loader

Topics (30)


loader Loading content ...

Explanations (30)


 • @Becky   2 weeks ago
  We all die. The goal isn't to live forever, it's to create something that will.

  ወይራ ዘይት ከወይራ ዛፍ ቅባታማ ፍሬ የሚዘጋጅ ሲሆን 75 - 80% ውሃ፣ 11 - 15% ስብ፣ 4 - 6% ካርቦሃይድሬት፣ እና በትንሹ ፕሮቲንም ይይዛል።

  -     የወይራ ዘይት ጤናማ በሆኑ ሞኖአንሳቹሬትድ (Monounsaturated) ስቦች የተሞላ ነው

  -     ከፍተኛ የአንቲኦክሲደንትስ (Antioxidants) መጠን አለው

  -     ጠንከር ያለ የፀረ-ማቃጠል (Anti-Inflammatory) ባህሪያት አሉት

  -     ስትሮክን (Strokes) ለመከላከል ይረዳል

  -     የወይራ ዘይት የልብ በሽታን ይከላከላል

  -     የወይራ ዘይት ለክብደት መጨመር ሆነ ከመጠን በላይ ለሆነ የሰውነት ክብደት አስተዋጽዎ የለውም

  -     የአልዛይመር (Alzheimer’s) በሽታን ለመዋጋት ይረዳል

  -      አይነት 2 የስኳር በሽታ (Type 2 Diabetes) ተጋላጭነትን ለመቀነስ ይረዳል

  -     የወይራ ዘይት የያዘው አንቲኦክሲደንትስ (Antioxidants) የፀረ-ካንሰር ባህሪያት አሉት

  -     የወይራ ዘይት (Rheumatoid Arthritis) ለመንከባከብ ሊረዳ ይችላል

  -     የፀረ-ባክቴሪያ ባህሪያት አሉት

 • loader Loading content ...
 • @Becky   2 months ago
  We all die. The goal isn't to live forever, it's to create something that will.

  ቴምር ፋይበር፣ ካርቦሃይድሬት፣ ፕሮቲን፣ ቫይታሚን ቢ6፣ ፎሌት፣ ፖታሺየም፣ ማንጋኒዝ፣ ማግኒዝየም እና ኮፐር ያሉት ሲሆን የሚከተሉትን የጤና ጥቅማ ጥቅሞች ይሰጠናል፦


  • ድርቀት ለማስወገድ፣ ጤናማ የአንጀት እንቅስቃሴ እንዲኖረን እና ተቅማጥን ለማስወገድ የረዳል
  • ለአጥንት ጥንካሬ፣
  • ለደም ማነስ፣
  • ኃይልን ለማግኘት፣
  • የነርቭ ጤንነትን ለመጠበቅ
  • የልብ ጤንነትን ለማበረታታት እንደ ስትሮክ እና የመሳሰሉ የልብ በሽታዎችን በመከላከል
  • በፍጥነት ከመጠጥ ስካር ለመንቃት ይረዳል
  • የሆድ ካንሰርን ለመከላከል እና የአንጀት በሽታን ለማዳን ይረዳል 
 • loader Loading content ...
 • @Becky   2 months ago
  We all die. The goal isn't to live forever, it's to create something that will.

  • አቮካዶ ድንቅ የሆነ ገንቢ ምግብ ሲሆን ጤናማ ከሚባሉት የምግብ ዓይነቶች አንድ ነው(ቫይታሚን ኬ፣ ሲ፣ ቢ5፣ ቢ6፣ ኢ፣ ፖታሺየም እና ፎሌት ያካትታል)
  • አቮካዶ ከሙዝ የበለጠ ፖታሺየም አለው
  • አቮካዶ ለጤናማ ልብ የሚሆን ሞኖሳቹሬትድ ፋቲ አሲድ (Monounsaturated Fatty Acids) እና ፋይበር (Fiber) ክምችት አለው
  • አቮካዶ መመገብ የኮሌስትሮል (Cholesterol) እና ትራይግላይስራይድ (Triglyceride) ደረጃን ለመቀነስ የረዳል
  • የአቮካዶ ቅባት የሌላ ተክሎች ምግብ ንጥረነገሮችን ሰውነታችን እንዲቀበል ለማድረግ ይረዳል
  • አቮካዶ ለዓይን ጤንነት የሚጠቅም አንቴኦክሲደንት (Antioxidants) ክምችት አለው
  • አቮካዶ ጥሩ ጣዕም ያለው ሲሆን በቀላሉ በአመጋገባችን ወይም ምግታችን ውስት ልናካትተው እንችላለን
 • loader Loading content ...
 • @Becky   2 months ago
  We all die. The goal isn't to live forever, it's to create something that will.

