loader

Topics (147)


loader Loading content ...

Explanations (117)


 • @የቆሎ ተማሪ   1 year ago
  ስለምንተ ማሪያም
  እግዚአብሔር እንዲህ ይላል;- " በመንገድ ላይ ቁሙ ተመልከቱም የቀደመችዉንም መንግድ ጠይቁ መልካሚቱ መንገድ ወዴት እንደሆነች እወቁ፣ በእርሱዋም ላይ ሂዱ ለነፍሳችሁ ዕረፍትን ታገኛላችሁ።" ኤር ፮፣ ፩፮

  ፩። የቤተክርስትያን ታሪክ ትርጉም

  የቤተክርስትያን ታሪክ ማለት የክርስትና እምነት ታሪክ ማለት ነው። በቤተክርስቲይን ታሪክ ትምህርታችን የክርስትና እምነት የአምላክ መገለጥ ነው። ይሁን እንጂ በዘመንና በቦታ የተደረገ ስለሆነ መቼ፣ እንዴት እንደሆነ የምናውቅበትና በጉዞው ሁሉ የገጠሙትን ችግሮችና ምቾቶች የምንማርበት ነው።

  ፪። በቤተክርስቲያን ታሪክ ጥቅም

  • በቤተክርስቲያን ታሪክ ከአለም ታሪክ አንዱን ክፍል ይዞ ስለሚገኝ የህዝቦችን የስልጣኔ እርምጃና ታሪክ ለማጥናት ለሚፈልግ ሰው ጠቃሚ መረጃ ይሰጣል
  • አንድም ምእመናል  በቤተክርስቲያን ታሪክ ለማጥናት በሚፈልጉበት ጌዜ
   • የእምነቱን ታሪክ ለማወቅ 
   • አባቶች በየጊዜው ስላስተማሩት የትምህርት፣ የህዝብ ፀባይ እንዴት እንደተሻሻለ ለማወቅና ራሱን ለማነፅ
   • በቤተክርስቲያንን ከፍተኛነትና ጠቃሚነት ለመገንዘብና ራሱንም በእምነት ለማፅናት ከፍተኛ ጥቅም አለው።

  ፫። በቤተክርስቲያን ታሪክ ጥናት  ምንጮች

  • ብሉይ  ኪዳንና ሃዲስ ኪዳን መፀሃፍ ቅዱስ እና የትርጓሜ መፃህፍት
  • በቤተክርስቲያን ታሪክ አባቶች የፃፏቸው መፀሃፍት
  • ታሪኩ በተፈፀመበት ቦታ ተገኝተዉና ታሪኩ በተፈፀመበት ዘመን የኖሩ በቤተክርስቲያንና የዉጭ ታሪክ ፀሃፊዎች የፃፏቸው መፀሃፍት
  • በየጊዜው የተገኙ የክርስቲያኖች መቃብራት፣ መቅደሶች፣ ስእሎች፣ ገንዘቦች፣ ፀሁፎች
  • የበተክርስቲያን ትዉፊታዊ መረጃዎች  ናቸው

