loader

Topics (143)


loader Loading content ...

Explanations (106)


 • @Hilina   8 months ago
  Sewasewer

  በድንገተኛ አደጋ ምክንያት አጥንት ከመታጠፊያው ሲወጣ ውልቃት ይባላል። የአጥንት መጋጠሚያ ጡንቻዎች ሲጎዱ ወይም ሲጠማዘዙ ደግሞ ወለምታ ወይም ቅጭት ይባላል።

  የውልቃት መለያ ምልክቶች:

  • የተጎዳው መጋጠሚያ የሕመም ስሜት ሲያስከትል፣ እብጠት ሲኖረው፣ ሕሊናን የመሳት ችግር ሲፈጠር፣ የቅርጽ መዛባት ሲኖርና የመሳሰሉት የውልቃት መለያ ምልክቶች ናቸው።


  የውልቃት ህክምና

  • የወለቀውን አጥንት ወዲያውኑ ወደቦታው መመለስ፡፡

  • ተመልሶ እንዳይውልቅ ለዘጠኝ ወር ያህል በፋሻ ጠበቅ አድርጎ ማሰር።

  • የተጎዳው እጅ መ•ሉ ለመ`ሉ እስኪድን ድረስ ቢያንስ ለሁለት ወይም ለሦስት ወር ከባድ ሥራ ከመስራት መቆጠብ።

  በእጅና በእግር ላይ አደጋ ሲደርስ ጉዳቱ የወለምታ ወይም ስብራት ለመሆኑ ራጅ ካልተነሳ በስተቀር አይታወቅም።

  ለምሳሌ፣ ግለሰቡ ቁርጭምጭሚቱ ተጎድቶ ትንሽ እንኳን : መራመድ ካልቻለ ስብራት የመሆን እድሉ ጠባብ ነው :: አብጦ የህመም ስሜትም ቢኖር እንኳን ወለምታ ሊሆን የሚችለው :: እግሩን መሬት ላይ  ማድረግ ካልቻለ ግን ስብራት ይሆናል ብሎ መጠርጠር ተገቢ ነው :: ስለዚህ ቶሎ የሃኪም እርዳታ መጠየቅ ይገባል።

  ለወለምታ የሜደረገ እርዳታ

  የህመምና የእብጠቱን ስሜት ለማስታገስ ወለም ያለውን ክፍል ወደላይ ያድርጉት :: በመጀመሪያውና በሁለተኛው ቀን በረዶ ወይም ቀዝቃዛ ውሃ በጨርቅ በመንከር ያበጠው እግር ላይ ከ20-30 ደቂቃዎች በየሰዓቱ ማስቀመጥ ይረዳል :: ህመሙንም ይቀንሰዋል :: እብጠቱንም ያስወግደዋል፡፡ ከ2 ወይም 3 ቀናት በኋላ (ዕብጠቱ መጨመሩን ባቆመበት ጊዜ) ወለም ያለውን ክፍል በየቀኑ ለብዙ ጊዜያት መውቅ ውሃ ውስጥ መንከር ይጠቅማል፡፡

  ጥንቃቄ:- ስብራት ወይም ወለምታ መታሸት የለበትም :: ጥቅምም የለውም፣ እንዲያውም ጉዳቱ ያመዝናል:: አደጋው የደረስበት ሰው እግሩ የሚዝለፈለፍ ሆኖ ማነቃነቅ ካቃተው ወደ  ሆስፒታል መውሰድ ይገባል :: ቀዶ ጥገና ሊያስፈልገው ይችላል፡፡

  ምንጭ

  ሐኪም በሌለበት ፣ በዴቪድ ወርነር ፣ በጠና አበረ


 • loader Loading content ...
 • @Hilina   8 months ago
  Sewasewer


  ብፁዕ አቡነ አብርሃም በጎጃም ሀገረ ስብከት በሞጣ አውራጃ ልዩ ስሙ አሸመን ከተባለው ቦታ ሐምሌ 5 ቀን 1861 ዓ.ም. ተወለዱ:: ዕድሜያቸው ለትምህርት ሊደርስ በምሥጢረ ጥምቀት ልጅነትን ባገኙባትና አጥቢያቸው በሆነችው የቅድስት ማርያም ቤተ ክርሰቲያን ፈደል አና የቃል ትምህርቱን ተምረው ዳዊት ደገሙ።