  ሁለቱም ፍራፍሬዎችም፣ አትክልቶችም ከዕፅዋት የተገኙ ናቸው። ስለዚህ በመካከላቸው ለመለየት አስቸጋሪ ሊሆን ይችላል። እንደ እውነቱ ከሆነ መለያየት የሚቻልበት መደበኛ መንገድ የለም። ይሁን እንጂ ዋነኛው ልዩነት የሚመነጩት ከየትኛው የእጽዋት ክፍል ነው የሚገኙት የሚለውን ከግምት ውስጥ በማስገባት ነው።


  • ፍራፍሬዎች ከአንድ ዕፅዋት የአበባ ክፍል የሚገኙ ሲሆን ብዙውን ጊዜ ዘሮች ወይም ፍሬዎች ይኖራቸዋል። አጠራጣሪ ፍራፍሬዎች፦ ቴማቲም፣ አቮካዶ፣ ቃሪያ፣ ዱባ፣ ዝኩኒ

  

  • አትክልቶች የሚገኙት ከአንድ ዕፅዋት የአበባ እንቡጦች፣ ስራ ስር፣ ወይም ቅጠሎች ነው።


  ምንም እንኳ እነዚህ መመሪያዎች የማይቀየር ህግ ነው ባይባልም፤ አብዛኛውን ጊዜ ፍራፍሬዎችን እና አትክልቶችን ለመለየት በቂ ናቸው።


 • loader Loading content ...
 • @Becky   2 months ago
  We all die. The goal isn't to live forever, it's to create something that will.

  ደጃዝማች ዑመር ሰመተር በኢትዮጵያ ሱማሌ ክልል በ1871 ዓ.ም. ካልካዩ በተባለ ቦታ ተወለዱ። በጎሣቸው ባህልና ልምድ መሠረት አስፈላጊውን ሁሉ ሲያጠኑ ኣደጉ፡፡ ለአካለ መጠን ከደረሱበት ጊዜ አንስቶ ደግሞ በአስተዳደር ውስጥ ገብተው የአገር ባላባት በመሆን አገልግለዋል። መጋቢት 5 ቀን 1977 ዓ.ም. በወጣው የ"አዲስ ዘመን" ጋዜጣ ከተፃፈው ለመረዳት እንደሚቻለው ከ1927 ዓ.ም. አንስቶ ጣሊያን በሶማሊያ በኩል የትንኮሳ ጦርነት ስታደርግ የኢትዮጵያ ድንበር እንዳይጣስ ይከላከሉ ከነበሩት አንዱ ደጃዝማች ዑመር ሰመተር ናቸው፡፡ አንድ ጊዜ በኢትዮጵያና በጣሊያን መካከል በኦጋዴን ድንበር የተከሰተውን ችግር ለመፍታት ለእርቅ በተቀመጡ ጊዜ ተወካዩ “በጣሊያን ላይ በደል የፈፀመው ዑመር ሰመተር እጁን ተይዞ ይሰጠኝ” ሲል ጠይቆ ነበር። የጣሊያን ጥያቄ ምን እንደነበር በተነገራቸው ጊዜ ”ከአፈር የሚደባልቅ ቤልጅግና ጐራዴ ይዤ ነው እጄን የማሳየው፤ ጫት ተሸክሜ የምሄድ አልምሰለው” ሲሉ መልስ መስጠታቸው ተመዝግቧል። ደጃዝማች ዑመር ሰመተር የዋናው የኢትዮጵያና የጣሊያን ጦርነት ከመደረጉ ቀደም ብለው የደጃዝማች አፈወርቅ ወልደሰማዕት ረዳት በመሆን ገርለጉቤ በተባለ ቦታ ተዋግተው በጠላት ላይ ከባድ ጉዳት አድርሰዋል። በኋላ ግን ኤልቡር በተባለ ሥፍራ ጠላት ስድስት ባታሊዮን ጦር ይዞ ከበባቸው፡፡ አካባቢውን ለቆ ዘወር ማለት አንዱ የጦር ስልት በመሆኑ በሚያፈገፍጉ ጊዜ የተወሰኑ ወታደሮች ተማረኩባቸው፡፡ ከአምስት ወር በኋላ በ1927 ዓ.ም. ሌሊት ኃይላቸውን አጠናክረው በመሄድ ድንገተኛ አደጋ ጣሉበት። በዚህ ጥቃት ስድስቱም ባታሊዮን የሞተው ሞቶ የቀረው ተበታተነ፡፡ ብዙ መሣሪያና ቁሣቁስ ማርከው ሺላቦ በተባለ ቦታ ላይ ሠፈሩ። ከዚህ በኋላ የመሃል አማራው፣ ትግሬውና ሌላውም ከሚመሩት የሱማሌ ጦር ጋር አንድነት ሆኖ ቆራሂ ላይ ገጥመው ጠላትን ድል አደረጉት። በዚህ ጦርነት የሚዋጉበት ጥይት ባነሳቸው ጊዜ ጠላትን ሙሉ በሙሉ ለማሸነፍ የበቁት በጨበጣ ውጊያ እንደነበር ታሪካቸው ያስረዳል:: ከዚህም ወደደገሃቡር ተመልሰው የበላይ አዛዣቸውን ደጃዝማች ገብረማርያምን አኣግኝተው ተጨማሪ ወታደር ሲጠይቁ ከኦጋዴን አውራጃ እንዲመለምሉ ፈቀዱላቸው። የፊታውራሪነት ማዕረግም ሰጧቸው:: የተዋጊ ወታደሮቻቸውን አቅም ካነገቡ በኋላ እንደገና ወደ ጦርነቱ በመግባት በገርለጉቤ፣ በቆራሂና በሃነሌ የሚያስደንቅ የአርበኝነት ሙያ ፈፀሙ:: በነዚህ ጦርነቶች ሁሉ በስድስት ጥይት መቁሰላቸው ታውቋል:: ደጃዝማች አፈወርቅ በሞቱ ጊዜም ክፉኛ ቆስለው ወደጅጅጋ መጥተው ዘመናዊ ህክምና ተደርጎላቸዋል፡፡ ቁስሉ ከባድ ስለሆነ ከኢትዮጵያ በሃርጌሳ በኩል ወደ ኬንያ ወጥተው አምስቱን ዓመታት በለንደን ቆይተው ነፃነት እንደተመለሰ ወደ አገራቸው ገቡ:: ከዚያም ከቀዳማዊ ኃይለሥላሴ ፊት ቀርበው በደጃዝማችነት ማዕረግ የኦጋዴንና የጅጅጋ ገዥ ሆኑ:: ይህ ሁሉ ሲሆን በአካላቸው ውስጥ ስድስት ጥይቶች ነበሩ፡እያደር ግን ይኸው በህክምና ለማውጣት አስቸጋሪ የነበረው ጥይት ቁስሉ አመርቅዞ መጋቢት 6 ቀን 1936 ዓ.ም. በ65 ዓመታቸው አርፈው ሐረር ከተማ በሚገኘው አብዱል መካነ-መቃብር በሙሉ ወታደራዊ ሥነ-ሥርዓት ተቀበሩ፡፡ ደጃዝማች ዑመር ለኢትዮጵያን አንድነት ደከመኝ ሰለቸኝ ሳይሉ መሥራታቸውን ታሪካቸው ያረጋግጣል::


