loader

Topics (143)


loader Loading content ...

Explanations (27)


 • @Yared   2 years ago
  Sewasewer
  አስቴር አወቀ ጎንደር ውስጥ ተወልዳ አዲስ አበባ ውስጥ ያደገችና ላለፉት  30   አመታ ት ገደማ  ዝነኛ  ሆና  የዘለቀች  ድምፃዊት  ናት።  የዘፈን  ሙያዋን  የጀመረችው  በሀገር  ቅር  ቲያትር  በድምፃዊነት  እና  በተወዛዋዝነት  በመቀጠር ሲሆን   በመጀመሪያዎቹ  ውዝዋዜ  እና  የዘፈን  ስራዎቿ ጊዜ  የብዙነሽ  በቀለ ፣  ሂሩት  በቀለ  እና  የሙሉቀን  መለሰን ስራዎች  በመጫዎት  እንደጀመረች  ትናገራለች ። በዚህ ረጅምና ስኬታማ የሙያ ጊዜየዋ  ውስን   ዘፈኖች  የሚይዙትን  ሽክ ላ  አልበሞችን   ጨም ሮ  ሃያ  በላይ   አልበሞችን  አሳትማለች


   
   

  አስቴር በትምህርቷ ጎበዝ እንደነበረች እና የቤተሰቦቿ ፍላጎትም ዘፈን ሳይሆን በትምህርቷ እንድትቀጥልና ብሎም ከፍተኛ ደረጃ እንድትደርስ ነበርና የተወሰኑ አልበሞቿን እንደሰራች በዚሁ በቤተሰቦቿ ግፊት እና እሷም የዘፈን ህይወት ይህን የመሰለ ውጤትን እንደሚያመጣ በወቅቱ እርግጠኛ ባለመሆን የዘፈኑን ሙያ ወደጎን በማለት በፈረንጆቹ አቆጣጠር በ1981 ለትምህርት ወደ አሜሪካን አገር፣ ሳን ፍራንሲስኮ  (San Francisco)  ከተማ እንደተጏዘች ሸገር ላይ በሰጠችው ቃለ ምልልስ ገልፃለች። ሆኖም ግን ሳን ፍራንሲስኮ አካባቢ ለሁለት አመታት ከኖረች በሇላ  ኑሮው ከበድ እንዳላት እና ደስታን እንደፈለገችው ባለማግኘቷ ዋሽንግተን ዲሲ ያሉ ኢትዮጵያውያን ያቀርቡላት የነበረውን ግብዣ ተቀብላ ወደዛው ተጉዛ ስራ መስራት እንደጀመረች ትናገራለች።

  አስቴር በስራዋ የሀገሯን ሰዎች ብቻ ሳይሆን የውጭ ሀገር ሰዎችን ጆሮዎችም የሳበች ሲሆን ከሲቢኤስ  (CBS)  ኮርፖ ሬሽን ጋር የሰባት አመት ኮንትራት እንደነበራት ተገልፇል። በተመሳሳይም ከሌላ ከእንግሊዝ ሀገር ካምፓኒ ጋር ሌላ ኮንትራት ተዋውላ ስራዎቿን አበርክታለች። ተዋቂው ታይም (TIME) መፅሄትም ላይ አዲስ አይነት የሙዚቃ ስልት ዘርፍ ላይ ትልቅ አድናቆትን ተሰቷታል። ከዚህም ባሻገር "ካቡ" የተሰኘው አልበሟ በፈረንጆች አቆጣጠር በ1990 በ" CMJ New Music Charts " ላይ ለአራት ሳምንታት ከፍተኛ ቦታ (top  position) ላይ እንዲሁም በ" Billboard's World Music Charts " ላይ ለአስር ሳምንታት አስሩ ዝነኛ ዘፈኖች (top ten of  Billboard's World Music Charts ) ሆኖ ቆይቷል።

  አስቴር ወደ ኢትዮጵያ መጥታ ትልልቅ የሙዚቃ ዝግጅቶችን በጃንሜዳ፣ አዲስ አበባ ስታድየም፣ ሸራተን አዲስና ሚሊኒየም አዳራሽ አድርጋለች። ከዚህ ባሻገር በተደጋጋሚ እየደረሰ ያለውን የረሃብ አደጋ ሰለባዎች ለመርዳት በተደረገው ጥረት "ለወገን ደራሽ ወገን ነው" የሚለውን መሪ መፈክር ተቀብላ ወደሃገሯ በመምጣት በሙያዋ አስተዋፅኦ አድርጋለች። 
   
  የራስሽን ዘፈን ስትሰሚ ምን ይሠማሻል ተብላ ተጠይቃ "ተለዋዋጭ ነው፣ በወጣትነት ጊዜየ በጣም አፍር ነበር፤ የኔን ዘፈን ካዘፈንሽ ያንቺ መኪና ውስጥ አልገባም ነበር፣ የኔን ዘፈን ካዘፈንሽ እቤትሽ አልመጣም ነበር። ምክንያቱን ሁሌም በሰማሁ ቁጥር ይህን እንዲህ ማድረግ ነበረብኝ የምላቸው ስሜቶች ይሰሙኝ ነበር። አሁን ግን ዘፈኖቸን በሰማሇቸው ቁጥር በጊዜው የነበሩትን ነገሮች ቁልጭ አድርገው ስለሚያስታውሱኝ ደስ ይለኛል" ብላለች።

