loader

Topics (757)


loader Loading content ...

Explanations (851)


 • @ቆብአስጥዬ   3 months ago
  Sewasewer

   አባተ መኩሪያ ኢትዮጵያ ውስጥ ስመጥር ከሆኑ የተውኔት አዘጋጆች አንዱ ናቸው:: በሰኔ ወር 1998 .ታትሞ የወጣው "መኩሪያ ቲአትርመፅሄት የአቶ አባተን ታሪክና ሙያዊ አመለካከት ፅፎ አውጥቷል:: አቶ አባተ የአንደኛ እና ሁለተኛ ትምህርታቸውን ቀድሞ ቀዳማዊ ኃይለሥላሴ ዴይ ስኩል ይባል በነበረው በአሁኑ ኮከበ ባህ ትምህርት ቤት ተማሩ::  ከዚያም ዩኒቨርሰቲ ኮሌጅ ይባል በነበረው በአሁኑ የአዲስ አበባ ዩኒርሲቲ ገብተው ትምህርታቸውን ጠሉ:: የእንግሊዘኛ ቋንቋን በማጥናት ላይ እንዳሉ / ፊሊፕ በሚባለ የውጭ ዜጋ አማካኝነት "ኪነጥበብ ወ ቲያትር" የሚባል ክፍል ተቋቋመ እና የመጀመሪያው ተማሪ በመሆን ወደዚያ ተዛወሩ:: "ኪነጥበብ ወ ቲያትር ̈ እንደተመሰረተ አቶ አባተን ጨምሮ በተለያዩ የኪነ-ጥበብ ዘርፎች የፈጠራ ችሎታ የነበራቸው ከያንያን ንቁ ተሣትፎ ማድረግ ጀመሩ:: ጉልህ እንቅስቃሴ ከነበራቸው መካከል ተስፋዬ ገሠሠ፣ አፈወርቅ ተክሌ፣ ገብረክርስቶስ ደስታ፣ መንግሥቱ ለማ፣ ዮሐንስ አድማሱ፣ ፀጋዬ ገ/መድህን፣ ዳኛቸው ወርቁ እና ሌሎችም ነበሩ:: 

  ከአቶ አባተ ቃለ-መጠይቅ ለመረዳት እንደሚቻለው "ኪነጥበብ ወ ቲያትር" ደጃዝማች ካሣ ወልደማርያም በ 1954 ዓ.ም. የቀዳማዊ ኃይለሥላሴ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዘዳንት ሆነው እስከመጡ ድረስ በዶ/ር ፊሊፕ መሪነት ከፍተኛ እንቅስቃሴ ያደርግ ነበር:: የተውኔት ዝግጅቶችን፣ ግጥሞችን፣ የስዕል አውደ-ርዕዮችን እና ሌሎችንም ዝግጅቶች በማቅረብ ታዳሚውን ያዝናናና ያስተምርም ነበር:: ደጃዝማች ካሣ ወልደማርያም የዩኒቨርስቲው ፕሬዘዳንት ሆነው እንደመጡ ተዘጋጅቶ በነበረው የግጥም ምሽት ዮሐንስ አድማሱ "ላም እሣት ወለደች በሬ ቀንድ አወጣ በስልጣን ሊቅ መሆን ይኸም አለ ለካ" የሚል ግጥም አቀረቡ:: ግጥሙ አዲሱን ፕሬዘዳንት ለመንካት ነበር:: የዩኒቨርሲቲው ፕሬዘዳንት በሴኔቱ መሾም ሲገባው ቀዳማዊ ኃይለሥላሴ በቀጥታ ደጃዝማች ካሣን እንዲሾሙ በመደረጉ በተማሪውና በማህበረሰቡ ዘንድ ቅሬታ ነበር:: ዮሐንስ አድማሱ ይህን ቅሬታ የሚያባብስ ግጥም በመግጠማቸው "ኪነጥበብ ወ ቲያትር" በሣምንቱ በእሣቸው ትዕዛዝ እንዲዘጋ ተደረገ:: የክፍሉ ኃላፊ ዶ/ር ፊሊፕ ካፕላንም ኮንትራታቸው እንዲቋረጥ ተደረገ:: በዚህ ጊዜ አባተ መኩሪያ እና ጓደኞቻቸው ከ"ኪነ ጥበብ ወ ቲያትር” ተባረሩ:: አቶ አባተ ከዩንቨርሲቲው "ኪነጥበብ ወ ቲያትር” ከተባረሩ በኋላ አዲስ በመቋቋም ላይ በነበረው የኢትዮጵያ ቴሌቪዥን በአዘጋጅነት ተቀጠሩ:: ቴሌቪዥን ሥራውን በጀመረ ጊዜ የሚያስተዳድሩት እንግሊዞች ስለነበሩ አቶ አባተ ለአራት ወራት እንዳገለገሉ ግላስኮት ቴሌቪዥን ኮሌጅ ውስጥ ገብተው እንዲማሩ ወደ እንግሊዝ አገር ተላኩ:: በእንግሊዝ አገር ቆይታቸው ሚዲያ ኮሚዩኒኬሽን አጥንተው እና በቢቢሲም እንዲሁ እየሰሩ የሥራ ልምድ አግኝተው ወደ አገራቸው ተመለሱ:: ከዚያ እንደተ መለሱ በኢትዮጵያ ቴሌቪዥን እና በሀገር ፍቅር ቲያትር ቤት አዘጋጅና እንዲሁም አሰልጣኝ በመሆን ቀጠሉ:: በመሃሉ የሲኒማ ቶፖግራፊ ትምህርት እንዲማሩ እድል አግኝተው ወደጀርመን ሄዱ:: 

