loader

Topics (55)


loader Loading content ...

Explanations (12)


 • @Mesfin   6 months ago
  Sewasewer
  • ማርዳ - ከወርቅ ፣ ከብር ሞለል ወይም ጠፍጠፍ ተደርጎ በአንጥረኛ እጅ የሚሰራ ፤ ከዶቃም ጋር ተሰክቶ በልጆች አንገት የሚታሰር የህፃናት ጌጥ ነው።


  • እርባን - የቀለበት አይነት
  • ድሪ - አንጥረኛ ብሩን እያቀለጠ እንደ ሰንሰለት እያደረገ የሚሰራው ፣ በጣምየቀጠነ የብር ሰንሰለት ፣ ከማተብ ጋር እየተጠመጠመ ሴቶች በአንገታቸው የሚያደርጉት የብር ፣ የወርቅ ድሪ።


   • ጠልሰም - ደብተራ ፣ ጠንቋይ በፀሎት በአይነ ጥላ ላይ ልዩ ልዩ ሐረግን ፣ የሐረግ  ቅጠልን ፣ የሰው ስእልን ፣ የእንስሳት ፣ የአራዊትን ፣ የክፉ መናፍስትን ስእል እያስመሰሉ የሚስሉት ስእል።


  ምንጭ
  ከሳቴ ብርሃን ተሰማ የአማርኛ መዝገበ ቃላት  
 • loader Loading content ...
 • @Mesfin   1 year ago
  Sewasewer
  በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ እምነት ዘንድ ከንፁህ የስንዴ እህል ፣ በንፅህና ተፈጭቶ ፣ ተለውሶና ተዘጋጅቶ በፃህል የቀረበውን ህብስትደግሞ ከንፁህ የወይን ፍሬ በንፅህና ተለቅሞ ታሽቶና ተጣርቶ በፅዋ የቀረበውን ጭማቂ ካህኑ ሁለቱንም መባዖች በቅዳሴው ፀሎት ሲባርካቸው ህብስቱ ተለውጦ ሥጋ መለኮት ፣ ወይኑ ተለውጦ ደመ መለኮት የሚሆንበት የእምነት ስርዓት ምስጢረ ቁርባን ይባላል።

  የዚህ ስርዓት መሰረቱ ኢየሱስ ክርስቶስ በእለተ አርብ በመስቀል ላይ ተሰቅሎ ለአለሙ ዘለአለማዊ ቤዛ ሆኖ ደሙን ከማፍሰሱ በፊት በነበረችው የሓሙስ ምሽት ከደቀ መዛሙርቱ ጋር በቤተ መስዋዕት ምሕረት በሾመባት ገበታ ጊዜ የሰራው ስርአት ነው። በዚያ ስርአት ኢየሱስ ክርስቶስ የቀረበለትን ኅብስት ፣ የተቀዳለትንም የወይን ፅዋ አንስቶ 'ይህ ኅብስት ስጋዬ ይሆን ዘንድ ፣ ይህም ወይን ደሜ ይሆን ዘንድ የእኔ ፈጋድ እንደሆነ የአንተም ፈቃድ ይሁን!' ለማለት 'ወደ ሰማይ ወደአባቱ አየ!' በዚህ አድራጎቱም 'እኔና አብ አንድ ነን' ባለው ቃሉ መሰረት የአብ ፈቃድ የርሱ ፈቃድ መሆኑን አረጋገጠ። 'አመሰገነ ፣ ባረከ' በሚለው ቃሉም ጌታ ኅብስቱን ወደስጋ መለኮትነት ፣ ወይኑንም ወደደመ መለኮትነት እንዲለውጥ ማድረጉን ያመለክታል።

  ኢየሱስ ህብስቱን ፈትቶ (ዛሬ ካህኑ በቅዳሴ ጊዜ ከታች ሳይለየው ከላይ ብቻ በጣቱ እየወጋ እንደሚለየው) እና  13 ቦታ ቆርሶ አንዱን ለራሱ ፣ 12ቱን ደግሞ ለ12ቱ ሃዋርያት አቀበላቸው ፤ ደሙንም በመጀመሪያ እርሱ ከቀመሰበት ከአንዱ ፅዋ እነርሱም ሁላቸውም በተራ እየተቀበሉ እንዲቀምሱ ማድረጉ ከእርሱ ጋር ለዘለአለም ይኖሩበት ዘንድ የመሰረተላቸውን የህይወት አንድነት ብቻ ሳይሆን የመከራውና የክብሩም ተካፋዮች መሆናቸውን ጭምር ለማመልከት መሆኑ እንደሆነ ስርአቱ ያስተምራል።

