loader

Topics (26)


loader Loading content ...

Explanations (26)


 • Sewasewer
  ሰውየው በቀቀን ለመግዛት አንድ ሱቅ ይገባና “በደንብ የሚዘፍን ወፍ መግዛት እፈልጋለሁ” ይላል። ባለቤትየውም አንድ ወፍ እያሳየው “ይህ የምታየው ወፍ ልክ እንደ ፍራንክ ሴናትራ ነው የሚዘፍነው። በዓለም ተወዳዳሪ የሌለውም ስለሆነ ከሶስት ሺህ ብር በታች አይሸጥም” በማለት ይመልሳል። 

  "ዋጋህ እንኳን የሚቀመስ አይደለም:: ቢሆንም እንደ ፍራንክ ሲናትራ የሚዘፍን ከሆነ እገዛሃለሁ።”

  “አሳምሮ ይዘፍናል እንጂ ጌታው ። ሆኖም አንድ ግዴታ ሊገቡ ነው ። ይኸውም እሱን ከገዙ አጠገቡ ያለውንም ወፍ አብረው መግዛት ይኖርብዎታል።"

  ገዢው ሁለተኛውን ወፍ ተመለከተው ወፉ ያረጀና የመነመነ ከመሆኑም በላይ ሊሞት አንድ ሐሙስ የቀረው ነበር። ይሄኔ ገዥው ብስጭት ብሎ “ምን በወጣኝ ነው ይሄን የምገዛህ?” ቢለው “ዜማና ግጥም የሚያዘጋጅለት እሱ ነዋ!” ሲል መለሰለት ።

  ምንጭ፤
  ቀልዶች፣ በአረፋይኔ ሃጎስ እና ኤፍሬም እንዳለ።
 • loader Loading content ...
 • Sewasewer
  አንድ ሸውራራና ነጭናጫ ሰው ብዙ ህዝብ በሚተራመስበት አውራ ጎዳና ሰዉን እየገፈተረና እየገላመጠ ሲጓዝ ካንዱ ጋር ይጋጫል። ይኼኔ “አንተ ደደብ እያየህ አትሄድም!” ብሎ ሰውየውን መስድብ ታዲያ የተገጨው ሰውዬ ቀልደኛ ኖሮ “አንተስ ወደምታይበት አቅጣጫ ለምን አትሄድም ወዳጄ?” ብሎ አፌዘበት።

  ምንጭ፤
  ቀልዶች፣ በአረፋይኔ ሃጎስ እና ኤፍሬም እንዳለ።
 • loader Loading content ...
 • Sewasewer
  ዶክተሩ ሁለት እብዶችን ለረጅም ጊዜ ሲያከሙ ከቆዬ በኋላ በሽተኞቹ የተሻላቸው ስለመሰላቸው ፈተና ሠጥተው ሊለቋቸው ይወስናሉ። 

  “ወዳጆቼ ከሆስፒታል ለመውጣት ከፈለጋችሁ በተግባራችሁም ሆነ በአነጋገራችሁ ጤነኞች መሆናችሁን ልታረጋግጡልኝ ይገባል።” አሉ ዶክተሩ።

  በሽተኞቹም በዚሁ ተስማሙና አንደኛው ድንች ሻጭ ሲሆን ሌላው ገዥ ሆነ። ከዚያም “ማለፊያ ነው ወዳጄ የድንች ነጋዴ ከሆንክስ አንድ ሊትር ድንች ስፈርልኝ።" ሲል ገዢው ጠየቀ። ድንች ሻጭ ጓደኛው ግን ይህን ሲሰማ ከት ብሎ ሳቀበት። በዚህን ጊዜ ዶክተሩ ክንች ሻጩ በርግጥ ጤነኛ መሆኑን በማመን  “ለምን ትስቅበታለህ ስጠው እንጂ!” በማለት ለማረጋገጥ ያክል ቢጠይቁት ፤ “ዶክተር መስጠቱንኰ እሰጠው ነበር። ጠርሙሱን ሳይዝ መጣ እንጂ” ብሎ መለሰላቸው ።

  ምንጭ፤
  ቀልዶች፣ በአረፋይኔ ሃጎስ እና ኤፍሬም እንዳለ።
 • loader Loading content ...
 • Sewasewer
  መምህርት፦ “ከብሩህ አእምሮና ከቆንጆ ፊት የትኛው ይበልጣል ቆንጂት?”
  ቆንጂት፡- “ቆንጆ ፊት ይበልጣል መምህርት“
  መምህርት:- "ለምን ቆንጂት?” 
  ቆንጂት፡- “ወንዶች ቆንጆ ፊትን በቀላል ማየት ሲችሉ ብሩህ አእምሮን ግን ለማየት ስለሚያዳግታቸው።”

  ምንጭ፤
  ቀልዶች፣ በአረፋይኔ ሃጎስ እና ኤፍሬም እንዳለ።
 • loader Loading content ...
 • Sewasewer
  ማሙሽ፦ “ኣብዬ ስንት ዓመት ሲሆነኝ ነው እንደልቤ መኖር የምችለው?”
  አባት፡- “ኧረ እንጃ የኔ ልጅ ፤ እንደፈቀደው ለመኖር የሚያስችለውን ያክል የኖረ ሰው ግን እስክ ዛፊ እንደሌለ ነው የማውቀው።"