  ምንጭ፦ ታሪካዊ መዝገብ_ሰብ


 • loader Loading content ...
 • @Becky   2 months ago
  We all die. The goal isn't to live forever, it's to create something that will.

  ልዕልት ዘነበወርቅ የቀዳማዊ ኃይለሥላሴ አራተኛ ልጅ ናቸው:: የልዕልት ዘነበወርቅ ታላቅ እህትና ወንድም ልዕልት ሮማንወርቅ፣ ልዕልት ተናኘወርቅ እና ልዑል አልጋወራሽ አስፋወሰን ናቸው:: ቀዳማዊ ኃይለሥላሴ ልጆቻቸውንና የልጅ ልጆቻቸውን በአያት ቅድመ-አያቶቻቸው የመሰየም ልማድ ነበራቸው:: ልዕልት ዘነበወርቅ ኃይለሥላሴም ስማቸውን የወረሱት የመንዝ ተወላጅና የማደሬ ወገን ከነበሩት የንጉሥ ሣህለሥላሴ እናት ስም ነው:: ልዕልት ዘነበወርቅ ገና በልጅነታቸው የአፄ ዮሐንስ ልጅ የራስ አርአያ ሥላሴ የልጅ ልጅ ለሆኑት ለደጃዝማች ኃይለሥላሴ ጉግሣ ተድረው ወደትግራይ ሄዱ:: ጋብቻው ከጥንት ጀምሮ በአማራና በትግራይ መካከል የነበረው ፖለቲካዊ ጋብቻ ቀጣይ ታሪክ ነው፡፡ ልዕልት ዘነበወርቅ የሰባት ወር ነፍሰጡር እንደነበሩ በጠና ታመሙ:: በዚህ ጊዜ ጣሊያናዊው ሃኪም ልዕልት ዘነበወርቅን ለማከም ወደመቀሌ መጣ፡፡ ሃኪሙ ከመረመረ በኋላ የሚዋጥ መድሃኒት አዘዘ:: ልዕልት ዘነበወርቅን ተከትለው ከሸዋ የሄዱት የነፍስ አባታቸው ግን ሐኪሙ የሚሰጣቸውን መድሃኒት እንዳይውጡ ከለከሉ:: በመሃሉ ሁኔታውን ያወቁት ለቀዳማዊ ኃይለሥላሴ ተደውሎ ተነገራቸው:: በዚህ ጊዜ ቀዳማዊ ኃይለሥላሴ ጣሊያናዊ ሃኪም ያዘዘውን መድሃኒት ተቀብለው እንዲውጡ ትዕዛዝ አስተላለፉ፡፡ ልዕልት ዘነበወርቅ የታዘዘውን መድሃኒት ሲውጡም ህመማቸው የባሰ ጠንቶ ባቸው የህይወታቸው ፍፃሜ ሆነ፡፡ የልዕልት ዘነበወርቅ አስከሬንም በአውሮፕላን ተጉዞ ሥርዓተ-ቀብራቸው በአዲስ አበባ ከተማ ተፈፀመ:: በወቅቱ ለወጣቷ ለልዕልት ዘነበወርቅ መሞት ምክንያቱ ጣሊያናዊው ሃኪም እንደሆነ ተደርጉ ተወርቷል::