  ከወላጆቻቸው ሳይርቁ በእማረ ሁናቴ የጀመሩትን ትምህርት በመቀጠል በአካባቢያቸው ወደ ሚገኙ · የዜማና የቅኔ ትምህርት ቤቶች በመዘዋወር ጸዋትወ ዜማንና ቅኔን በአግባቡ ተማሩ:: በመቀጠ ልም በወቅቱ በጎጃም ከፍለ ህገር ስመ ጥር የመጻሕፍት ትርጓሜ ቤት ከነበረው ሞጣ ጊዮርጊስ ብሉያቱንና ሐዲሳቱን አጠኑ፡፡ መጻሕፍተ ሊቃውንቱንና መነኮሳቱንም በሚገባ አጠናቀቁ ::

  ብፁዕነታቸው የተማርኩት ትምህርት ይበቃኛል ሳይሉ ዕውቀታቸውን ለማስፋፋት ወሎ ቦሩ ሥላሴ ወደ ነበሩት ስመ ጥርው መ/ር አካለ ወልድ ዘንድ ሔዱ፡፡ ጎጃም የተማሩትን እንደ ገና እንደ አዲስ በመጀመር አራቱንም ጉባኤያት በሚገባ በመከለስ ዕውቀታ ቸውን አስፋፉ:: የብፁዕ አቡነ አብርሃምን ሊቅነት ያዩ የመ/ር አካለ ወልድ ተማሪዎች ከመማር ጐን ለጐን ጉባኤ ዘርግተው እንዲያሰተምሩ ጥያቄ አቀረቡ:: መምህር አካለ ወልድም የተማሪዎቻቸውን ጥያቄ ተቀብለው ቁጥሩ ከበዛው ተማሪያቸው በመክፈል የተወሰኑ ተማሪዎች ለብፁዕነታቸው ሰጧቸውና እየተማሩ ማስተማር ጀመሩ። ብፁዕነታቸው ለሚያስተምሯቸው ተማሪዎች ምሥጢር ከምሥጢር አገናኝተው፣ የራቀውን እቅርበው፣ የረቀቀውን አፍታተው ሲያቀርቡ እንኳን ተማሪዎቻቸው ታላቁ ሊቅ መ/ር እካለ ወልድም ይደነቁ ነበር ይባላል ::


  ቦሩ ሥላሴ ከላይ በተገለጠው ሁኔታ እያስተማሩ ረዘም ላለ ጊዜ ከመምህር አካለ ወልድ ዘንድ ከተማሩና የምሰክር ወረቀታቸውን ከያዙ በኋላ ወደ ተወለዱበት አካባቢ ጎጃም በመሔድ ጉባኤያቸውን አሰፋፍተው ማስተማር ጀመሩ:: የዘረጉት ጉባኤ ዕለት ከዕለት እየሰፋና እየጐለበተ በመምጣት ላይ ሳለ እንደ አባታቸው እብርሃም አበ ብዙኃን ሊያደርጋቸው ያሰበ አምላክ በስውር ጥበቡ ወደ አዲስ አበባ እንዲመጡ አደረገ፡፡

  ከጎጃም ተነሥተው ወደ እዲስ አበባ የመጡት ብፁዕ አቡነ አብርሃም ሳይውሉ ሳያድሩ በአዲስ አበባው መንበረ መንግሥት ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን በእልቅና ተሾሙ:: ብፁዕነታቸው በዚያ ጊዜ የንግሥተ ንግሥታት ዘውዲቱ ምኒልክ የጸሎት መጻሕ ፍት አንባቢና አሳላሚ ሆነው ያገለግሉ ነበር። ከተሾሙም በኋላ ሊቅነታቸውን የሰሙ የመጻሕፍት ተማሪዎች ከከፍለ ሀገርም ሆነ ከአዲስ አበባ በመሰባሰብ ስለ ከበቧቸው ጉባኤያቸው ከመቼውም ጊዜ በበለጠ ሁኔታ እየሰፋ መጣ፡፡ በዚህም ሐዲስ ለሚማረው ሐዲስ፣ ብሉይ ለሚማረው ብሱይ፣ ሊቃውንት ለሚማረው መጻሕፍተ ሊቃውንት፣ መነኮሳት ለሚፈልገው መጻሕፍተ መነኮሳት በየዓይነቱ በሚያጠግብ ሁኔታ ያስተምሩ ጀመር :: ለተማሪው ዕውቀት መንፈሳዊን ከመመገብ ጋርም ዐቅማቸው የፊቀደውን ያህል ለተራበው እያጐረሱ፣ ለተጠማው እያጠጡ፣ ለታረዘው እያለበሱ ተማሪዎቻቸውን ይንከባከቡ ነበር ይባላል ::

