loader

Topics (14)


loader Loading content ...

Explanations (16)


 • @Birhanu Mekuria   7 months ago
  investing on my own ignorance!
  ነጋ፣
  ቀን ሌትን ፈንግሎ፣ ባምባው ሊገንበት 
  ሰው ሕልሙን ሊራመድ፣ ነቃ ከተኛበት 
  ሲማስን - ሲኳትን፣ አይተጉ ሲተጋ 
  ላልጨበጠው አልፋ፣ ኦሜጋ ፍለጋ
  መሸ፣
  ፍጥረት አፏሸከ፣ አይዘጉት አዛጋ 
  ሁሉም ተከተተ፣ ሁሉም በሩን ዘጋ
  ሲያፈጥ እንዳልዋለ፣ ቀን አይኑን ከደነ 
  በእንቅልፍ ቡልኮ፣ መስሚያዉን ሸፈነ 
  ሌት ሆይ ባለተራው፣ አምባገነን ሆነ።
 • loader Loading content ...
 • @Birhanu Mekuria   7 months ago
  investing on my own ignorance!
  ሕይወት ሸኝታችሁ፣ ሃውልት ልታኖሩ
  በእድሩ ጥሩንባ፣ ቀበቶ እምታስሩ 
  ለሂያጅ መታወሻ 
  ለሞቱ ማርከሻ 
  ብረት ስታቀልጡ 
  አለት ስትፈልጡ 
  አፈር ስታቦኑ 
  አሸዋ ስትዘግኑ 
  ነፍሱን እንዲደላት፣ በአፀደ-ገነት 
  ስትገቡ ሱባኤ፣ በደብር ሰገነት 
  ይልቅ አንድ ነገር፣ ጠይቁ መርምሩ 
  የት ጋር እንደሆነ፣
  ቀሪዉን ከሂያጁ፣ መለያ መስመሩ።
 • loader Loading content ...
 • @Birhanu Mekuria   10 months ago
  investing on my own ignorance!

  የኦሪዮን ክዋክብቱ፣ 

  ርጌልና ቤቴልጌስ፣

  ነጥተው ገዝፈው የቀሉበት

  ምሽት ነበር፣ዉድ ምሽት

  ለመተመን የሚፈትን ዋጋው ካልማዝ 'ንቁ በላይ

  ወዙ ቀልጦ የፈሰሰ፣ ከፊቴና ከፊትሽ ላይ

  ምሽት ነበር አይረሴ፣ ተስፋው ከማር የጣፈጠ 

  ለመግባባት ስንታገል፣ ሳንጨብጠው ያመለጠ።

 • loader Loading content ...
 • @Birhanu Mekuria   11 months ago
  investing on my own ignorance!
  በእኔና አንተ ምድር፣
  ሆነህ አትፈጠር፣ ችግኝ ባለ ተስፋ
  ከቶ ብቅ አትበል፣ በኮትኳች ልትፋፋ።
  ባርባ ቀን እድልህ፣ ብታመልጥ ከ'ርግጫ
  በመርፌ ቀዳዳ፣ ብትሾልክ ከድፍጥጫ
  ዋ ሽተህ፣
  ዋ ብትል፣
  የሽንት ጎርፍ ነው፣ የጥምህ መቁረጫ።

  ይህን ሁሉ ችለህ፣
  በጥቂት ኮትኳቾች፣ ጠንተህ ብትፀድቅ
  በፀሐይ እስትንፋስ፣ ብትወዛ ብትደምቅ
  አንሰራራሁ እንዳልክ፣ አየሁ አዲስ ዓለም
  ቅጠሎችህ ረግፈው፣ ቅርንጫፍህ የለም።

  አይችሉትን ችለህ፣
  ዳግመኛ ሥር ሰደህ፣
  መክሰም መጠውለግን፣ ቀንጣት ሳትፈራ
  ግንድህ አቆጥቁጦ፣ ፍሬ ስታፈራ
  እልፍ ነው ቀጣፊህ፣ በሰልፍ በተራ።

