loader

Topics (111)


loader Loading content ...

Explanations (6)


 • @Biruk   2 years ago
  Sewasewer
  የከፍተኛ ትምህርት አገባብነትና ጥራት ኤጀንሲ (ከትአጥኤ) ራሱን የቻለ ህጋዊ ሰውነት ያለው አካል ሆኖ በከፍተኛ ትምህርት አዋጅ ቁጥር 351/1995 የተቋቋመ ሲሆን ተጠሪነቱም ለትምህርት ሚኒሰቴር ነው፡፡

  የእጀንሲው ስልጣንና ተግባር

  በአዋጅ ቁጥር 351/1995 ከተገለፀው የኤጀንሲው ስልጣንና ተግባራት መካከል ዋና ዋናዎቹ የሚከተሉት ናቸው

  • በማንኛውም ተቋም የሚሰጡ የከፍተኛ ትምህርት ስልጠናዎች ደረጃቸውን የጠበቁ አግባብነትና ጥራት ያላቸው መሆናችውን ያረጋግጣል፡፡
  • በማንኛውም ተቋም የሚሰጠው የከፍተኛ ትምህርት ስልጠናዎች ከሀገሪቱ የኢኮኖሚ፤ ማህበራዊና ሌሎች አግባብነት ያላቸው ፖሊሲዎች ጋር መገናዘባቸውን ያረጋግጣል፡፡
  • በዚህ አዋጅና አግባብነት ባላቸው ህጎች መሰረት ለሚኒስትሩ ወይም ለኤጀንሲው የቀረበን የቅድመ እውቅና ፈቃድ፤ የእውቅና ፈቃድ ወይም የእውቅና እድሳት ፈቃድ ጥያቄን መርምሮ ለሚኒሰትሩ የውሳኔ ሃሳብ ያቀርባል፡፡
  • ተቋማቱ ያሉበትን ሁኔታና ደረጃ በየጊዜው ለህዝብ በተለያዩ መንገዶች ያሳውቃል፡፡

