loader

Topics (22)


loader Loading content ...

Explanations (22)


 • @Abigel   7 months ago
  Sewasewer

  ሙሉቀን መለሰ በ1958 ዓ.ም. ገና 13 ዓመት ልጅ ሳለ ድምጻዊነት ሙያውን በፈጣን ኦርኬስትራ በመጀመር በ፲፱፻፰ ዓ.ም. አሁን ወደሚገኝበት ወደ ፖሊስ ኦርኬስትራ ክፍል ገብቶ ዝነኛነቱን አሳውቋል። ሙሉ ቀን በሙዚቃ ዓለም በነበረበት ጊዜ በርካታ ዜማዎች የተጫወተ ሲሆን ዜማዎቹም በሸክላ ተቀርጸው ወጥተዋል።

  « እናቴ ስትወልደኝ መች አማከረችኝ፤ የፊት ጉዴን ትታ እደግ ማሞ አለችኝ » የተባለችው ዜማ የመወደድዋን ያህል ድምጻዊው ሙሉቀን መለሰም ተደናቂ ሁኗል። ሙሉ ቀን መለስ እንደዚሁም:- « ወንበር ተደግፎ ክብ ጠረጴዛ የሰነፎች በትር ትችት በጣም በዛ » እያለ የሚጫወታት ዘፈንም ሙሉቀንን ታዋቂና ዘፈኖቹንም ተወዳጅ አድርጎታል።


  ምንጭ፣ የአንጋፋ አርቲስቶች መዝገበ የሕይወት ታሪክ።


 • loader Loading content ...
 • @Abigel   7 months ago
  Sewasewer

  የቡልጋው ተወላጅ ለማ ገ/ሕይወት በሀገር ባሕል ዜማ የታወቀና በተለይም ኃይለኛ የሆነ ድምፅ ያለው ድምጻዊ ነው።

  ለማ በ1942 ዓ.ም. በአዲስ አበባ ማዘጋጃ ቤት ተቀጥሮ በሙያው ተደንቆና ብዙ የወዳጅ አገሮችንም ጐብኝቶ በሕዝብ ዘንድም በመታወቁ ተደስቶ የኖረ ሰው ነበር። ለማ ብዙ ዜማዎች ደርሷል፣ ከእነርሱም መካከል « ያዘው ጐበዝ » የተባለው እና የሠርግ ዘፈኖቹም በሕዝብ ዘንድ በጣም ይወደዳሉ። የለማ ልዩ ስጦታው በሽለላ ላይ ያዘነበለ ነው ፤ ድምፁ ያለ ድምፅ ማጐያ የጐላ ነው።

  ለማ ከ፲፯ ዓመት ዕድሜው እስከ ፵፪ ዓ.ም. ድረስ በጦር ሠራዊትና በክብር ዘበኛ ወታደርነት ተቀጥሮ አገልግሏል፤ « የዜማ ፍቅር የያዘኝ በሕፃንነቴ ወራት በደን ከብቶችን በምጠብቅበት ወቅት እንደ ቀረርቶ የመሳሰሉትን ሳንጐራጉር ነበር » ሲል እራሱን አስተዋውቋል፤ ለማ ከድምጻዊነቱም በላይ « አይረሳም» በሚል አርእስት ስለኢትዮጵያ አርበኞች ታሪክ በግጥም የሚታወስ መጽሐፍ ደርስዋል።


  ምንጭ፣ የአንጋፋ አርቲስቶች መዝገበ የሕይወት ታሪክ።


 • loader Loading content ...
 • @Abigel   7 months ago
  Sewasewer

  ጌታቸው መኩሪያ ለሙዚቀኛነት የተቀጠረው በ1942 ዓ.ም. ነው። የቴኖርን ሙዚቃ ድምፅ የሚወደው ጌታቸው መኩሪያ የሙዚቃ መሳሪያውን ይዞ እየተቁነጠነጠ «አልማዝ ምን እዳ ነው»፣ « ሽለላ » ና የመሳሰሉትን በሚጫወትበት ወቅት ከማስደሰቱ የተነሳ ከሕዝብ ዘንድ ከፍተኛ የመወደድን ዕድል ለማግኘት ችሏል። በችሎታው ብዙ አገሮችንም ጐብኝቷል፣ በጉብኝቱም ወቅት ባጨዋወቱ ተደንቋል።