  ዛሬ ቀሳውስት ህዝቡን ከማቁረባቸው በፊት አስቀድመው ራሳቸው ይቆርቡና ለምእመናኑ 'ራሳችሁን ለክፋት መንፈስ በማስገዛት የሰራችሁትን ኃጥያት ያስተሰርይላችሁ ዘንድ ፣ እየራሳችሁ ላመጣችሁት ለነፍስና ለስጋ ደዌያችሁም መድሃኒት ሆኖ የፈውሳችሁ ዘንድ ፣ በኃጥያታችሁ ምክንያት ከተዳረጋችሁበት የሞት ፍዳም ድናችሁ የዘለአለምን ህይወት ትወርሱበት ዘንድ ይህን የጌታን ቅዱስ ስጋና ክቡር ደም ተቀበሉ' ብለው የሚያቆርቧቸው ይህ የጌታ ስርአት አብነት ሆኗቸው እንደሆነ የምስጢረ ቁርባን ስርአት ያስተምራል።

  ምንጭ  
  ኢትዮጵያ እና ኢትዮጵያዊነት፣ ሁለተኛ መፅሃፍ (ንቡረ ዕድ ኤርምያስ ከበደ ወልደ ኢየሱስ) 
 • loader Loading content ...
 • @Mesfin   1 year ago
  Sewasewer
  በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ እምነት መሰረት ምስጢረ ጥምቀት ከአምስቱ አእማደ ምስጢራት ውስጥ አንዱ ሲሆን 'ኢየሱስ ክርስቶስ' ተብሎ የተገለፀው ራሱ እግዚአብሄር ወልድ እድሜው 30 አመት ሲሆነው በመጥምቁ ዮሓንስ እጅ በዮርዳኖስ ወንዝ ተጠምቆ የመሰረተውን እና የቀደሰውን ስርአት የተከተለ ነው። 

  የዚህ ስርአት ምስጢር ሰው ነፍሱ በምድራዊው ኑሮዋ ገዝፋ የምትታይበትንና ለትወሰነ ዕድሜ በጊዜያዊነት የምትቆይበትን ፣ ማንነቷንና ምንነቷንም በሃይማኖታዊ አቋሟና በምግባራዊ ድርጊቷ የምትገለፅበትን አካለ ስጋ ለብሳ ከማህፀን እንደምትወለድ ሁሉ እንዲሁ በሰማያዊ ዓለም ለዘለዓለም በህይወት ለመኖር የሚያበቃትን መንፈሳዊ አካል ለብሳ ከእግዚአብሄር በመንፈስ የምትወለድበት ረቂቅ ስርአት ነው። ይህም ስርአት የተመሰረተው 'ከስጋ የተወለደ ስጋ ነው ፣ ከመንፈስም የተወለደ መንፈስ ነው!' በሚለው መለኮታዊ ቃል ነው።

  ምስጢሩ ሰው ወደእግዚአብሄር መንግስት የሚገባበት ስርአት የሚፈፀመው በጥምቀት ከውኃና ከመንፈስ ዳግመኛ ተወልዶ የእግዚአብሄር ልጅ የመሆንን ፀጋ በመቀዳጀት መሆኑን ያስተምራል። ለስርአቱ ለመብቃት ደግሞ የእድሜ ክልል የማይወስነው ሲሆን ኢየሱስ ክርስቶስ ከትንሳኤው በኋላ ደቀ መዛሙርቱን 'ወደ አለም ሁሉ ሂዱ! ወንጌልንም ለፍጥረት ሁሉ ስበኩ!' ብሎ የሃዋርያነት ተልእኮአቸውን አስታውቆ በላካቸው ጊዜ 'ያመነ ፣ የተጠመቀ ይድናል ! ያላመነ ግን ይፈረድበታል!' ያለውን የፍርድ ቃል መሰረት ያደረገ እንደሆን ይተነትናል።