  ጀርመን ውስጥ ኮሎኝ በሚገኘው ቪዲ ኤፍ ስቱዲዮ ስልጠና አግኝተው ተመለሱ:: ከጀርመን እንደተመለሱ በሀገር ፍቅር ቲያትር ቤት በአዘጋጅነት ተቀጥረው ለመጀመሪያ ጊዜ "ኦ! ዘመቻ" በሌላ ስሙ "መልክአ ምድር" በሚል የሚታወቀውን የኢዩኤል ዮሐንስን ተውኔት አዘጋጅተው አቀረቡ:: ተውኔቱ ማህበራዊ ህይወትን የሚዳስስ የዝቅተኛ መደብ አባላትን ህይወትን የሚያሣይ ነበር:: አራት መድረኮችን በአርብ የምሽት ፕሮግራሞች እንደቀረበ በቅድመምርመራ (ሳንሱር) መሥሪያ ቤት ተጠርተው ተውኔቱን ማሣየት እንዲያቆሙ መወሰኑ ተነገራቸው:: ከዚህ ተውኔት ጋር በተያያዘ ከሀገር ፍቅር ቤትም ከቴሌቪዥንም እንዳይሰሩ በአንድነት ታገዱ:: ከሥራ ታግደው ሁለት ሳምንታትን እንዳስቆጠሩ ታሪኩን ይከታተሉ የነበሩ የብሪትሽ ካውንስል ሃላፊዎች እንግሊዝ አገር ንደን ከተማ ውስጥ የኦፔራ ሴንተር በአዘጋጅነት የስኮላርሽፕ እድል እንደተሰጣቸው ተነገራቸው:: ወደእንግሊዝ አገር ለሁለተኛ ጊዜ ከመሄዳቸው በፊት ስኮላርሽኘ በሰጧቸውና ጉዳዩ በሚመለከታቸው የኢትዮጵያ ባለሥልጣናት መካከል ስምምነት ነበር:: አቶ አባተ ትምህርታቸውን ጨርሰው ሲመለሱ እንደ ገና ከሥራ የመገለል ችግር እንዳይገጥማቸው በማሰብ የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቲያትር አርቲስቲክ ዳይሬክተር ሆነው እንዲሰሩ ስምምነት ተደርሶ ወደ ውጭ ሄዱ:: አቶ አባተ በእንግሊዝ የነበራቸውን የትምህርት ቆይታ አጠናቀው ወደኢትዮጵያ እንደተመለሱ አብዛኛውን የሥራ ዘመናቸውን ያሣለፉት በብሄራዊ ቲያትር እና በአዲስ አበባ ማዘጋጃ የቲያትርና ባህል አዳራሽ ነው:: በልዩ ልዩ ደሪሲዎች ተፈው በነዚህ ቲያትር ቤቶች አዘጋጅተው ለህዝብ ካቀረቧቸው የሙሉ ጊዜ ተውኔቶች መካከል ቀጥለው የተዘረዘሩት ይገኙባቸዋል::

