loader

Topics (147)


loader Loading content ...

Explanations (173)


 • @ህይወት በቀለ   1 year ago
  Sewasewer
  1. ለጠላና ለአበሻ አረቄ አወጣጥ የምንጠቀምባቸው እርሾዎች አንድ ናቸው
  እነርሱም 
       ሀ:- ብቅል
       ለ:- ጌሾ
  2. ብቅልን በምን እናዘጋጃለን 
      ሀ. ከስንዴ ለ. ከገብስ ሐ. ከበቆሎ 
  3. ብቅልን እንዴት እናዘጋጃለን
  - ሶስቱንም አበጥረን አላስፈላጊ የሆነውን ቆሻሻ እናስወግዳለን
  - ከዛም ሶስቱንም በተናጠል ለ24 ሰዓት ውሃ ውስጥ ነክረን እናስቀምጣለን
  - ከዛ ብኋላ የነከርንበትን ውሃ እናጠነፍፋለን
  - ያጠነፈፍነውን ሶስቱን እህሎች በጎድጓዳ እቃ የጉሎ ቅጠል ከሌለም እሱን በሚተካ እንደ (Paper Towel) ያለ በማንጠፍ ለየብቻቸው እቃዎቹ እናስቀምጣለን ላያቸውንም ሸፍነን መቀት ያለው ቦታ ማስቀመጥና ከላያቸው ከበድ ያለ ነገር መጫን
  - ከዛ በኋላ በ3ኛ ቀናቸው ሁለንም ከፍቶ ማየት
  - ውሃ አንሷቸው በጣም ከደረቁ እላያቸው ላይ ጥቂት ወሃ ማርከፍከፍና እንደገና ሸፍኖ እንደነበር ማስቀመጥ
  - በውስጣቸው ያዘሉት እርጥበት በቂ ከሆነና በደንብ ያልበቀሉ ከሆነ በደንብ እንዲበቅሉ እንደገና መሸፈንና ማስቀመጥ
  - በትክክል በቆልት መሆናቸውን ስታረጋግጡ ፀሐይ ላይ ብትንትን አድርጎ በማስጣትና በማድረቅ ወደ ዱቄትነት ቀይሮ መጠቀም ይቻላል

  ማሳሰቢያ:- ብቅልን ብቅል የሚያሰኘው በደንብ አበንቁሎ እርስ በርስ ሲያያዝ ነው
  መቀት ቦታ የምናስቀምጠው ለመብቀል ሙቀት ስለሚያስፈልገው ነው
  4. ቀጥሎም ለጠላና ለአረቄ እንደመነሻ ወይም እንደእርሾ የሚጠነሰሰው የቅጠል ጌሾ ዱቄት ነው 
  አሰራሩም
  -------
  ሀ. ከቅጠል ጌሾ ውጪ የሆኑትን ነገሮች ከራሱ የጌሾ ፍሬ ጭምር ይለቀምና ይወገዳል
  ለ. ተወቅጦ ዱቄት ይሆናል
  ሐ. እርሾ ወይም መነሻ እንዲሆን በርከት ያለ ውሃ ከጌሾ ዱቄቱ ጋር በመበጥበጥ እንዳይነፍስበት በደንብ ከድኖ ሞቅ ያለ ቦታ ለ 3 ቀን ማስቀመጥ ከዛ በኋላ እንደቅደም ተከተሉ አስፈላጊውን ሁሉ ጨምሮ በማዋሃድ በተናጠል አረቄውንና ጠላውን መስራት ይቻላል::
 • loader Loading content ...
 • @ህይወት በቀለ   3 years ago
  Sewasewer

  3) Fasil Ghebbi, Gondar Region

  In the 16th and 17th centuries, the fortress-city of Fasil Ghebbi was the residence of the Ethiopian emperor Fasilides and his successors. Surrounded by a 900-m-long wall, the city contains palaces, churches, monasteries and unique public and private buildings marked by Hindu and Arab influences, subsequently transformed by the Baroque style brought to Gondar by the Jesuit missionaries.

  for more details about this and the remaining six heritage list please visit http://whc.unesco.org/en/statesparties/et

 • loader Loading content ...
 • @ህይወት በቀለ   3 years ago
  Sewasewer

  2) Rock-Hewn Churches, Lalibela

  The 11 medieval monolithic cave churches of this 13th-century 'New Jerusalem' are situated in a mountainous region in the heart of Ethiopia near a traditional village with circular-shaped dwellings. Lalibela is a high place of Ethiopian Christianity, still today a place of pilmigrage and devotion.

  for more details please visit http://whc.unesco.org/en/list/18

 • loader Loading content ...
 • @ህይወት በቀለ   3 years ago
  Sewasewer

  1) Axum

  The ruins of the ancient city of Aksum are found close to Ethiopia's northern border. They mark the location of the heart of ancient Ethiopia, when the Kingdom of Aksum was the most powerful state between the Eastern Roman Empire and Persia. The massive ruins, dating from between the 1st and the 13th century A.D., include monolithic obelisks, giant stelae, royal tombs and the ruins of ancient castles. Long after its political decline in the 10th century, Ethiopian emperors continued to be crowned in Aksum

  for more info please see http://whc.unesco.org/en/list/15

 • loader Loading content ...
 • @ህይወት በቀለ   3 years ago
  Sewasewer
  መሰደድስ ካብሮ አደግ
  እንዳትጠፋ እንዳትበረግግ
  ካብሮ አደግስ አትሰደድ
  እንዳታብድ እንዳትነድ
 • loader Loading content ...
 • @ህይወት በቀለ   3 years ago
  Sewasewer

