loader

Topics (2)


 • @Hamere   6 months ago
  Sewasewer
  ምነው? በጥቅም ተደልሎ ኅሊናን አቁስሎ የኋሊት ተሸሸቶ ላይደበቅ ከቶ ውስጣዊው ገመና እንድያው! አገሩን በጥብጦ ዓይንን አጉረጥርጦ ሰዉን ሰላም መንሳት እንደ አንበሳ ማግሳት አያሰኝም ጀግና! ወገኔ! እውን ልብ ካለ አርሮ ካልከሰለ እ... Read more
 • loader Loading content ...
 • @Hamere   7 months ago
  Sewasewer
  ሂሳብ ሳይንስ ፍልስፍና ዜማ ቅኔ ሳጠና አቤት! ኣእላፍ ነው ሚስጢሩ እዉቀትን መመርመሩ ገለባዉን ማበጠሩ ታዲያ! አሃዱ ላይ ረፈደብኝ ሰአት ሮጦ ነጎደብኝ ስል! ፕሌቶና ሰቅራጦሰ ዳርዊን ከክርስቶስ ኣዳም ስሚዝ ከማርክስ ኒች ሳርትረ ደ... Read more
 • loader Loading content ...
loader Loading content ...

Explanations (2)


 • @Hamere   6 months ago
  Sewasewer

  ምነው?

  በጥቅም ተደልሎ

  ኅሊናን አቁስሎ

  የኋሊት ተሸሸቶ

  ላይደበቅ ከቶ

  ውስጣዊው ገመና


  እንድያው!


  አገሩን በጥብጦ

  ዓይንን አጉረጥርጦ

  ሰዉን ሰላም መንሳት

  እንደ አንበሳ ማግሳት

  አያሰኝም ጀግና!


  ወገኔ!


  እውን ልብ ካለ

  አርሮ ካልከሰለ

  እንደ ዕሬትም ቢመር

  ራስን ነው መመርመር

  በእውነት ጎዳና


  ያኔ!


  ትዕቢትን ጋሻ አድርጎ

  ክሕደት ውስጥ መሽጎ

  በባዶ ቀረርቶ

  መሸለሉ ቀርቶ

  ጉራው ያበቃና


  እውነትም!


  የቆሰለው ሽሮ

  ያልተሣካው ሰምሮ

  ከራስ ጋር ተዋድዶ

  ዕርቀ-ሰላም ወርዶ

  ፍስሐ ይሰፍንና


  እንዲያውም!


  የውሸት ጥላሸት

  ያስጠላባት ሕይወት

  ብርሃን ትለብሳለች

  ሐቅን ትቀኛለች

  በጉባኤ ቃና

  ምንጭ : ግጥም በኪሮስ ብርሃነ

 • loader Loading content ...
 • @Hamere   7 months ago
  Sewasewer

  ሂሳብ ሳይንስ ፍልስፍና

  ዜማ ቅኔ ሳጠና


  አቤት!


  ኣእላፍ ነው ሚስጢሩ

  እዉቀትን መመርመሩ

  ገለባዉን ማበጠሩ


  ታዲያ!


  አሃዱ ላይ ረፈደብኝ

  ሰአት ሮጦ ነጎደብኝ


  ስል!


  ፕሌቶና ሰቅራጦሰ

  ዳርዊን ከክርስቶስ

  ኣዳም ስሚዝ ከማርክስ

  ኒች ሳርትረ ደስቶሺሰክን

  ጎጉል ቶለስቶይ ፑሽክን

  ያሬድ ቬቶቭን ዘርኣያእቆብን ስጨምር

  ኣንዱን ከአንዱ ስመርምር

  ከወቅት ጋር ስወዳደር


  ሆኖም


  ቀኑ መሸና አገደኝ

  ጨለማ ነግሶ ጋረደኝ

  ጊዜ ጊዜን ወሰነብኝ

  ገና ሳይነጋ መሸብኝ

  ባዶ ባዶኔቴን አጎላብኝ

  ምንጭ: ግጥም በኃይሌ ገብሬ

 • loader Loading content ...
loader Loading content ...

Comments (0)


  This user has no comment yet.