  በዚህ ዓይነት ለተወሰኑ ዓመታት የቆዩት ብፁዕ አቡነ አብርሃም በቤተ ክርሰቲያኗና በህገሪቱ መንግሥት በ1921 ዓ.ም. በተደረገው የእጨሩ ጳጳሳት ምርጫ ከተመረጡት አባቶች አንዱ ሆኑ።

  በዚህም ብፁዕነታቸው ግንቦት 18 ቀን 1921 ዓ.ም. በካይሮ ቅዱስ ማርቆስ ቤተ ከርሰቲያን ከሌሎች ሦስት ወንድሞቻቸው ጋር መዓርገ ጵጵስናን ተቀበሉ:: ወደ ህገራቸው ከተመለሱም በኋላ «አባ አብርሃም ጳጳስ ዘምዕራበ ኢትዮጵያ ተላዌ አሠሩ ለአቡነ ሐራ » በሚል ተሠይመው በጎጃም፣ በጎንደርና ስሜን አህጉረ ስብከት ተሾሙ።

  ከሕፃንነታቸው ጀምሮ ለትምህርት ሲሉ ከቦታ ቦታ ሲዘዋወሩ የኖሩት ብፁዕ አቡነ አብርሃም ቅዱሳት መጻሕፍትን አብዝተው ከመመርመራቸው የተነሣ ዓይናቸውን፣ ትኅርምት ከማብ ዘታቸው የተነሣም አንጀታቸውን በተለያዩ ጊዜያት ያማቸው ነበር :: ይሁን እንጂ የሚደርሰባቸው ሥጋዊ ፈተና እንቅፋት ሳይሆንባቸው ሕማሙ ጠንቶባቸው አልጋ ላይ አስኪውሉ ድረሰ ሕዝበ ክርስቲያኑን ከማስተ ማር፣ ሥራቸውንም ከመሥራት አልታቀቡም ነበር :: በዚህ ሁሉ ደገኛ ተግባራቸው የተነሣ ምእመናን «አማናዊው አብርሃም» አያለ ይጠራቸው ነበር ይባላል።

  ብፁዕነታቸው ቃለ እግዚአብሔርን ስሕዝበ ምአመናን በማዳረሰ በኩል ላቅ ያለ አስተዋጽኦ ያበረከቱ አባት ነበሩ። ከዚህም ውስጥ የሚጠቀሰው በዐውደ ምሕረት ቃለ አግዚአብሔርን ለምእመናን መስበክ በመጀመር የከፈቱት አዲስ የአገልግሎት መስመር ነው። ብፁዕነታቸው ይህንን : አገልግሎት ክመጀመራቸው በፊት ቃለ እግዚአብሔር በቅዳሴ ጊዜ ተነቦ በአጭሩ ከሚተረጎም በስተቀር ሰባክያን ለስብከተ ወንጌል ሰፊ መርሐ ግብር ይዘው ምእመናንን አያስተምሩም ነበር። የዐውደ ምሕረት ሰብከተ ወንጌል አገልግሎት በብፁዕነታቸው ከተጀመረ በኋላ ግን ይኸውና ዛሬ ድረስ በብዙ አብያተ ክርስቲያናት ምእመናን ዘወትር በሠርክ በዐውደ ምሕረት እየተሰባሰቡ ቃለ አግዚአብሔርን ይማራሉ።

