loader

Topics (18)


loader Loading content ...

Explanations (21)


 • @Tola (ቶላ)   2 years ago
  ከተኛ አንበሳ ዞር ዞር ያለ ቀበሮ ይሻላል!
  How about these? Depending on when the action occurs ...

  • እሷ መሄድ ስላልቻለች፣ ልጆቹ እንዲሄዱ ኣድርጋለች።
  • እሷ መሄድ ስለማትችል፣ ልጆቹን እንዲሄዱ ታደርጋለች።
  • እሷ መሄድ ባትችልም፣ ልጆቹ እንዲሄዱ ታደርጋለች።
  • እሷ አልሄደችም ልጆቹ ግን ሄደዋል።
 • loader Loading content ...
 • @Tola (ቶላ)   2 years ago
  ከተኛ አንበሳ ዞር ዞር ያለ ቀበሮ ይሻላል!
  ዳግማዊ አፄ ምኒልክ እየተሰራ የሚላክላቸው ገሶ እና ማረሻ ስስ እየሆነ ቢያስቸግራቸው የሚከተለውን ደብዳቤ ለደጃዝማች ደምስ ላኩ።

  -----------

  ይድረስ ከደጃዝማች ደምስ፣

  እስካሁን ድረስ የሚመጣልን ገሶ እና ማረሻ ስስ እየሆነ ስራ ያስፈታ ጀመር። አሁን የማረሻ እና የገሶ ስራ መዝገብ የሚሆን አሰርቼ ሰድጃለሁና ገሶውንም ማረሻውንም በዚህ በሰደድኩልህ ልክ እየተሰራ እንዲመጣልኝ ይሁን። ደግሞ የዶማ አይነትም መዝገብ ጨምሬ ሰድጃለሁና ዶማም በዚሁ አይነት እየተሰራ እንዲመጣልኝ። ነገር ግን በደሃው ሸክም እንዳይበዛበት ሁለት መቶ ገሶ በሚመጣበት ጊዜ መቶውን ዶማ መቶውን ገሶ፣ አራት መቶም አምስት መቶም ገሶ በሚመጣበት ጊዜ እንደዚሁ ገሚሱን ዶማ ገሚሱን ገሶ ማድረግ ነው።

  ጥር ፳፰ ቀን ፲፰፻፺፱ ዓ.ም. አዲስ አበባ ተፃፈ።

  ምንጭ:
  አጤ ምኒልክ በአገር ውስጥ የተፃፃፏቸው ደብዳቤዎች
  በጳውሎስ ኞኞ
 • loader Loading content ...
 • @Tola (ቶላ)   2 years ago
  ከተኛ አንበሳ ዞር ዞር ያለ ቀበሮ ይሻላል!
  የአፂ ፋሲል ግቢ አስራ ሁለት በሮች አሉት። አሁን ያለው ዋና የመግቢያ በር ከጥንቶቹ በሮች አንዱ ሳይሆን በጣልያን ወረራ ዘመን የተሰራ ነው። የጥንቶቹ በሮች ስያሜ በአቀማመጣቸው ቅደም ተከተል ሲዘረዘሩ የሚከተሉት ናቸው።
  1. ጃንተከል በር (ፊት በር) : ንጉሰ ነገስቱ የሚገቡበት በር።
  2. ወምበር በር : ዳኞች የሚገቡበት በር።
  3. ተስካር በር : ለሙታን መታሰቢያ የሚመጡ ታዳሚዎች የሚገቡበት በር።
  4. አዛዥ ጥቁሬ በር : የግቢው አዛዞች የሚገቡበት በር።
  5. አደናግር በር : ጥጥ ፈታዮች የሚገቡበት በር።
  6. ኯሊ በር : የነገስታቱ አጃቢዎች የሚገቡበት በር።
  7. እምቢልታ በር : የመሳሪያ ተጫዋቾች የሚገቡበት በር።
  8. ራስ በር (ቇረኞች በር) : መሳፍንት እና መኯንንት የሚገቡበት በር።
  9. ባልደራስ በር : የቤተመንግስት ፈረሶች አለቃ የሚገባበት በር።
  10. ርግብ በር (ቀጭን አሸዋ በር) : ስጦታዎች የሚገቡበት በር።
  11. እንኮዬ በር : የእቴጌ ምንትዋብ እናት ልዕልት እንኮዬ የሚገቡበት በር።
  12. ግምጃ ቤት ማርያም በር : ወደ ግምጃ ቤት ማርያም የሚያስኬድ በር።

  ምንጭ:
  ህብረ ኢትዮጵያ -- በቴዎድሮስ በየነ


 • loader Loading content ...
 • @Tola (ቶላ)   2 years ago
  ከተኛ አንበሳ ዞር ዞር ያለ ቀበሮ ይሻላል!
  ብላቴን ጌታ ማህተመ ስላሴ ወልደመስቀል ስለ ምሳሌያዊ ንግግሮች ጠቀሜታ የሚከተለውን ይላሉ --

  "... ምሳሌዎች አንዳንድ ጊዜም ተረቶች የምንላቸው በልዩ ልዩ ሁናቴ የሀገራችንን ጠቅላላ መልክ የሚያሳዩ ናቸው፤ እነዚህም በሕዝብ እጅ ገብተው በዘመን ብዛት መልካቸው ቢለወጥም ከተመራማሪዎች፤ ከአርቆ ተመልካቾች፤ ከአስተዋዮች፣ በእውቀት ከበሰሉ ሰዎች የተገኙ መሆናቸው የማያጠራጥር ነው።  በተለይም በህሊና ርትዕን መሰረት በማድረግ የሚነገሩት ምሳሌዎች ምን ያህል የማስረዳት ኃይለ ቃል እንዳላቸው መገንዘብ አስቸጋሪ አይደለም፤ እነዚህም ከአባት ለልጅ እየተላለፉ ለእኛ የደረሱን ምሳሌዎች በአለፈው ጊዜ የሕግ አንቀፆች ሆነው በየአደባባዩ ሲሰራባቸው ቆይተዋል።"