  ምንጭ  
  ኢትዮጵያ እና ኢትዮጵያዊነት፣ ሁለተኛ መፅሃፍ (ንቡረ ዕድ ኤርምያስ ከበደ ወልደ ኢየሱስ)
 • loader Loading content ...
 • @Mesfin   1 year ago
  Sewasewer
  በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ሃይማኖት ዘንድ እግዚአብሔር ሰው ኾኖ ዓለሙን የማዳኑን ስራ የሚያስረዳው ትምህርት ምስጢረ ሥጋዌ በመባል ይታወቃል። ይህ ትምህርት እግዚአብሔር ከሦስቱ አካላቱ 'ወልድ' በተባለው የተለየ አካሉ ሰው ሆኖ ፍጥረቱን በተለይም ሰብአዊ ፍጥረቱን ለማዳን መወለዱን በበለጠ አጉልቶ የሚያብራራ ትምህርት ነው።

  እግዚአብሔር ወልድ በመለኮታዊ ፍቅሩና ቸርነቱ ሰው የሆነበት ምክንያት ሰብአዊ ፍጡር ከእርሱ ከፈጣሪው የተሰጠውን የህይወት መመሪያ በራሱ ምርጫ አፍርሶ በራሱ ላይ ታላቅ ጉዳትን ያስከተለበትን የዲብሎስን አገዛዝ በገዛ ፈቃዱ በመቀበሉ ከሚማቅቅበት ከክፉው የባርነት ኑሮው ነፃ ሊያወጣው፣ ከዚህ የተነሣም እየተጫነው የኼደውን የኃጢአት ቀንበር ሊሰብርለትና በዚህ ምክንያት ከተፈረደበት የሞት ፍዳ ሊያተርፈው መሆኑን ይህ ምስጢር ያብራራል።

  እግዚአብሔር ወልድ ሰው ኾኖ ወደዚህ አለም የመጣበት ምክንያት በዚህ ምስጢር (ትምህርት) መሰረት እንደሚከተለው ሊጠቃለል ይችላል።
  1. ከአዳም እና ሔዋን ጀምሮ በብሉይ ዘመን ኪዳናት አጽንቶ ያቆያትን በአምልኮተ እግዚአብሔር ላይ የተመሰረተችውን መንግስቱን በአዲሱ ኪዳን ቅዱስ ስጋውና ክቡር ደሙ አድሶ ለዘለዓለማዊነት ህልውና ሊያበቃት ነው።
  2. የመልካሙ ነገር ተቃዋሚና የሰው ጠላት የሆነው የዲያብሎስን ኃይል ከኃጢአትና ከሞት ጠንቆች ጋር ፈፅሞ አስወግዶ ፍጡሩ ሰው በዚች መለኮታዊት መንግስቱ ውስጥ ዛሬ በመንፈስ ቅዱስ በታደሰው ስጋዊ አካሉ በሚታየው አለም ላይ ፣ ኋላም በኢየሱስ ክርስቶስ በሚጎናፀፈው የትንሳኤ አካል በማይታየው አለም የዘለአላም ህይወት ወርሶ ለመኖር የሚያበቁትን ፀጋዎች ሊያስገኝለት ነው።
  3. እነዚህ ጸጋዎች ወደአማኙ ሰው ሊተላለፍ የሚችሉበትን ምስጢራትና ስርአታት ሊመሰርት ነው
  4. እኛ የእግዚአብሔር ወገኖች የሆንነው ሰዎች ስጋዊውንም ሆነ መንፈሳዊውን ህይወት በዚህ አለም በስጋ እንዴት መኖር እንደሚገባን ማለትም ዐሥሩን የእግዚአብሔር የህይወት ትዕዛዛት ልንፈጽማቸው የሚገባን እንዴት እንደሆነ ደግሞም ልንፀልይ ፣ ልንፆምና ልንመፀውት ፣ በጠቅላላም ሃይማኖታችንን በእውነተኛው መንፈሳዊ አምልኳችን አጽንተንና በንስሓ አንጽተን በበጎ ምግባር ልንገልፀው የሚገባን እንዴት እንደሆነ በአርአያነቱ ጭምር ሊያስተምረን ነው።
  5. 'እግዚአብሔር ማነው? ምንድር ነው? መልኩስ፣ ግብሩስ ምንን ይመስላል? እውነት ምንድር ናት?' ለሚሉት የሰብአዊ ፍጡር የማያቋርጡ ረቂቃን ጥያቄዎች ራሱ በገሃድና በእውን ተገልጦ ግዙፍ የሆነውን አጥጋቢ መልስ ለመስጠት ነው።

