loader

Topics (1098)


loader Loading content ...

Explanations (91)


 • @Demoze   10 months ago
  Sewasewer
  ይህ ሚኒስቴር የመንግሥት ግምጃ ቤት ዋና ጠባቂ ነው ፤ የሱ ሥራ ይህ ነው ። 
  • መዠመሪያ ። 
  የመንግሥት ግምጃ ቤት የንጉሥ የራሳቸው ግምጃ ቤትና የንጉሥ ያልጋቸው ገንዘብ የልዩ ልዩ ፤ ነው ። 
  • ሁለተኛ ። 
  የንጉሥ የራሳቸውና ያልጋቸው ግምጃ ቤትን ይጠብቃል ። (ሀ) የራሳቸውን ከራሳቸው በኋላ ወራሻቸው ይወርሳቸ ዋል ፤ ደግሞ በደብዳቤ ለአብያተ ክርስቲያናት ፤ ለበሽተኛ ቤቶች ፣ ለምጿት ወይም ለሰው ስጦታ መስጠት ይችላል ። (ለ) የግላቸው ገንዘብ ግን በሕይወታቸው የርሳቸው ገንዘብ ነው ፤ ነገር ግን ከርሳቸው በኋላ አዲሱ ንጉሥ ይወርሳል ። 
  • ሦስተኛ ። 
  የመንግሥት ገንዘብ ስላገር ግዛትና ስለ መንግሥት ሥራ ነው ። 
  • አራተኛ ። 
  የገንዘብ ሚኒስቴር በባንክና በሌላ ገንዘብ ቤት የመንግ ሥት ምስለኔ ነው ። 
  • አምስተኛ ። 
  ርሱ ያገር ግምጃ ቤት አለቃ ነው ፤ ርሱ ነው የሚያሾማ ቸው በንጉሠው ቃል ። 
  • ስድስተኛ ። 
  የመንግሥትን ገቢ ሁሉ ወደ ሣጥኖቹ ይሰበስባል ፤ የሌላ ሚኒስቴር ገቢ ፣ የግዛትም ፤ የትልልቆችም ቤቶች የባንኮችም ፤ የሞ ኖፖልም ፣ የመንግሥት መሥሪያ ቤትም ፤ ሌሎችም ወደ ገንዘብ ሚኒስቴር ሲገባ ከደብተሩ ጋራ ይገባል ። ደብተሩም በገንዘብ ሚኒስቴር ቤት እሣጥን ውስጥ ይቀመጣል ፣ ሚኒስቴሩም ተቀ በልኩ የሚል ወረቀት ይሰጣል ። 
  • ሰባተኛ ። 
  የመንግሥት ወጪ ሁሉ ከገንዘብ ሚኒስቴር ሣጥን ይወ ጣል ተቀበልኩ የሚል ወረቀት እየተቀበለ ። 
  • ስምንተኛ ። 
  ብዙ ገቢና ወጪ ወር ሲዝ`መር በአምስቱ መዠመሪያ ቀን መጨረሻ ነው ። 
  • ዘጠነኛ ። 
  ሚኒስቴሮቹ ወር ሲገባ እስካ፭ኛ ቀን ድረስ ደብተ ሩን ደምረው ወደ ገንዘብ ሚኒስቴር ይልካሉ ። የተረፈውን ፣ ያገባሉ ፤ ወይም ያነሰውን ይከፍላሉ ። 
  • ዐሥረኛ ። 
  ከብዙ ገቢና ወጪ ነገር በቀር ሌላ ልዩ ወጪ አለንጉሥ የሚያዙት ። ስለዚህ ግምጃ ቤት ዘወትር ክፍት እንዲሆን ይገባል ፣ በቀን በቀን ፬ ሰዓት ፣ ከሰንበትና ከበዓላት ቀን በቀር ። 
  • ዐሥራ አንደኛ።
  የገንዘብ ሚኒስቴር ነው በመንግሥትና በነጋዴ የመንግሥት አሰናጂዎች መካከል ውል የሚያደርግ ፤ ሲመች ኀራጅ ያደርጋል ። 
  • ዐሥራ ሁለተኛ ። 
  ለፈረንጆች የሚሰጥ ውል ፤ ሞኖፖል ፤ እርሻ ሌሎች ፤ ለገን ዘብ ሚኒስቴር ማስታወቅ ነው ። የመንግሥት ግምጃ ቤት ጠባቂ ነው ። 
  • ዐሥራ ሦስተኛ ። 
  የመንግሥት ስሌት ደብተር ሁሉ በገንዘብ ሚኒስቴር እጅ እንዲሆን ነው ። 
  • ዐሥራ አራተኛ ። 
  የመንግሥት ስሌት ደብተር ዕጥፍ ፤ እንዲሆን ያስፈልጋል ። ስለ ምን አንዱ ቢጠፋ አንዱ ይጸናል፣ ሒሳቡም ሲፈለግ ይገኛል። 
  • ዐሥራ አምስተኛ ። 