  ይሉና የሚከተሉትን በሕግ ረገድ ሲጠቀሱ የነበሩ ምሳሌያዊ ንግግሮችን ያስረዳሉ :-

  • ሞኝ ወርውረው ቢስቱት ያልወጉት ይመስለዋል።
  ማስተዋል እና ማመዛዘን ያነሰው ሰው ባይመታም፤ ባይረታም፤ በአቅም ማነስ ወይም በልዩ ምክንያት ቢሳትም ድርጊቱ እንዳልተፈፀመ ያህል ይቆጥረዋል። እንደእውነቱ "የወጋ ቢረሳ የተወጋ አይረሳ" የተባለውን ምሳሌ መዘንጋት አይገባም።

  • ዋስ ካለው ዱቄትህን ለንፋስ አበድረው።
  ብድር ጠያቂው ያልታመነ ወይም ንብረቱ ዝቅተኛ ቢሆንም ዋሱ አጥጋቢ ከሆነ በሱ አማካኝነት ብድሩ ይሰጠው ማለት ነው።

  • ከአፍ የወጣ ቃል ከእጅ የወደቀ እንቁላል።
  ከእጅ የወደቀ እንቁላል መፍረጡ፣ መፍረሱና መሰበሩ እንደማይጠረጠር ሁሉ ከአፍ የወጣውን ቃልም እሰው ጆሮ ስለሚደርስ ማስቀረት አልመቻሉን ስለመግለፅ።

  • አሳ ጎርጉዋሪ ዘንዶ ያወጣል፤ የሰው ፈላጊ የራሱን ያጣል።
  አሳ በመቃጥን እና በመረብ ሲያዝ አልጠግብ ባይ በእጅ ለመያዝ አለቱን በመፈንቀል ዘንዶ እንዲያወጣ፤ ሰርተው ያላገኙትን የሰው ሀብት አንጋጦ መመኘትም የራስን እስከማጣት ያደርሳል።

  • ሳይበሉ ማግሳት፣ ልክበር ብሎ መጏጏት።
  ሳይበሉ ማግሳት እንደማይቻል ሁሉ፣ ሳይሰሩ ለመክበር መመኘትም በሃሳብ ውቅያኖስ ተውጦ እንደመቅረት ያለ ነው።

  • ሳይተርፋት አበደረች፣ ሳትቀበል ሞተች።
  ለብልጭልጭ እና ለከንቱ ነገር እንዲሁም ለይወቁልኝ የሚሰራ ራሱን እንኯ እንደማይጠቅም፤ ለውዳሴ ከንቱ ያበደረችም ሳትቀበለው ሞተች።

  • የወጋ ቢረሳ፣ የተወጋ አይረሳ።
  ሞት ቢዘገይም እንደማይቀር ሁሉ በደል ቢቆይም አይረሳም፤ በነገር የወጋው ቢዘነጋ እንኯ የተበደለው ሲቆረቁረው ይኖራል፤ ቁስሉ ቢሽርም መዳው አይጠፋም።

  • አመልና ቀንድ በስተሇላ ይበቅላል።
  የእንስሳት ቀንድ ቆይቶ እንደሚወጣ ሁሉ፤ ሰውም በጊዜ ብዛት የሚያስከትለው ነገር ስለማይታወቅ ፍፃሜውን ሳታይ በመጀመሪያ አትውደደው፣ አታመስግነው።

  • እወቁኝ ብሎ ደብቁኝ።
  ወረተኛ ሰው በመጀመሪያ አለሁ አለሁ በማለት ባለሟል ወይም ዘመድ የምስልና በሕዋላ የአገዳ መብራት ሲሆን ይታያል። እንዲሁም በሰላም ጊዜ ፎካርና ባለጉራ ሆኖ ጦርነት ሲመጣ ለሚርበደበድ እና በነገር ሰው ሲያጠቃ ቆይቶ በተገለጠበት ጊዜ እንዳልሰማ ለመሆን ለሚጣጣር ወስላታ ሊጠቀስ ይችላል።

  • ጥንቱን ባልዘፈንሽ፣ ከዘንፈንሽም ባላሳፈርሽ።
  ቀድሞውኑ አለመጀመር፣ አቅምን ማወቅ፣ በጉዳዩ አለመግባት ደግ ነው፤ ከጀመሩ ግን በነገሩ፤ በሁኔታው መዝለቅ ይገባል።

  • ወስፌ ሲለግም ቅቤ አይወጋም።
  ሰው ያለፍቃዱ ቢሰራ ፈር አያወጣም፤ የሚያውቀውን እንክዋን አላውቅም ሊል ይችላል፤ ጉዳዩንም ከፍፃሜ አያደርስም።

