loader

Topics (31)


loader Loading content ...

Explanations (37)


 • @Haset   2 weeks ago
  Sewasewer

  “አንዱ ስለሁሉ ሞተ” (2ቆሮ 5÷14)

   


  የስሞነ ሕማማት ዕለተ ዓርብ በቤተክርስቲያናችን ልዩ ቀን ነው፡፡ ይህ ቀን ልዩ ነው፣ የማይታመመው ታሞ የዋለበት፣ የወደቁትን ከተረሱበት ከትቢያ የሚያነሳ እሱ ሲወድቅ ሲነሣ የዋለበት፣ ሕመምተኞችን የሚፈውስ እሱ ሲያቃስት የዋለበት፣ ከሲኦል የዲያብሎስ ግርፋት ነፃ የሚያወጣ ሲገረፍ የዋለበት ወልደ እግዚአብሔር ለወዳጆቹ ድኅነት በመስዋዕትነት ሙሽራ የሆነበት የደስታ ቀን የዓመፃ መዝገባችን መገልበጡ እርግጥ የሆነበት ፣ አሳዳጃችን አሳሪያችን ዲያብሎስ ከነወጥመዱ ድል የተነሳበት ቀን ነውና፣ ከዚህም የተነሳ በቤተክርስቲያን የተለያየ ምስጢራዊ ስያሜዎች ተሰጥቶታል፡፡

   

  የስቅለት ዓርብ ይባላል

  የዓለም ሁሉ መድኀኒት የሆነው ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ለአዳምና ለልጆቹ ሁሉ ቤዛ ሆኖ በመልዕልተ መስቀል ላይ ተሰቅሎ ለዓለም ድኅነት መስዋዕት ሆኖ የዋለበት ዕለት በመሆኑ የስቅለት ዓርብ ተብሏል (ማቴ 27፡35)

   

  መልካሙ ዓርብ (GOOD FRIDAY) ይባላል

  ይህም የሚያስገነዝበን ከስቅለተ ክርስቶስ በፊት ማንም ሰው ስያጠፋ በመስቀል ተሰቅሎ እንዲሞት ይደረግ ነበር፡፡ በተለይ በሮማውያንና በፈሪሳውያን ሕግ መስቀል የወንጀለኞች መቅጫ ነበረ፣ በዚህ ዕለት ግን ታሪክን የሚቀይረው፣ ነገርን የሚገለብጠው አምላክ የወንጀለኞች መቅጫ ምልክት የነበረውን መስቀል በደሙ ቀድሶ የምህረት ምልክት፣ የሕይወት አርማ፣ የዲያብሎስ ድል መንሻ ፣ የቤተክርስቲያን ጌጥ፣ የገዳማት ዘውድ፣ ስለአደረገውና በዕለተ ዓርብም በሞቱ ሕይወትን ስለአገኘን መልካሙ ዓርብ ተብሏል፡፡

   

  ነፍሳት ከሲኦል የወጡ መቼ ነው?

   

  ነፍሳት ከሲኦል የወጡ ዓርብ በሠርክ ነው፡፡ ሐዋርያው ጴጥሮስ “ነጻነት አወጃላቸው” ይላል፡፡ ጌታ በአካለ ነፍስ ወደ ሲኦል ወርዶ “ሰላም ለኵልክሙ” “ሰላም ለእናንተ ይሁን” እንዴት ሰነበታችሁ? አስታረቋችሁ ሲላቸው ነው፡፡ አዳም የተቀጠረች የድኅነት ዕለት ዛሬ ናት ተንሥኡ ለጸሎት ሲል ነፍሳትም ምስለ መንፈስከ አሉ፡፡ጌታም “በጽልመት ውስጥ ያላችሁ ውጡ፣ በሲኦል ያላችሁ ተገለጡ ብርሃንም አዩ” ብሎ እልፍ ፀሐይ ቢገባበት የማይለቅ የሲኦልንም ጨለማ ብርሃነ መለኮቱን ነዛበት ያኔ ጨለማው ለቀቀ የዚያን ጊዜ ወጐዩ ዓቀበተ ሥጋ መናፍስት /አጋንንት/ በዚህ ጊዜ ነፍሳትን የተቆራኙ አጋንንት ሸሹ፣ እለ ውስተ ሲኦል ጻኡ፤ ወእለ ውስተ ጽልመት ተከሠቱ ብሎ ባሕረ እሳትን ከፍሎ ወደ ገነት አገባቸው፡፡

   

  በዕለተ ዓርብ ስንት ታምራት ታይቷል?