  ኤጀንሲው የሚሠጣቸውአገልግሎቶች
  1. የግል የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት በመደበኛ እና በርቀት የዕውቅና ፈቃድ እና ዕውቅና እድሳት ጥያቄዎች ሲያቀርቡ የማመልከቻ ሰነዱን መመርመር፣ የመስክ ግምገማ ማካሄድ፣ሪፖርት ማዘጋጀት ውሳኔውን ማሳወቅ
  2. ድንበር ዘለል የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት በ2ኛና በ3ኛ ዲግሪ የስልጠና መስኮች የዕውቅና ፈቃድ እና ዕውቅና ፈቃድ እድሳት ጥያቄ ሲያቀርቡ የማመልከቻ ሰነዱን መመርመር፣ የመስክ ግምገማ ማካሄድ፣ ሪፖርት ማዘጋጀትና ውሳኔውን ማሳወቅ።
  3. ዕውቅና ከተሰጣቸው የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የተገኙ የትምህርት ማስረጃዎችን ጥያቄዎች ሲቀርቡ የማረጋገጥ (Authentication) አገልግሎት መስጠት
  4. አንድ የግል የከፍተኛ ትምህርት ተቋም የሚሰጠው ፕሮግራም ዕውቅና ያለው ስለመሆኑ ማወቅ ለሚፈልጉ መረጃ መስጠት
  5. ከውጭ አገር ለተገኙ የከፍተኛ ትምህርት ማስረጃዎች ጥያቄዎች ሲቀርቡ የአቻ ግምት (equivalence) አገልግሎት መስጠት 
  6. በውጭ አገር የሁለተኛ ደረጃ ትምህርታቸውን አጠናቀው በአገር ውስጥ የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ትምህርት መቀጠል ስለመቻላቸው እንዲረጋገጥላቸው ለሚፈልጉ ተገልጋዮች ማረጋገጫ መስጠት
  7. ዕውቅና የተሰጣቸውን ተቋማት፣ ካምፓሶች፣ ፕሮግራሞችና እንዲሁም ሌሎች ኤጀንሲውን የሚመለከቱ መረጃዎችን ማጠናቀርና ለሕብረተሰቡ ማሳወቅ
  8. የዕውቅና ፈቃድ ከተሰጣቸው በኋላ የደረጃ ብቃት መመዘኛውን ሳያሟሉና የዕውቅና ፈቃድ ሳይኖራቸው ትምህርት በሚሰጡ ተቋማት ላይ ሕጋዊ እርምጃ መውሰድ እና ለሕብረተሰቡ ማሳወቅ
  9. ለከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ስለ ጥራት ማጎልበትና ማረጋገጥ ፅንሰ ሐሣቦችና ተሞክሮዎች እንዲሁም የውስጥ ጥራት ማረጋገጥ ሥርዓት ዝርጋታ ፣አደረጃጀትና አሰራር በተመለከተ ስልጠና መስጠት
  10. ለከፍተኛ የትምህርት ተቋማት ስለ ተቋማዊ የጥራት ኦዲት ግለ-ግምገማ አፈፃጸምና ሪፖርት አዘገጃጀት ስልጠና መስጠት
  11. የጥራት ኦዲትና የዕውቅና አሰጣጥ ተግባር ላይ ኤጀንሲው ለሚያሰማራቸው የውጭ ባለሙያዎች ስልጠና መስጠት
  12. ስለከፍተኛ ትምህርት የጥራት ኦዲት ግለ-ግምገማ ሪፖርት ላቀረቡ የከፍተኛ የትምህርት ተቋማት የቅድመ-ኦዲት ገለጻ ማድረግ፣ ተቋማዊ የጥራት ኦዲት ማካሄድ፣ ሪፖርት ማዘጋጀትና ለአስተያየት ማቅረብ፥ለህትመት ማዘጋጀት
  13. ተቋማዊ እና የፕሮግራም የጥራት ኦዲት ሪፖርቶችን አሳትሞ ለባለድርሻ አካላት ማሰራጨት
  14. ተቋማዊ እና የፕሮግራም የጥራት ኦዲት ተካሄዶ ሪፖርታቸው ለባለድርሻ አካላት ለተሰራጨው ተቋማት የጥራት ማጎልበቻ ዕቅድ እንዲያቀርቡ ማድረግና ባቀረቡት የጥራት ማጎልበቻ ዕቅድ መሠረት እየተንቀሳቀሱ መሆኑን መከታተል 
  15. የከፍተኛ ትምህርት ጥራት ማጎልበትና ማረጋገጥን በተመለከተ እገዛ ለሚፈልግ ማንኛውም ተቋም ሙያዊ ድጋፍ መስጠት
  16. የከፍተኛ ትምህርት ጥራትን ለማረጋገጥ የሚያግዙ ጥናቶችን ማካሄድ እና የጥናቱን ውጤት ለባለድርሻ አካላት ማሰራጨት/ማሳወቅ
  17. የከፍተኛ ትምህርትን ጥራት ለማረጋገጥ የሚያግዙ ምርጥ ተሞክሮዎችን ማሰባሰብና ማሰራጨት
  18. የከፍተኛ ትምህርት ጥራት ማጎልበትና ማረጋገጥን በተመለከተ የግንዛቤ ማስጨበጫና የተሞክሮ መለዋወጫ መድረኮችን ማዘጋጀት
  19. የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የደረጃ ስያሜ መስጠት

  አድራሻ:-
  • ስልክ
   • ቀጥታ - +251- 111-23-61-30/23-22-30
   • ዳይሬክተር ቢሮ - 251-111- 23-22-27
  • ፋክስ
   • +251 111236127
  • ፖሣቁ
   • 27424/1000

  ምንጭ    
  • የከፍተኛ ትምህርት አግባብነትና ጥራት እጀንሲ ድህረ-ገፅ (http://www.herqa.edu.et/)
  • የኢትዮጵያ ትምህርት ሚንስቴር ድህረ-ገፅ (http://www.moe.gov.et/)