  • እንባ ሲሻኝ፣ ጢስ ወጋኝ።
  ስፈልገው ተወሳልኝ፤ ስመኘው ሳለ ሆነልኝ ወይም እንደፍላጎቴ ታዘዝሁ።

  ምንጭ:
  የብላቴን ጌታ ማህተመ ስላሴ ወልደ መስቀል ስብስብ ስራዎች
 • loader Loading content ...
 • @Tola (ቶላ)   2 years ago
  ከተኛ አንበሳ ዞር ዞር ያለ ቀበሮ ይሻላል!
  የኢጣልያ ፋሺስት መንግስት ኢትዮጵያ ላይ ወረራ ባደረገ ጊዜ ከጠላት ጋር ሆነን አገራችንን ኢትዮጵያን አንወጋም ካሉት የኤርትራ ተወላጆች መካከል አንዱ አቇ ሰለባ ናቸው። በሁዋላ ደጃዝማች የተባሉት አቇ ሰለባ በኤርትራ በነበረው የኢጣልያ ጦር ሰራዊት ውስጥ ነበሩ። አቇ ሰለባ በኢጣልያ መንግስት ዘንድ የታመኑ እና የተከበሩ ሰው ነበሩ። በኢጣልያኖች ዘንድ ክብርና ማዕረግ ይኑራቸው እንጂ ያገራቸው የኢትዮጵያ ጉዳይ ዘወትር ይከነክናቸው ነበር። ኢጣልያኖች በኢትዮጵያ ላይ የሚያደርጉትን ምክር እየሰሙ ይቆጫቸው ነበር።

  አቇ ሰለባ ለኢጣልያ ታማኝነታቸውን እያረጋገጡ ውስጥ ውስጡን ግን በኢጣልያ ላይ አድማ ያካሄዱ ጀመር። አቇ ሰለባ በኢትዮጵያ ላይ ጠላት የሚዶልተውን ዱለታ አጥብቀው የሚቃወሙ 29 ጉዋደኞች አበጁ። እነዚህ 29 የኤርትራ ክፍለ አገር ተወላጆችና የኢጣልያ ጦር ሰራዊት አባሎች በድብቅ የኢትዮጵያን የአገር ፍቅር ማህበር አቇቇሙ። መስከርም አንድ ቀን 1928 ዓ.ም. የእንቁጣጣሽ እለት አቇ ሰለባ በጦር ሰራዊት ውስጥ የጥበቃ ሥራ ወይም የፓትሮልነት ሥራ ተርኛ ሆኑ። ሌሊቱን በጥበቃ ላይ እንዳሉ የበላያቸው ኢጣልያዊው ኦፊሰር የመጨራሻውን ጉብኝት እስኪያደርግ ጠበቁ። የበላይ አለቃቸውን ኢጣልያዊው መኮንን የጥበቃው ሥራ በትክክል መካሄዱንና ሌሊቱን ፀጥ ያለ መሆኑን ካወቀ በህዋላ መልካም ተግባራቸውን እነ አቇ ሰለባን አመስግኖ እና አበረታቶ ወደ መኝታው ሄደ።

  ከዚህ የመጨረሻ ፍተሻ በህዋላ ነው አቇ ሰለባ እና 29 ጉዓደኞቻቸው የማህበራቸውን ሥራ የጀመሩት። 12ኛ ዓመት ቁጥር ሁለት ኢትዮጵያን ኦብዘርቨር ስለዚያች ሌሊት ተግባር ሲገልፅ እነ አቇ ሰለባ 13,500 ጠመንጃ፤ 5 መድፍ፤ 30 አልፓይን የሚባለውን መድፍ 12 ረጃጅም መድፍ ይዘው ኢጣልያኖችን እራሳቸውን ባስደነቀ ሁኔታ ሌሊቱን ያን መሳሪያ ሁሉ ይዘው ጠፉ።

  በ30 ሰዎች የተመሰረተው የኢትዮጵያ ፍቅር ማህበር የኤርትራ ተወላጆችን አባላት ያን ሁሉ መሳሪያ ይዘው መቀሌ ደረሱ። በመቀሌ ከደጃዝማች ኃይለስላሴ ጉግሳ ዘንድ ቀርበው ለኢትዮጵያ ለመዋጋት መነሳታቸውንና ኢጣልያን መክዳታቸውን ነገሩ። ኢትዮጵያን ከድቶ የኢጣልያ አሽከርነት የገባው ኃይለስላሴ ጉግሳ እነ አቇ ሰለባን ይዞ ለእትአልያኖች ለማስረከብ አስከበባቸው። እነ አቇ ሰለባ በሰው ብዛት የማይወዳደሩትን የደጃች ኃይለስላሴ ጉግሳን ጦር ለመዋጋት ተዘጋጁ።በነገሩ መሃል የአክሱሙ አስተዳዳሪ ንቡረዕድ ተስፋዬ ገብተው ሰለባ ወልደ ስላሴና ደጃች ኃይለስላሴ ጉግሳ እንዲታረቁ አደረጉ። እርቁ፤ ሰለባ ወልደ ስላሴ የያዙትን መሳሪያ በሙሉ ለደጃች ኃይለስላሴ እንዲያስረክቡና ኃይለስላሴ ጉግሳ ደግሞ ከትግራይ በሰላም እንዲወጡ እንዲፈቅድላቸው የሚል ነበር።

  ሰለባ ወልደ ስላሴ በዚህ እርቅ አልስማማ ብለው ከደጃች ኃይለስላሴ ጋር ለመዋጋት ተዘጋጁ። የአክሱም ቀሳውስትና መነኮሳት, ንቡረዕዱ ጭምር እነአቇ ሰለባ ወልደስላሴን ተጭነው ስለያዟቸው በእርቁ ተስማሙ። ከሀዲው ደጃዝማች ኃይለስላሴም እነ ቀኛዝማች ሰለባ ወልደስላሴ ከኢጣልያ ዘርፈው ያመጡትን መሳሪያ በሙሉ አስቀርቶ እነኛ ጀግኖችን አንድ አንድ የታጠቁትን ሽጉጥ ብቻ ይዘው ወደ መሃል ኢትዮጵያ እንዲሄዱ ተፈቀደ።