  ምንጭ፣ የአንጋፋ አርቲስቶች መዝገበ የሕይወት ታሪክ።


 • loader Loading content ...
 • @Abigel   7 months ago
  Sewasewer

  በ1957 ዓ.ም. በፖሊስ ሠራዊት ሙዚቃ ክፍል አገልግሎቱን የጀመረው የጠይም ሽንቅጥ በኃይሉ እሸቴ ከድምጻዊነት ችሎታው በላይ ጠቃሚ መልእክት ያዘሉ ግጥሞች ከነዜማቸው በመድረስ ተደናቂ ነው።

  በኃይሉ ለሕዝብ ካቀረባቸው ዜማዎች « ኮሳሳ ጎጆዬ » ና « የጥቁር ድምፅ » የተባሉት ዘፈኖች በሕዝብ ዘንድ የተወደዱ ናቸው። « የኪዎስኳ እመቤት » የተባለችው የራሱ ድርሰት የበለጠ ዝና አስገኝታለች።  ምንጭ፣ የአንጋፋ አርቲስቶች መዝገበ የሕይወት ታሪክ።

 • loader Loading content ...
 • @Abigel   7 months ago
  Sewasewer

  አለማያ ተወልዶ ድሬዳዋ ያደገው አሉላ ዩሐንስ ዕድገቱ በአዳሪ ት/ቤት ውስጥ ነበር። በዚህ አዳሪ ት/ቤት ውስጥ እያለ የሙዘቃ ስሜት አድሮበት መጫወት ጀመረ። ከሙዚቃ መሳሪያዎች ጊታር በደንብ መጫወት የጀመረው ወደ አዲስ አበባ በመምጣት ትንሽ እንደቆየ ነበር። በ195ዐ ዓ.ም. መጨረሻዎች ለትምህርት ወደ ጀርመን ሀገር ሄደ። ከዚያም ለሦስት ዓመት ተኩል የሕክምና ትምህርቱን ከተማረ በኃላ በማቋረጥ ወደ ኮንሰርቫቶሪ የሙዚቃ ት/ቤት ገባ እዚህ የሙዚቃ ት/ቤት እያለም " Mr president " የተባለውን የመጀመሪያውን ሸክላ አሳተመ። አሉላ ወደ አሜሪካ በመሄድ ከሁለት አልበሞች በተጨማሪ አራት ሸክላዎች አሳትሟል። አሉላ በአሥራ አንድ ቋንቋዎች ይጫወታል። አማርኛ፣ ትግርኛ፣ እንግሊዝኛ ስፖንኛ፣ ጣሊያንኛ፣ ፈረንሳይኛ፣ ጀርመንኛና ኢብራይስጥኛ ወዘተ... አቀላጥፎ ይናገራል። ድሬዳዋ እያለ ስንታየሁ ይባል ነበር። « ስንታየሁ » የምትባለውም ሙዚቃ ከሕዝብ ጋር አስተዋወቀችው። አሉላ ከ3ዐ ዓመታት በላይ ረጅም የመውዚቃ ሕይወት ያለው አርቲስት ነው። አሉላ ቮካሊስት ከመሆኑም በተጨማሪ፣ ጊታር፣ ኪቦርድ፣ አርሞኒካ፣ ድራምንና ፒያኖን በደንብ የሚጫወት ሁለገብና ዘመናዊ አርቲስት ነው።


  ምንጭ፣ የአንጋፋ አርቲስቶች መዝገበ የሕይወት ታሪክ።


 • loader Loading content ...
 • @Abigel   7 months ago
  Sewasewer

  Addis Gezehagn was born in 1978 in Addis

  Ababa. He was educated in Art at the Addis

  Ababa University School of Fine Arts and

  Design. After graduating in 2001, he worked as

  a full-time artist at the Ethiopian Art Studio.

  The key to the variety in his art is his ability to

  draw inspiration from many diverse sources.