  1.      ሀሁ በስድስት ወር (1966)

  2.     አቡጊዳ ቀይሶ (1971)

  3.     መልዕክተ ወዛደር (1971)

  4.     የመንታ እናት (1971)

  5.     መቅድም (1972)

  6.     ጋሞ (1973)

  7.     ኦቴሎ (1973)

  8.     ቴዎድሮስ (1973)

  9.     ሐሙስ (1978)

  10.   አሉላ አባነጋ (1979)

  11.     ያላቻ ጋብቻ (198ዐ)

  12.    ታርቲዩፍ (1980)

  13.    ኤዲፐስ ንጉሥ (1988) ይገኙባቸዋል :: 

  ከመንግሥት ቲያትር ቤቶች ከለቀቁ በላ አቶ አባተ "መኩሪያ ቲያትር" የሚል የቲያትር ድርጅት አቋቁመው በመሥራት ላይ ይገኛሉ:: መኩሪያ ቲያትር ስቱዲዮ እና መዝናኛ ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ኩባንያ ከአሥራ ሁለት ዓመታት በፊት ከተቋቋመ አንስቶ ብዙ ስራዎችን አከናውል:: የቲያር ኩባንያው "ቲያትር ለልማት" የሚባለውን የቲያትር አቀራረብ ፈለግ መሠረት በማድረግ ብዙ ትምህርት ስጭ ተውኔቶችን በማህበራዊ ጉዳዮች ላይ ተመስርተው በማዘጋጀት ለመድረክ አብቅተዋል:: ይህን ፈለግ በመከተል አዘጋጅተው ለመድረክ ከበቁ ተውኔቶችና ዘጋቢ ፊልሞች መካከል የሚከተሉት ተጠቃሾች ናቸው ::

  1. ሕሊና                                                                  5. ድንቅ ሴት

  2. ጠለፋ                                                                 6. የፍትህ ፍለጋ (ዘጋቢ ፊልም)

  3. ጃሮ ዳባ                                                               7. የመስከረም ጥቃት (ዘጋቢ ፊልም)

  4. በሐምሌ ጨረቃ ጉዞ ይገኙባቸዋል ::

  አቶ አባተ የመሰረቱት መኩሪያ የቲያትር ኩባንያ በየክልሉ እና በአዲስ አበባ ከተማ ለሚገኙ አማተር ከያንያን የቲያትር፣ የሰርከስ እና የሙዚቃ ስልጠና ከመስጠቱም ሌላ ከኢትዮጵያ ውጭም ወደተለያዩ አገሮች እየተጓዘ ትርኢት በማቅረብና የሙያ ገጠመኝ ልውውጥ በማድረግ ይሳተፋል:: አቶ አባተ መኩሪያ በቲያትር ዝግጅት ወቅት የመራሄ- ተውቱን ሚና በተመለከተ ለተጠየቁት ሲመልሱ ሶስት አበይት ተግባራትን ማከናወን እንደሚጠበቅበት ይናገራሉ:: እነዚህም ሶስት ተግ ባራት "ተዋንያንን ማሰልጠንና የተውኔት ሙያን ማበልፀግ፣ የድራማን ሥነፅሁፍ በምሁራዊ ዓይን አይቶ ማዳበርና ደራሲውም እንዲበረታታ ማድረግና የቲያትር ተመልካችን መፍጠር ነው” ናቸው ብለዋል::  የኢትዮጵያን የቲያትር እድገት እና የተመልካቹን ሁኔታ በተመለከተም አቶ አባተ ሲናገሩ 'የኢትዮጵያ ህዝብ የራሱን ባህል አትኩሮ የሚያጣጥምና የሚወድ ነው:: ቲያትር ቤቱ ይሞላል:: ግን ከቲያትር አንፃር (ከድርሰቱ) ያየነው እንደሆነ ብዙ የሚተቹ ነገሮች አሉ:: እንደቲያትር አዋቂ ተመልካች ቲያትሮቹን ብናያቸው ብዙ ግድፈቶች እናገኛለን:: ተመልካቹ ለዛሁሉ ደንታ የለውም። የራሱን ህይወት ማየት ይወዳልና ይመጣል:: በአሁኑ ጊዜ ጥበቡ ሳይሆን ተመልካቹ ነው የሚፈታተነን:: ደሞ የእኛን አገር ቲያትር እንዳያድግ የገደለው የቲያትር ቤቶች በመንግሥት እጅ መሆናቸው ነው:: ቲያትር ቤቶች አንድ አይነት ሥራ ነው የሚሠሩት" ብለዋል:: መራሄ-ተውኔት አባተ መኩሪያ አሁንም በሥነ-ተውኔት መስክ በአጭርና በረጅም ጊዜ የሚተረጎሙ ብዙ እቅዶች ነበርራቸው::