  ምንጭ   
  ኢትዮጵያ እና ኢትዮጵያዊነት፣ ሁለተኛ መፅሃፍ (ንቡረ ዕድ ኤርምያስ ከበደ ወልደ ኢየሱስ)
 • loader Loading content ...
 • @Mesfin   1 year ago
  Sewasewer
  በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ሃይማኖት እምነት ምስጢረ ስላሴ የእግዚአብሔርን አንድነትና ሦስትነት የሚያስረዳ ጥልቅ የሆነ መንፈሳዊና ሃይማኖታዊ ትምህርት ነው። መንፈሳዊና እውነተኛ፤ ዘለዓለማዊና ህያው በሆነው ህላዌውና ባህርይ፣ ረቅቆ የሚኖረው የሚሰራውና በፍጥረቱ ገዝፎ የሚታየው እግዚአብሔር ፍጡር ሊያውቀውና ሊደርስበት በማይቻለው በማንነቱና በአሳቡ ፣ በመለኮቱና በጌትነቱ ፣ በፈቃዱና በምክሩ ፤ በፈጣሪነቱ እና በባለቤትነቱ፤ በአምላክነቱ እና በመንግስቱ፤ በስልጣኑና በኃይሉ፤ በክብሩና በምስጋናው አንድ ሲሆን፤ "እግዚአብሔር አብ፤ እግዚአብሔር ወልድ፤ እግዚአብሔር መንፈስ ቅዱስ" ተብሎ በሶሥት ስም ይጠራል፤ በሦስት አካል ይገለጣል፤ በሦስት ግብር ተግባሩን ይፈፅማል።

  በዚህ ትምህርቱ መሰረትም እግዚ አብ ሔር  እንዲህ  አንድ  አምላክ  ሲሆን  በሦስት  ስም  መጠራት ፤  በሦስት  አካል  መገለጥ ና  በሦስት  ግብር  ስራውን  መፈፀም  የፈለገውና  ያስፈለገው  የህል ውናው   የህይ ወቱ  ፤  የእ ውቀቱና  የጌትነቱ ፣  የመንግስቱና  የስልጣኑ ፤  የክብሩና  የምስጋናው  ተካፋይ  እንድን ሆን  ፤  እንድናመልከውም  በመልኩ  በአ አያው  ለፈጠረን  ጥረቱ  ሁሉ  በተለይም  ለሰው  ዘለ ዓለ ማዊ  ደኅን ነትና  መልካም  ይወት  ሲል  ነው ።  ፈጣሪ  በአንድ  በእ ግዚ አብ ሔር ነቱ  ባህርይና  ህላዌ  " አብ ወይም  " አባት ብቻ  ተብሎ ና  ሆኖ  መኖር  ፤  መታወቅም  ይችል  ነበር ።  ነገር  ን  በመጀመሪያ  የማይታየውን  ረቂቁንና  የሚታየውን  ግዙፉን  ፍጥረቱን  በቃሉ  ለማስገኘት ፣  ለማስተዳደርና  ለመጠበቅ ፣  በመካከሉም  ይኸ ው  ፍጥረቱ  በተቃራኒ ው  የክፋት  ኃይል  አበጋዝነትና  በራሱ  የስ ህተት  ምርጫ  በጠፋ  ጊዜ  ሊያድነው  በአ ርአ ያው  በፈጠረው  ፍጡር  መልክ  " ወልድ ወይ ም  " ልጅ ተብሎና  ሆኖ  በስጋ  ለመገለፅ ፤  በመጨረሻም  ቦታ  ፣  ጊዜ ና  ሁነታ  ሳይወስነው  እርሱ  ፍጡሩን  ፤  ፍጡሩም  እርሱን  በቀጥ ታ  ሊያገ ና  በቀላሉ  ሊገናኝ  እንዲቻለው  " መንፈስ  ቅዱስ ተብሎ  በፍጥረተ  ዓለሙ  ሁሉ  ዘንድ  መንፈስ  ሆኖ  ለመንፈስ  ፈቃዱ  ሆነ   ይህንንም  ፈቃዱን  ፈፅሞ  እውን  አደረገው