  Deriving ideas from his subconscious, his

  work is a reflection of life, depicting both live

  and inanimate objects. To date, he has held

  a number of solo and group exhibitions in

  Ethiopia and various other countries.  Here are some of his paintings;

  Reference: ART OF ETHIOPIA

 • loader Loading content ...
 • @Abigel   8 months ago
  Sewasewer
  መልካሙ ተበጀ የተወለደው በ1938 ዓ.ም. በሲዳሞ ክ/ሀገር ክብረ መንግስት በሚባል ቦታ ነው። መልካሙ የሙዚቃ ፍቅር ከሕፃንነቱ ጀምሮ አብሮት ያደገ ነው። ቤተሰቦቹ ለስራ ጉዳይ ወደ ሐረር ከዚያም ወደ አዲስ አበባ ሲዛወሩ አብሮ በመምጣት በአምኃ ደስታ ት/ቤት ይገባል። በት/ቤት በተለያዩ በዓላት በተለይም በወላጆች ቀን በሚያደርገው ተሳትፎ የሙዚቃ ስሜቱ ከእሱ አልፎ በተመልካች ዘንድ እየጎላ በመሄድ ነሐሴ 15 ቀን 1957 ዓ.ም. በብሔራዊ ቲያትር የታዳጊ ኦርኬስትራ |ዳዊት ኦርኬስትራ/ በድምፃዊነት ተቀጠረ። መልካሙ እስካሁን ድረስ በመቶዎቹ የሚቆጠሩ ዜማዎችን ተጫውቷል። ከእነዚህም ዜማዎቹ አንድ መቶ ሃምሳ ያህል የራሱ ድርሰቶች ናቸው። « የሲዳሞ ቆንጆ » ፣« በይ እንግዲህ ተለያየን »፣ « ቸብ ቸብ » ፣ « ዳህላክ » እና «ሙዚቃ »የተሰኙ ዜማዎቹ እራሱ ደርሶ ከተጫወታቸው ዘፈኖች መካከል በዋቢነት ሊዘከሩ የሚችሉ ናቸው።  መልካሙ ከግጥምና ዜማ ደራሲነቱ ባሻገር ቲያትርም የመድረስና በተዋናይነት የመሳተፍ ችሎታ ያለው አንጋፋ ከያኒ ነው። የድርሰት ችሎታውን ካስመሰከረባቸው ስራዎቹ አንዱ የሆነውና እራሱም በተዋናይነት የተሳተፈበት « ቢሮክራሲያዊ የከበርቴ አሻጥር » የተሰኘው ድርሰቱ አንዱ ነው። መልካሙ በበርካታ የቴሌቪዥን ድራማዎች ከመጫወቱ ሌላ በፀጋዬ ገ/መድህን በተደረሰው « አቡጊዳ ቀይሶ » በአያልነህ ሙላት በተደረሰው « ሻጥር በየፈርጁ » እና በሌሎችም ቲያትሮች ተሳትፎአል። መልካሙ ተበጀ ስለ ማህበራዊ ህይወት፣ ስለወጣነት ስለ ተፈጥሮ ስለፍቅር እና ስለ ሌሎችም ብዙ የተጫወተ መልከ መልካም አንጋፋ ከያኒ ነው።


  ምንጭ፣ የአንጋፋ አርቲስቶች መዝገበ የሕይወት ታሪክ።
 • loader Loading content ...
 • @Abigel   8 months ago
  Sewasewer