  ፬። በቤተክርስቲያን ዘይቤዎች ፍቺ

  በሰዋሰው አወጣጥ  " በቤተክርስቲያን" የሚለው ቃል ሶስት ትርጉም አለው።

  • "በቤተክርስቲያን " የግዕዝ ቃል ሲሆን በአማርኛ እንጠቀምበታለ። ፍቺዉም ህፃኑ፣ ሽማግሌው ወንዱ፣ ሴቱ የተማረው፣ ያልተማረው አንድ ላይ ተሰባስቦ ፀሎት የሚያደርስበት የጌታችን ቅዱስ ስጋና ክቡር ደሙ የሚገተትበት ቅዱስ ቦታ ያመለክታል።   የሐ ስራ ፳፣፪፰
  • ጌታቸን መድሃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የባሕሪ አምላክ የአለም መድሃኒት መሆኑን የሚያምኑ ሰዎች ሁሉ ቤተክርስቲያን ይባላሉ። የሐ ስራ ፭፣፩፩
  • የክርስቲያች ማህበር፣ የክርስቲያኖች ጉባዬ፣ የክርስቲያኖች ስብስባ ቤተክርስቲያን ይባላል።  ሮሜ ፩፮፣፩ 
 • loader Loading content ...
 • @የቆሎ ተማሪ   1 year ago
  ስለምንተ ማሪያም
  አንድ አምላክ እግዚአብሔር  ብቻ ነው። ከሁሉ በፊት ለዚህ አለም ፈጣሪና አስገኝ፣አሳላፊ፣ መጋቢ አለዉ። እርሱም እግዚአብሔር ነው ብሎ ማመን አለበት። ከ እግዚአብሔር በቀር ሌላ ፈጣሪ መጋቢ የለም።
   ፈጣሪ እንደሆነ መዝ ፱፱፣፫  ዘፍ ፩፣፩   ዮሐ ፩፣፫  ዮሐ ፩፬፣፩፭
  መጋቢ እንደሆነ ዘፍ ፩፣፪፱  መዝ ፩፫፭፣፪፭ መዝ ፩፬፮፣፯-፩፩  ማቴ ፮፣፪፭ -፫፫  እንዲህም ከሆነ አምላክ እግዚአብሔር ብቻ ነው።
  ሰው ሌሎች አማልክት የሚመኘው የእዉነተኛው አምላክ  የ እግዚአብሔር ሕልውና ሲክድ ነው ስለዚህ የመጀመሪያዉ ትሀዛዝ ሌሎች አማልክትን እንዳናመልክ  ብቻ ሳይሆን የእውነተኛዉን አምላክ ህልዉና መካድና አምልኮቱን መዘንጋት እንደማይገባ ያስተምረናል።  ኢሳ ፬፮፣፱ አምላክ የለም የሚል ሰው ግን መፅሃፍ ቅዱስ ዉስጥ ሰነፍ ተብሏል። መዝ ፩፫፣ ፩-፪ እግዚአብሔር ሁሉን ቻይ ነው።
                                                       አማልክት ዘበፀጋ
  መፀሃፍ ቅዱስ ቅዱሳን አማልክት ይላቸው። መዝ ፰፩፣፮  ዮሐ ፲፣፫፬  ለምሳሌ ሙሴን ለፈርሆን አምላክ አድርጌለሁ በማለት እግዚአብሔር ነግሮታል ።  ዘፀ ፯፣፩ ከዚህም ጋር ሁላችንም የ እግዚአብሔር ልጆች የመሆን ስልጣን ተሰቶናል።  ዮሐ ፩፣፩፪  ራዕ ፫፣፪፩  በቤተክርስትያናችን ቅዱሳንን እናከብራለን ይሀውም ከመጀመሪያው ትዕዛዝ ጋር የሚያጋጭ አይደለም። የ እግዚአብሔርን አክብሮት አምልኮት ለቅዱሳን አንሰጥምና እንዲያዉም ለነርሡ  የምሠጠው ክብር እግዚአብሔር ማክበር ስለሆነ በብዙ ምስጋና ለ እግዚአብሔር እናቀርባለን። ፪ኛ ቆሮ ፱ ፩፫  ስለዚህ ቅዱሳንን ማክበር ከ እግዚአብሔር ዉጭ ልዩ አምልኮት አለመሆኑን መገንዘብን ማስገንዘብ ያስፈልጋል።
  ሌሎች አማልክት የተባሉ
  ሰው  እንደ እግዚአብሔር የሚያያቸውና ብቻቸውን የ  እግዚአብሔር ባሕርይ የሚሰጣቸው ነገሮች ሁሉ አማልክት ሊሆኑ ይችላሉ።
  • ገንዘብ                   ማቴ ፮፣፪፬   ፩፱፣፪፪  የሐ ሥራ  ፭፣፩
  • የሰው ኃይል             ኤር  ፩፯፣፭
  • የሰው ጥበብ / እዉቀት    ኤር ፱፣፪፫
  • ራስ ወዳድነት               ፊል ፫፣፩፱
  • የምንታመንባቸው  ሰዎች    መዝ ፩፬፭፣፫
  • አባት እና እናት      ማቴ  ፲፣፫፯
  • ጌጣጌጥ            ዘፍ ፫፭፣፪-፬
  • ተድላ /ደስታ     ፪ኛ ጢሞ ፫፣፬
  • የጠቀረፀ  መስል   የሐ ሥራ ፲፣፩-፮