  ብፁዕ አቡነ አብርሃም የዐውደ ምሕረትን የስብከተ ወንጌል አገልግሎት አንዲያከናውኑ የነፍስ ልጃቸው የነበሩት ንግሥተ ንገሥታት ዘውዲቱ ትልቅ ድጋፍ እንዳደረጉላቸው ይነገራል :: እንደሚታወቀው ንግሥተ ንገሥታት ዘውዲቱ ለቤተ ክርስቲያን ሊቃውንትና ካዐናት ይሰጡት ከነበረው አከብሮትና እንክብካቤ እንዲሁም ሥልጣን የተነሣ የእሳቸው ዘመን «ዘመነ ካህናት » ተብሎ ይጠራል፡፡

  ከላይ እንደ ተገለጠው ብፁዕነታቸው በነበራቸው ዕውቀትና ቅድስና፣ በንግሥቷ ዘመን በቤተ መንግሥቱ ላቅ ያለ ከብርና ሥልጣን ካገኙት አባቶች አንዱ ነበሩ:: የንግሥቷ አበ ነፍስ በመሆናቸው በቤተ መንግሥቱ አካባቢ በነበረው መንፈሳዊ እንቅስቃሴና በሚወጣው መመሪያ ትልቅ ተሳትፎ ነበራቸው:: ታዲያ በዚህ መዓርግና አገልግሎት ላይ ሳሉ ንግሥቷ ከዚህ ዓለም በሞት ይለያሉ። በዚህ የተነሣ ምንም አንኳን በንግሥቷ ሞት መላው የኢትዮጵየያ ሕዝብ ይልቁንም በንግሥቷ እንክብካቤ በከፍተኛ ሹመትና መዓርግ የበቁት ሊቃውንት በእጅጉ አዝነው ነበር፡፡ ከእነዚህ ስዎች አንዱ ደግሞ ብፁዕ አቡነ አብርሃም ነበሩ ታዲያ ብፁዕነታቸው ዘወትር ባገኙት እጋጣሚ ሁሉ ይህንን ሐዘናቸውን ይገልጹ ነበር ይባላል :: አንድ ቀን እንደ ተለመደው በዐውደ ምሕረት ቃለ እግዚአብሔርን : ለምእመናን ሲያስሙ ያስተማሩበት ርዕስ «እንከስ ጸርሐት ቤተ ከርበቲያን ፤ እንግዲህስ ቤተ ከርስቲያን ትጮኻለች» የሚል ነበር። በዚህ ርዕስ በነበራቸው የጣዕመ ስብከት ጸጋ በቃለ አግዚአብሔር አያዋዙ ንግሥተ ንግሥታቷ አዝነውና ተጎሳቁለው ከዚዐ ዓለም በሞት በመለየታቸው ቤተ ክርስቲያን አንደምታዘን፣ እግዚአብሔር ለቤተ ከርስቲያንና ልጆቿ ያደረጉትን በጎ ሥራ ሁሉ ቆጥሮ ነፍሳቸውን በአብርሃም፣ በይስሐቅና በያዕቆብ አጠገብ አንዲያስቀምጥ ቤተ ክርስቲያን በእጅጉ እንደ ምትጸልይ ያስተምራሉ። ይህንኑ ትምህርታቸውን በሌሎች ጉባኤያትም ይደጋግማሉ:: በዚህ ጊዜ ብፁዕነታቸው ስለ ንግሥተ ንገሥታቷ መሞት የተሰማቸውን ሐዘንና ስለ አሟሟታቸው ሁኔታ በዐውደ ምሕረት እየገለጹ እንደሆነ ንጉሡ ይስማሉ። ንጉሡም ወዲያውኑ ብፁዕነታቸውን አስጠርተው «ምነው በንግሥተ ንግሥታቷ ማረፍ ይኸንን ያዐል አዘኑ? አኛስ ክርስቲያኖች አይደለንም አንዴ? አንደዚህ ሊሆኑ አይገባም» አሏቸው። ብፁዕነታቸውም የንጉሡን አባባል ባለመቀበል «ሐዘንተኛ እንደ ቢጤቱ ነው የሚያለቅሰው :: በተስማው መንገድ ሊያለቅስ ይችላል እንጂ በዚህ መንገድ አልቅስ ፤ በዚያ መንገድ አታልቅስ አይባልም» አሏቸው ይባላል::