  ጌታ ሁሉ ተፈጸመ ብሎ ቅድስት ነፍሱን ከቅድስት ስጋው በራሱፈቃድ ከለየ በኋላ አምላክነቱን ለመግለፅ የታዩ ተአምራት የሚከተሉት ናቸው፤

   

  በሰማይ፤ (ማቴ 24፦29 እና 27፦45)

   

  1. ፀሐይ ጨለመች

  2. ጨረቃ ደም ሆነች

  3. ከዋክብት ረገፉ

   

  በምድር፤(ማቴ 27፦51_53)

   

  4. የቤተ መቅደስ መጋረጃ ከላይእስከ ታች ተቀደደ

  5. ምድር ተናወጠች

  6. መቃብሮች ተከፈቱ

  7. ሙታን ተነሱ

   

  ለምን 400 ጊዜ እግዚኦ ይባላል?

  በዚሁ ዕለት ስአራት መዓዘን እየዞርን 400 ጊዜ ምሕላ እናደርጋለን፣ ምሕላ የምናደርገውም አምስት ሺህ አምስት መቶ ዘመን የአዳም ልጆች በሲኦል ሆነው አቤቱ ይቅር በለን ብለው የለመኑትን ለማስታወስ ነው ከምሕላው በኋላ በወይራ እየተጠበጠቡ የንስሐ ስግደት እንደየ አቅሙ ይሰጣል። ከምን የተነሣ ነው ሲባል የክርስቶስን መከራ እንቀበላለን። በክርስቶስ ክርስቲያን ተብለናልና። የኛን መከራ ተቀብሎ እንዳዳነን እሱ የተቀበለውን መከራ እንቀበላለን፣ እንገረፋለን፣ አላውያን ነግሥታት፣ አላውያን መኳንንት፣ ሃይማኖታችሁን ካዱ ሲሉን ቢጎርፉን እንገረፋለን በሰይፍ ሲመቱን፣ ሲሰቅሉን፣ መከራውን በጸጋ እንቀበላለን ለማለት ነው፡፡ እሱ የተቀበለው መከራ ተቀበሉ

  ተብሎ ታዟልና።

   

  በዕለተ ዓርብ ንሴብሖ ለእግዚአብሔር የሚባለው ለምንድነው?

  በስቅለት፣ ዓርብ ማታ ከእግዚኦታ /ምሕላ/ በኋላ ንሴብሖ ይባላል፡፡ ምክንያቱም እስራኤል በምድረ ግብጽ 215 ዘመን በባርነት ቀንበር ሲገዙ ከነበሩ በኋላ በሙሴ መሪነት የኤርትራን ባሕር ስላሻገራቸው “ንሴብሖ ለእግዚአብሔር ስቡሐ ዘተሰብሐ” እያሉ አመስግነውታል፡፡ እኛ ደግሞ ከአጋንንት አገዛዝ ነጻ አውጥቶ ባሕረ እሳትን ከፍሎ ወደ ገነት ስለአገባን “ንሴብሖ" እያልን እናመሰግነዋለን።ንሴብሖ ለእግዚአብሔር ከተባለ በኋላ እግዚአብሔር ይፍታህ ይባላል። እግዚአብሔር ይፍታህ የሚባልበት ምክንያትም ካሣ ከተፈጸመ ወዲያ፣ ልጅነት የተመለሰ፣ ነጻነት የተገኘ ነፍሳት ከሲኦል የወጡ ስለሆነ ነው፡፡

  በዓመት አንድ ጊዜ የምናገኘው ይህ ዕለት ቀራንዮን የምናስብበት ነገረ መስቀሉን የምናስተውልበት እንጂ ስለምድራዊ ኑሮአችን ስንባክን ኃጢዓት ስንሰራ የምንውልበት ሊሆን አይገባም።

   

  ለብርሃነ ትንሣኤው አምላካችን በሰላም ያድርሰን፡፡

   

  ምንጭ:- የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስትያን ታሪክ (አቡነ ጎርጎርዮስ) • loader Loading content ...
 • @Haset   7 months ago
  Sewasewer

  Ethiopian artist, Yonatan Wondwosen, was born in

  1988 in Addis Ababa, Ethiopia. He graduated from

  Addis Ababa University Alle School of Fine Arts

  & Design of in Sculpture Department.

