loader

Topics (3)


loader Loading content ...

Explanations (3)


 • @Miss Counselor   6 months ago
  Sewasewer

  ድህረ ወሊድ ድብርት ማለት ከወሊድ በኋላ በአካልና በአኗኗር ዘይቤ ለውጥ ምክንያት በአንዳንድ እናቶች ላይ የሚከሰት ነው። ግማሽ የሚሆኑ ሴቶች በሚወልዱበት ወቅት ከጥቂት ቀናት ጀምሮ ለሳምንት ያክል መደበት (ድብርት) ሊያጋጥማቸው ይችላል :: በመጀመሪያ ደረጃ የሚጠቀሰው የችግሩ መከሰት ምክንያት በእርግዝና ወራት በከፍተኛ መጠን የሚገኙት የኤስትሮጅን (Estrogen) እና የፕሮጅስትሮን (Progesterone) ሆርሞኖች ከወሊድ በኋላ በአጭር ጊዜ ውስጥ መጠናቸው መቀነሱ ነው፡፡ በሁለተኛ ደረጃ ችግሩ የሚመጣው የታይሮይድ (Thyroid) ሆርሞን መጠን አነስተኛ ከሆነ ነው :: የታይሮይድ ሆርሞን መጠን ማነስ የምግብ ፍላጎት ማጣት፣ የድካምና የድብርት መጫጫንን ያስከትላል :: የድህረ ወሊድ ድብርት መንስኤዎች ሆርሞናዊ ለውጦች ብቻ ሳይሆኑ ውጫዊ ሣፊቶችም ጭምር ናቸው፡፡


  ከወሊድ በኋላ በመንፈስ መረበሽ፣ በአካል መድከምና በክብደት መጨመር ምከንያት የሰውነት ቅርፅ መቀየር (መበላሸት) ያጋጥመኛል ብሎ መስጋት፣ ከመደበኛ ሥራ እርቆ በጓዳ ሥራ ብቻ እንደታሰሩ በማሰብ መተከዝ፣ ሌላ የእነርሱን እንከብካቤ የሚፈልግ ሕጻን እንደ ተጨመረባቸው በማሰብ መጨነቅ፤ ይህንንም ኃላፊነት ለመወጣት አብዝቶ ማሰብ፣ ጤናማ ያልሆነ ፅንስ መገላገል፣ የፅንስ በወሊድ ላይ መጥፋት (ሕይወቱ ማለፍ)፣ ረጅም ጊዜያቸውን ከፍቅር ጓደኛ ጋር ወይም ከጎረቤት ጋር ከማሳለፍ ይልቅ በልጅ እንክብካቤ ቤት ውስጥ ብቻ በመወሰናቸው የሚፈጠር ጥሩ ያልሆነ የቢታችነት ስሜት፣ በቂ እንቅልፍ አለማግኘት፣ ቀድሞ ሲወዱትና ሲያደርጉት የነበረ የሚያዝናናቸው ድርጊትና እንቅስቃሴ መቋረጥና በመሳሰሉ መንስዔዎች ይከሰታል። ከወሊድ በኋላ የሚፈጠረው ድብርት የሚገለጸው መሠረት የሌላቸው ነገሮች በመስማት፣ በማየት፣ በመናገርና የከንቱነት ስሜትና የአእምሮ ሕመም ሰለባ በመሆን ነው።


  ምንጭ 
  የግጭት መንስኤዎቻቸው እና መፍትሔዎቻቸው ፣ ፓስተር ዶ/ር ሙላቱ በላይነህ።
 • loader Loading content ...
 • @Miss Counselor   6 months ago
  Sewasewer
  ድህረ ወሊድ ድብርት ማለት ከወሊድ በኋላ በአካልና በአኗኗር ዘይቤ ለውጥ ምክንያት በአንዳንድ እናቶች ላይ የሚከሰት ነው። ግማሽ የሚሆኑ ሴቶች በሚወልዱበት ወቅት ከጥቂት ቀናት ጀምሮ ለሳምንት ያክል መደበት (ድብርት) ሊያጋጥማቸው ይችላል :: እንደ ኢትዮጵያ የቢሃይቭ ድህረ ገጽ አገላለጽ ድህረ ወሊድ ድብርት ከ7o-80 በመቶ የሚሆኑ ሴቶች ላይ ይከሰታል :: እነዚህ ሴቶች ከወሊድ በኋላ (ቤቢ ብሉ) የሚባለው ስሜት ይሰማቸዋል:: ይህም የመከፋት የመጨነቅና የመደበር ስሜት ነው በማለት ይዘግባል :: 

  ከወሊድ በኋላ ሰውነታቸው የሆርሞን ለውጥ፤ ጭንቀትና ድካም እንዲሁም በቂ እንቅልፍ የማጣት ስሜት ይሰማቸዋል። የፍርሃት የመጨነቅና የመደበር ስሜት ለተወሰኑ ቀናት የተለመደ ነው፡: ነገር ግን አንዳንድ ሴቶች ይህ ስሜት ሊቆይባቸው ይችላል :: አስፈላጊ ክትትል ካልተደረገ ሳምንታትና ወራት ድረስ ሊቀጥል ይችላል ::ይህ ማለት ከወሊድ በኋላ ያለው ዋናውና ትክክለኛው የድብርት ወይም የመጫጫን ስሜት (Clinical Depression) ማለት አይደለም።