  ምንጭ  
  ኢትዮጵያ እና ኢትዮጵያዊነት፣ ሁለተኛ መፅሃፍ (ንቡረ ዕድ ኤርምያስ ከበደ ወልደ ኢየሱስ)
 • loader Loading content ...
 • @Mesfin   1 year ago
  Sewasewer
  "ተዋሕዶ "የሚለው ቃል በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስትያን ዘንድ ከአምስቱ አዕማደ ምስጢር አንዱ በሆነው በምስጢረ ስጋዌ ላይ የተመሰረት ነው። ይህም አዕማደ ምስጢር፣ መለኮት ( አምላክነት ) እና ትስብእት ( ሰውነት ) በአካል እና  በባህርይ የመዋሓዳቸው ማለትም አንድ የመሆናቸው ነገር የሚታወቅበት ስርአተ እምነት ነው።  ይህም ውሕደት በጋለ የብረት ፍሕም ይመሰላል ። መለኮት እንደፍሕሙ፣ ትስብእት እንደብረቱ።  ብረቱ እና ፍሕሙ ሳይለያዩ ፣ ብረቱ የብረትነቱን ባህሪይ ሳይለቅ ፣ ፍህሙም የእሳትነት ባህርዩን ሳይለቅ ሁለቱም ምንነታቸውን እንደጠበቁ እርስ በርሳቸው ተጠባብቀው እንደሚገኙ ማለት ነው ። ፍሕሙ  በብረቱ  ገዝፎ  እንድሚታይ ፣  ብረቱም በፍሕሙ ግለት በሌጣ  እጅ ሊዳሰስ  እምደማይቻል  ሁሉ  እንዲሁ  ረቂቅ  መለኮትም  ይህን  ርቅቀቱን  ሳይለቅ  በተዐቅቦ  ( ባህርዩን  እንደጠበቀ  በመገኘት) ግዙፍ ስጋን ሆነ! ግዙፍ ስጋ ግዙፍነቱን ሳይለቅ በተዐቅቦ ረቂቅ መለኮትን ሆነ !  የሚለውን  የሚወክል  ነው ።

  "ተዋሕዶ" የሚለው ቃል ግእዝ እንደመሆኑ ፣ ከኢትዮጵያና ከኢትዮጵያውያን በቀር ሌላ የሚጠቀምበት አገር፣ ህዝብ፣ ሃይማኖት ወይም ቤተክርስትያን የለም። ስለዚህ የኢትዮጵያውያንን የቅዱሳን ኪዳን ሃይማኖት ከሌሎች ተለይቶ እንዲታወቅ ለማድረግ ሲባል በራሳቸው በኢትዮጵያውያን የተሠጠ ልዩ መጠሪያ ነው። 

  ምንጭ   
  ኢትዮጵያ እና ኢትዮጵያዊነት፣ ሁለተኛ መፅሃፍ (ንቡረ ዕድ ኤርምያስ ከበደ ወልደ ኢየሱስ) 
 • loader Loading content ...
 • @Mesfin   1 year ago
  Sewasewer
  የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስትያን መሰረት የሆኑ አምስት ምስጢራት አሉ። እነሱም አዕማደ ሃይማኖት ተብለው እንደሚከተለው የተዘረዘሩት ናቸው።
  1. ምስጢረ ሥላሴ
  2. ምስጢረ ሥጋዌ
  3. ምስጢረ ጥምቀት
  4. ምስጢረ ቁርባን
  5. ምስጢረ ትንሣኤ ሙታን