  በኋላም ለልዕልት ዘነበወርቅና ለአማታቸው ለደጃዝማች ጉግሣ አርአያ ተከታትሎ መሞት የጣሊያን እጅ አለበት እየተባለ ተዕፏል። አሟሟታቸው አሳዛኝ በመሆኑም በመላው ኢትዮጵያ የተደረገው ሃዘን የበረታ ነበር፡፡ በመጨረሻም ዝክረ ነገር በተባለው መፅሃፍ ተገልፆ የሚገኘውን የሚከተለውን አዋጅ በማሳወጅ ቀዳማዊ ኃይለሥላሴ የሚደረገው ሃዘን እንዲቆም ጠየቁ፡፡ “አሁን ዛሬ በልጄ በዘነበወርቅ ሞት ሃዘን የፀናብኝ ስለሶስት ነገር ነው:: አንደኛው በህፃንነቷ፣ ሁለተኛው በአዲስ ሙሽራነቷና ሶስተኛው ነፍሰጡር ሆና ሳትገላገል በመሞቷ ነው:: እነዚህ እጅግ የከበዱ ሶስት ነገሮች በአንድ ጊዜ ስለደረሱብኝ ሃዘኔን እያፀናሁ ብቆይ እወድ ነበር፡፡ ነገር ግን በአንድ ወገን ፅኑ ሐዘን አድርጐ መቆየት ተስፋ የሌላቸውን አህዛብን መምሰል ነው ተብሎ በመፅሃፍ መከልከሉን ስላወቅሁ በሁለተኛውም ወገን ለእናንተ ለሁላችሁም የጉዳት አብነት (ምሳሌ) ማሳየት የማይገባኝ መሆኑን ስላወቅሁ ሃዘኔን ትቼዋለሁ:: የሰውን ሌላውን ኣካሉን ቢመቱት ስለባህርዩ አንድነት ያልተመታው ዓይኑ ለማልቀስ ግዴታ ይሆንበታል፡፡ እንደዚሁም ከአካላችን የተከፈሉት ልጆቻችንና ዘመዶቻችን በፍቅርም የተዋህድናቸው ወዳጆቻችን ሲሞቱ ማዘንና ማልቀስ ለባህሪያችን ግዴታ ነው፡፡ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ እንኳን አልዓዛር በሞተ ጊዜ ስለወዳጅነቱ አልቅሶለታል:: ነገር ግን ሃዘን አብዝተን ተስፋና ትንሣኤ የሌላቸውን አህዛብን እንዳንመስል ሃዘንንም በጭራሽ ትተን ርህራሄ የሌለን ጨካኞች እንዳንሆን ሃዘናችንን በልክ ማድረግ ይገባናል" ብለዋል። ልዕልት ዘነበወርቅ በሞቱ ጊዜ እድሜአቸው ሃያ አመት አለመሙላቱን የፅሁፍ መረጃዎች ያረጋግጣሉ፡፡ ከነፃነት መልስ አዲስ አበባ ውስጥ የተቋቋመው የአካል ጉዳተኞች ሆስፒታል በስማቸው እንዲጠራ ተደርጓል፡፡

  

  ምንጭ፦ ታሪካዊ መዝገብ_ሰብ

 • loader Loading content ...
 • @Becky   2 months ago
  We all die. The goal isn't to live forever, it's to create something that will.

  ጥር 29 ቀን 1957 ዓ.ም. ታትሞ በወጣው የዛሬይቱ ኢትዮጵያ ጋዜጣ እንደተፃፈው አፄ ነአኩቶ ለአብ የዛጉዬ መንግሥት ዘር ሲሆኑ የቅዱስ ሐርቤ ሹም ልጅ ናቸው። ቅዱስ ሐርቤ ሹም ደግሞ የአፄ (ቅዱስ) ላሊበላ ታላቅ ወንድም ናቸው። አፄ ነአኩቶ ለአብ ከልጅነት ዘመናቸው አንስቶ ያደጉት በአጉታቸው በአፄ ላሊበላ እጅ ነው። አራት አመት ከአራት ወር እድሜ በሞላቸው ጊዜ አፄ ነአኩቶ ለአብ ይስሐቅ ለሚባሉ መምህር ተሰጥተው በእሣቸው እየተማሩ አደጉ፡፡ ትምህርታቸውን እንደጨረሱ የዲቁናን ማዕረግ ተቀበሉ። እድሜአቸው 20 አመት ሲሞላው አቅሌሲያ የሚባሉትን እስጢፋኖስ የተባሉ ባለፀጋ ልጅ አገቡ። ወዲያውኑ አፄ ላሊበላ የአንድ ክፍለ አገር ገዥ አደረጓቸው:: በዚያን ዘመን ንጉሠ-ነገሥቱ በሰጧቸው ሶስት የውጭ አገር የእጅ ሙያ አዋቂዎች እየተረዱ የቅድስት ማርያምን ቤተ-ክርስቲያን አነፁ። በመሃሉም ጐጃም ውስጥ ሰላም ደፈረሰና በአፄ ላሊበላ ትዕዛዝ ዘምተው ፀረ-ቅሞስ የሚባለውን አማፂ በውጊያ ማርከው በመያዝ ሮሃ ከተማ በድል ተመለሱ፡፡ ይህን የጀግንነት ሥራ በመሥራታቸውም የአፄ ላሊበላ ባለቤት እቴጌ መስቀል ክብራ ባለቤ ታቸውን ለምነው በትረ-መንግሥቱን አፄ ነአኩቶ ለአብ እንዲይዙ ተደረገ፡፡