  የገንዘብ ሚኒስቴር በ፫ ወር አንድ ጊዜ የመንግሥት ሒሳብ ሚዛን ያደርጋል ። ደግሞ የዳር አገር ግምጃ ቤቶች ሁሉ ደብተራቸውን ይደምራሉና ወደ ገንዘብ ሚኒስቴር ይል ካሉ ፤ ከሒሳባቸውም የ፫ ወር ቀሪ ይጽፋሉ ፤ የግምጃ ቤታቸ ውን ብር ሁሉ ። 
  • ዐሥራ ስድስተኛ ። 
  በዓመት መጨረሻ የሒሳብ ሚዛን ማድረግ ነው ፤ በገንዘብ ሚኒስቴር ስሌቱን ማስቀመጥና ለንጉሥ ለመማክርቱ ማኅበር ማሳየት ነው ። 
  • ዐሥራ ሰባተኛ ።
   የገንዘብ ሚኒስቴር እንደ ወደደ ወደ ዳር አገር መር ማሪ መስደድ ይችላል ፤ ይህ መርማሪ የግምጃ ቤቶችን ሣጥንና መዝገብ ይመረምራል ። 
  • ዐሥራ ስምንተኛ ። 
  ባመት መጨረሻ የገንዘብ ሚኒስቴር የጓዳ ዕቃ ቈጥሮ በመዝገብ ይጽፋል ፤ ዕቃውን በያይነቱ ባ፩ ልዩ መዝገብ ይጽ ፋል ፤ ደግሞ ለመንግሥት ሥራ ሚኒስቴር የቃ ቤቱ መዝገብ ይጠይቃል ። 
  • ዐሥራ ዘጠነኛ ። 
  የገንዘብ ሚኒስቴር ባመት መጨረሻ መዝገቡን ደምረው የሌላ ሚኒስቴሮችን መዝገብ ጨምረው የመንግሥት ይደረጋል ። 
  • ካያኛ ። 
  ዓመት ከተጨረሰ በኋላ ገቢና ወጪ ከተደመረ በኋላ የተረፈውን ብር በሣጥን ለብቻ ያስቀምጡታል ፤ ይህ ሣጥን የመንግሥት ድልብ ይሆናል ፤ ለዚህም ለድልብ ሣጥን አንድ አለቃ ለብቻ ይደረግለታል ፣ መዝገቡ ለብቻ ነውና ፤ ከዚህም ሣጥን ሲያወጡ ለማኅበር መማክርት ማስታወቅ ነው ። 
  • ካያ አንደኛ ። 
  በክፉ ዓመት ድንገት ገቢ ከወጪ ያነሰ እንደ ሆነ መን ግሥት ከድልብ ሣጥኑ ያወጣል ፤ ክፉ ዓመት ማለት ጦርነት የሆነ እንደ ሆነ ወይም ረኃብ ወይም “ኮሌራ” ወይም ክፉ ሌላ በሽታ ። 
  • ካያ ሁለተኛ ። 
  ድንገት ገንዘብ የተበደረ እንደ ሆነ ፣ ትልቅ ሥራ እዲሠራበት ፥ የገንዘብ ሚኒስቴር ነው ይህንን ብድር የሚጠብቅ ፣ ወለዱ ባመት ባመት ይሰጣልና ዋና ገንዘቡን ይከፍላል ፣ ለብ ድሩ ውል ተብሎ እንደ ተጻፈ ። 
  • ካያ ሦስተኛ ። 
  ከገንዘብ ሚኒስቴር ሣጥን የሚወጣና የሚገባ ብር በባለ ዕጥፍ ወረቀት ደብተር ይጻፋል ፣ አንዱን ወረቀት ቀደው አን ሥተው ሁለተኛው በመዝገብ ውስጥ ይቀራል ፣ በ፪ኛ ወረቀት የተጻፈው ቃል አንድ ይሆናል ። 
  • ካያ አራተኛ ። 
  የገንዘብ ሚኒስቴር መዝገቦች ሁሉ ሒሳባቸው በልክ እን ዲሆን ፣ የመንግሥት ስሌት ልክ ያልሆነ እንደ ሆነ መንግሥቱ ኪሳራ ይገባል ። 
  • ካያ አምስተኛ ። 
  ንጉሥ የመንግሥት ማኅበርም መማክርት እንዲያደርጉ ብለዋል ፣ ይህ ማኅበር ሲሰበሰብ በስብከተ ገና ጊዜ የገንዘብ ሚኒስቴር ስለዚህ መማክርት ያገር ሀብት ማሳየት ያስፈልጋል ። 
  • ካያ ስድስተኛ ። 
  የገንዘብ ሚኒኒስቴር ሥራውን እንደዚሁ ይከፍላል ፤ ለየክፍሉ አንዳንድ አለቃ እያደረገ ። ፩ኛ ፤ የግብርና የጉምሩክ ክፍል ። ፪ኛ ፤ የጽፈት ክፍል ፫ኛ ፤ የግምጃ ቤት ክፍል ፬ኛ ፤ የባንኮች ክፍል ፭ኛ ፤ የድልብ ሣጥን ክፍል ፮ኛ ፤ የልብስና የጌጥ ዕቃ ክፍል ፯ኛ ፤ የጓዳ ክፍል ከልብስና ከጌጥ በቀር ። 