  እግዚአብሔር መንፈስ በመኾኑ፣ በመንፈሳዊው አእምሮና ዓይን፣ ጆሮና እጅ ካልሆነ በቀር በነፍሳዊውና በስጋዊው አእምሮና ዓይን፣ ጆሮና እጅ ብቻ ሊታሰብና ሊታይ፣ ሊሰማና ሊዳሰስ ስለማይቻል ትምህርቱና እውቀቱ "ምስጢር" ተባለ። ምስጢር የተባለበት ምክንያት በሚከተሉት ሦስት ቁም ነገሮች በበለጠ ይብራራል።
  1. የእግዚአብሔርን የአንድነትና የሦስትነት ነገር፣ ቀጥሎ ከሦስቱ አካላት አንዱ ሰው የመሆኑ ነገር፣ እንዲሁም ሰው ከእግዚአብሔር በመንፈስ የመወለዱን ነገር፣ ደግሞም ሰው የሆነውን አምላክ ስጋውን በመብላትና ደሙን በመጠጣት በእግዚአብሔር መንግስት ለዘለአለም ሕያው ሆኖ የመኖርን ነገርና በመጨረሻም ሰው ለዘላለማዊው ህይወት ወይም ሞት በማይበሰብስ አዲስ አካል እንደገና የመነሳቱን ነገር የሚያስረዳ ጥልቅ የሆነ መንፈሳዊና ሃይማኖታዊ ትምህርት በመሆኑ ነው።
  2. ትምህርቱና እውቀቱ እንደስጋዊ ትምህርትና እውቀት ተፅፎ የሚቀርብና ተነቦ የሚጠና፣ በስጋዊው ቁሳቁስ ግዙፍ ማስረጃነት እየተደገፈ የሚሰጥ ሳይሆን በአንድ ወገን ከሃይማኖታዊና መንፈሳዊ ልቦና በእውነተኛ አምልኮ ፈልቆ የሚናገሩትና የሚያስተምሩት፣ በሌላው ወገን ደግሞ በእውነተኛ ፍላጎት በተመሰረት ሃይማኖታዊና መንፈሳዊ ልቦና ሆነው የሚሰሙትና የሚማሩት ረቂቅ የእግዚአብሔር ነገር ስልሆነ ነው።
  3. ለማያምኑ የማይገለጥ የተቆለፈ የብረት ሣጥን፣ ለሚያምኑ ግን በእውነተኛው መንፈሳዊና ሃይማኖታዊ የእውቀት ቁልፍ ከፍተው በዚያው በፍፁም ብርሃን ካዩት በኋላ አክብረው የሚጠብቁት "የማይጠፋ እንቁ" በመሆኑ ነው።

  ምንጭ 
  ኢትዮጵያ እና ኢትዮጵያዊነት፣ ሁለተኛ መፅሃፍ (ንቡረ ዕድ ኤርምያስ ከበደ ወልደ ኢየሱስ) 
 • loader Loading content ...
 • @Mesfin   1 year ago
  Sewasewer
  "ቅድስት ሥላሴ" የሚለው ስያሜ የእግዚአብሔር የአንድነቱና የሦስትነቱ ምስጢር መገለጫ ነው። ይኸውም "ቅድስት" የእግዚአብሔር አንድነቱን፣ "ሥላሴ" ሦስትነቱን ያመለክታል። "ቅድስት" ለአንዲት ሴት በነጠላ ቁጥር የሚሰጥ ሲሆን፣ "ቅዱስ" ደግሞ ለአንድ ወንድ በነጠላ ቁጥር የሚሰጥ ተነፃፃሪ አንቀፅ ነው። መውለድ ለሴት ነውና፣ ኢየሱስ ክርስቶስ ባገኘነው ፀጋ እግዚብሔር አብ እኛን ሰዎችን በምስጢረ ጥምቀት ከውኃና ከመንፈስ ቅዱስ ወልዶን የዘለዓለም ልጆቹ ስላደረገን "ቅድስት" የሚለው ቅፅል ተሰቶታል።