  የፅሁፍ መረጃዎች እንደሚያረጋግጡት ልጃቸው ይትባረክ በዚያን ዘመን ሥልጣን ለመረከብ እድሜአቸው ይፈቅድ ነበር፡፡ ሆኖም ግን በጦር ሜዳ ዘምታው ጀብዱ የሠሩት ነአኩቶ ለአብ ሥልጣን ቢረከቡ ኢትዮጵያን በጠላት ሳያስደፍሩ ሊገዙ ይችላሉ የሚል እምነት በአፄ ላሊበላና በባለቤታቸው በእቴጌ መስቀል ክብራ በማደሩ ተመርጠው በትረ-መንግሥቱን ጨበጡ፡፡ አፄ ነአኩቶ ለአብ በዚህ መልኩ ሥልጣን ተረክበው ሲገዙ እንዳሉ የተለያዩ ስህተቶችን በመሥራታቸው አፄ ላሊበላና ባለቤታቸው እቴጌ መስቀል ክብራ እንደገና መክረው መልሰው ከሥልጣን እንዲወርዱ አድርገዋቸዋል፡፡ ክርስቲያናዊ ስነ-ምግባርን የሚፃረር ሥራ ሠርተ ዋል ተብለው ከተነቀፉባቸው ምግባሮቻቸው አንደኛው ዮዲት የተባለችውን የአክስታቸውን ልጅ ለጋብቻ መጠየቃቸው እንደሆነ ተፅፋል፡፡ አፄ ነአኩቶ ለአብ ይችን ወጣት ለማግባት በወሰኑ ጊዜ ዮዲት ድንግል ከላስታ ሸሽታ ሐማሴን ወደሚገኘው ሀዘጋ ወደ ተባለው አገር ሄደች፡፡ የሀዘጋ አገረ ገዥ ንጉሠ-ነገሥቱን ፈርተው እንደ ማይቀበሏት በነገሯት ጊዜ እራሷን በራሷ እንደሰዋች ታሪኳ ያስረዳል፡፡ በመጨረሻም አፄ ላሊበላ ለወንድማቸው ልጅ መስጠቱን ተውትና መልሰው ለልጃቸው ለይትባረክ በትረ_ሥልጣኑን እንደሰጡ ያስረዳል።


  ምንጭ፦ ታሪካዊ መዝገብ_ሰብ

 • loader Loading content ...
 • @Becky   2 months ago
  We all die. The goal isn't to live forever, it's to create something that will.

  ሰዓሊ ገብረክርስቶስ ከአባታቸው ከአለቃ ደስታ ነገዎ እና ከእናታቸው ከወ/ሮ አፀደማርያም ወንድምአገኝ ጥቅምት 5 ቀን 1924 ዓ.ም. በሀረር ከተማ ተወለዱ:: የሰዓሊ ገብረ ክርስቶስ ደስታ የህይወት ታሪክ እና አንዳንድ ግጥሞች በሚለው የብርሃነመስቀል ደጀኔ ጥናታዊ ፅሁፍ እንደተብራራው የሰዓሊ ገብረክርስቶስ አባት አለቃ ደስታና የአባታቸው አባት ደብተራ ነገዎ መሠረታቸው ሰሜን ሸዋ ውስጥ በአንኮበር አካባቢ ሲሆን ሁለቱም የቤተ-ክርስቲያን ሊቃውንት ነበሩ፡፡ አለቃ ደስታ ወደሀረር የሄዱትም ልዑል ራስ መኰንን ወልደ ሚካኤልን ተከትለው እንደሆነ ተብራርቷል፡፡ ገብረክርስቶስ እድሜአቸው ለትምህርት በደረሰ ጊዜ በአዲስ አበባ ሲማሩ ቆይተው በመጨረሻ በአዲስ አበባ ዩንቨርሲቲ ገብተው ለሁለት ዓመታት ተማሩ:: በመሃሉ ለከፍተኛ ትምህርት ወደጀርመን አገር በመንግሥት ተልከው በኮሎኝ የሥዕል አካዳሚ ውስጥ በመግባት ሥዕልና ግራፊክስ ተምረው አጠናቀቁ፡፡ ወደአገራቸው እንደተመለሱ በመምህርነት ሙያ ተሠማርተው እያገለገሉ ብዙ የረቂቅ አሳሳል ስልትን መሠረት በማድረግ የተሳሉ ስዕሎችን በአገር ውስጥና ከኢትዮጵያ ውጭ በሚዘጋጁ አውደርዕዮች እያቀረቡ አሳይተዋል።