  ለየክፍሉ አንዳንድ ልዩ ማኅተም ይደረጋል ፥ ስለ ትንሽ ነገር ፤ ስለ ቁም ነገር ፥ ግን የሚኒስቴሩ ማኅተም ያስፈልጋል ።

  ምንጭ፤
  ዝክረ ነገር
  ባላምባራስ ማህተመ ስላሴ ወልደ መስቀል።
 • loader Loading content ...
 • @Demoze   10 months ago
  Sewasewer
  የኢትዮጵያ ዜጋ ሁኖ ለመቈጠር ለሚገባው ለውጭ አገር ዜጋ ከዚህ ቀጥሎ ያለውን ሕግ አቁመናል ። 

  • መዠመሪያ ። 
  በኢትዮጵያ ወይም በውጭ አገር ካንድ " ኢትዮጵያዊ " ወይም ካንዲት ኢትዮጵያዊት የተወለደ ሁሉ የኢትዮጵያ ዜጋ ነው ። 
  • ሁለተኛ ። 
  አንድ የኢትዮጵያ ዜጋ ከውጭ አገር ሴት ጋራ በሥር ዐት የተጋባ እንደ ሆነ ሴትዮዋ የኢትዮጵያ ዜጋ ትሆናለች ። 
  • ሦስተኛ ። 
  ይህን በመሰለ ጊዜ በሥርዐት የተደረገ ሁኖ የሚቈጠረው ጋብቻ ። (ሀ) አንድ የኢትዮጵያ ዜጋ ካንዲት የውጭ አገር ሴት ጋራ እንደ ኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን ሥርዐት ወይም እንደ ኢትዮጵያ ጋብቻ ልማድ በባለኩል ደንብ (ሲቪል) በኢትዮጵያ የሚደረገው ጋብቻ ነው ። (ለ) አንድ የኢትዮጵያ ሰው ካንዲት የውጭ አገር ሴት ጋራ በተጋቡበት አገር እንደሚደረገው የጋብቻ ሥርዐት በውጭ አገር በሚደረገው ጋብቻ ነው ። 
  • አራተኛ ። 
  አንዲት የኢትዮጵያ ዜጋ የሆነች ሴት ካንድ ከውጭ አገር ሰው ጋራ በሥርዐት የተጋባች እንደ ሆነ ከውጭ አገር ሰው ጋራ በመጋባቷ ምክንያት የባሏን ዜግነት የምትይዝ የሆነች እንደ ሆነ የኢትዮጵያ ዜጋ መሆንዋ ይቀራል ። የጋብ ቻዋ ሥርዐት የባሏን ዜግነት የማይሰጣት የሆነ እንደ ሆነ ግን የኢትዮጵያ ዜጋ እንደ ሆነች ትቀራለች ፤ ነገር ግን በጋ ብቻ ምክንያት የውጭ አገር ዜጋ የሆነችው ሴት ባለርስት የሆነች እንደ ሆነ የርስቷ ነገር የኢትዮጵያ ንጉሠ ነገሥት መንግሥት ባቆመው የርስት ደንብ ይጨረሳል ። 
  • አምስተኛ ። 
  ይህን በመሰለ ጊዜ በሥርዐት የተደረገ ሁኖ የሚቈጠረው ጋብቻ ። (ሀ) የኢትዮጵያ ሴት ካንድ የውጭ አገር ሰው ጋራ በባሏ ቆንስል ፊት በኢትዮጵያ የምታደርገው ጋብቻ ነው ። (ለ) የኢትዮጵያ ሴት ካንድ የውጭ አገር ሰው ጋራ እንደ ባሏ አገር ሕግ ጋብቻውም በሚፈጸምበት አገር እንደሚደረ ገው ሕግ ሥርዐት በውጭ አገር የምታደርገው ጋብቻ ነው ። 
  • ስድስተኛ ። 