  እነ ሰለባ ወደ አማባልጌ ሄዱ። በአምባላጌም ከደጃች መኮንን እንዳልካቸው ጋር ተገናኙ። ምግብና ጥይት ተቀብለው ጉዟቸውን ወደ አዲስ አበባ ቀጠሉ። የነሰለባ ወደ አዲስ አበባ መጉዋዝ በከሃዲው በደጃች ኃይለስላሴ ጉግሳ ዘንድ እንደተሰማ ራያ አዘቦ ውስጥ እንዲፈጁ አድፋጭ ጦር ቀድሞ ጠበቃቸው። ቆቦን አልፎ ቀውቂ ከሚባል ቦታ ላይ ሲደርሱ ጥቅምት 21 ቀን ያ የታዘዘ ጦር ገጠማቸው። ከአቇ ሰለባ ሶስት ሰዎች ሞቱ። አራት ሰዎች ቆሰሉ። አቇ ሰለባ ክፉኛ ቢቆስልም እስከ መጨረሻው ጥይት ድረስ ከነኛ ወመኔዎች ጋር ተታኩሰው ጥይታቸው ሲያልቅ ሸሹ። ከብዙ ድካም በህዋላም ደሴ ገቡ።

  ደሴ እንደደረሱ አቇ ሰለባ ወደ አዲስ አበባ ሄደው እንዲታከሙ አስፋው አሊ በሚነዱት አውሮፕላን ወደ አዲስ አበባ ተላኩ። አዲስ አበባ ሆስፒታል እንደተኙ የቀኝ አዝማችነት ማዕረግ ተሰጣቸው። ሁለት ከፍተኛ ኒሻኖችንም ተሸለሙ።

  የማይጨው ጦርነት በተጀመረበት ግዜ ቀኛዝማች ሰለባ ገና ማገገማቸው ስለነበረ የኢትዮጵያ ጦር ማይጨው ሲዘምት ቀኛዝማች ሰለባ ለጊዜው አዲስ አበባ ከተማን ጠብቁ የተባሉትን ትዕዛዝ ቢቀበሉም የኢትዮጵያ ጦር ወደ ማይጨው ከዘመተ በህዋላ ጀግናው ሰለባ የወኔ ለቅሶ ጀመሩ። ከአለቃቸው ከደጃች ይገዙ ዘንድም ገብተው "ከኤርትራ ተነስቼ ኢጣልያን ከድቼ እዚህ የመጣሁት ለዋጋ እንጂ ልቀመጥ አይደለም። ይልቀቁኝ። በፍቃድዎ ባይለቁኝ በፍቃዴ የማደርገውን ላደርግ ነኝ" አሏቸው። ደጃች ይገዙ ያዲስ አበባን ሹማምንት ሰብስበው ጉዳዩን አዋዩ። የሰለባን ሁኔታ ያዩና የሚያውቁ ሹማምንት የንጉሱን ትዕዛዝ ፈርተው ሰለባን ላለመልቀቅ ይያስቡም ሰለባ ግን ቢከለከሉ ጠፍተው መሄዳቸው ስለታወቀ በፈለጉበት አቅጣጫ እንዲዘምቱ ተፈቀደላቸው።

  እውነተኛው ኢትዮጵያዊ ቀኛዝማች ሰለባ የደጃች ይገዙን ፈቃድ እንዳገኙ ያራዳን ዘበኛ ሰብስበው ጃንሜዳ ላይ ያሰለጥኑ ጀመር። ስልጠናው ካለቀ በህዋላ በጥር ወር በ1928 ዓ.ም. ልጅ ኃይለመስቀልን፤ በጅሮንድ ተክለስላሴን፤ ቀኛዝማች አሰፋ ባህታን ከነ ጭፍሮቻቸው ይዘው ከደጃዝማች በየነ መርዕድ ጦር ጋር ተደባለቁ። ወዲያው ቀኛዝማች ሰለባና ቀኛዝማች አሰፋ ባህታ ከጦሩ ተለይተው ለበሽ ዲስ ከተባለው ቦታ የደረሰውን የኢጣልያን ጦር እንዲወጉ ታዘዙ። ከታዘዙበትም ቦታ ደርሰው የኢጣልያን ጦር ድል አድርገው ብዙ ጠመንጃዎች፤ ምግብ፤ ልብስ፤ ገንዝብና በጣም ብዙ ጥይት ማረኩ። ይህን ሁሉ ምርኮ ይዘው የተረፈውንና የሚሸሸውን ጦር ሲያባርሩ 15 የኢጣልያ አውሮፕላኖች ያንን ቀበሌ በሙሉ በቦምብ እንዲደበድቡ ታዘው ደረሱባቸው። እነ ቀኛዝማች ሰለባ ግን ምንም ሳይጎዱ ምርኮአቸውን ይዘው ከዋናው የወገን ጦር ጋር ተደባለቁ።