  ሰዓሊ ገብረክርስቶስ ከኢትዮጵያ ውጭ አውደርዕይ ካሳዩባቸው አገሮች መካከል ጀርመን፣ ቼኮዝሎቫኪያ፣ ግሪክ፣ ስፔን፣ ጋና፣ ሶቭየት ህብረት፣ ህንድ፣ ብራዚል፣ ሴኔጋል፣ ካናዳ፣ ቤልጅግ፣ ዩጎዝላቪያ፣ ጣሊያን፣ ናይጀሪያ፣ ኮሪያና አሜሪካ ዋና ዋናዎቹ እንደሆኑ አንዳንድ የኢትዮጵያ ሠዓሊዎች አጭር የህይወት ታሪክ በተባለው መፅሃፍ ተፅፎላቸዋል። ሰዓሊ ገብረክርስቶስ በሙያቸው ላበረከቱት አስተዋፅዖ ከዓለም ሎሬት ሜትር አርቲስት አፈወርቅ ተክሌ ቀጥሎ በ1958 ዓ.ም. የቀዳማዊ ኃይለሥላሴ ሽልማት ድርጅት ተሸላሚ ለመሆን በቅተዋል፡፡ ሰኔ 24 ቀን 1955 ዓ.ም. ታትሞ በወጣው "አዲስ ዘመን" ጋዜጣ ካወጣው ዜና ለመረዳት እንደሚቻለው በግንቦት ወር 1955 ዓ.ም. በኪነ ጥበብ ት/ቤት አዳራሽ የሥዕል አውደ ርዕይ ሲያሣዩ መርቀው የከፈቱት ቀዳማዊ ኃይለሥላሴ ናቸው:: ሰዓሊ ገብረክርስቶስ ደስታ በዚህ አውደ ርዕይ ያቀረቧቸው 71 ሥዕሎች ሲሆኑ አብዛኛዎቹ ጀርመን አገር ተማሪ በነበሩ ጊዜ ከትምህርት ጋር በተያያዘ የሳሏቸው ናቸው:: ለ38 ቀናት በቆየው አውደ ርዕይ 22 ስዕሎችን ከ6,000 ብር በላይ በሆነ ዋጋ መሸጣቸው ታውቋል፡፡ ስለኢትዮጵያ የሥዕል ሙያ እድገት ተጠይቀው ሰዓሊ ገብረክርስቶስ ሲናገሩ “ሙዚየም ካልተቋቋመ የአገራችን አርት መሻሻል አይችልም፡፡ ይህም ሙዚየም በሶስት ከፍሎ ማለትም የኢንተርናሽናል የአርት ክፍል፣ ጥንታዊ የኢትዮጵያ አርት ክፍልና ዘመናዊ የኢትዮጵያ አርት ክፍል ተብሎ ሊሰየም ይችላል” ብለዋል።በውጭ ሀገር ዘመናዊ ሥዕል ምን ያህል ዋጋ እንዳለው ሲያስረዱም “እንዲህ ያለው ኢግዚቢሽን ሲደራጅ በከተማው ውስጥ ያሉ ትልልቅ ድርጅቶች ሥዕሉን ይገዛሉ፡፡ ለምሳሌ የከተማው ማዘጋጃ ቤት ወይም በከተማው ያለው ሙዚዬም ሥዕሉን ገዝቶ የሀገሩን ባህል ለጎብኝዎች ሊያስረዳበት ይችላል፡፡ ከዚህም በቀር የመንግሥት ንብረት ሆኖ መንግሥቱ ቢፈልግ ለውጭ ድርጅት ሊሽጠው ሊያከራየው ወይም በኢንተርናሽናል ኢግዚቢሽን ተካፋይ ሊሆንበት ይችላል” ብለዋል፡፡


  ሰዓሊ ገብረክርስቶስ ደስታ ሰዓሊ ብቻ ሳይሆኑ እንደሰዓሊ አገኘሁ እንግዳ ሁሉ የታወቁ ገጣሚም ነበሩ፡፡ የአገጣጠም ስልታቸው አቅጣጫ ለመመልከት ይቻል ዘንድ "ሀገሬ" ከሚለው ግጥማቸው ውስጥ ተቀንጭቦ የተወሰደውንና ቀጥሎ የቀረቡትን መስመሮች እንመልከት፡፡

  አገሬ አርማ ነው የኔነቴ ዋንጫ፣

  በቀይ የአጌጠ ባረንጓዴ ቢጫ።

  እሾህ ነው አገሬ፣

  በጀግና ልጅ አጥንት የተከሰከሰ፣

  ጠላት ያሳፈረ አጥቂን የመለሰ፡፡

  አገረ ታቦት ነው መቅደስ የሃይማኖት፣

  ዘመን የፈተነው በጠበል በፀሎት::

  ለምለም ነው አገሬ፣ ሀብት ነው አገሬ፣

  ብሞት እሄዳለሁ ከመሬት ብገባ፣

  እዚያ ነው አፈሩ የማማ የአባባ፡፡

  ባሳብ እሄዳለሁ ቢሰበርም እግሬ፣

  አስብኝ ቃጠሮ ከትውልድ አገሬ።


  ሰዓሊ ገብረክርስቶስ በሥነ-ሥዕልና በሥነ-ግጥም ፈጠራዎችና እንዲሁም በመምህርነት ሙያ ላበረከቱት አስተዋፅዖ በ1964 ዓ.ም በትምህርትና ሥነ-ጥበብ ሚኒስቴር በአርአያነት ተመርጠው ተሽልመዋል:: ሰዓሊ ገብረክርስቶስ ደስታ በ1969 ዓ.ም. በተካሄደው የእድገት በህብረት የእውቀትና የሥራ ዘመቻ ባሳዩት ንቁ ተሳትፎ በወታደራዊ አስተዳደር ደርግ መሸለማቸውን አርአያዎች በተባለው መፅሃፍ ተገልፆአል:: በ1971 ዓ.ም. ወደአሜሪካን አገር ሄደው ሲኖሩ መጋቢት 21 ቀን 1973 ዓ.ም. ኦክላሆማ በተባለው ግዛት ከዚህ ዓለም በሞት ተለይተው በዚያው ሥርዓተ-ቀብራቸው ተፈፅሟል፡፡


  ምንጭ፦ ታሪካዊ መዝገብ_ሰብ

 • loader Loading content ...
 • @Becky   2 months ago
  We all die. The goal isn't to live forever, it's to create something that will.