  በመጀመሪያ አዳም ሳተ
  ከገነትም ተጎተተ
  አዳም ከገነት ሲባረር
  እነሆ እርቃኑን ነበር
  ብርዱ፣ ውርጩ አንዘፈዘፈው
  ዶፉ፣ ጠሉ ወረደበት
  ይንዠረገገውን አይተው
  አእዋፍ አራዊት ሳቁበት
  ይሄኔ አዳም ተማረረ
  ተማረረና ተመራመረ
  ተመራምሮም አልቀረ
  ጋቢ መስራት ጀመረ
  ጅማሬውን ወደደ
  ተጀምሮ እስኪፈጠም
  የእድሜውን ግማሽ ወሰደ
  ያሳዝናል
  ጋቢውን ጨርሶ ሲቋጭ
  ገላው ብርዱን ለመደ::

  በእውቀቱ ሥዩም

 • loader Loading content ...
 • @ህይወት በቀለ   3 years ago
  Sewasewer

  ልረሣሽ እየጣርኩ ነው
  በጣራው ላይ ሲረማመድ፣የዝናቡ ልዝብ ኮቴ
  መጋረጃው ሲውለበለብ፣ሰንደቅ ሆኖ ለመስኮቴ
  ዋርካው፣ በቅጠል ጥዋ
  ውኃ ሲያቁር ፣ከህዋ
  የምድርን ጉሮሮ ሊያርስ
  መሬት ፣ፍጥረትን ስትጸንስ
  በዚህ ሁሉ ጸጋ መሀል ፣ያንችን መሄድ ስተምነው
  ምንም ነው፣ኢምንት ነው
  ልረሣሽ እየጣርሁ ነው፡፡
  መጣ፣ መጣ ፣መጣ፣ የዝናቡ ኮቴ አየለ
  ክረምት የፍጥረት መሲሕ፣ በቀጠሮው ከተፍ አለ፡፡
  ስስ የጉም አይነርግብ፣ውብ ገጽሽን ሸፋፈነው
  የርጥብ አፈር፣ርጥብ ሽታ ፣ውብ ሽቶሽን አዳፈነው
  ልረሣሽ እየጣርኩ ነው፡፡
  የዝናቡ ኮቴ ይደምቃል
  እንደ ብስል ሾላ ፍሬ፣አሮጌው ሰማይ ይወድቃል
  አዲስ ሰማይ ይነቃል
  አዲስ ጅረት ይፈልቃል
  እንኳንስ የእግርሽ ኮቴ፣ ጎዳናሽም ታጥቦ ያልቃል፡፡
  ልረሳሽ እየጣርኩ ነው፡፡


  በእውቀቱ ሥዩም 2005

 • loader Loading content ...
 • @ህይወት በቀለ   3 years ago
  Sewasewer

  እቴ
  ይስጥሽ ከቁመቴ ከላዬ ቀንሶ
  ያስረዝምሽ አንቺን እኔን አሳንሶ
  ከሰጎን እረዝመሽ ስትቆሚ ከጎኔ
  ቁመቴን መጽውቼሽ ጫጩት ላክል እኔ፤
  ይስጥሽ ከፀጉሬ ከአናቴ ላይ ዘግኖ
  ይገጠብ ራሴ ያንቺ ተጎንጉኖ
  አወይ ፀጉሯ ብለው ኮረዶች ሲያወሩ
  ድጥ ራስ ነህ ብሎ ይዝለፈኝ ሰፈሩ፤
  እቴ
  ይስጥሽ ከወዜ ላይ ጨልፎ ከፊቴ
  ይቅዳልሽ ከደሜ ጠልቆ ከጅማቴ
  ከዓይን ያውጣሽ እያለ ሲመርቅ አድናቂ
  እስቲ እግዜር ይማርህ ይበለኝ ጠያቂ።
  እቴ
  እጄን ብትፈልጊ
  እግሬን ብትፈልጊ
  አንገቴን ደረቴን
  ተሰጥኦ ሀሳቤን
  ያደምቀኛል ብለሽ ያሰብሺውን ሁላ
  እግዜር ከኔ ወስዶ ከሰጠሽ በኋላ
  ያስቀርልኝ ዓይኔን
  አንቺን ማየት ብቻ ያኖረኛል እኔን።


  ገጣሚ በእውቀቱ ስዩም

 • loader Loading content ...
 • @ህይወት በቀለ   3 years ago
  Sewasewer

  ፀሀይ ስትገባ
  ጥያቄ ይወጣል ፀሀይን ተክቶ
  ልቤም እስከንጋት ያልፈዋል ተኝቶ
  ግድ ነው በለሊት አዳፍኖ ማለፉ
  እሳትን ባመድ ሆድ ጥያቄን በን'ቅልፉ
  ከጎረምሶች ከንፈር ጪስ እየነጠቀ
  ከኮረዶች ጡት ላይ ሽቶ እየሰረቀ
  ነፋሱ ይዞራል
  ግና በምላሹ ምስጢር መች ይነግራል
  መስኮቴን ብከፍተው
  በብርድ ልብሴ ላይ ኮከቦች ፈሰሱ
  እውነትለፈለገ ውበት ነው ወይ መልሱ

  / በእውቀቱ ስዩም/

 • loader Loading content ...
 • @ህይወት በቀለ   3 years ago
  Sewasewer
  Dire Dawa in Ethiopia (the other being the capital, Addis Ababa). It is divided administratively into two woredas, the city proper and the non-urban woreda of Gurgura.
 • loader Loading content ...
  Load more...
loader Loading content ...

Comments (2)


loader Loading content ...