  በማይጨው ጦርነት ድል መሆናችንን ከራዲዮ ሰራተኛው ከአቶ ቴዎድሮስ መንገሻ ሰሙ። ወደ ባሌ ሲሄዱ እነ እነበጅሮንድ ተክለስላሴን አጡ። ወዴት ሄዱ? ቢሉ በእርሻ እኖራለሁ ብለው ወደ አገር ቤት ሄዱ አሏቸው። ከዚያ በሁዋላ ቀኛዝማች ሰለባ ሲዳሞ ገብተው ሀገርሰላም ላይ ከራስ ደስታ ጦር ጋር ተደባለቁ። ተፈሪ ኬላ እና አርቤ ጎና ላይ በተደረጉት ጦርነቶች ተካፋይ ሆነው የኢትዮጵያ ጦር ድል ሆነ። ከዚያም አርበኞች ወደ ባሌ ለመሻገር ሲወስኑ ቀኛዝማች ሰለባ አልሄድም ብለው 150 ወታደሮቻቸውን ይዘው ወደ ሲዳሞ መሃል ሲመለሱ የኢጣልያ ጦር ገጠማቸውና 15 ቀናት ያህል ተዋጉ። በህዋላ እንደገና ክብረ መንግስት አካባቢ አርሜራ ከተባለ ቦታ ላይ ከሚያባርራቸው የኢጣልያ ጦር ጋር ተጋጠሙ። ከዚያም ግንቦት 24 ቀን በ1930 ዓ.ም. ለአገራቸው ለኢትዮጵያ ሲሉ ታላቁ የኢትዮጵያ ጀግና በዚያች ጦር ሜዳ ላይ ወደቁ።

  ምንጭ:
  የኢትዮጵያ እና የኢጣልያ ጦርነት
  ከጳውሎስ ኞኞ
 • loader Loading content ...
 • @Tola (ቶላ)   2 years ago
  ከተኛ አንበሳ ዞር ዞር ያለ ቀበሮ ይሻላል!
  ብላቴን ጌታ ማህተመ ስላሴ፣ አንድ ኢትዮጵያዊ የሚከተሉት ፀባዮች አሉት ይሉናል።

  • ፈሪሃ እግዚአብሔር
  የኢትዮጵያ ህዝብ ትንሳኤ ሙታንን ስለሚያምን፤ ደግ በመስራት ፅድቅ፤ ክፉ በመስራት ኩነኔ እንዳለ ያውቃል። ስለዚህም፣ "የጥበብ መጀመርያ እግዚአብሄርን መፍራት ነው።" የሚለውን መሰረታዊ ህግ ጠብቆ ህሊናውን ንፁህ አድርጎ ለመኖር ይጣጣራል፤ የፈጣሪው ረድኤት እንዳይለየውም ፆምና ፀሎትን ማዘውተር ይወዳል። ይህንን በመፈፀም ክፉ ከማሰብና ከመስራት ታጋሽነትን እንደሚያገኝ ያምናል።

  • ትሕትና
  የኢትዮጵያ ህዝብ በተፈጥሮው ትሁትና ሰው አክባሪ ነው። እንኯን የሚያውቀውን የማያውቀውንም ቢሆን በእድሜ ከበለጠው እጅ በመንሳት ሰላምታ ሠጥቶ እርስዎ ብሎ ቦታ ይለቃል።  ተቀምጦም  እንደሆነ ተነስቶ ያነጋግራል፤ በከብት ላይ እንደሆነ ይወርዳል። በማእረጋቸውና በጨዋነታቸው ሊከበሩ የሚገባቸውን ሰዎች ጌታዬ፣ እመቤቲ፤ እንዲሁም በእድሜ ታላቅ የሆኑትን አያ፣ እንኮዬ እያለ ማነጋገር የተለመደ ተግባሩ ነው። ወጣቶች እንኯን እርስ በርሳቸው ሲከባበሩ ጋሼ፣ አብዬ፣ አበባዬ፣ እትዬ ይባባላሉ።

  • ርህራሄ
  የኢትዮጵያ ህዝብ ሩህሩህ ነው። ወገኑ በተቸገረ ጊዜ ያለውን ከፍሎ ይሰጣል፤ ታስሮም እንደሆነ ዋስ ሆኖ ወይም እንደ አቅሙ እዳውን በመክፈል ያስፈታዋል። የታመመን ይጠይቃል፤ የታረዘን ያለብሳል፤ የተራበን ያበላል፤ የተጠማን ያጠጣል።

  • ታማኝነት
  የኢትዮጵያ ህዝብ በጣም ታማኝ ነው። ጏደኛውን እንደ ወንድሙ ይወዳል። የጌታውን ውለታ አይዘነጋም። አሳዳሪው ቢደኀይ እንኯን "በነበረው ጊዜ በልቼ፣ ሲቸግረው አልለይም፤ አልከዳም" ብሎ ተጎድቶም ቢሆን አብሮት ይቀመጣል። አንዳንድ አሽከር ጌታው ሲሞት ውለታ ለመመለስ ብሎ ከልጅየው ጋር መኖርን ይቀጥላል። አሽከሮቹም ጌታቸውን ዘመድ በሞተው ጊዜ የሃዘኑ ተካፋይ በመሆን ያፅናኑታል። ይህም የኢትዮጵያን ሰው ታማኝነት ከሚገልፁት ማስረጃዎች አንዱ ነው።

  • ቃል ኪዳን መጠበቅ
  የኢትዮጵያ ህዝብ ቃሉን አክባሪ ነው። በፅህፈትም ባይሆን ያደረገውን ስምምነት ይጠብቃል። በጋብቻም ሆነ በንብረት ግዢና ሽያጭ ላይ የወረቀት ስምምነት ሳያስፈልገው በሰጠው ቃል ብቻ ይፀናል። ብድሮ ጊዜ ከአባቶቻችን እንደሰማንው ብዙ መኯንንት እና ሃብታሞች ገንዘባቸውን ለነጋዴ እንዲሰራበት ሲሠጡ ያለፅሁፍና ያለምስክር ነበር ይባላል። አንዳንድ ጊዜ ምንም እንኯን ቃሉን የማያከብር ሰው ባይጠፋም፣ በጠቅላላው በአንድ ኢትዮጵያዊ ላይ የሚገኘው ታማኝነት መጠኑ በቀላሉ የሚገለፅ አይደለም።