  ከቅጥፈቱ ናዳ፣ አፅምህን አትርፈህ
  ከራስ በስትያ ስሌት፣ ዋርካነት አልመህ
  ባሸለበች ፀሐይ፣ በነቃች ጨረቃ
  ከትንሣኤህ ምኞት፣ ድንገት ስትነቃ
  መንጋው ተሰልፏል፣ መጋዙን አሹሎ
  ገዝግዞ ሊጥልህ፣ ከሥርህ መንግሎ።
 • loader Loading content ...
 • @Birhanu Mekuria   1 year ago
  investing on my own ignorance!
  አእላፍ ነው ዝምታ፣
  በገለባ ቃላት
  ባንገት በላይ ቅርሻት 
  በሃሜት ሹል ምላስ፣ በባዶ ድንፋታ 
  ግርማዊ ጥልቀቱ፣ ከቶ 'ማይረታ።
  *****
  ዝምታ ዉበት ነው፣
  የእውነት ስብሃቷ
  የሀቅ ደም ግባቷ
  ያለም ጆሮ ቢቆም፣ 
  ኡኡ አለማለቷ።
  *****
  ሰላም ነው ዝምታ፣
  ፍፁም ብፁዕ እረፍት 
  ሀሴት ነው ዝምታ፣
  የምናበ-ሹለት መመዘኛ ልኬት 
  የሕይወት ቅራሪ ከቶ ያልበረዘው 
  የንዋይ ሆምጣጤ ወትሮ ያልመረዘው። 
  *****
  እንባ ዝም ያለ ነው፣
  የአዞ ካልሆነ 
  ፈገግታም ዘም ያለ፣
  ካንጀት ከበቀለ 
   ፍቅር ዝም ያለ ነው፣
  ሲሆን ምክንያት አልባ 
   ሞትም መጥቶ ሲወስድ፣
  በዝምታ ጩኸት፣ ቀጥሮ ሳያግባባ።
 • loader Loading content ...
 • @Birhanu Mekuria   1 year ago
  investing on my own ignorance!
  ማነህ የተኛኸዉ?
  እንቅልፍ የደበተህ ሥጋህን ጥለኸው። 

  ምን ኖረኻል አንተ
  ንጉሥ ኖረኻል ወይ፣ ኖረኻል ወይ ጌታ?
  ወይ ቆሩንጮ ለባሽ ለማኙ ከርታታ?
  ሚኒስትር ደጃዝማች ወይም ፊታውራሪ 
  ባለብዙ ገንዘብ አሽከር አሳዳሪ 
  ኖረኻል ወይ አንተ?
  አጥንትህ ወላልቆ እንዲሁ የሻገተ!
  ሥራህ ምን ነበረ ቤትህ የት ነበረ?
  እርስትህ የት ቀረ?
  የተመራመረ አዋቂ ፈላስፋ 
  ብዙ መስናክል ካለም ላይ የገፋ 
  ሳትሆን አልቀረህም፣
  ጉድ ነው! መልክህ የለም።

  ማነሽ? ማነህ አንተ?
  ማናችሁ እናንተ?
  ማነሽ በዘመንሽ የዉበት እመቤት 
  ሆነሽ የገዛሽው የወንዶችን ጉልበት?
  በክንድሽ ያለቀው 
  ወጣቱ ጎልማሳ የት ነው የወደቀው?
  ምን ኖረሻል አንቺ አጥንትሽ ይናገር?
  እንጨት ተሸካሚ 
  ወይ  ኩበት ለቃሚ
  ወይ ልብስሽ ያደፈው ጥሬዋ ባላገር፣
  ወይም ሽቅርቅሯ እስቲ ተናገሪ?
  ሽቶሽ የጎረፈው መንጭቶ ከፓሪ 
  በወርቅና ባልማዝ በሉል እንደሆነ 
  ተጫውተሽ የሄድሽው ዝናሽ የገነነ።

  እስቲ ተናገሪ ቋሚ ያዳምጣል 
  አንቺ ለመሆንሽ ምስክርሽ የታል?
  ያሻሃል ምስክር 
  ሞተህ ስትቀበር
  ድንጋይ ላይ ተፅፎ የሚናገርልህ 
  ምልክት የሚሰጥ አንተ ለመሆንህ፣
  ሃውልት የሚያቆይህ 
  ዘመድ ያስፈልጋል ከሌላው ለይቶ
  መንገደኛ እንዲያውቅህ ቆሞ ተመልክቶ።

  "እገሌ ነው" ብሎ ታሪክ የሚያወራ
  እንዲደነቅልህ ቀሪው ያንተ ሥራ 
  ተነስ አንተው ጥራ!
  እጎንህ ከተትኙት ዓፅሞች በጉድጓድ 
  አለ ወይ ዘመድህ የምታውቀው ጓድ?
  ወዴት ነው አበባ የታለች እማዬ 
  ጋሼ ወዴት ይሆን የት ቀረች እትዬ?
  ጠፍቷል ምልክቱ 
  አጥንትና ሥጋህ ሲሰነባበቱ።