  ሆኖም ሐምሌ 14፣ 2008. በኢትዮጵያ የተውኔት ታሪክ ደማቅ አሻራ ማሳረፍ የቻለው አንጋፋው መራሄ-ተውኔት አባተ መኩሪያ ከዚህ ዓለም በሞት ተለዩ።

  የአቶ አባተ መኩሪያ ምስል


  ምንጭ:- ታሪካዊ መዝገበ-ሰብ   

   

   

   

 • loader Loading content ...
 • @ቆብአስጥዬ   3 months ago
  Sewasewer
  ኢትዮጵያ ውስጥ የታወቁና የተደነቁ የሆቴል ባለሃብት ነበሩ። አቶ በቀለን ከሌሎች ባለሃብቶች ልዩ የሚያደርጋቸው ከትንሽ ሻይ ቤት ተነስተው በመላው ደቡባዊ የኢትዮጵያ ክፍል የሆቴል ሙያን ለማስፋፋት በመቻላው ነው። ጋዜጠኛ አለምነህ ዋሴ በ2005 ዓ.ም. የእሁድ ጧት ፕሮግራሙ በፋና ሬዲዮ ስለአቶ በቀለ ሞላ ካቀረበው ታሪክ ለመረዳት እንደሚቻለው የሻይ ቤት ሥራቸው በአብዛኛው ከአዲስ አበባ ወደ ድሬዳዋ በባ ቡር የሚጓዙ መንገደኞችን በማገልገል ላይ ያተኮረ ነበር። ሻይ የሚወጡ ደንበኞችን የበለጠ ለመሳብም “ሻይ የጠጣ ይከብራል ጠጅ የጠጣ ይከስራል።” የሚል ማስታወቂያ ለባቡር ተጓዠች ያስነግሩ እንደነበር ጋዜጠኛው ባቀረበው ታሪካቸው አብራርቷል። 

  አቶ  በቀለ ከሻይ ሥራ ወጥተው የመጀመሪያውን ዘመናዊ ሆቴል ያቋቋሙት በ 1941 ዓ.ም.  በዚያው ተወልደው ባደጉበት ሞጆ ከተማ  ሲሆን ከአዲስ አበባ ወደ ደቡብና ምሥራቅ የኢትዮጵያ ግዛቶች በባቡር ወይም በመኪና ለሚጓጓዙ መንገደኞች የሚያገለግሉ  21 የመኝታ ክፍሎች እንደነበሩት ታውቋል። ከዚያም በ 1945   ዓ.ም. መቂ ላይ፣ በ 195 1   ዓ.ም.  ደብረዘይት ላይ እና በ 195 3   ዓ.ም.  ሌላ የተሻሻለ ሆቴል በሞጆ ከተማ በመገንባት ቅርንጫፎቻቸውን ማስፋፋት ቀጠሉ። በቀለ ሞላ ባለሃብት ብቻም ሳይሆኑ አስተናጋጅ ገንዘብ ተቀባይና በአጠቃላይ በድርጅታቸው ውስጥ ከተራ ሠራተኝነት አስከ አስተዳዳሪነት ባለው ዘርፍ ሁሉ እየገቡ ተሳትፎ በማድረግ የሆቴል ሙያን ያስፋፉ መሆኑን የተረዱት በወቅቱ የኢትዮጵያ ንጉሠ - ነገሥት የነበሩት አፄ ኃይለሥላሴ ላንጋኖ የሚገኘውን በቀለ ሞላን ሆቴል በድንገት ሄደው ለመጐብኘት ችለዋል። ንጉሠ - ነገሥቱ እየተሰጠ ባለው አገልገሎት በመደስት በቀለ ሞላ የውጭ አገሩን የአሠራር ልምድ ቢቀስሙ ላገራቸው የተሻለ የሥራ ፍሬ ሊያስመዘገቡ ይችላሉ በሚል እምነት ወደ አውሮፓ ተጉዘው በመሰል የሙያ መስክ ያለውን የአሠራር ባህል ጎብኝተው እንዲመለሱ አድርገዎቸዋል። እንደተጠበቀውም ከሙያ ጉብኝታቸው በኋላ አሠራራቸውን ዘመናዊ ከማድረጋቸውም በተጨማሪ ከምጆ እስከ ሞያሌ፤ ከወላይታ እስከ ባሌ እና እንዲሁም ከአዋሽ እስከ ጅቡቲ በርካታ ቅርንጫፎችን ለመክፈት በቅተዋል፡፡ በቀለ ሞላ ከገነቧቸው ታዋቂ የሆቴል ቅርንጫፎቻቸው መካከል በሞጆ፣  በመቂ፣ በላንጋኖ፣ በሐዋሳ፣ በአርባምንጭ፣ በሞያሌ፣ በወላይታ፣ በባሌ ጎባ፣ በአዋሽ፣ በድሬዳዋ፣ በጅቡቲ፣ በደብረዘይትና በአዲስ  አበባ የሚገኙት ተጠቃሾች ናቸው፡፡ በእነዚሀና በሌሎች ሆቴሎቻቸው ጭምር የተጠቃሚውን ምቾት ለመጠበቅ ሲባልም የጀኔሬተር መብራት እየዘረጉ በዚያን ዘመን የነበረውን የኤሌክትሪክ ችግር በመቅረፍ ሲሰሩ ኖረዋል። 