  He has participated in several workshops and courses

  in photography, bronze casting & illustration of

  books. He is now a full-time Studio Artist.

  He has participated in several group exhibitions in Ethiopia, including:

  – Alliance Ethio-Francaise

  – American Embassy

  – Italian Cultural Institute

  – Gojo Art Gallery

  – Beharawi Theater

  – “Listro” School of Fine Arts Gallery in Addis Ababa University

  – Taitu Hotel


  Reference: ART OF ETHIOPIA


 • loader Loading content ...
 • @Haset   7 months ago
  Sewasewer

  Born in 1977 in Assela, Ethiopia, Yosef Lule typically

  draws inspiration for his paintings from daily life, as

  well as from his own travels around the world. He once

  moved to the South of France to paint for an entire

  year. It is his personal conviction that an artist’s work

  should bring about happiness rather than sadness.

  He also believes in nurturing an original style, saying,

  “It is important for an artist to maintain his own

  individual style and develop it further.”

  He graduated from the Addis Ababa University School

  of Fine Arts and Design in 2001. Since then, he has

  worked on several projects for UNICEF and UNFPA,

  and has been a part of several multicultural

  artists’ residencies.

  Nationally, his work has been displayed in group

  exhibitions at the Habesha Art Studio, Alliance

  Ethio-Francaise and the French Embassy. He has

  also held solo exhibitions at the National Theatre

  Art Gallery and the Alliance Ethio-Francaise.

  His works have also been showcased internationally in

  France, Switzerland and the United States. He currently

  works as a full-time artist at the Habesha Art Studio.

  Reference: ART OF ETHIOPIA


 • loader Loading content ...
 • @Haset   7 months ago
  Sewasewer

  Yonas Degefa was born in Addis Ababa in 1987. He took

  some courses at Russian Cultural Center (Pushkin) and

  later joined Addis Ababa University Alle School of Fine

  Arts & Design, where he graduated in Arts.

  Yonas’ initial interest was to write poems on a regular

  basis. He also maintained a personal diary. Over the

  years, upon analyzing his diary, he realized that romance

  and the explosive nature of poetry could be reflected

  in paintings. In his endeavors of finding the visual

  counterpart of his poems, he features female figures in

  his paintings, as a sign of beauty and romance.

  Yonas’ works mainly focusses on Ethiopian calligraphy,

  icon, tradition and colors. He has participated in

  different group exhibitions and fairs apart from

  competing in various art competitions.

  Some of his exhibitions:

  2009 & 2010 Alliance Ethio-Francaise

  2011 Art Fair around Boston Spa

  2011 The forth Ethiopian Annual Art Exhibition

  2012 Alliance Ethio-Francaise

  Reference: ART OF ETHIOPIA


 • loader Loading content ...
 • @Haset   7 months ago
  Sewasewer

  Zerihun Yetmgeta has established a trademark with his

  magic scroll paintings based on weaver’s tools and strips of

  parchment framed on pieces of wood. His unique art form

  “transforms traditional motifs into a modern idiom”, in the

  words of art critic Elizabeth Biasio.

  He hails from what was known as the Renaissance Period of

  Ethiopian Art. After receiving his Art Diploma from Emperor

  Haile Selassie I in 1967, he opened his first one-man show

  to the public. It consisted of a mixture of canvas, skin and

  wood, and was such a success that half his artworks were

  sold at the exhibition itself.

  Owing to his extraordinary choice of medium, numerous

  art books and other publications have featured his work.

  His art boldly tackles major Ethiopian issues, and has been

  displayed at many museums around the world.

  He has been recognised not just as an Ethiopian artist,

  but as a renowned African artist. He won first place at

  the prestigious Second Dakar Biennale of Contemporary

  African Art in 1992, and secured second place at the

  Kenyan Panorama Awards in 1994. He is currently a

  member of the Fine Arts Faculty at Addis Ababa University,

  where he works as an Instructor of Graphic Art.