  ምንጭ
  ኢትዮጵያ እና ኢትዮጵያዊነት፣ ምስጢረ ሥላሴ (ንቡረ ዕድ ኤርምያስ ከበደ ወልደ ኢየሱስ)
 • loader Loading content ...
 • @Mesfin   1 year ago
  Sewasewer
  1. እህል በእህል- በቀድሞ ዘመን ኢትዮጵያውያን በእህል በከብት ቢበለፅጉም የገንዘብ ችግር ስለነበረባቸው በገንዘብ ከሚገበያዩ ይልቅ አንዱን ነገር በአንዱ መለወጥ ይቀላቸው ነበር። ለምሳሌ ቃሪያ (በርበሬ) በገንዘብ ከሚገዙ በእህል፣ በሱፍ፣ በስንዴ፣ በልዩ ልዩ ጥራ ጥሬ ይለውጡ ነበር፤ ለምሳሌ ጤፍን በምሥር፣ ሌላውን እህል ወይም ተክል እንዲሁ እንደተፈላጊነቱ ይለዋወጡ ነበር። እንደጊዜው ሁኔታ አንድ ጊዜ እኩል ለእኩል ይለዋወጣሉ፤ አንዳንድ ጊዜም ደግሞ አንዱ ይወደድና 3 ለ 1 ወይም እንዲህ እየተባለ ይለዋወጣሉ። በጠቅላላው ኢትዮጵያውያን ሁሉ በዚህ መልክ ይገበያዩ ነበር፤ የቀረው ቀርቶ ጥጡ ሳይቀር በእህል፣ እህሉም በጨው ይለወጥና ይገዛ ነበር። 
  2. ው - እህል በእህል ከሚለወጠው ጋር በሁሉም ዘንድ የታወቀው የወል ዋጋ የነበረው፣ እንደዛሬ ብር በኢትዮጵያ ዋጋ ሆኖ የታወቀው ጨው ነበር። ማለት እያንዳንዱ ሰው ብዙ ሊያተርፍ የሚቻለው በጨው የነገደ ሲሆን፣ ውድ የሆነውን ነገር ሁሉ የሚገዛ በጨው ነበር። እዳም ቢኖርበት የሚከፍለው በጨው ነበር፤ የቀረው ቀርቶ ባርያ ይሸጥበት በነበረ ጊዜ እንኳን በዚህን ያህል ጨው የተገዛ ባሪያ እየተባለ የነገር ነበር። የጨውም የዋጋ ግምት የተለያየ ደረጃ ነበረው፤ ማለት ዝቅተኛው አይነት "እየሌ" እየተባለ ይጠራ ነበር። ከዚያም ቀጥሎ የነበረው "ልመደው" የተባለው ከባድ አይነት ጨው ነበር። የመጨረሻው ደግሞ "ጋንፋር" የተባለ ነበር። የሆነ ሆኖ፣ ከነዚህም ውስጥ እየተሸረፈ "ግማሽ እየሌ" "ግማሽ አሞሌ" እየተባለ ይሸጥበት ወይም ይገዛበት ነበር።
  3. ጥይት - የብር ያህል ዋጋ ኑሮት ሁሉም ደስ ብሎት የገበያይበት ይለዋወጥበት የነበረ ልዩ ልዩ ዋጋ የነበረው ጥይት ነው። ስለዚህ ለሳበው ጠበንጃ ከሚያገለግለው ባሩድ ጀምሮ፣ የወጡትን ጠበንጃዎች ጥይቶች ሁሉ እንደ አይነታቸው፣ እንደ ተወዳጅነታቸው ዋጋ ነበራቸው፤ ይሸጡባቸው ይገዛባቸውም ነበር። እንዲያውም ከሌላው አይነት ማለት ጨውን ከመሰለ ዋጋ ይልቅ ጥይት ለአያያዝ ተስማሚ ስለሆነ፣ ከእህልና ጨው ይልቅ በጥይት መሸጥ ይወዱ ነበር። ምክንያቱም በአንድ በኩል ላያያዙ ይመቻል፣ ሁለተኛ የጦርነት ጊዜ ስለነበር በየጠረፉ ጠላት ስለሚያስቸግር፣ አንዱ ጎሳም ከሁለተኛው ጋር መጋጠም እንደ ጉብዝና ስለሚቆጠር ማንኛውም ኢትዮጵያዊ ጠበንጃ መያዝና ጥይት መግዛት ይወድ ስለነበር ጥይት በጣም ውድ ዋጋ የነበረው፣ ለመሸጥም ለመግዛትም ትንሹም ትልቁም የሚፈልገው ነበር።

  ምንጭ
  ማህበራዊ ኑሮ በኢትዮጵያ (ሊቀ ሥልጣናት ሀብተ ማርያም ወርቅነህ )
 • loader Loading content ...
 • @Mesfin   2 years ago
  Sewasewer
  ጢሥ አባይ ፏፏቴ በጢስ አባይ ከተማ ወይም ከባህር ዳር በስተምስራቅ  30 ኪሜ ርቀት ላይ የሚገኝ ፏፏቴ ነው። ፏፏቴው የሚፈጠረው የአባይ ወንዝ ትልቄቱ በግምት ከ40 እስከ 50 ሜትር እና ስፋቱ 400 ሜትር የሚሆን ገደል ውስጥ ተውርውሮ ሲገባ ነው። የአባይ ውሃ ወደዚህ ገደል ሲወረወር እጂግ ማራኪ የሆነ የነጎድጏድ ድምፅ እና አካባቢውን እንደ ጢስ የሚሸፍን የውሃ ብናኝ ይስተዋላል። በተወሰነ ጊዜ ልዩነትም ብልጭ እያለ የሚጠፋ ቀስተ ደመና ይታያል።