  ብፁዕነታቸው በተለይ በህገረ ስብከታቸው ጎጃም ሕዝቡ ቃለ ወንጌል በሰፈው እንዲስማ፣ የአብነት ትምህርት ቤቶች እንዲስፋፉ፣ ሊቃውንትም ርስት ጉልት እንዲያገኙ ስፊ ጥረት ያደርጉ ነበር ይባላል:: በወቅቱ በአካባቢው የቅብዐት፣ ትምህርት በስፋት ነበረና የቅብዐት ሊቃውንትን ጥልቅ በሆነ ዕውቀታቸው በቃልም በመጣፍም ይረቷቸውና ያስረቷቸው እንደ ነበር ይነገራል። በዚህ ከተደሰቱት የተዋሕዶ ሊቃውንት መካከል አንዱ በቅኔ ሊያወድሳቸው የሚከተለውን ሐረግ ሊቀኝ፤ በጅምሩ የተደስቱት ብፁዕነታቸው ወደ ሁለተኛው ሐረግ ሳይሔድ «በቃ በቃ፤ ይኸው ይበቃል ታበለሸዋለህ» አሉት ይባላል :: በመሆኑም እስከ ዛሬ ድረስ በርካታ ሊቃውንት የሚያውቋት ከዚህ በታች የተጻፈችዋን ስንኝ ብቻ ነው።

  "ኣ ኣብርሃም ነድፅ የቅብዐት ማቅለጫ"

  ታዲያ አንረታም ያሉት የቅብዐት መምህራንም ለተበረከ ተላቸው ቅኔ መልሰ ይሆን ዘንድ በሚከተለው ሐረግ የሚጀምር ቅኔ ዘርፈዋል ይባላል።

  "ቅብዕ እስመ ያለፉፍኣ ለኣብራም ኣነዳ"

  ብፁዕነታቸው በጎጃም ባበረከቱት ስፊ አገልግሎት ዛሬ ድረስ በአካባቢው አረጋውያን ዘንድ ስማቸው አልተረሳም። ከላይ እንደ ተገለጠው በነበራቸው ሊቅነት የቅብዐትን ሊቃውንት ከመርታታቸው በተጨማሪ በነበራቸው የተቸገረን የመርዳት ጸጋ በገንዘባቸው እየረዱ ብዙዎችን አስተምረው ለወግ ለመዓርግ አብቅተዋልና።

  ብፁዕነታቸው የኢጣልያ ወራሪ ጦር ህገራችንን በግፍ በወረረ ጊዜ በሊቃውንት ተመርጠው ግብፃዊው የኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳሳት አቡነ ቄርሎስ ትተውት የሔዱትን መንበረ ጵጵስና ኅዳር 21 ቀን 1930 ዓ.ም በመረከብ በሊቀ ጳጳሳትነት አስከ ዕለተ ዕረፍታቸው በቅንነትና በትጋት አገልግለዋል :: በተሾሙበት ዕለትም አንደ ታላቁ የኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን ሊቃውንት ጉባኤ ውሳኔ ሌሎች አምስት ጳጳሳትንና አንድ ኤጲስ ቆጳስን ሹመዋል። እነሱም እቡነ ዮሐንስ ጳጳስ ዘሸዋ፣ አቡነ ማርቆስ ጳጳስ ዘኤርትራ፣ አቡነ ሰላማ ጳጳስ ዘሐረር፣ አቡነ ገብርኤል ጳጳስ ዘጎንደር፣ አቡነ ማቴዎስ ጳጳስ ዘወሎና አቡነ ሉቃበ ጳጳስ ዘወለጋ ናቸው፡፡ በዚህ የተነሣ የግብፅ ቤተ ክርስቲያን አላግባብ አውግዛቸው ነበር፡፡

  በመጨረሻ ብፁዕነታቸው በዚህ ዓለም ከአንድ ማንፈሳዊ አባት የሚጠበቀውን ካከናወኑ በኋላ ሐምሌ 24 ቀን 1931 ዓ.ም. ስኞ ከጠዋቱ ልክ በአንድ ስዓት ተኩል ከዚህ ዓለም በሞት ተለዩ።