  ከዚህ በላይ በተጻፈው ክፍል እንደ ተነገረው የኢትዮጵያና የውጭ አገር ሰዎች በሥርዐት ተጋብተው ልጆች የወለዱ እንደ ሆነ የተወለዱት ልጆች ሁሉ ያባታቸውን ዜግነት ይይ ዛሉ ። ስለ ሆነ ፤ የጋብቻ ሥርዐት ፈጽመው ከተጋቡ ካንድ ኢትዮጵያዊና የውጭ አገር ሴት የተወለደ ልጅ የናቱን የቀ ድሞ ዜግነት አለመያዙን ሥልጣን ባላቸው በኢትዮጵያ ሹማ ምት ፊት ተጠይቆ ማስረዳት አለበት ። 
  • ሰባተኛ ።
  የጋብቻ ሥርዐት ፈጽመው ከተጋቡ ካንዲት የኢትዮጵያ ሴትና ካንድ የውጭ አገር ሰው የተወለደ ልጅ በኢትዮጵያ ነዋሪ የሆነ እንደ ሆነ ካባቱ ዜግነት መውጣቱን አስመስክሮ በማናቸውም ጊዜ ቢሆን ወደ ኢትዮጵያ ዜግነት ሊመለስ ይችላል ። 
  • ስምንተኛ ። 
  አንድ የውጭ አገር ሰውና አንዲት የኢትዮጵያ ሴት ፣ ልጅ ከወለዱ በኋላ እንዳባትዮው አገር ሕግ በሥርዐት የተጋቡ እንደ ሆነ ደግሞ ያባትዮው አገር ሕግ ልጁን የውጭ አገር ዜጋ የሚያደርገውና የውጭ አገር ዜጋም በመሆኑ ምክንያት የሚቀበለውን ሥልጣን ሁሉ የሚያሰጠው የሆነ እንደ ሆነ ከጋ ብቻ በፊት የተወለደው ልጅ ያባቱን የውጭ አገር ዜግነት ይይዛል ። በዜግነቱ የሚቀበለውን ሥልጣን ሁሉ ለማግኘት ያል ቻለ እንደ ሆነ ግን የኢትዮጵያ ዜግነቱን ጠብቆ ይኖራል ። 
  • ዘጠነኛ ። 
  አንድ የውጭ አገር ሰውና አንዲት የኢትዮጵያ ሴት ሳይ ጋቡ ልጅ የወለዱ እንደ ሆነ የውጭው አገር ሰው ልጄ ነው ብሎ ቢቀበለውም ልጄ ነው ብሎ በተቀበለ ጊዜ ያባት ዮው አገር ሕግና ሥርዐት ለልጁ ያባቱን ዜግነትና ዜጋ በመ ሆኑ ምክንያት የሚቀበለውን ሥልጣን ሁሉ የሚያገኝ ካልሆነ በቀር የኢትዮጵያ ዜጋ መሆኑ ሊቀርበት አይችልም ። 
  • ዐሥረኛ ። 
  የውጭ አገር ሰዎች እንዳገራቸው ሥርዐትና ሕግ አንድ የኢትዮጵያ ልጅ ሞጋሳ አድርገው ያሳደጉ እንደ ሆነ የልጁ የቀድሞ የኢትዮጵያ ዜግነቱ ምንም ቢሆን አይለወጥም ። 
  • ዐሥራ አንደኛ ። 
  (ሀ) አንዲት የኢትዮጵያ ዜጋ ከውጭ አገር ሰው ጋራ በመጋባቷ ምክንያት የሌላ አገር ዜጋ ሁና ልትቈጠር የተገ ባት እንደ ሆነ ። (ለ) አንድ የኢትዮጵያ ዜጋ ዜግነቱን ለውጦ የውጭ አገር ዜጋ የሆነ እንደ ሆነ የኢትዮጵያ ዜጋ መሆናቸው ይቀራል ። 
  • ዐሥራ ፤ ሁለተኛ ። 
  (ሀ) እንዳገሩ ሕግ በፈቃዱ አዳሪ ለመሆን ወደሚችልበት ዕድሜ የደረሰ ። (ለ) ቢያንስ ቢያንስ አምስት ዓመት በኢትዮጵያ የኖረ ። (ሐ) ለሕይወቱና ለራሱ ለቤተ ዘመዱም የሚያስፈልገውን ነገር ለማግኘት የሚችል ። (መ) የዐማርኛ ቋንቋ የሚናገርና የሚጽፍ ። (ሠ) ከዚህ ቀድሞ በኀጢአት ወይም በወንጀል ያልተ ፈረደበት መሆኑን የሚያስመሰክር የውጭ አገር ሰው ሁሉ የኢትዮጵያ ዜጋ ለመሆን ይችላል ። 
