load more...
loader Loading content ...

Comments (3)


 • @Tesfaye Atew   1 year ago
  Member of Team Sewasew, and believes in social learning!
  በጣም መሳጭ ነው! እናመስግናለን ብሬ!
 • @Tesfaye Atew   1 year ago
  Member of Team Sewasew, and believes in social learning!
  አዝናኝ፣ወቅታዊ እና ቁምነገር አስጨባጭ ፅሁፍ ነው፣እጅግ በጣም እናመስግናለን ክቡር!  እንደዚህ አይነት ግሩም ፅሁፍ ማበርከትህን እንደምትቀጥል ተስፋ አለን!!!
 • @Tesfaye Atew   1 year ago
  Member of Team Sewasew, and believes in social learning!
  @golden ladder, thanks for the explanation! It is much appreciated if you can add some reference material!
loader Loading content ...