  አስቴር በምኒልክ መፅሄት በተደረገላት ቃለ መጠይቅ ላይ ደግሞ እራሷን በራሷ እንድትገልፅ ተጠይቃ "አስቴር አወቀ በጣም ደግ፣ ስስ ቆዳ ያላትና ትልቅ ለመሆን የምትፈልግ ሴት ናት። መፈቀርም ማፍቀርም የምትፈልግ ናት። ሌላ ትርጉም ሊሰጣት አይገባም ከተፈቀረች ይበቃታል። ሌላ ነገር አትፈልግም" ብላለች።


  አስቴር  አወቀ  ንድ  ሴት  ልጅ ያላት ሲሆን    የግል ህይወቷን ከሰው ሸሸግ አድርጋ የምትኖር እና ከ   አደባባይ  ይ  ልቅ  የግል    ሰው እንደሆነች  ትልቅ  የሆነም  የመድረክ  ፍርሃት እንዳለባት ትናገራለች።

  ምንጭ
  • የሸገር ኤፍኤም፣ የጨዋታ እንግዳ ዝግጅት ቃለ ምልልስ (ማዕዛ ብሩ)
  • ታሪካዊ መዝገበ ሰብ (ፋንታሁን እንግዳ)
  • ምኒልክ መፅሄት
  • http://www.billboard.com/artist/280125/aster-aweke/biography

 • loader Loading content ...
 • @Yared   2 years ago
  Sewasewer
  ማንኛውም ሰው ቢሆን በአለም ፊት ሲመለከቱት ኢምንት መሆኑን አንድ ትልቅ ዐዋቂ እንዲህ ተናገረ።

  በግራዬና በቀኜ፣ በፊቴና በሇላዬ ዞሬ የአለምን ሰፊነት አይቼ፤ ደግሞ የኔን የራሴን የቁመቴን አጭርነትና የጎኔን ጠባብነት ከተመለከትሁ ሀሇላ የአለምን ትልቅነትና የኔን ትንሽነት አስተያይቼ ሳመዛዝነው፣ ኢምንትነቴን እየተረዳሁት ከኅፍረት ብዛት የተነሳ መንፈሴ ይኮማተራል። ነፍሴም ትርገበገባለች።

  ምንጭ
  • ታሪክና ምሳሌ (ከበደ ሚካኤል)

 • loader Loading content ...
 • @Yared   2 years ago
  Sewasewer
  ሰው ደስ ባለውና በተመቸው ሰዓት የጊዜው ሁኔታ ሳይለወጥ እንዳለ ሆኖ ቢኖር ይፈቅዳል። በከፋውና በተበሣጨ ጊዜ ደግሞ አለም ብትበጠበትና የጊዜውም ሁኔታ ቢለዋወጥለት ይወዳል። ግን መሬትን ከመዞሯና ከመሽከርከሯ አንዲት ደቂቃ እንኯን ሊያቆማት የሚችል ነገር እንደሌለ፤ የአለምና የጊዜውን ሁኔታም እንደዚሁ ቢከፋም ቢበጅም ከመለዋወጡ ሊያግደውና ሊከለክለው የሚችል ሰው አይገኝም።

  ምንጭ
  • ታሪክና ምሳሌ (ከበደ ሚካኤል)

 • loader Loading content ...
 • @Yared   2 years ago
  Sewasewer
  በዓለም ላይ ትልቅ ስራ ለመስራት የሚቻለው ሠሪው ሰውና ለመሥራት የተመቸበት ጊዜ እነኚህ ሁለቱ ሲገናኙ ነው። ትልቁን ስራ ለመስራት የሚችለው ሰው ባልተመቸ ጊዜ ሲፈጠር ሊሠራው የሚችለውን ስራ ሣይሰራው መቅረት ግድ ይሆንበታል። ትልቅ ስራ ለመስራት የተመቸ በሆነበት ጊዜ ደግሞ ሊሰራው የሚችል ሰው ባላመፈጠሩ መልካሙ ጊዜ በከንቱ ያልፋል። እነዚህም ሁለቱ ተፈላላጊ
  ነገሮች የሚገናኙት በብዙ ዘመን ውስጥ ጥቂት ጊዜ ነው።

  ምንጭ
  • ታሪክና ምሳሌ (ከበደ ሚካኤል)