  ደጃዝማች ጆቴ ቱሉ በአፄ ምኒልክ ዘመን ምዕራብ ወለጋን ይገዙ የነበሩ ናቸው:: የምስራቅ ወለጋ ገዥ የደጃዝማች ሀብተማርያም ገብረእግዚአብሄር ቤተሰቦች እንደነበራቸው ቅርበት ሁሉ የደጃዝማች ጆቴ ልጆችና የልጅ ልጆች ከቀዳማዊ ኃይለሥላሴና ከሌሎች የአማራ መኳንንት ጋር የጋብቻ ዝምድና መስርተዋል። በቀዳሚነት አንደኛዋ ልጃቸው ወ/ሮ አስካለማርያም ጆቴ ለአጭር ጊዜም ቢሆን ልጅ ኢያሱን አግብተው ነበር፡፡ በኋላኞቹ ዘመናትም የልጃቸው የወ/ሮ ጃሌ ጆቴ ልጅ የሆኑት ወ/ሮ የሺእመቤት ጉማ ራስ መስፍንን፣ ሌላው የልጃቸው ልጅ ደጃዝማች ካሣ ወልደማርያም የቀዳማዊ ኃይለሥላሴን የልጅ ልጅ ልዕልት ሰብለ ደስታን፣ የልጅ ልጃቸው የሆኑት ማህፀንተ ሀብተማርያም አሁንም የቀዳማዊ ኃይለሥላሴን ልጅ ልዑል ሣህለ ሥላሴን አግብተዋል፡፡ የደጃዝማች ጆቴ ልጆች አስካለማርያም ጆቴ፣ ጃሌ ጆቴ፣ ትርፌ ጆቴ፣ መርዳሳ ጆቴ፣ ዮሐንስ ጆቴ፣ ዮሴፍ ጆቴና ጆበኔ ጆቴ የሚባሉ ሲሆኑ በንግሥት ዘውዲቱ፣ በቀዳማዊ ኃይለሥላሴና በጣሊያን ዘመንም ሳይቀር ብዙዎቹ የፖለቲካ ተሳትፎ እንደነበራቸው መረጃዎች ይጠቁማሉ፡፡ ከንግሥት ዘውዲቱ ወደቀዳማዊ ኃይለሥላሴ በተደረገው የሥልጣን ሽግግር ወቅት ከልጆቻቸው አንዱ የሆኑት ፊታውራሪ መርዳሣ ጆቴ ንቁ ተሳታፊ እንደነበሩ በታሪክ ማስታወሻ ተፅፎላቸዋል። በሪሁን ከበደ የአፄ ኃይለሥላሴ ታሪክ በተባለው መፅሃፋቸው የደንቢ ዶሎው ገዥ ደጃዝማች ጆቴ በሰላሙ ጊዜ የሹመቱ፣ የማዕረጉ፣ የግዛቱና የሽልማቱ ሁሉ ተካፋይ ሲሆኑ ኖረው አፄ ምኒልክ ለአደዋ ዘመቻ ጥሪ ባቀረቡላቸው ጊዜ አልዘምትም ብለው መቅረታቸውን ፅፈዋል። ደጃዝማች ጆቴ ከትልቁ የአደዋ ዘመቻ ሳይዘምቱ መቅረታቸው ቢታወቅም በ1996 ዓ.ም. አካባቢ በአዲስ አበባ ከተማ የሚገኙ ትልልቅ አውራ መንገዶች በታወቁ አርበኞች ስም እንዲጠራ በተደረገ ጊዜ በአራዳ አውራጃ ውስጥ ከጊዮርጊስ ወደ ምኒልክ ቤተመንግሥት የሚያመራው አውራ መንገድ በስማቸው እንዲጠራ ተደርጓል።


  ምንጭ፦ ታሪካዊ መዝገብ_ሰብ


 • loader Loading content ...
 • @Becky   2 months ago
  We all die. The goal isn't to live forever, it's to create something that will.

  ቀኝ ጌታ ዮፍታሄ ንጉሤ በኢትዮጵያ የሥነ-ተውኔት ታሪክ ከፊታውራሪ ተክለሃዋርያት ተክለማርያም ቀጥሎ ስማቸው በቀዳሚነት የሚጠቀስ ነው:: ቀኝ ጌታ ዮፍታሄ ከአባታቸው ከቄስ ንጉሤ ወልደኢየሱስና ከእናታቸው ከወ/ሮ ማዘንጊያ ወልደሄር በ1887 ዓ.ም. ጐጃም ውስጥ ደብረ ኤልያስ በተባለ አካባቢ ተወለዱ። ሐምሌ 2 ቀን 1939 ዓ.ም. ታትሞ በወጣው "ሰንደቅ ዓላማችን” በተባለው ጋዜጣ ላይ ከሰፈረው የህይወት ታሪካቸው ለመረዳት እንደሚቻለው ቀኝ ጌታ ዮፍታሄ ንጉሤ በዚያው በተወለዱበትም አገር ዜማና ቅኔ እየተማሩ አደጉ፡፡ በቤተ-ክርስቲያን ትምህርት እጅግ ምስጉን ስለነበሩ ቀኝ ጌታ የሚያሰኘውን የሽማግሌዎች ማዕረግ ገና በህፃንነታቸው ለማግኘት በቅተዋል፡፡ በ1911 ዓ.ም. ወደአዲስ አበባ መጥተው በልዩ ልዩ ክፍሎች እየተቀጠሩ ማገልገል ቀጠሉ:: ቀጥሎም በዳግማዊ ምኒልክና በተፈሪ መኰንን ተማሪ ቤት በአማርኛ መምህርነት ሲያገለግሉ ቆዩ:: ከዚያም በማስከተል በቅዱስ ጊዮርጊስ ተማሪ ቤት አስተዳደርና ርዕሠ-መምህር ሆኑ:: ኢትዮጵያ በጠላት በተወረረች ጊዜ ቀኝ ጌታ ዮፍታሄ በወለጋ በኩል አልፈው ወደሱዳን ተሰደዱ:: ከ1929 ዓ.ም. አንስቶ በዚያ ሲኖሩ ቆዩ:: በ1933 ዓ.ም. ቀዳማዊ ኃይለሥላሴን ተከትለው የሳቸውን የጉዞ ማስታወሻ እየፃፉ በጉጃም ላይ እየተዋጉ አልፈው አብረው አዲስ አበባ ገቡ። ቀኝ ጌታ ዮፍታሄ ንጉሤ በሥነ-ፅሁፍ ካበረከቷቸው ሥራዎቻቸው መካከል የላቀውን ሥፍራ የሚይዙት የተውኔትና የህብረመዝሙር ፈጠራዎቻቸው ናቸው:: ምንም እንኳን በጠላት የወረራ ዘመን ተቋርጦ የነበረ ቢሆንም ተውኔቶቻቸውን እና የህብረ-መዝሙር ግጥሞቻቸውን ፅፈው ለመድረክ ያበቋቸው ከ1919 እስከ 1935 ዓ.ም. ባለው ጊዜ ውስጥ ነው፡፡ ከቀኝ ጌታ ዮፍታሄ ንጉሤ ታዋቂ የተውኔት ድርሰቶች መካከል ቀጥሉ የተዘረዘሩት ይገኛሉ።