  Reference: ART OF ETHIOPIA


 • loader Loading content ...
 • @Haset   7 months ago
  Sewasewer

  Born in 1970, Yitagesu Mergia was born in

  Addis Ababa. Since graduating from the

  Addis Ababa University School of Fine Arts

  and Design, he has conducted a number

  of solo and group art exhibitions at venues

  that include the Bulgarian Embassy, Greek

  Community, Italian Cultural Institute,

  Swedish School, Alliance Ethio-Francaise,

  National Museum and various hotels

  throughout Addis Ababa.

  His paintings are also on permanent display

  at the American, Egyptian and German

  embassies in Addis Ababa

  Reference: ART OF ETHIOPIA


 • loader Loading content ...
 • @Haset   7 months ago
  Sewasewer

  Yared Olivelli was born in 1985. He graduated from the

  Addis Ababa University School of Fine Arts and Design

  in Graphics Art in 2010.

  Since 2010, he has been working as an Instructor at the

  School of Fine Arts & Design of Addis Ababa University.

  Yared’s works have been featured in solo and group

  exhibitions in Addis Ababa and other countries.

  These include:

  2004 Red Cross Hall Dessie

  2005 Adama

  2007 Makush Art Gallery- Addis Ababa

  2008 Lalibela Exhibition Centre

  2008 “Listro” School of Fine Arts Gallery with

  international artists in Addis Ababa & Germany

  2009 At US Embassy Addis Ababa, Ethiopia

  Reference: ART OF ETHIOPIA

 • loader Loading content ...
 • @Haset   7 months ago
  Sewasewer

  Despite his international background, Worku

  Goshu remains a genuine Ethiopian artist. He

  began his Art education at the Addis Ababa

  University School of Fine Arts and Design before

  earning a scholarship to the Academy of Fine

  Arts in Krakow, Poland. He graduated from there

  with a Master’s degree in Pure and Applied

  Graphic Art.

  Soon after his marriage, he returned to Ethiopia,

  and taught at the Addis Ababa University School

  of Fine Arts and Design for 27 years. Although his

  exhibitions are rare, he has been part of the

  Art of Ethiopia show since its 2nd year. The

  privileged few who have seen his art would agree

  that it is an experience in itself that serves to

  open your imagination. His paintings reflect his

  sources of inspiration - they serve as a constant

  interpretation of Ethiopia’s artistic traditions,

  yet are still tinged with a modern appeal.

  At present, Worku resides in Addis Ababa, where

  he owns the Goshu Art Gallery along with his

  wife Barbara.
  Reference: ART OF ETHIOPIA

 • loader Loading content ...
 • @Haset   8 months ago
  Sewasewer

  መሐሙድ አህመድ አዲስ አበባ አሜሪካን ግቢ አካባቢ (መርካቶ) በ1933 ዓ.ም. ተወለደ። በየዓመቱ በሚመጣው የቡሄ ጨዋታ ላይ የድምፁን ምንነት ያሳወቀው መሐሙድ በወቅቱ እነ ጥላሁን ገሠሠ የሚያሰሙትን ዘፈን በሚማርበት የአርበኞች ት/ቤት ውስጥ ሲዘፍን የሰሙት አስተማሪው ድምፁን ስለወደዱለትና በየዓመቱ በሚከበረው የወላጆች ቀንም ይዘፍን ስለነበር ወደ ሙዚቃው ዓለም በዚሁ የተነሳ ለመግባት ችሏል ።

  እነ ጥላሁን ገሠሠ ፣ ታምራት ሞላ፣ ተዘራ ኃ/ሚካኤል እና ሌሎችም በሚጫወቱበት አሪዞና በሚባል የምሽት ክበብ ውስጥ በሌላ ስራ ተቀጥሮ ይሠራ ስለነበር የእነዚህን አንጋፋ ዘፋኞች ሙዚቃ በማጥናትና በመዝፈን ይጫወት ስለነበር የዘፈን ችሎታውን ያዩት የምሽት ክበቡ ባለቤት ( ግብፃዊ ) አበረታትተውት እነ ጥላሁንን በማጀብ እንዲሠራ ፈቀዱለት። ሻለቃ ግርማ ሀድጉ ግጥምና ዜማ ፈልገው አውጥተውለት የመጀመሪያውን « ጭቅጭቁ ቀርቶ » የሚለውን ዘፈን ዘፈነ።