                  ጢስ አባይ ፏፏቴ (ምስጋና - http://www.ethiovisit.com/)

  ከባህር ዳር ከተማ ተነስቶ ወደ ጢሥ አባይ ከተማ የሚሄድ የመኪና መንገድ ያለ ሲሆን፤ ከከተማዋ አንስቶ ደግሞ ወደ ፏፏቴው ለመሄድ ሁለት አማራጮችን መጠቀም ይቻላል።  አንደኛው  አማራጭ  ከከተማዋ  1.5 ኪሜ ያክል በመኪና ከተጏዙ በሇላ ቁልቅለት እና አቀበት የሆነውን የእግር መንገድ ለ20 ደቂቃ ተጉዘው ፏፏቴው ጋር መድረስ ይቻላል። በዚህ መንገ ሲሄዱ እግረመንገድን በ17ኛው ክፍለ ዘመን በአፄ ሱስንዮስ ዘመነ መንግስት እንደተሰራ የሚነገርለት የአላታ ድልድይን ማየት ይቻላል። 


                   የአለታ ድልድይ (ምስጋና  -  የአማራ ቱሪዝም እና ማሥታወቂያ ቢሮ)

  ሁለተኛው አማራጭ ደግሞ እዚያው ወንዙ አጋባቢ በሚሰራ "ደንገል" በመባል የሚታወቅ ጀልባ በመጠቀም እዚያው ፏፏቴው ድረስ መሄ ይቻላል። በዚህም አማራጭ ፏፏቴው ለመድረስ በአጠቃላይ ከ30 እስከ 40 ደቂቃ ይወስዳል።

  ምንጭ
        - የአማራ ክልል የቱሪሥት መሥህብ ሃብቶች (የአማራ ቱሪዝም እና ማሥታወቂያ ቢሮ)
 • loader Loading content ...
  Load more...
loader Loading content ...

Comments (8)


 • @Mesfin   1 year ago
  Sewasewer
  ባሮ ከውብ ፀሃይ ግባቱ ጋር በጣም ያምራል! ግሩም መስህብ!
 • @Mesfin   1 year ago
  Sewasewer
  ግሩም የሃገር የማንነት መገለጫ! አመሰናለ!
 • @Mesfin   1 year ago
  Sewasewer
  እጅግ አመሰግናለሁ፣ ህሊና ስለ ገለፃሽ!
 • @Mesfin   1 year ago
  Sewasewer
  እንዲህ ጥግብ በልልኝ፣ የሀገሬ ገበሬ :) ጥሩ ነው እንዲህ የማንነት መገለጫዎቻችንን መመዝገብ! እናመሰግናለን!
 • @Mesfin   1 year ago
  Sewasewer
  እንደዚህ ልብ ዘልቆ የሚገባ ግጥም ካነበብኩ ቆይቻለሁ! ማንኛውም ኢትዮጵያዊ ሊያነበው የሚገባ! እናመሰግናለን ገጣሚውንና ፖስት ያረጉትን!
 • @Mesfin   1 year ago
  Sewasewer
  እንዲህ ልብን ዘልቆ የሚገባ ግጥም ካነበብኩ ቆይቻለሁ! ማንኛውም ኢትዮጵያዊ ሊያነበው የሚገባ ግጥም! ከልብ አመሰግናለሁ ገጣሚውን፣ ፖሥት ያረገውን እንዲሁም ሰዋሰውን!
 • @Mesfin   1 year ago
  Sewasewer
  መቸ ይሆን የሀገሬ ገበሬ ዘመናዊ የእርሻ መሳሪያዎችን ለመጠቀም በመታደል ድካሙን የሚያቃልለው! እናመሰግናለን ታሪኩ፣ እንዲሁም ሰዋሰዎች እነኝህን መረጃዎች እንድንለዋወጥ ስላረጋችሁን!
 • @Mesfin   1 year ago
  Sewasewer
  ምስጋና፣ Abigel! ብዙ ጊዜ ቃሉ "አስራት በኩራት" እየተባለ ሲነገር እሰማለሁ። "በኩራት" የሚለው ቃል ለምን እንደተጨመር የምታውቁ ብትገልጹልን ደግሞ መልካም ነው።
loader Loading content ...