  ጌታመሳይ በአሩሲ ክ/ሀገር ልዩ ስሙ አልባሶ በተባለ ቦታ በ1935 ዓ.ም. ተወለደ። ባለመሰንቆው ጌታ መሳይ በመ·ያው ተለክፎ እጁን ለመውዚቃ የሰጠው ገና አንድ ፍሬ ልጅ ሳለ በሚኖርበት ሠፈር አካባቢ ሠርግና ክርስትና ሲኖር የሙዚቃ መሳሪያ |ማስንቆ| ይጫወቱ የነበሩትን በማየት ልቡ እጅግ ከተነካ በኋላ ነው። ጌታመሳይ በግል ጥረቱ እንጨት እያጎበጠ የፈረስ ጭራ በማሠር መሰንቆ መጫወት በመቻሉ ስሜቱ ወደዚህ መውያ እንዲያመራ አስገደደው። ጌታመሳይ በ1953 ዓ.ም. ከሀገር ቤት መጥቶ ብሔራዊ ቲያትር ቤት ልምምድ ሲያደርግ ከቆየ በኋላ በአንዳንድ ተፅዕኖዎች ምክንያት ቲያትር ቤቱን ተሰናበተ። በ1956 ዓ.ም. በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ የባህል ማዕከል የኢትዮጵያ ኦርኬስትራ እንደተቋቋመ ተቀጥሮ በርካታ ዘፈኖችን ተጫውቷል። በ196ዐ ዓ.ም. ወደ ሀገር ፍቅር ቲያትር ቤት ተዛወረ።

  ጌታመሳይ በሀገር ፍቅር ቲያትር ቤት ከዘፋኝነት በተጨማሪም የቲያትር ሙያን ሊማር በመቻሉ ከአስር በላይ በሚሆኑ ተያትሮች ከዕውቅ አርቲስቶች ጋር በመሆን ሠርቷል። ለዚህም ማስረጃ ሊሆኑ የሚችሉት በአቤ ጉበኛ « የደካሞች ወጥመድ »፣ በብርሃኑ ዘሪሁን « የለውጥ አርበኞች » እና በጌታቸው አብዲ « ስንት አየሁ » ከብዙ ጥቂቶቹ ናቸው ::

  ጌታመሳይ ከሁለት መቶ የማያንሱ ዜማዎችን ተጫውቷል። ከእነዚህም ውስጥ « ሆብዬ እመጣለሁ »፣ « ሀገር መውደድ ማለት »፣ « ዳይመኔ »፣ « የመኖሪያ ቤቴ » እና « የኔ ሀያል » የተባሉት ለዛ ያላቸው ዜማዎቹ በአድማጭ ዘንድ ያላቸው ተወዳጅነት ከፍተኛ ነው ጌታመሳይ ያለው የጠለቀ የመሰንቆ ዕውቀትና ችሎታው « የመሰንቆው ሊቅ » የሚል መጠሪያ አጎናፅፎቷል። ጌታመሳይ አበበ መሰንቆን ከምንም ነገር የበለጠ ይወዳል። ጌታመሳይ አበበ በሰሜን አሜሪካ በአውሮፖና በአፍሪካ በመዟዟር የሀገራችንን የባሕል ጨዋታ በተለያዩ አለም አቀፍ መድረኮች ላይ ያንፀባረቀ አንጋፋ የባሕል ተጫዋች ነው።  ምንጭ፣ የአንጋፋ አርቲስቶች መዝገበ የሕይወት ታሪክ።
 • loader Loading content ...
 • @Abigel   8 months ago
  Sewasewer
  ግርማ በየነ አዲስ አበባ ተወልዶ ያደገ ሲሆን ትምህርት ቤት ሲዘጋ በጊዜያዊነት በቀ.ኃ.ሥ.ቲ በድምፃዊነት በመቀጠር በ1952 ዓ.ም. ለመጀመሪያ ጊዜ ለህዝብ ታየ ከዚያም እንደገና የ1ዐኛ ክፍል ትምህርቱን በማቋረጥ እሰከ 1953 ዓ.ም. ድረስ በራስ ባንድ በሙዚቃ ክፍል በድምፃዊነት ሲያገለግል ከቆየ በኋላ የራሱን ባንድ በማቋቋም በራሱ ፍቃድ ሥራውን ለቆ ወጣ።

  ምንጭ፣ የአንጋፋ አርቲስቶች መዝገበ የሕይወት ታሪክ።
 • loader Loading content ...
 • @Abigel   8 months ago
  Sewasewer