  አምላክ ሲባል እምነት ተስፋን ፍቅርን በአምላክ ላይ መጣል ነው። እምነቱ ተስፋዉን ፍቅሩን ከ እግዚአብሔር ላይ አንስቶ በሌሎች አማልክት ላይ ሲጥል ነው ሌላ አምላክ አመለክ የሚባለው። ሌሎች አማልክትም አይሁንልህ ሲባል እምነትና ተስፋ ፍቅር ከ እግዚአብሔር በቅር በሌሎች ላይ አይሁኑ ማለት ነው። አምልኮት በተግባር የሚዉለው በሚከተሉት ነገሮች ነው።

  • በስግደት
  • መስዋት
  • ፀሎት
  • ዉዳሴ
  • መገዛት
  • ፍርሃት ወዘተ

  በመጀመሪዉ ትዕዛዝ መሰረት እነዚህ ነገሮች ከ እግዚአብሔር በቀር ሌሎች አማልክት ማድረግ ተገቢ አይደለም። አለመከተልና አለማምለክን ብቻ ሳይሆን  እግዚአብሔርን ማምለክ በሚደረገው ህብረት አምላኮ በግል በምንፈፅመው ለ እግዚአብሔር ታዛዥነታችንን ልንገልፅ ይገባናል። ኢሳ ፬፬፣፭   እግዚአብሔርን እያመለኩ በሌላ በኩል ሌላ አምላክ መከተል ደግሞ እጅግ የከፋ ሃጢያት ነው። በኤልያስ ጊዜ ሶስት አመት ከመንፈቅ ድርቅ የሆነዉ የባቢሎን ምርኮ የሆነው በዚህ ሃጢያት ምክንያት ነው። ፩ኛ ነግ ፩፰፣፩፮-፪፬ ኤ ር ፩፩፣፱-፩፬ 


 • loader Loading content ...
 • @የቆሎ ተማሪ   1 year ago
  ስለምንተ ማሪያም
  • ልጅ ከወለዱ ከአንድ ቀን ወይም ከዚያ በኋላ ይጀምራል።
  • በመጀመሪያ ትኩሳት መጠነኛ ይሆንና እየቆየ እየጨመረ ይሀዳል።
  • መጥፎ ጠረን ያለው ፈሳሽ ከማህፀን ይወርዳል።
  • ዉጋትና የደም ፈሳሽም ሊኖር ይችላል።

  ምንጭ:  ሃኪም በሌለበት  ከ ዴቪድ ወርነር  ትርጉም ጠና አበረ  
 • loader Loading content ...
 • @የቆሎ ተማሪ   1 year ago
  ስለምንተ ማሪያም
  • ድካም፣ ራስ ምታትና የአጥንት ህመም በማስከተል ቀስ በቀስ ይጀምራል።
  • ማታ ማታ ትኩሳትና ላብ የተለመደ ይሆናል።
  • ትኩሳቱ ከጥቂት ቀናት በኋላ የሚመለስ ቢሆንም ለጊዜው ይጠፋል።
  • ይህ ሁኔታ ለወራት ወይም ለዓመታት ሊዘልቅ ይችላል።

  ምንጭ:  ሃኪም በሌለበት  ከ ዴቪድ ወርነር  ትርጉም ጠና አበረ  
 • loader Loading content ...
 • @የቆሎ ተማሪ   1 year ago
  ስለምንተ ማሪያም
  • በወጣቶችና በልጆች ላይ አዘውትሮ ይታያል።
  • የመጋጠሚያዎች ህመም ያመጣል።
  • ሃይለኛ ትኩሳትም ይከተላል።
  • ከጉሮሮ መቁሰል በኋላ ይይዛል።
  • የደረት ዉጋትና የጥንፋሽ ማጠር ሊኖር ይችላል።
  • ወይም ከቁጥጥር ዉጭ የሆነ የእጅና የእግር መንቀጥቀጥ ሊያደርስ ይችላል።

  ምንጭ:  ሃኪም በሌለበት  ከ ዴቪድ ወርነር  ትርጉም ጠና አበረ  
 • loader Loading content ...
 • @የቆሎ ተማሪ   1 year ago
  ስለምንተ ማሪያም
  • ላይ በላይ የሚያስቃስት ፈጣን አተነፋፈስ አለዉ።
  • ትኩሳት በፍጥነት ይጨምራል ።
  • አረንጓዴ፣ቢጫ ወይም የደም አክታ ያሚያስተፋ ሳል ይኖረዋል።
  • የደረት ዉጋት ሊኖረው ይችላል።
  • ግለሰቡ ከባድ ህመም ይታይበታል።