  • እንግዳ ተቀባይነት
  የኢትዮጵያ ህዝብ እንግዳ በመቀበል የታወቀና ስመ ጥሩ ነው። ይልቁንም ለውጭ አገር ሰዎች ባይተዋር በመሆናቸው፣ የተለየ ክብር እና አስተያየት ይሰጣቸዋል። ሰው ወደ ቤቱ በመጣ ጊዜም መብሉን፣ መጠጡን፣ ከብቱን ለእርድ ያቀርባል። የአንዳንድ ክፍለ አገር ህዝብ ደግሞ እንግዳ ባየ ጊዜ ተሽቀዳድሞ ከቤቱ እንዲገባለት ይለምናል። ሃሳብ ሳይፈፀምለት ቢቀር ግን ያዝናል፤ ይቀየማል። ይህም በእውነቱ እጅግ የሚያስደስትና የሚያኮራ ደግነት እና ሩህሩህነት የተሞላበት የትቀደሰ ተግባር ስለሆነ ሊያስመሰግነው ይገባል። በኢኮኖሚም ረገድ ቢሆን እንኯን ዝናን አትርፎ ወዳጅ ስለሚገዛበት ያለግባብ ሃብት ባከነ የሚያሰኝ አይደለም።

  • እውነተኛነት እና ሃቀኝነት
  የኢትዮጵያ ህዝብ በታም ሃቀኛ ነው። ሙት ካለ ቃሉን ኣያጥፍም፤ በራሱ ይመሰክራል፤ ቅጣት የሚያስከትልበትም ቢሆን ያደረገውን አይክድም። በነፍስ ግዳይ የተያዘ እንኯን ቢሆን "ቢያናድደኝ፤ ቢዝትብኝ ገደልኩት" ይላል እንጂ አልታየሁም በማለት የሚያከራክር እና የሚያንጏትት ነገር ኣያመጣም። ይህም የኢትዮጵያ ህዝብ ምን ያህል እውነተኛ መሆኑን ያስረዳል። 

  ምንጭ: 
  የብላቴን ጌታ ማህተመ ስላሴ ወ/መስቀል ስብስብ ስራዎች 
 • loader Loading content ...
 • @Tola (ቶላ)   2 years ago
  ከተኛ አንበሳ ዞር ዞር ያለ ቀበሮ ይሻላል!
  • ለዳኛ አመልክት፤ እንዲሆን መሰረት።
  • ለወሬ የለው ፍሬ፤ ላበባ የለው ገለባ።
  • ማን ይመስክር የነበረ፤ ማን ያርዳ የቀበረ።
  • ምስክር ለበለጠ፤ ውድማ ለመለጠ።
  • ምስክር ከተጠራ፤ መስዋዕት ከተሰራ።
  • ምንዝር ሲለቅ ላለቃ፤ አለቃ ሲለቅ ለሻለቃ።
  • ሰማንያ ለማገጃ፤ ስለት ለማረጃ።
  • ሳይገሉ ጎፈሬ፤ ሣያስረግጡ ወሬ።
  • ስለት ድግሱን፤ ደባ ራሱን።
  • በሰማንያ ያለቀ፤ በፀሃይ የደረቀ።
  • በቆረጡት በትር ቢመቱ፤ ባወጡት ዳኛ ቢረቱ፤ የእግዜር ግቡ ከብቱ።
  • በተለሙ ያርሷል፤ በዠመሩ ይጨርሧል።
  • ባጉራህ ጠናኝ የተረታ፤ ማህል አገዳውን የተመታ።
  • ባፈሳ ይታፈሳል፤ በነጠረ ይመለሳል።
  • ባፍ ይጠፉ በለፈለፉ።
  • ንጉስ አይከሰስ፤ ሰማይ አይታረስ።
  • ንጉስ የፈረደው፤ ሰይፍ የቆረጠው።
  • ተቀምጦ የሰቀሉትን፣ ቆሞ ማውረድ ይከብዳል።
  • ተዋጊ በሬህን፣ ተናካሽ ውሻህን ያዝ።
  • አባት ያቆየው፣ ለልጅ ይበጀው።
  • አንድ አይነድ፤ አንድ አይፈርድ።
  • ርስት በሺህ አመቱ ለባለቤቱ።
  • እውነት የተናገረ፤ በመርከብ የተሻገረ።
  • ከራስ ወዲያ መስካሪ፤ ከእግዜር ወዲያ ፈጣሪ።
  • ከኑግ የተገኘን ሰሊጥ፤ አብረህ ውቀጥ።
  • ካነጋገር ይፈረዳል፤ ካያያዝ ይቀደዳል።
  • አሳ ጎርጏሪ ዘንዶ ያወጣል፤ የሰው ፈላጊ የራሱን ያጣል።
  • የሞተ አይከሰስ፤ የፈሰሰ አይታፈስ።
  • የሥራት መቇሚያው ፈጠም፤ የስጋ መቇሚያው ቅልጥም።
  • የተበደለ ከነጋሽ፤ የተጠማ ከፈሳሽ።
  • የንጉስ ቃል የቆመ ይጥላል፤ የተቀመጠ ይፈነግላል።
  • ያባት እዳ ለልጅ፤ ያፍንጫ እድፍ ለእጅ።
  • ያዋቂ ኣጥፊ፤ የእስራዔል ጣፊ።
  • ከድሎ ካለቃዬ፤ ከሶ ከጠበቃዬ።
  • ግፍ የተሰራ በኛ፤ ካሱ ይሉናል በዳኛ።