  ባለራዕይ የነበሩት አቶ በቀለ ሞላ በተወለዱ በ82 ዓመታቸው ከዚህ ዓለም በሞት ቢለዩም በየከተማው የተገለቡት ሆቴሎቻቸው ዛሬም ድረስ አገልግሎት በመስጠት ላይ እንደሆኑ ይለገራል።

  የበቀለ ሞላ ሆቴሎች ላንጋኖ

  ምንጭ:- ታሪካዊ መዝገበ-ሰብ


   

   

 • loader Loading content ...
 • @ቆብአስጥዬ   3 months ago
  Sewasewer

  -  ሀፐታይተስ በቫይረስ አማካይነት የሚከሰት ጉበትን የሚያጠቃ በሽታ ነው

  -   አብዛኛው ጊዜ ሰዎች በቫይረሱ ለመጠቃታቸው ምንም ዓይነት ምልክት ሳያሳዩ ይኖራሉ። በአንዳድንድ ሰዎች ግን ትኩሳት ከባድ ድካም የሰገራ ግራጫ መሆን የሽንት መደፍረስ አና የአይን ወደ ቢጫነት መቀየር የመሳሰሉ ምልክቶች ይታያሉ።

  -   ከሰሐራ በታች ባሉ የአፍሪካ ሀገራት በሽታው እስከ አሁን ድረስ በስፋት ተንሰራፍቶ ይገኛል።

  -  በሽታው ይኑሮት ወይም አይኑሮት እርግጠኛ ለመሆን ብቸኛው መንገድ የደም ምርመራ ማድረግ ነው።

  -  ሀፐታይተስ የሚተላለፍው በወሲብ አማካይነት  በደም ንክኪ ማለትም በሽታው ካለበት ሰው በተበከሉ መርፌ እና ሊሎች የሰሉ ነግሮች እንዲሁም በወሊድ ጊዜ ከእናት ወደ ልጅ መተላለፍ ይችላል።

  -   እስከ አሁን ሀፐታይተስ መዳኛ መድሃኒት የለውም፡ ግን ጥሩው ነገር የጉበት ጉዳቱን የሚያዘገዩ መድሃኒቶች አሉ።

  -  በሽታው ለመከላከል ዋነኛው መንገድ መከተብ ነው። ክትባቱ የሚሰጠው በሶስት የተለያዩ ጊዜያት ሲሆን በስድስት ወራት ጊዜ ውስጥ መጠናቀቅ አለበት። ክትባቱ እንዲሰራ ሶስት ጊዜ መወሰድ አለበት። 

  ምንጭ:- ኢንተርናሽናል ኮምዩኒት ሄልዝ ሰርቪስስ

 • loader Loading content ...
 • @ቆብአስጥዬ   3 months ago
  Sewasewer
  -  የመፀው ዘመን  - ከመስከረም 26  - ታኅሣሥ 25