 • loader Loading content ...
 • @Biruk   2 years ago
  Sewasewer
  አገልግሎቱን ለማግኘት የሚያስፈልጉ መስፈረቶች  
  • የትምህርት ማስረጃ
  • ሬኮማንዴሽን ሌተር
  • መሸኛ ደብዳቤ

  አገልግሎቱን ለማግኘት የሚከናወኑ ሂደቶች  
  1. ስኮላር ሺ በትምህርት ሚኒስቴር በተቋቋሙ ኮሚቴ በኩል የተደለደለ ከሆነ ተመራጭ እዎች አሟልተው መላክ ያለባቸውን መረጃ በትክክል ተሟልተው እድሉ በተሰጠው መስሪያ ቤት ሀላፊ ተፈርሞና ተረጋግጦ ወደ ትምህርት ሚኒስቴር የከፍተኛ ትምህርት ስርዓት ማሻሻያ ለውጥ መምሪያ ቢሮ ማቅረብ
  2. አመልካቹ በግንባር መቅረብ ካልቻለ በወኪል የውክልና ማረጋገጫ ደብዳቤና ማንነት ማረጋገጫ መታወቂያ በመያዝ ማቅረብ
  3. አመልካች በግንባር እንዲገኙ ካልፈለጉ መረጃውን በመስሪያ ቤቱ በፖስታ ቤት ወይም በመልእክተኛ መላክ ይቻላል
  4. ከላይ የተገለፁት ማስረጃዎች በከፍተኛ ትምህርት ስርዓት ማሻሻያ ለውጥ መምሪያ ቢሮ ይገመግማል
  5. ማስረጃዎች ተሟልተውና አስፈላጊው ሁሉ ከቀረበ በኃላ እድሉን ለሠጠው ኢንባሲ ይልካል


  ምንጭ    
  • የኢትዮጵያ ትምህርት ሚንስቴር ድህረ-ገፅ (http://www.moe.gov.et/)

 • loader Loading content ...
 • @Biruk   2 years ago
  Sewasewer

  አገልግሎቱን ለማግኘት የሚያስፈልጉ መስፈረቶች
  • የትምህርት ተቋሙ ማስረጃ እንዲላክላቸው የጠየቁበት ደብዳቤ
  • ስድስት ወር ያልሞላው 1 ጉርድ ፎቶ ግራፍ ሁለቱም ጆሮዎች የሚታዩበት
  • የውክልና ማረጋገጫ ደብዳቤና ማንነት ማረጋገጫ መታወቂያ

  አገልግሎቱን ለማግኘት የሚከናወኑ ሂደቶች
  1. ምዝገባ ክፍል በመሄድ የሚሞላ ፎርም ይወሠዳል
  2.  የተሞላውን ፎርም በዛው ቢሮ ማስገባት
  3. የሚመለከተው አካል ማመልከቻውን ይመለከታል
  4.  ማመልከቻውን ከተመለከተ በኋላ የአገልግሎት ክፍያ እንዲፈፀም ማመልከቻው ላይ ፈርመው ወደ ገንዘብ ቤት ይመራል
  5.  የተመራውን ደብዳቤ በመውሠድ ገንዘብ ቤት እንደ አገልግሎቱ ክፍያ ይከናወናል
  6. የተከፈለበትን ደረሰኝ በመዝገብ ቤት ይዞ ይሄዳል
  7. በዛው ቢሮ ቀጠሮ ይሠጠዋል
  8. በተሠጠበት ቀጠሮ መታወቂያ ይዞ በመምጣት የትምህርት ማስረጃውን የሚመለከተው አካል ይወስዳል

  ምንጭ   
  • የኢትዮጵያ ትምህርት ሚንስቴር ድህረ-ገፅ (http://www.moe.gov.et/)