  ምንጭ:  ሃኪም በሌለበት  ከ ዴቪድ ወርነር  ትርጉም ጠና አበረ  
 • loader Loading content ...
 • @የቆሎ ተማሪ   1 year ago
  ስለምንተ ማሪያም
  • ህመምተኛው የምግብ ፍላጎት አይኖረውም። 
  • ምግብ መብላት ወይም ሲጋራ ማጨስ አይፈልግም
  •  ማስታወክ ያሰዋል
  •  ዐይኖቹና ቆዳው ቢጫ ይሆና
  •  ሽንቱ ቢጫ ወይም ጥቁር ሻይ ይመስላል። 
  • ሠገራዉ ነጭ ይሆናል።
  • አንዳንድ ጊዜ ጉበቱ ያብጥና የህመም ስሜት ይፈጥራል ።
  • መጠነኛ ትኩሳት ይኖራል።
  • ከባድ የድካም ስሜት ይታይበታል።

  ምንጭ:  ሃኪም በሌለበት  ከ ዴቪድ ወርነር  ትርጉም ጠና አበረ  
 • loader Loading content ...
 • @የቆሎ ተማሪ   1 year ago
  ስለምንተ ማሪያም
  ከታይፎይድ ጋር ይመሳሰላል። ሰውነት ላይ የሚታየው ሽፍታ የመገሽለጥ ምልክት ከመኖሩ በስተቀር የኩፍኝ ሽፍታ ይመስላል።


  ምንጭ:  ሃኪም በሌለበት  ከ ዴቪድ ወርነር  ትርጉም ጠና አበረ  
 • loader Loading content ...
 • @የቆሎ ተማሪ   1 year ago
  ስለምንተ ማሪያም
  ልክ እንድ ጉንፋን ይጀምራል ። ትኩሳት እያለ  የደም ስር ትርታ ዝግተኛ ይሆናል። አንዳንድ ጊዜ ተቅማጥና ድርቀት ሊኖረው ይችላል። የሰውነት መንቀጥቀጥና የተደናገረ አስተሳሰብ (ቅዥት) ይኖራል። በጣም የመታመም ሁኔታ ይታያል።

  ምንጭ:  ሃኪም በሌለበት  ከ ዴቪድ ወርነር  ትርጉም ጠና አበረ
 • loader Loading content ...
 • @የቆሎ ተማሪ   1 year ago
  ስለምንተ ማሪያም
  ድክምክም በማድረኛ ብርድ ብርድ በማለት እያንቀጠቀጠ ሳለ  ትኩሳት ድንገት ይጨምራል። ትኩሳቱ በየሁለተኛው ወይም ሶስተኛው ቀን ይመላለሳል ። በመሃሉ ከሞላ ጎደል በሽተኛዉ ፋታ ያገኝና ጤነኛ ይመስላል። 

  ምንጭ:  ሃኪም በሌለበት  ከ ዴቪድ ወርነር  ትርጉም ጠና አበረ
 • loader Loading content ...
  Load more...
loader Loading content ...

Comments (9)