  1. ምስክር፣

  2. ሙሽሪትና ሙሽራ፣

  3. ጥቅም ያለበት ጨዋታ፣

  4 የሆድ አምላኩ ቅጣት፣

  5. የህዝብ ፀፀት፣

  6. ታላቁ ዳኛ፣

  7. ሙሾ በከንቱ፣

   8 አፋጀሽኝ፣

  9. ዓለም አታላይ፣

  10. እያዩ ማዘን እና

  11.አርባተ ፀሐይ ናቸው።

  በየትምህርት ቤቱ እና በመገናኛ ብዙሃን በወላጆች ቀን፣ በመዝሙር ክፍለጊዜ፣ ሰንደቅ ዓላማ ሲወጣና ሲወርድ ለህብረት የሚዘመሩ መዝሙሮችን ደግሞ በመድረስና በማዘጋጀት በዚያን ዘመን እንደቀኝ ጌታ ዮፍታሄ ንጉሤ ታዋቂ እና ተደናቂ ሰው አልነበረም ለማለት ይቻላል፡፡ ቀኝ ጌታ ዮፍታሄ ፅፈው ለመድረክ ካበቋቸው የመዝሙር ግጥሞች መካከል ቀጥሎ የተዘረዘሩት ይጠቀሳሉ።

  1. መዝሙረ ሐዋዝ ዘምስለ መስንቆ፣

  2. አብሪ ብርሃንሽን፣

  3 ኢትዮጵያ ሆይ፣

  4. የባህር ዳር ጨፌ፣

  5 ተፈሪ ማርሽ፣

  6. ድንግል አገሬ ሆይ፣

  7. አጥንቱን ልልቀመው፣

  8. ጐህ ፅባህ፣

  9. ምጣተ-እስራኤል፣

  10. ተጠማጅ አርበኛ እና

  11.ደሙን ያፈሰሰ ናቸው።


  በየመድረኩ ይቀርቡ ከነበሩት የቀኝ ጌታ ዮፍታሄ መዝሙሮች አንዱና ተማሪዎች ጠዋት ጠዋት ተሰብስበው የሚዘምሩት እንዲህ የሚል ነው::

  ደሙን ያፈሰሰ ልቡ የነደደ፣

  በአርበኝነ፡ ታጥቆ ጠላት ያስወገደ፣

  ንጉሡን አገሩን ክብሩን የወደደ፣

  ነፃነቱን ይህ መልካም ተራመደ።

  ገናናው ክብራችን ሰንደቅ ዓላማችን፣

  እጅግ ያኮራሻል አርበኝነታችን።


  ቀኝ ጌታ ዮፍታሄ ከጥቅምት 1935 ዓ.ም. አንስቶ የህግ መወሰኛ ምክር ቤት ምክትል ፕሬዚዳንት ሆነው ተሾሙ:: ቀደም ሲል በተጠቀሰው " ስንደቅ ዓላማችን” ጋዜጣ እንደተፃፈው እስከ እለተ ሞታቸው ሲያገለግሉ ቆይተዋል፡፡ ቀኝ ጌታ ዮፍታሄ ሰኞ ሰኔ 30 ቀን 1939 ዓ.ም. የተለመደውን ሥራቸውን በቢሯቸው ሲሰሩ ውለ ውና አምሽተው ከቤታቸው ገብተው ከተኙ በኋላ በማግስቱ ማክሰኞ ጧት በአልጋቸው ላይ ሞተው ተገኙ:: የአሟሟታቸው ጉዳይ አስገራሚ በመሆኑ የጤና ጥበቃ መስሪያ ቤት ጉዳዩን አጣርቶ ይገልጠዋል ተብሎ ተጠብቆ ነበር፡፡ ቀኝ ጌታ ዮፍታሄ ንጉሤ ሐምሌ 1 ቀን 1939 ዓ.ም. በቅድስት ሥላሴ ቤተ-ክርስቲያን።


  ምንጭ፦ ታሪካዊ መዝገብ_ሰብ

 • loader Loading content ...
  Load more...
loader Loading content ...

Comments (0)


  This user has no comment yet.