  ከሙታን ማኅበር በመዝገብ ገብተሃል 
  ማንኛውም አጥንት አስከሬን ሆነሃል 
  የሞት ጠባሳ ነህ አስታዋሽ ስራዉን 
  ከንቱ ነው የምትል አውይ ፍጡር መሆን!
  የተንቀራፈፈው እጅ እግሩ ሸምበቆ 
  የተከፋፈለው ሰረሰሩ ለቆ፣
  ጥርሱ ያገጠጠ አይኑ የወለቀ 
  ጎድኑ ተቆጥሮ ጅማቱ ያለቀ 
  የተገጣጠመ የተሠራ ባጥንት 
  ሥጋ ወዝ የሌለው የሰው ዘር ምልክት፣
  ሆነህ የተኛኸዉ 
  የማትታወቀው፣
  ማን ኖረሃል አንተ? 

  ምንጭ: "መንገድ ስጡኝ ሰፊ" የግጥም መድበል
 • loader Loading content ...
 • @Birhanu Mekuria   1 year ago
  investing on my own ignorance!
  የማልመደብ ከክርስቲያኑ፣
  ከሙስሊሙ ወይ ካ'ይሁዱ
  የማልፈረጅ ከቡድሃው፣
  ከሱፊው ፣ ከዜኑ ወይ ከሂንዱ
  ከሃይማኖት ከባህል፣
  የማይመራኝ መንገዱ  
  ያልተከሰትሁ ከምሥራቁ፣ 
  ያልመጣሁ ከምዕራቡ   
  ያይደለሁ ከሰሜኑ - ያልሆንኩ ከደቡቡ  
  ያልፈለቅሁ ከባህሩ - ከጥልቁ ከውቅያኖሱ  
  ያልወረድሁ ከደመናው - ከሰማያዊ ክርታሱ
  ከትቦ ያልመዘገበኝ ፣ የፍጥረት ሀተታ ድርሳን
  ዘሬ ግንዱ ማይመዘዝ ፣ ካ'ዳምና ከሔዋን 
  ስፍራዬ ስፍራ የሌለው ፣ ሊጎበኘኝ ለሚተጋ  
  ዱካዬ ዱካው ማይገኝ ፣ የሚፈትን ለፍለጋ 
  መደቤ ከቶ ያልለየ ፣ ከመንፈስ ይሁን ከሥጋ  
  አይደለሁኝም ማንም
  አይደለሁም የማንም  
  ከዚህኛዉ የለሁም
  አልኖር ከሚመጣዉም
  ያልመጣሁኝ ከየትም
  የማልሄድ ወደ የትም
  ማንም ነኝ ከየትም።
 • loader Loading content ...
 • @Birhanu Mekuria   1 year ago
  investing on my own ignorance!

  ምን ይሆን ዕጣፈንታው፣ ሕልምን በይደር ሲያቆዩት?
  ፀሐይ እንዳሸው ቴምር፣ ይሟሽሻል ይደርቃል?
  ወይስ እንደ መረቀዘ ቁስል፣ በመግል ጠበል ያጠምቃል?
  እንደ ከረመ ሥጋ፣ ክርፋቱ ከሩቅ ይጣራል?
  ወይስ እንደ ጣፋጭ ጭማቂ፣ የስኳር ኮረት ያበቅላል? 
  ምናልባት፣አንደ ከባድ ሸክም፣ ከላይ ወደታች ይጫናል? 
  ወይስ ቀን ሞልቶ ሲፈስ፣ ተወጥሮ ይፈነዳል?
  ------
  መነሻ: "Harlem", Langston Hughes
 • loader Loading content ...
 • @Birhanu Mekuria   2 years ago
  investing on my own ignorance!
  ወጡ ቀለም ሆኖ እንጀራው ብራና 
  ይድረሰኝ ደብዳቤ ተርቤአለሁና 
  ይሽተተኝ ቁሌቱ 
  የቅመም ሽንኩርቱ 
  በርበሬው ይበተን ነፋስ ይዞት ይምጣ 
  በዝናብ ላኩልኝ ጠላዉን ልጠጣ 
  ልስከር በፊልተሩ 
  ይረሳኝ ችግሩ...

  ገብረክርስቶስ ደስታ
  ምንጭ፣ "መንገድ ስጡኝ ሰፊ" የግጥም መድበል  
 • loader Loading content ...
 • @Birhanu Mekuria   2 years ago
  investing on my own ignorance!
  ሰም፣ የማንለወጠው አርሶ ከመብላት መላቀቅ ስላልቻልን ነው።
  ወርቅ፣ የማንለወጠው በስንፍናችን ነው (አረስን፣ በላን ፣ ተኛን)
 • loader Loading content ...
  Load more...
loader Loading content ...

Comments (1)


loader Loading content ...