  -  የበጋ ዘመን  - ከታኅሣሥ 26 - መጋቢት 25

  -  የጸደይ ዘመን  - ከመጋቢት 26 - ሰኔ 25

  -  የክረምት ዘመን  - ከሰኔ 26  - መስከረም 25

  ምንጭ:- ባሕረ ሐሳብ
 • loader Loading content ...
 • @ቆብአስጥዬ   3 months ago
  Sewasewer

  እኛ ነን፤ እኛው ነን፤ እኛ የዛሬዎች
  በአጭር የተቀጩ ሩቅ መንገደኞች
  ሰላሳ ህልመኞች፣ ሰላሳ ተስፈኞች፣ ሰላሳ ወጣቶች
  ሀገር እንደሌለው በሰው ሀገር ምድር ሲቀላ አንገታቸው
  ወገን እንደ ሌለው ከሰው ሀገር ባህር ሲቀየጥ ደማቸው
  በአገር ቁጭ ብለን ከአለም ጋራ እያየን
  ከሬት የመረረ ከቋጥኝ የሚከብድ
  ከቶን የሚያቃጥል ከብራቅ የሚያርድ
  ሀገር ያህል መርዶ በሰንበት አመሻሽ በአገር የተሸከምን
  በገዛ ሞታችን እዝን የተቀመጥን፡፡
  ካሳለፍነው ህይወት ካለፈው መከራ
  መማር የተሳነን ደመና ወራሾች፣
  የሞትነውም እኛ ያለነውም እኛ
  ከፋይም ተቀባይ እኛው ነን ባለእዶች፡፡

  እኛው ነን…. …. ….
  ከቅጣትም ቅጣት ከመርገምትም መርገት፣
  የገዛ አንገታችን በስለት ሲቀላ
  የገዛ ደማችን ባህሩን ሲያቀላ
  የራሳችንን ሞት ቆሞ መመልከቱ፣
  ምን ያህል ነው ፍሙ ምን ያህል ይከብዳል ሰቆቃው እሳቱ?
  ምን ያህል ነው ሸክሙ? ምን ያህል ይዘፍቃል? መከራው ክብደቱ
  ምን ያህል ይጠልቃል? ምን ያህል ይሰማል? መጠቃት ስለቱ
  ሀዘን ነው? ቁጣ ነው? ጸጸት ነው? ምንድነው መጠሪያው? ምንድነው ስሜቱ?
  እውን ይህን መአት ይኼን የእኛን መቅሰፍት
  ቋንቋዎች በቃላት ችለው ይገልጹታል?
  እውን ይህ ስቃይ፣ ይህንን ሰቆቃ፣ እናትና ሀገር ሸክሙን ይችሉታል?

  እኛው ነን እኛው ነን… …. ….
  ለዚህ ክፉ እጣችን ለዚህ መርገምታችን
  ለአለም ለፈጣሪ አልፈታ ላለው እንቆቅልሻችን
  መነሻም መድረሻም ጥያቄዎች እኛ መልሶችም እኛው ነን፡፡
  እኛው ነን የገፋን፣ እኛው ነን የከፋን
  እኛው ነን ያጠፋን ፣እኛው ነን ያጠፋን፡፡
  ከዘመን ጋር አብሮ መዘመን ተስኖን
  ሰፊ አገር ይዘን በሀሳብ እየጠበብን
  በፍቅር ተሳስቦ አብሮ መራመዱ አቀበት የሆነን
  ቂም እየቆነጠርን፣ ቂም እየመነዘርን
  በዛሬ መንጋጋ የትናንቱን ድርቆሽ የምናመነዥክ
  በዛሬ ምድጃ የትናንቱን አመድ ታቅፈን የምንሞቅ
  ባንድ ላይ ከመጓዝ በየፊና ሩጫ አረፋ ምንደፍቅ

  እኛው ነን እኛው ነን…. …. ….
  ከእምነት የተፋታን ከፈጣሪ የራቅን፡፡
  እኛው ተጋፊዎች፣ እኛው ተገፊዎች
  እኛው አሳዳጆች፣ እኛው ተሳዳጆች
  ካሳለፍነው ህይወት ካለፍነው መከራ
  መማር የተሳነን ደመና ወራሾች
  እኛው ነን እኛው ነን እኛ የዛሬዎች
  የነገ፣ የታሪክ ያገር ባለእዳዎች፡፡