  ሌላው "Postpartum psychosis" ድህረ ወሊድ ድብርት ከመጀመሪያዎቹ ሁለትና ሶስት ሳምንታት ጀምሮ ለወራት ሊዘልቅ የሚችልን የድብርት ስሜት የሚያመላክት ነው። ይህ ከውሊድ በኋላ የሚገጥም ከፍተኛ የሆነ የድብርት ሌላው ተጠቃሽ ነው። ይህ ዓይነቱ ከወሊድ በኋላ ያለው ድብርት የሚያጋጥማቸው ከወለዱ ከአንድ ሺ ሴቶች በቁጥር አንድ ወይም ሁለት ሴቶች ይሆናሉ ተብሎ ይገመታል። በተለይ ላልተፈለገና ላልታሰበ እርግዝና ተጋላጭ የሆኑ ሚስቶች ከፍተኛ ለሆነ ድብርት ተጋላጭ መሆናቸው እሙን ነው።

  ምንጭ
  የግጭት መንስኤዎቻቸው እና መፍትሔዎቻቸው ፣ ፓስተር ዶ/ር ሙላቱ በላይነህ።
 • loader Loading content ...
 • @Miss Counselor   6 months ago
  Sewasewer
  የግብረ ስጋ ግንኙነት ወይም ሩካቤ ስጋ ማለት ባለትዳር በሆኑ ጥንዶች መካከል ማለትም በአንድ ወንድና በአንዲት ሴት መካከል ለጠለቀ ግንኙነት፣ ለስሜት እርካታና ልጅን ለመውለድ የሚደረግ አካላዊ ወይም ወሲባዊ ግንኙነት ነው :: የግብረ ስጋ ፍላጎትን በማሟላት ፍቅርን የመሥራት ወይም የመገንባት ሂደት ነው። ባለትዳሮች መካከል ችግሮችና አለመግባባቶች እንዲፈጠሩ ከሚያደርጉ ምክንያት አንዱ በግብረ ስጋ ግንኙነት አለመጣጣምና አለመርካት ወይም መልካም የሆነ ግንኙነት አለመኖር ነው። በግብረ ስጋ ግንኙነት አለመጣጣም ራሱን የቻለ ያለመግባባት መንስኤ መሆኑ ብቻ ሳይሆን በትዳር መካከል የሚፈጠሩ የተለያዩ ችግሮችን የሚያባብስ አቀጣጣይ የመሆን ሚናም ይጫወታል ::

  በግብረ ስጋ ግንኙነት አለመጣጣም የሚፈጠሩ ችግሮች ግለት ቶሎ እንዳይበርድ የሚያደርግና ቀስ በቀስም የትዳርን ህልውና የሚያጠፋ የተዳፈነ እሳት ሊሆን ይችላል። ከባህላችን ተጽዕኖ የተነሳ በትዳር ውስጥ ፍላጎታችንና ችግራችንን በፍጹም ግልጥነት የማናወራበትና የማንወያይበት ጉዳይ ቢኖር የግብረ ስጋ ግንኙነት ነው። የጋብቻ አስተማሪዎችም ሆንን አማካሪዎች እንደ ሌሎች ችግሮች በድፍረት የማናስተምርበትና የማናማክርበት ርዕሰ ጉዳይ ከመሆኑ የተነሳ ችግሩ ከመቼውም በበለጠ እየጨመረና እየተባባሰ በመምጣቱ ብዙዎች ለአለመግባባት፣ ለመለያየትና ለፍች ተጋላጭ እንዲሆኑ እያደረገ ይገኛል። በትዳር ላይ የሚፈጠር የግብረ ስጋ ግንኙነት አለመጣጣም ችግር ጥንዶቹ ሊያስተካከሉት ፍላጎት ካላቸውና ተገቢ ጥረት ካደረጉ በሂደት ሊቀንስ ይችላል፡፡ እንደገናም በተለያዩ እርዳታዎችና ሕክምናዎች የመሻሻልና የመስተካከል ሁኔታዎች ሊፈጠሩ እንደሚችሉ ልንገነዘብ ይገባል።

  በትዳር ውስጥ የግብረ ስጋ ግንኙነት ፍላጎትና ድርጊት አንዱ የጋብቻ ክፍል እንጂ የትዳር ሁሉ ነገር አድርገን ከማሰብ መቆጠብና ሌላው የትዳር ገጽታ የሚጠይቀውን የሁለትዮሽ መሰጠት፣ መተሳሰብና መረዳዳት መዘንጋት አይገባንም። በሌሎች ጉዳዮች ላይ ስንተሳሰብና ስንረዳዳ በግብረስጋ ግንኙነት ጊዜ ወደ መጣጣም መምጣት የሚያስችለንን መልካም ስሜት መፍጠርና ማሳደግ እንችላለን:: በርዕሰ ጉዳዩ ላይ ትምህርትና ምክር ሊሰጥበትና ባለትዳሮች የሆንን አንዱ ሌላውን በመረዳት፣ በመተሳሰብና በመጣጣም አንድነታችንና የጠለቀ ግንኙነታችንን እያጠናከርን ልንኖር ይጠበቅብናል።

  ምንጭ
  የግጭት መንስኤዎቻቸው እና መፍትሔዎቻቸው ፣ ፓስተር ዶ/ር ሙላቱ በላይነህ።
 • loader Loading content ...
loader Loading content ...

Comments (0)


  This user has no comment yet.