  ምንጭ:
  የብላቴን ጌታ ማህተመ ስላሴ ወ/መስቀል ስብስብ ስራዎች
 • loader Loading content ...
 • @Tola (ቶላ)   2 years ago
  ከተኛ አንበሳ ዞር ዞር ያለ ቀበሮ ይሻላል!
  ይህ ሰፈር ስያሜውን ያገኘው በደርግ ዘመነ መንግስት የተለያዩ እህሎችን ለማጠራቀሚያ ተብለው በተሰሩት ግዙፍ የቆርቆሮ/የብረት ጎተራዎች ምክንያት እንደሆነ ይነገራል። ባሁኑ ሰአት ባካባቢው ለአዲስ አበባ የመጀመሪያ የሆነው የትራፊክ ማሳለጫ የተገነባበት በመሆኑ ሰፈሩ ጎተራ ማሳለጫ፣ ወይም የብሄር ብሄረሰቦች አደባባይ በመባልም ይታወቃል።


                  የእህል ማጠራቀሚያ ጎተራዎች።


                  የጎተራ ማሳለጫ ወይም የብሄር ብሄረሰቦች አደባባይ።
 • loader Loading content ...
 • @Tola (ቶላ)   2 years ago
  ከተኛ አንበሳ ዞር ዞር ያለ ቀበሮ ይሻላል!
  በኢትዮጵያ ቴሌቪዥን ሲተላለፍ የነበረ አንድ ፕሮግራም ላይ እንደሰማሁት ከሆነ ካሳ ተሰማ ይህንን ዘፈን የዘፈነበትን ምክንያት አባባ ተስፋዬ (ተስፋዬ ሳህሉ) እንደሚከተለው ገልፀውታል።

  "... የቃኘው ሻለቃ ወደ ኮሪያ በዘመተበት ጊዜ ከጦሩ ጋር ከነበርነው አርቲስቶች መካከል አንዱ ካሳ ተሰማ ነበር። ጦሩ ሙሉ ዝግጅቱን ጨርሶ ወደ ኮሪያ ለመሄድ መጀመሪያ ጉዞ የጀመረው በባቡር ነበር። እናም የቃኘው ሻለቃ ጦር ወደ ባቡሩ ሲገባ ብዙ ህዝብ (ቤተሰብን ጨምሮ) ሊሸኘው መጥቶ ነበረና ለቅሶ በረከተ። በዚህም የተነሳ ወታደሩ ሆዱ ስለባባ ግማሹ ማልቀስ ጀመሮ ነበር እናም ይህንን የሃዘን ድባብ ለማጥፋት ካሳ ተሰማ አንድ ዘዴ ማምጣት ነበረበት። ካሳ ተሰማም ክራሩን አውጥቶ ለወታደሩ ዘፈን መዝፈን ጀመረ። ዘፈኑም እልም አለ ባቡሩ የሚለው ነበር...

  እልም አለ ባቡሩ፣ እልም አለ ባቡሩ
  ወጣት ይዞ በሙሉ።
  ...."

                 አርቲስት ካሳ ተሰማ።
 • loader Loading content ...
 • @Tola (ቶላ)   2 years ago
  ከተኛ አንበሳ ዞር ዞር ያለ ቀበሮ ይሻላል!
  የሚከተለው ፅሁፍ በእውቀቱ ስዩም "እንቅልፍ እና እድሜ" ከሚለው መፅሃፉ ውስጥ ስለ አንድ ገፀ ባህሪ የግጥም አጀማመር ታሪክ ከሚተርከው የተወሰደ ነው። እኔ ሳስበው ሳስበው በእውቀቱ ስለራሱ የሚያወራ ነው የሚመስለኝ።

  ---------------------------------

  ግጥም የጀርምኩት በልጅነቴ ነው።

  በልጅነቴ ከቁርባን መልስ እስከ አፍንጫዬ ተከናንቤ ወደ ቤቴ ስንደረደር፣ የወዲያ ማዶ ሰፈር ልጆች ድንገት እንደ ጉም ከበቡኝ። ከቁርባን የተረፈ መክፈልት ሊጠይቁኝ ነው ብዬ ሳስብ፣ 'እንኪያ ሰላንትያ ካልገጠምንህ' አሉኝ።

  "እንኪያ ሰላንትያ!" አለኝ ቤት የሚመታ ስድብ እንደ አቡነ ዘበሰመያት በቃሉ ሲያጠና የሚውል ድምፀ ሰላላ ልጅ። ጭጭ ብዬ ልቀር ፈልጌ ነበር። ግን በኔ መሰደብ ለመዝናናት የጎመዡ ጏደኞቹ ጭጭ ብል ሲጦም የዋለ ሆዴ ላይ እንደሚረግጡኝ ስላወቅሁ "በምንትያ!" አልኩ።

  "በአንበጣ!"

  "ምንለ ባንበጣ!" ካልኩ በሇላ በ"ጣ" የሚጠናቀቅ ስድብ ምን ሊሆን እንደሚችል በሃሳቤ ስመረምር "ቆማጣ"፣ "አይን  አውጣ"፣ እና "ፈጣጣ" የሚሉ ሥለመጡልኝ ለኒህ ስድቦች ጫንቃዬን አሰናድቼ ስጠብቅ፣ ድምፀ ሰላላው ልጅ ያልጠበኩትን አወረደው።