  እኛው ነን…. …. ….
  በንፍገት በስስት በስግብግብ መዳፍ
  ከድሆች ጉሮሮ ካፋቸው መንጭቀን
  ሌሎችን ረግጠን ሌሎችን ጨፍልቀን
  በሌሎች ጀርባ በሌሎች ጫንቃ ላይ ወደ ላይ መሳቡ ቅንጣት የማይጨንቀን
  በማስመሰል ጥበብ በአድርባይ አንደበት በሸፍጥ የሰለጠን
  ከብዙዎች ድርሻ ተሻምተን ተናጥቀን
  ላንድ ለራሳችን በወርቅ ላይ አልማዝ በህንጻ ላይ ህንጻ
  ስንቆልል ስንከምር የማይሰቀጥጠን፣
  የመንፈስ ድውዮች የንዋይ ምርከኞች
  የወንበር ሱሰኞች የሆድ አምላኪዎች
  ከሰውነት ወርደን በነፍስ የኮሰመን የስጋ ብኩኖች
  የራሳችን ሀጢያት የራሳችን ሲኦል እኛው ነን መርገምቶች

  እኛው ነን!
  በዚህ ሁሉ ግና ….. …. ….
  መቼም ቢሆን መቼ ሰው ይሞታል እንጂ ተስፋ አይሞትምና
  በመንገድ የቀሩት ወጣቶቻችን
  በአጭር የተቀጨው ሀሳብ ምኞታቸው
  ተስፋ አለን ተስፋቸው፡፡
  በአገራቸው አፈር በታናሾቻቸው
  ነገ ውብ ይሆናል ለምልሞ ይጸድቃል በዛሬው ደማቸው
  ዛሬ የመከነው ውጥን ርዕያቸው
  በጊዜና በአገር ነገ እውን ይሆናል ይፈታል ህልማቸው
  ይህ ነው መጽናኛችን ይህ ነው መዕናኛቸው፡፡
 • loader Loading content ...
 • @ቆብአስጥዬ   3 months ago
  Sewasewer
  ወንጀለኛ ቢሆን አለም አሸባሪ 
  አራጅ ቢሆን ኖሮ ቤት ንብረት መዝባሪ 
  ፑሽኪን አሌክሳንድር 
  “ባያቱ ሐበሻ ነው” መች እንለው ነበር!! 
 • loader Loading content ...
 • @ቆብአስጥዬ   3 months ago
  Sewasewer
  እንባ እንባ ይለኛል - ይተናነቀኛል
  ግን እንባ ከየት አባቱ! - ደርቆአል ከረጢቱ 
  ሳቅ ሳቅም ይለኛል - ስቆ ላይስቅ ጥርሴ
  ስቃ እያለቀሰች - መከረኛ ነፍሴ
   
 • loader Loading content ...
 • @ቆብአስጥዬ   3 months ago
  Sewasewer

  መስሎአቸው ውጭ አገር - ነፍስ የሚዘራበት

   ሰው ሞቶ በስብሶ - አድጎ ሚያብብበት

  መስሎአቸው አውሮፓ - የነፃነት አገር

  የሚችል መስሎአቸው - ሰው ሁሉን መናገር

  መስሎአቸው አውሮፓ - ያኛው ሌላ ገነት

  አዳም ከሄዋን ጋር - የሚጫወትበት

  እንየው አሉና - የአገር ልጆች ሄዱ - ሄዱ እየበረሩ

  የአገር ልጆች ጓጉ - ባህር ተሻገሩ

 • loader Loading content ...
 • @ቆብአስጥዬ   4 months ago
  Sewasewer

  መነሻው በ፲፱፻፲፩ ዓ/ም እንፍልዌንዛ ወረርሽኝ በሽታን ለመከላከል የተጀመረ ሲሆን ባሁኑ ወቅት በየአመቱ ህዳር ፩፪ ቀን ቆሻሻ የማቃጠል ልማድ ይከወናል፡፡  ምንጭ:-  ውክፔዲያ

 • loader Loading content ...
 • @ቆብአስጥዬ   8 months ago
  Sewasewer
  እንደ ቅባት ያለ ወይም ጎርፍ፡፡ 
 • loader Loading content ...
  Load more...
loader Loading content ...

Comments (0)


  This user has no comment yet.