 • loader Loading content ...
 • @Yared   2 years ago
  Sewasewer
  ደስታ ምንድን ነው ብለው ቢጠይቁት አንዱ ሊቅ "ደስታ ማለት ጤንነት ነው" ብሎ ተናገረ። ጤንነትስ ደግሞ ምንድን ነው ብለው መልሰው ቢጠይቁት፤ "ጤንነት ማለት ሁሉም ነው" ብሎ መለሰ። እውነት ነው ጤንነት ከሌለ ሁሉ ነገር ከንቱ ነው። ጤንነት ካለ ግን ሁሉም ነገር መገኘቱ አይቀርም።

  ምንጭ
  • ታሪክና ምሳሌ (ከበደ ሚካኤል)

 • loader Loading content ...
 • @Yared   2 years ago
  Sewasewer
  የሰው ሙያ ሦስት አይነት ነው። አንደኛው - ማሰብን ማወቅ ነው። ሁለተኛው - መናገርን ማወቅ ነው። ሦስተኛው - መስራትን ማወቅ ነው። አብዛኞቹ ብልኆች የሚባሉ ሰዎች ከእነዚህ ከሦስቱ አንደኛውን ብቻ ይይዛሉ። መስራት ያውቁና ትክክል ማሰብ አይችሉም ይሆናል። ስለዚህ ትክክል ካለማሰባቸው የተነሳ ደክመው የሰሩት ስራ ሁሉ ይፈርሳል። ወይም ንግገር አሳማሪዎች ሆነው ሃሳባቸውና ስራቸው ብላሽ ይሆናል። 

  ትክክል አስቦ ያሰበውን ትክክል አድርጎ በቃል ወይም በጽሕፈት አስረድቶ እንዳሰበውና እንደተናገረውም አድርጎ ትክክል የሚሰራ ሰው እውነት ትልቅ ዐዋቂ ነው ሊባል ይችላል።

  ምንጭ
  • ታሪክና ምሳሌ (ከበደ ሚካኤል)

 • loader Loading content ...
 • @Yared   2 years ago
  Sewasewer
  ምቀኛ ሰው የክፋቱ ብዛት የሞቱ ሰዓት በደረሰች ጊዜ እኔ ከሞትኩኝ በሇላ አለም ጨለማ ሁና ትቅር ብሎ በማሰብ የሚቻለው ቢሆን ኖሮ ፀሃይን አጥፍቷት ለመሞት በወደደ ነበር። ቅን ሰው ግን ለአለም የሚጠቅም ሥራ ለመስራት ሲል ህይወቱን ይሠዋል።

  ምንጭ
  • ታሪክና ምሳሌ (ከበደ ሚካኤል)

 • loader Loading content ...
 • @Yared   2 years ago
  Sewasewer
  ፀሃይ ጡዋት ጡዋት የምትወጣው የሱን ድምፅ ሰምታ እየመሰለው በልቡ ሲኮራ የሚኖር አንዳንድ አውራ ዶሮ አለ ይባላል። በሕዝብም መካከል እንደዚሁ ሊሰሩት የማይችሉትን ትልቅ ስራ የሰሩት እየመሰላቸው በከንቱ ሲመኩ የሚታዩ ሰዎች ይገኛሉ።

  ምንጭ
  • ታሪክና ምሳሌ (ከበደ ሚካኤል)

 • loader Loading content ...
 • @Yared   2 years ago
  Sewasewer
  በጌታና በድሃ መካከል የሚገኘው ልዩነት በጣም የተራራቀ ነው። ይሁን እንጂ ጌትነትና ድህነት ጎን ለጎን ሲሄዱ ይኖራሉ።

  ምንጭ
  • ታሪክና ምሳሌ (ከበደ ሚካኤል)

 • loader Loading content ...
 • @Yared   2 years ago
  Sewasewer
  ከጥንት ጀምሮ ሲነገር የሚኖር አንድ የላቲን ተረት እንዲህ ይላል። ጦርነት እንዳይመጣብህ ብትፈልግ ሁልጊዜ ለጦርነት የተሰናዳህ ሆነህ መቀመጥ ይገባሀል።

  ምንጭ
  • ታሪክና ምሳሌ (ከበደ ሚካኤል)

 • loader Loading content ...
  Load more...
loader Loading content ...

Comments (4)


 • @Yared   1 year ago
  Sewasewer
  Ethiopia has many attractions worth visiting, this is indeed one of them! Thanks for sharing!
 • @Yared   1 year ago
  Sewasewer
  very interesting! ታሪካችንን እንደዚህ ባለ አቀራረብ ስላካፈልከን እናመሰግናለን @Wubante!
 • @Yared   1 year ago
  Sewasewer
  በስንቱ ደም እና አጥንት መስዋእትነት የቆምሽ አንቺ አገር ፣ ሌላ ምን እልሻለሁ ፣ ገፅታሽ ይኑር ይከበር።
 • @Yared   2 years ago
  Sewasewer
  ምስጋና @ጎሳ። ሁሌም የምታስነብበን ኣጫጭር ታሪኮች አስተማሪ ናቸው። ግፋበት!
  አንድ አስተያየት - የአመተ ምህረቶችን የአረብኛ ትርጏሜም ብታካትትልን ጥሩ ነው እላለሁ።
loader Loading content ...