 • @የቆሎ ተማሪ   1 year ago
  ስለምንተ ማሪያም
  ማለፊያ ጽሑፍ!
 • @የቆሎ ተማሪ   2 years ago
  ስለምንተ ማሪያም
  ከላይ የተጠቀሱት ንጉስ ቅዱስ ላልይበላል በላሊበላ ከተማ ከቋጥኝ ፈልፍሎ የሰራቸዉ ሲሆን በኢትዮጵያ የሰራቸዉ ግን ወደ ፳፫ ይደርሳሉ።
  ላል ማለት በእገዉኛ ንብ ማለት ነዉ::
 • @የቆሎ ተማሪ   3 years ago
  ስለምንተ ማሪያም
  ፍልስፍና የሚለው ቃል ከግሪኩ «Philos» /ፊሎስ/ ማለትም ፍቅር እና፣ «sophos» /ሶፎስ/ (ጥበብ) የተገኘ ውሁድ ነው። በቀጥታው የጥበብ ፍቅር ወይም ፍቅረ ጥበብ ተብሎ ሊተረጎም ይችላል። በመሆኑም ፍልስፍና እውቀትን፣ እውነትን፣ ጥበብን መውደድ፣ መሻት፣ መመርመር ተብሎ ሊተረጎም ይችላል። ይህ የጥናት ክፍል በዋናነት ነገሮችን በመላምታዊ መንገድ ለመመርመር ይሞክራል።
 • @የቆሎ ተማሪ   3 years ago
  ስለምንተ ማሪያም
  አመሰግናለሁኝ @ ቀዮ ። ግን አንተ ያልከው አባባል ይመስለኛል(ማለት በተለምዶ የሚነገር ማለት ነው) ነገር ግን ትክክለኛ ትርጉም ነው ብዬ አላምንም። ስለዚህ አንተ ሃገር ቤት ስለሆንክ የአማርኛ መዝገበ ቃላት ፈልግና ትክክለኛዉን ንገረን ። ተሳስቼ ከሆነ እታረማረሁኝ። ትክክለናውን ትርጉም ካገኘን በኋላ በተለምዶ አባባል ብለን እናስተካክለዋለን።
 • @የቆሎ ተማሪ   3 years ago
  ስለምንተ ማሪያም
  ምሳሌው፥ ወፍ ልጆቿን በአፏ እንደምትመግብ ለማጠየቅ ሲሆን
  ትርጉሙ ግን፥ ሰው ከራሱ ተርፎ ባለ ነገር እንጂ የሱን በሚያጎድል ነገር ደግ አይደለም ለማለት ነው
 • @የቆሎ ተማሪ   3 years ago
  ስለምንተ ማሪያም
  አንድም፥ ቅኔ፡ ማለት፥ 'ተቀንየ'፡ ሙሾ፡ አወጣ፥ ግጥም፡ ገጠመ፥ አራቆ፡ ተናገረ፥ አዜመ፥ አንጐራጐረ፥ መራ፥ ዘፈነ፡ ካለው፡ የወጣ፡ ጥሬ፡ ዘር፡ ነው። ስለዚህ፥ ቅኔ፡ ማለት፥ ባጪሩ፥ ጠቅላላ፡ ትርጕሙ፥ ሰው፡ ከራሱ፡ አንቅቶ፡ ለእግዚአብሔር፡ ዐዲስ፡ ምስጋና፡ ላቅርብ፡ ባለ፡ ጊዜ፥ ምሳሌ መስሎ፥ ምስጢር፡ አሻሽሎ፡ ግጥም፡ በመግጠም፥ የልቡናውን፡ ዕውቀት፣ የአእምሮውን፡ ርቀት፡ የሚገልጽበት፥ የዕውቀቱን፡ ደረጃ፡ የሚያስታውቅበት፥ የሰሚንም፡ ልቡና፡ የሚያነቃቃበትና፡ የሚያራቅቅበት፡ ድርሰት፡ ማለት፡ ነው።
 • @የቆሎ ተማሪ   3 years ago
  ስለምንተ ማሪያም
  ቅኔ ማለት፡ 'ቀነየ' ፡ገዛ፡ ካለው፡ ግስ፡ የተገኘ፡ ጥሬ፡ ዘር፡ ነው። ወይም፡ 'ቀነየ' ፡ገዛ፡ የሚለውን፡ አንቀጽ፡ ያስገኘ፡ ጥሬ፡ ዘር፡ ነው። ፍችውም፡ 'መገዛት'፡ ማለት፡ ነው።
 • @የቆሎ ተማሪ   3 years ago
  ስለምንተ ማሪያም
  “ደብተራ” ማለት የዜማና የቅኔ ሊቅ ማለት ነው። ስያሜው የተወሰደው ከብሉይ ኪዳን ነው። ሌዋውያን የእግዚአብሔር ታቦተ ሕግ በሚያድርበት በደብተራ ኦሪት ሆነው በዝማሬና በሽብሸባ ፈጣሪያቸውን ያመሰግኑ ነበር። በኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያንም በቅኔ ማኅሌት ቆሞ ለረጅም ሰዓታት ቃለ እግዚአብሔር እየተናገረ ሳይደክምና ሳይሰለች ፈጣሪውን በዜማና በቅኔ የሚያመሰግን ሊቅ ደብተራ ይባላል።
 • @የቆሎ ተማሪ   3 years ago
  ስለምንተ ማሪያም
  በጥምቀት ቀን አይፆምም፣ ለምሳሌ የጥምቀት ቀን እሮብና አርብ እንኳን ቢዉል አይፆምም።
loader Loading content ...