  ከዚያም ኦሪዞና የሚባለው የምሽት ክበብ ሲዘጋ « ሾፌሮች » ቡና ቤት ወደ ሚባለው የምሽት ክበብ በመሄድ የነ ገላን ተሰማና፣ የታምራት ሞላን ዘፈኖች ሲጫወት ለመቀጠር እንዲችል በአዳራሹ ውስጥ ለተሰበሰበው ሕዝብ ለፍርድ ይቀርባል ። በዚህን ጊዜ « ተስፋ አትቁረጪ » እና « የቡጊ ጨዋታ » የተባሉትን ዘፈኖች ደጋግሞ ተጫውቶ ለመቀጠር ቻለ። በተመሳሳይ ሁኔታም ጃንሜዳ በሚገኘው የክብር ዘበኛ የሠራዊቱ ሆስፒታል ውስጥ ለሠራዊቱና ለቤተሰቦቻቸው በየ15 ቀናት የሙዚቃ ትርኢት ስለሚቀርብ ከዚያም ለድጋሚ ፈተና ቀርቦ በ1955 ዓ.ም. በሲቪልነት ተቀጠረ። መሐሙድ ካለፈባቸው የችግር ሕይወት በተጨማሪ የክቡር ዘበኛ ኦርኬስትራ ትልቁ ት/ቤቱ እንደነበረም ይናገራል ።

  የመሐሙድ የመጀመሪያ ዘፈኑም « አላወቅሽልኝም » የተባለው የጉሮሮው መክፈቻ ሲሆን « ጠይቀሽ ተረጂ » « የፍቅር አዳራሽ » የተባሉት ዘፈኞቹም ለመድረክ ከመቅረባቸው በፊት ለግሩንዲንግ ተሽጠው በቴኘ የተቀረፁ ስራዎቹ ነበሩ። መሐሙድ በድምፁ ታላቅነት በሀገር ውስጥ ብቻ ሳይሆን በአፍሪካና በአውሮፓ ትልቅ ክብርና ዝና ያለው አርቲስት ነው።  ምንጭ፣ የአንጋፋ አርቲስቶች መዝገበ የሕይወት ታሪክ።
 • loader Loading content ...
 • @Haset   8 months ago
  Sewasewer

  ታምራት ሞላ በ1939 ዓ.ም. በጎንደር ክ/ሀገር ተወለደ። ታምራት የ1ኛ ደረጃ ትምህርቱን እዚያው ጎንደር ከጨረሰ በኃላ ወደ አዲስ አበባ በመምጣት አድቬንቲስት ሚስዮን ት/ቤት በመግባት ትምህርቱን ተከታተለ። በ1951 ዓ.ም. በቀድሞ ክብር ዘበኛ በወታደርነት በመቀጠር እስከ 1954 ዓ.ም. ጃዝ፣ ሳክስፎንና ሌሎችንም የሙዚቃ መሣሪያዎች መጫወት ጀመረ። በድምፁም ጭምር ስሜቱን ለማርካት በ1955 ዓ.ም. በምድር ጦር ኦርኬስትራ ተቀጠረ። ታምራት ለመጀመሪያ ጊዜ ካዜማቸው ዘፈኖቹ « ታምሜ ተኝቼ »፣ « ዘወትር ብርቅነሽ » የተሰኙትን ዘፈኞቹን ለመጀመሪያ ጊዜ በመድረክ ላይ ሲያሰማ በተመልካቾች ዘንድ ከፍተኛ አድናቆትን አትርፈውለት ነበር።

  ታምራት የዘፈናቸው ዘፈኖች በርካታ ቢሆኑም « አስታውሺኝ »፣ « መሞት አለ ለካ »፣ « የለችም » እና « ጊዜው ለጨነቀው » የተሰኙት ዜማዎቹ የተዋጣላቸው ከመሆናቸው ባሻገር በሕዝብ ዘንድ ተወዳጅነት ያላቸው ናቸው ።  ምንጭ፣ የአንጋፋ አርቲስቶች መዝገበ የሕይወት ታሪክ።
 • loader Loading content ...
  Load more...
loader Loading content ...

Comments (9)


loader Loading content ...