  ምንጭ፤
  ቀልዶች፣ በአረፋይኔ ሃጎስ እና ኤፍሬም እንዳለ።
 • loader Loading content ...
 • Sewasewer
  ዳኛ፦ “ፈረሱን ስትሰርቅ ያዩ አምስት ምስክሮች ቀርበዋል።"
  ተከሳሽ፦ “ክቡር ዳኛ በኔ በኩል ደግሞ ስሰርቅ ያላዩ ሀያ አምስት ምስክሮች ማቅረብ እችላለሁ።”

  ምንጭ፤
  ቀልዶች፣ በአረፋይኔ ሃጎስ እና ኤፍሬም እንዳለ።
 • loader Loading content ...
 • Sewasewer
  “ያቺን ሽርሽር ላይ የተዋወቅናትን ሴትዮ ታስታውሳታለህ?”
  “አሳምሬ እንጂ” 
  "እንዲያውም ፍቅር ቢጤ ጀምራችሁ ነበር አይደል?"
  "እንዴታ!"
  “እኔን ሆነህ ቀርበህ በኔ ስምና አድራሻ ነበር ሁሉን ነገር የምታካሂደው። አይደለም?” 
  “አዎን ፤ ባንተ ስምና አድራጃ እየተጠቀምኩ ብዙ ቀናትን አብረን አሳልፈናል። ምነው ቅሬታ ተሰማህ እንዴ?"
  "ቅሬታስ ̧እልተሰማኝም፤ ብቻ ዛሬ ጠዋት ነገረ  ፈጇ እቤት ድረስ መጥቶ ነበር።"
  “አትለኝም! ምነው ፤ ምን ሆናለች እባክህ?”
  “መሆንስ ምንም አልሆነችም ብቻ ሁለት መቶ ሺህ ብር አውርሣኝ ሞታለች።” ቢለው ጓደኝየው ሕሊናውን ስቶ ወደቀ።

  ምንጭ፤
  ቀልዶች፣ በአረፋይኔ ሃጎስ እና ኤፍሬም እንዳለ።
 • loader Loading content ...
 • Sewasewer
  በሁለተኛው ያለም ጦርነት ወቅት ሙሶሎኒ ስንቅና ትጥቅ ያጥረውና የሚከተለውን ቴሌግራም ለወዳጁ ሂትለር ይልካል። 

  “ስንቅ ስላለቀብኝ አደራህን ፈጥነህ ላክልኝ ። ወዳጅህ ሙሶሎኒ።"
  “ምንም የምልክልህ ስንቅ ስለሌለኝ ቀበቶህን ጠበቅ ብታደርግ ይሻላል። ወዶጅህ ሂትልር "
  “በጀ ፤ ቀበቶ ላክልኝ። ወዳጅህ ሙሶሎኒ።”

  ምንጭ፤
  ቀልዶች፣ በአረፋይኔ ሃጎስ እና ኤፍሬም እንዳለ።
 • loader Loading content ...
 • Sewasewer
  ሁለት ሴተላጤዎች ጡረታ እንደተገለሉ የዶሮ ርቢ ጣቢያ ሲከፍቱ ይነሳሉ ከዚያም ዶሮዎቹን የሚሸጥላቸው ሰው ዘንድ ይሄዱና ሁለት መቶ ሴት ዶሮዎችና ሁለት መቶ አውራ ዶሮዎችን እንዲሸጥላቸው ይጠይቁታል። ሆኖም ባለቤቱ ፈገግ ብሎ “እመቤቶቼ ለሁለት መቶ ዶሮዎች ሁለት መቶ አውራ ዶሮዎች አያስፈልጓችሁም። ጥቂት አውራ ዶሮዎች ብትገዙ ለርቢ ይበቃሉ” አላቸው። 

  "አለማስፈለጋቸው ይገባናል ወዳጄ” አሉ አንደኛዪቱ ፈጠን ብለው። “ሆኖም የብቸኝነትን አስከፊነት በሚገባ ስለምናውቀው ጓደኞች እንዲያጡ አንሻም” ሲሉ መለሱ።

  ምንጭ:
  ቀልዶች፣ በአረፋይኔ ሃጎስ እና ኤፍሬም እንዳለ
 • loader Loading content ...
 • Sewasewer
  ከዕለታት አንድ ቀን የታወቀው ቦክሰኛ ቢል ባሸር ምሳውን ሊበላ ሆቴል ይገባል። ከዚያም ካፖርቱን አውልቆ ከሰቀለ በኋላ ብጣሽ ወረቀት ላይ “ይህ ካፖርት የታወቀው ተደባዳቢ የቢል ባሸር ነው። እርሱም በአሥር ደቂቃ ውስጥ ተመልሶ ይመጣል” የሚል ማስታወሻ ለጥፎበት ወደ ምግብ ቤቱ ይዘልቃል። 

  ይሁንና ሲመለስ ካፖርቱ ተወስዷል። በስፍራው የጠበቀው ማስታወሻ “ኳፖርቱ በታዋቂው ሯጭ አሌክስ ተወስዷል ። እርሱም ፈጽሞ አይመለስም።” የሚል ነበር።

  ምንጭ፤
  ቀልዶች ከአረፋይኔ ሃጎስ እና ኤፍሬም እንዳለ
 • loader Loading content ...
  Load more...
loader Loading content ...

Comments (1)


loader Loading content ...