  ምንጭ 

  • ዜና ጳጳሳት ኢትዮጵያውያን (ዲያቆን መርሻ አለኸኝ)


 • loader Loading content ...
 • @Hilina   2 years ago
  Sewasewer
  ምንጭ
  የኢትዮጵያ ጥንታዊ ምሳሌ (በሊቀ መዘምራን ሞገስ ዕቁበ ጊዮርጊስ)
 • loader Loading content ...
 • @Hilina   2 years ago
  Sewasewer
  ምንጭ
  የኢትዮጵያ ጥንታዊ ምሳሌ (በሊቀ መዘምራን ሞገስ ዕቁበ ጊዮርጊስ)
 • loader Loading content ...
 • @Hilina   2 years ago
  Sewasewer
  ምንጭ
  የኢትዮጵያ ጥንታዊ ምሳሌ (በሊቀ መዘምራን ሞገስ ዕቁበ ጊዮርጊስ)
 • loader Loading content ...
 • @Hilina   2 years ago
  Sewasewer
  ምንጭ
  የኢትዮጵያ ጥንታዊ ምሳሌ (በሊቀ መዘምራን ሞገስ ዕቁበ ጊዮርጊስ)
 • loader Loading content ...
 • @Hilina   2 years ago
  Sewasewer
  ምንጭ
  የኢትዮጵያ ጥንታዊ ምሳሌ (በሊቀ መዘምራን ሞገስ ዕቁበ ጊዮርጊስ)
 • loader Loading content ...
 • @Hilina   2 years ago
  Sewasewer
  ምንጭ
  የኢትዮጵያ ጥንታዊ ምሳሌ (በሊቀ መዘምራን ሞገስ ዕቁበ ጊዮርጊስ)
 • loader Loading content ...
 • @Hilina   2 years ago
  Sewasewer
  ምንጭ
  የኢትዮጵያ ጥንታዊ ምሳሌ (በሊቀ መዘምራን ሞገስ ዕቁበ ጊዮርጊስ)
 • loader Loading content ...
 • @Hilina   2 years ago
  Sewasewer
  ምንጭ
  የኢትዮጵያ ጥንታዊ ምሳሌ (በሊቀ መዘምራን ሞገስ ዕቁበ ጊዮርጊስ)
 • loader Loading content ...
  Load more...
loader Loading content ...

Comments (7)


 • @Hilina   1 year ago
  Sewasewer
  ልብን ዘልቆ የሚገባ፣ ድንቅ መዝሙር! ይልማ፣ መዝሙሮችህ ሁሌም ግሩም ሀሴትን ይሰጡኛል! መንግስተ ሰማይን ያውርስህ! አሜን!ከልብ አመሰግናለሁ መሰረቱን ስላካፈልከን @ Mikurab!
 • @Hilina   1 year ago
  Sewasewer
  ታዲያ በኣጭሩ rehab-center ልንለው እንችላለ! ፍቅር ያሸንፋል ማለት ይኸ ነው! Thanks for sharing!
 • @Hilina   1 year ago
  Sewasewer
  Thanks for sharing, Tariku!
 • @Hilina   1 year ago
  Sewasewer
  እንደኔ እንደኔ የሞኝ ደጅ ሞፈር ይሆናል፣
  በልባም ጎበዝ ተቆርጦ የታየ 'ለት የእግር እሳት ሆኖ እያደር ይፈጃል።

  @Birhanu, ከፍ ያለ ምስጋና ስላካፈልከን!
 • @Hilina   1 year ago
  Sewasewer
  Wow, good stuff!! Thanks for sharing, Kibur!
 • @Hilina   1 year ago
  Sewasewer
  መጎብኘት ያለበት የተቀደሰ ቦታ! ሃይማኖታዊም ታሪካዊም እሴቶች አሉት!! እናመሰግናለን።
 • @Hilina   2 years ago
  Sewasewer
  ምስጋና በፍቃዱ! እንደ አስተያየት - ምንጭ መጥቀሥ ሁሌም ሰዋሰው ላይ ያሉ መጣጥፎች ባህል ብናደርገው ደግሞ የበለጠ ዘላቂ እና ቀጣይ የሆነ አንባብያንን እናፈራለን።
loader Loading content ...