  "*****  *** ቅራሪ ልጠጣ!" ነው ያለኝ።

  መጋኛ እንደመታው ሰው ሁለመናዬ ተዟዟረ። ውጫጭ ጏደኞቹ እንደ ደጋን እየተቀለበሱ ሳቁብኝ። እቤቴ ገብቼ፣ እናቴ የነገረችኝን የሰማእቱን እስጢፋኖስን ታሪክ በማሰብ ልፅናና ሞከርኩ። ግን አይሁድ በሰማእቱ ላይ ካዘነቡት ኮረት ይልቅ የዚያ ማዶ ሰፈር ልጆች ስድብ የሚያም ሆኖ አገኘሁት። የሰማእቱን ገድል ትቼ ቤት የሚመታ ስድብ ሳሰላስል አደርኩ። አነጋግ ላይ ብድሬን ለመመለስ ወደ ወዲያ ሰፈር ሄድኩ።

  "ምንድር ፈልግህ?" አለኝ ድምፀ ሰላላው ልጅ፣ ከጏደኞቹ ጋር ብይ ሲጫወት ባገኘው።

  "እንኪያ ሰላንትያ ልገጥምህ ነው!" አልኩት።

  ጏደኞቹ በብይ መጫወቻ 'ሞር' ዙሪያ ከተንበረከኩበት ተነስተው የጉልበታቸውን አቧራ ያራግፉ ጀመር።

  "እንካሰላንታያ!" አልኩ የፉከራ በሚመስል ልበ ሙሉነት።

  "በምንትያ!" አለኝ ድምፀ ሰላላው ልጅ።

  "በጣሳ!"

  "ምናለ በጣሳ!"

  "እናትህ ወለደች የፍየል ጎረምሳ
  አባትህ ደስ ብሎት እንጣጥ ብሎ ፈሳ!"

  የግጥም ተሰጥዖ እንዳለኝ ብቻ ሳይሆን የተሰጥዖዬን ሃያልነት ያወቅሁት ያኔ ነው። ድምፀ ሰላላው ልጅ ፊቱ እሳት መሰለ። ቆይቶ አምድ መሰለ። ጏደኞቹ እንደወትሮው በመሳቅ ፈንታ እግሬ እስኪግል አባረሩኝ። ገና በልጅነቴ በግትም ምክንያት መከራ የደረሰበት የመጀመርያው ኢትዮጵያዊ እኔ ሳልሆን እቀራለሁ?

  ----------
  ምንጭ:
  እንቅልፍ እና እድሜ
  በበእውቀቱ ስዩም
 • loader Loading content ...
  Load more...
loader Loading content ...

Comments (21)


 • @Tola (ቶላ)   1 year ago
  ከተኛ አንበሳ ዞር ዞር ያለ ቀበሮ ይሻላል!
  "ሳያዩ የሚያምኑ ብፁዓን ናቸው" እዚህ ጋ ቦታ ያላት አትመስለም :) Thank you for the Q and A.
 • @Tola (ቶላ)   1 year ago
  ከተኛ አንበሳ ዞር ዞር ያለ ቀበሮ ይሻላል!
  ሃሃ @Demoze ... ከስተህ ሊሆን ይችላል እኮ ማን ያውቃል :) እኔ ለምሳሌ ሞሪንጋ እየተጠቀሙ ለውጥ ያመጡ ሰዎች አውቃለሁ።
 • @Tola (ቶላ)   1 year ago
  ከተኛ አንበሳ ዞር ዞር ያለ ቀበሮ ይሻላል!
  Thanks, Tariku!
 • @Tola (ቶላ)   1 year ago
  ከተኛ አንበሳ ዞር ዞር ያለ ቀበሮ ይሻላል!
  እናመሰግናለን፣ ህሊና!
 • @Tola (ቶላ)   1 year ago
  ከተኛ አንበሳ ዞር ዞር ያለ ቀበሮ ይሻላል!
  ahahaha... oops! አይ አዳም :) ጋቢውን ግን ከጥጥ ነው የሰራው?
 • @Tola (ቶላ)   1 year ago
  ከተኛ አንበሳ ዞር ዞር ያለ ቀበሮ ይሻላል!
  Thanks Dani and Hilina!
 • @Tola (ቶላ)   1 year ago
  ከተኛ አንበሳ ዞር ዞር ያለ ቀበሮ ይሻላል!
  Thanks Abigel! This is one of the places I would like to visit in the future!
 • @Tola (ቶላ)   1 year ago
  ከተኛ አንበሳ ዞር ዞር ያለ ቀበሮ ይሻላል!
  እናመሰግናለን ማሂ! አሁን አሁን ከተማ አካባቢ ጠላ እየቀረ የመጣ ይመስላል። እንደውም በቢራ ተተክቷል ማለት ይቀላል። መጥመቅ ለሚፈልግ ግን መረጃው በዚህ መልኩ መቅረቡ አሪፍ ነው! ይምችሽ!
 • @Tola (ቶላ)   1 year ago
  ከተኛ አንበሳ ዞር ዞር ያለ ቀበሮ ይሻላል!
  Thanks Aman and Adugna!! Shambel Abebe is one of the greatest African personalities of all time! Apart from olympics, he was also a good painter, i heard :)
 • @Tola (ቶላ)   1 year ago
  ከተኛ አንበሳ ዞር ዞር ያለ ቀበሮ ይሻላል!
  እናመሰግናለን! እኔም የመክሊትን አስተያየት እጋራለሁ። የሆነ ከማሪቱ ለገሰ ጋር የተያያዘ ርዕስ ቢሰጠው ለምሳሌ አሪፍ ነው። በነገራችሁ ላይ እኔም የማሪቱ አድናቂ ነኝ :) ይቺን ግጥም ያዙልኝማ --
  ...ወንዱን ልጅ ሴቲቱ በምን ደፈረችው፣
  አጋድማ በጡቷ እየጠቀጠቀችው፣
  ...
 • Load more...
loader Loading content ...