 • loader Loading content ...
 • @Biruk   2 years ago
  Sewasewer
  አገልግሎቱን ለማግኘት የሚያስፈልጉ መስፈረቶች
  • ስድስት ወር ያልሞላው 1 ጉርድ ፎቶ ግራፍ ሁለቱም ጆሮዎች የሚታዩበት
  • የቀበሌ ነዋሪነት መታወቂያ
  • ተወካይ ከሆነ የውክልና ማረጋገጫ ደብዳቤና የማንነት ማረጋገጫ መታወቂያ             በድጋሜ የምስከር ወረቀት እንዲዘጋጅላቸው መጠየቂያ ቅጽ


  አገልግሎቱን ለማግኘት የሚከናወኑ ሂደቶች
   
  1. ምዝገባ ክፍል በመሄድ የሚሞላ ፎርም ይወሠዳል
  2. የተሞላውን ፎርም በዛው ቢሮ ማስገባት
  3. የሚመለከተው አካል ማመልከቻውን ይመለከታል
  4. ማመልከቻውን ከተመለከተ በኋላ የአገልግሎት ክፍያ እንዲፈፀም ማመልከቻው ላይ ፈርመው ወደ ገንዘብ ቤት ይመራል
  5. የተመራውን ደብዳቤ በመውሠድ ገንዘብ ቤት እንደ አገልግሎቱ ክፍያ ይከናወናል
  6. የተከፈለበትን ደረሰኝ በመዝገብ ቤት ይዞ ይሄዳል
  7. በዛው ቢሮ ቀጠሮ ይሠጠዋል
  8. በተሠጠበት ቀጠሮ መታወቂያ ይዞ በመምጣት የትምህርት ማስረጃውን የሚመለከተው አካል ይወስዳል

  ምንጭ  
  • የኢትዮጵያ ትምህርት ሚንስቴር ድህረ-ገፅ (http://www.moe.gov.et/)

 • loader Loading content ...
 • @Biruk   2 years ago
  Sewasewer

  አገልግሎቱን ለማግኘት የሚያስፈልጉ መስፈርቶች  
  • የቀበሌ ነዋሪነት መታወቂያ
  •  የጠየቁት ብዛት ያህል ሠርተፊኬት ፎቶ ኮፒ             የትምህርት ማስረጃ ማረጋገጫ መጠየቂያ ቅጽ

    
  አገልግሎቱን ለማግኘት የሚከናወኑ ሂደቶች  
  1. ምዝገባ ክፍል በመሄድ የሚሞላ ፎርም ይወሠዳል
  2. የተሞላውን ፎርም በዛው ቢሮ ማስገባት
  3. የሚመለከተው አካል ማመልከቻውን ይመለከታል
  4. ማመልከቻውን ከተመለከተ በኋላ የአገልግሎት ክፍያ እንዲፈፀም ማመልከቻው ላይ ፈርመው ወደ ገንዘብ ቤት ይመራል
  5. የተመራውን ደብዳቤ በመውሠድ ገንዘብ ቤት እንደ አገልግሎቱ ክፍያ ይከናወናል
  6. የተከፈለበትን ደረሰኝ በመዝገብ ቤት ይዞ ይሄዳል
  7. በዛው ቢሮ ቀጠሮ ይሠጠዋል
  8. በተሠጠበት ቀጠሮ መታወቂያ ይዞ በመምጣት የትምህርት ማስረጃውን የሚመለከተው አካል ይወስዳል

  ምንጭ 
  • የኢትዮጵያ ትምህርት ሚንስቴር ድህረ-ገፅ (http://www.moe.gov.et/)