  አያሌው መስፍን በ1942 ዓ.ም በወሎ ክፍለ ሀገር በየጁ አወራጃ ተወለደ። አያሌው ገና በልጅነቱ የሙዚቃ /የዘፋኝነት/ ሙያ ፍቅር ስለነበረበት ወላጆቹ ወደ ት/ቤት ሲልኩት እሱ ግን የሚውለው አዝማሪዎች በማሲንቆ በሚጫወቱበት ሥፍራ ነበር። ይህንንም በውስጥ የሚነደውን የሙዚቃ ፍቅር ለማርካት ጠፍቶ በ1956 ዓ.ም ወደ አዲስ አበባ መጣ። አዲስ አበባ እንደመጣም ብሔራዊ ቲያትር ድምፃውያንን ለመቅጠር ማስታወቂያ አውጥቶ በነበረበት ጊዜ የተሰጠውን የመግቢያ ፈተና መቶ ከሚሆኑ ተወዳዳሪዎች በአንደኛነት ቢያልፍም ወላጆቹ በተለይም አባቱ የአያሌውን ዘፋኝ መሆን በሬዲዮ ከሰማ አዝማሪ ሆነ ብሎ ይጠላኛል በማለት ፈርቶ ሳይቀጠር ቀረ። ከዚያም አባቱ እንዳይቀየሙት በማለት ሙያውን ትቶ በቀድሞው የክብር ዘበኛ ሠራዊት ውስጥ በወጣት ሻምበልነት ተቀጥሮ አስከ 1959 ዓ.ም. ድረስ ቆየ። ሆኖም አያሌው ዓላማና ፍላጐቱ በሙዚቃ ሙያ ውስጥ ገብቶ ስሜቱን ማርካት በመሆኑ ወደ ሙዚቃው ዓለም የሚገባበትን መንገድ ቀይሶ በጊዜው በነበረው አንድ ባንድ ውስጥ ተቀጥሮ በ1959 ዓ.ም. ወደ ጅማ ሄደ።

  አያሌው ከጅማ ወደ አዲስ አበባ ተመልሶ ፈጣን ኦርኬስትራ በመባል በሚታወቀው በወ/ሮ አሰገደች አላምረው ቤት (ፖትሪስ ሉሙምባ የሚባል የማታ ክበብ ውስጥ) በሳምንት አምስት ብር እየተከፈለው ተቀጥሮ ይሠራ ነበር። ሆኖም ግን በዚያን ጊዜ ማለት በነሐሴ ወር 1959 ዓ.ም. 16 የሚሆኑ ዘፈኖቹን አዘጋጅቶ ለኢትዮጵያ ሕዝብ በሬዲዮ አቀረበ። ከዚያ በኋላ ከፍተኛ የሆነ የሕዝብ ፍቅርና አድናቆትን አትርፎ ክፍያው በቀን ወደ አሥራ አምስት ብር ከፍ አለ።

  ከዚያም በ1962 ዓ.ም. አያሌው የፈጣን ኦርኬስትራን ትቶ ብሔራዊ ቲያትር ገባ። ብሔራዊ ቲያትርም ለ3 ወራት ያህል ብቻ ከሠራ በኋላ ክፍሉን ለቆ በፖሊስ ሠራዊት የሙዚቃ ክፍል ተቀጥሮ እስከ 1966 ዓ.ም. የዘመን መለወጫ በዓል ድረስ ሲያገለግል ቆይቶ ከ1966 ዓ.ም. በኋላ ጥቁር አንበሳ የተባለ የግሉ የሙዚቃ ጓድ አቋቁሞ በ14ቱም ክፍላተ ሀገራት ተዘዋወሮ የሙያ ግዳጁን ተወጥቷል።

  አያሌው ከ3ዐዐ የሚበልጡ ዘፈኖችን የተጫወተ ሲሆን ከእነዚህም ውስጥ « ቻለው ሆዴ»፣ « ማሩኝ ዘመዶቼ »፣ « ማን ልበል ወዳጄ »፣ « በምላስ በስሎ »፣ « አላጐበድድም »፣ « ቀኔን እገፋለሁ »፣ « ወልደሽ ያሳደግሽኝ እናቴ ናፈቅሽኝ » የተሰኙት በሕዝብ ዘንድ በጣም ተወዳጅ ናቸው።
  ምንጭ፣ የአንጋፋ አርቲስቶች መዝገበ የሕይወት ታሪክ።
 • loader Loading content ...
  Load more...
loader Loading content ...

Comments (43)


loader Loading content ...