 • loader Loading content ...
 • @Biruk   2 years ago
  Sewasewer
  ተልእኮ 
  • በሁሉም ደረጃዎች ጥራቱን የጠበቀ ችግር ፈቺ እንዲሁም የሃገሪቱን የተማረ  የሰው ሃይል ፍላጐት በበቂ ሁኔታ መመለስ የሚችል የትምህርት እና ስልጠና ስርዓት በመላ ሃገሪቱ መዘርጋት፤ 
  • የትምህርት ስርዓቱን አስተዳደራዊ መዋቅር ያልተማከለ፣ የተቀናጀ፣ አሳታፊ፣ ሙያዊ፣ እና ብቁ ማድረግ 
  • የትምህርት ዘርፉን የገንዘብ አቅም ማሳደግ፣ 
  • የትምህርት ዘርፉን ከሌሎች ተዛማጅ ዘርፎች ጋር ያለው ግኙነት ማሳደግ እና የልዩ እና መደበኛ ያልሆኑ ትምርት ጥያቄዎችን መመለስ፡፡                የኢትዮጵያ ትምህርት ሚንስቴር ዋናው መስሪያ ቤት

  አድራሻ
  • ዋናው መስሪያ ቤት የሚገኝበት ቦታ - አራት ኪሎ ፣ አዲስ አበባ
  • ፖሥታ ሣጥን ቁጥር - 1367 አ.አ
  • ስልክ - 0111553133
  • ፋክስ -  0111570686

  ዳይሬክቶሬቶች
  • የትምህርት ዘርፍ ዕድገት፣ዕቅድና ፓሊሲ ዳይሬክቶሬት
  • ግዢና ንብረት አስተዳደር ዳይሬክቶሬት
  • ፋይናንስ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክቶሬት
  • የሰው ኃይል ሀብት አሰተዳደር ዳይሬክቶሬት
  • የፃታ እኩልነት ዳይሬክቶሬት
  • የውጭ እና የህዝብ ግኑኝነት ዳይሬክቶሬት
  • የኦዲት አገልግሎት ዳይሬክቶሬት
  • የእንግሊዝኛ ቋንቋ ዳይሬክቶሬት
  • የኢንፎርሜሽን ኮሚኒኬሽን ቴክኖሎጂ ዳይሬክቶሬት
  • አጠቃላይ የትምህርት ካሪኩለም ቀረፃ ዳይሬክቶሬት
  • የቴክኒክና ሙያ ትምህርት ተቋሞች የአሰራር መሻሻያና አቅም ግንባታ ዳይሬክቶሬት
  • የትምህርት መርሀ ግብሮችና የመምህራን ስልጠና ዳይሬክቶሬት
  • የከፍተኛ ትምህርት ማስፋፊያና ማጠናከሪያ ዳይሬክቶሬት
  • የይዞታ ደረጃና ምዘና ዳይሬክቶሬት

  የሚንስቴር መስሪያ ቤቱ መዋቅር


  መስሪያ ቤቱን በኃላፊነት የመሩት ሚንስትሮች
  • አቶ ሽፈራው ሸጉጤ (Shiferaw Shegute) - ከ2005 ዓ.ም. እስከ አሁን

     • አቶ ደመቀ መኮንን (Demeke Mekonen) - ከ2000 ዓ.ም. እስከ 2005 ዓ.ም.

  • ወ/ሮ ገነት ዘውዴ (Genet Zewde)
  ምንጭ
  • የኢትዮጵያ ትምህርት ሚንስቴር ድህረ-ገፅ (http://www.moe.gov.et/)


 • loader Loading content ...
loader Loading content ...

Comments (3)


 • @Biruk   1 year ago
  Sewasewer
  የሚገርም ነው :) ይሄኔ ስንቱ አልቋል ሢሻገር! ምስኪን ህዝብ።
 • @Biruk   1 year ago
  Sewasewer
  የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርት ቤት እያለሁ የአማርኛ መፅሃፍ ምንባብ ላይ ሲነበብ በህፃንነቴ የመሰጠኝ ታሪክ ነበር። አሁንም፣ ሁሌም እጅግ የሚያኮራ የጀግንነት ታርካችን ነው! ኢትዮጵያ ለዘላለም ትኑር!!
 • @Biruk   1 year ago
  Sewasewer
  Wow! Thanks a lot!
loader Loading content ...