  • ዐሥራ ሦስተኛ ። 
  የኢትዮጵያ ዜጋ ለመሆን የሚፈልገውም የውጭ አገር ሰው ጥያቄውን ወደ ውጭ ጕዳይ ሚኒስቴር ያቀርባል ፤ ከዚህም ጥያቄ ጋራ ማን እንደ ሆነ የሚመሰክርለትን ወረቀትና ከዚህ ቀድሞ ተከሶ እንደ ሆነ የተፈረደውን ነገር የሚያስረዳ የፍርድ ወረቀቱን ጨምሮ ያቀርባል ። 
  • ዐሥራ አራተኛ ። 
  በተለየ ያገር ግዛት ሚኒስትርና የውጭ ጕዳይ ሚኒስትር ሌላም አንድ የመንግሥት ሹም ባንድነት ሁነው የኢትዮጵያ ዜጋ ለመሆን ከሚጠይቀው ሰው ጋራ በቀጥታ ከተነጋገሩ በኋላ ጥያቄውን ተመልክተው የሚያስፈልገውን ምርመራ አድ ርገው የኢትዮጵያ ዜጋ እንዲሆን ይፈቅዱለታል ፤ ወይም ይከ ለከላል ። 
  • ዐሥራ አምስተኛ ። 
  ዜግነቱንም በመንግሥት ማስታወቂያ (በዴክሬ) ይቀበላል ። አዲሱም የኢትዮጵያ ዜጋ በነዚሁ ዳኞች ፊት ቀርቦ የኢትዮ ጵያን መንግሥት እንዳይከዳ ይምላል ። 
  • ዐሥራ ስድስተኛ ። 
  የውጭ አገር ሰው በዚህ አደራረግ የተቀበለው የኢትዮጵያ ዜግነት ለራሱ ብቻ ይረጋል እንጂ ሚስቱ የኢትዮጵያ ዜጋ ለመሆን ካልጠየቀች በቀር አስቀድሞ የያዘችውን ዜግነት አይ ለውጠውም ። 
  • ዐሥራ ሰባተኛ ። 
  አስቀድሞ የኢትዮጵያ ዜጋ የነበሩ የውጭ አገር ዜጋ የሆኑ ሰዎች በኢትዮጵያ ለመኖር ተመልሰው " መጥተው " እንደ " ገና ወደ ኢትዮጵያ ዜግነት ለመመለስ ከመንግሥት የጠየቁ እንደ ሆነ የኢትዮጵያ ዜጋ ለመሆን ይችላሉ ። 
  • ዐሥራ ስምንተኛ ። 
  ከውጭ አገር ሰው ጋራ በመጋባቷ ምክንያት የኢትዮጵያ ዜጋ መሆኗ የቀረ የኢትዮጵያ ሴት ከባሏ ተፋታ ወይም ባሏ ሙቶባት ጋብቻዋ ፈርሶ ወይም ከርሱ በመለያየቷ ምክ ንያት ወደ ኢትዮጵያ ተመልሳ የተቀመጠች እንደ ሆነና እንደ ቀድሞ የኢትዮጵያ ዜጋ ልሁን ብላ ከኢትዮጵያ መንግሥት የጠየቀች እንደ ሆነ እንደ ገና የኢትዮጵያ ዜጋ ለመሆን ትችላለች ። 

  ይህ ሕግ ከዚህ ቀድሞ ስለ ዜግነት ነገር የወጡትን ሕጎች ሁሉ ያፈርሳል ።

  ምንጭ፤
  ዝክረ ነገር
  ባላምባራስ ማህተመ ስላሴ ወልደ መስቀል።
 • loader Loading content ...
 • @Demoze   10 months ago
  Sewasewer
  • መዠመሪያ ክፍል ። 
  የኢትዮጵያ መንግሥት ባገሩ ውስጥ ያለውን የውጭ አገር ሰው ለማወቅ አዲስ የሚመጣውን ካሁንም በፊት በኢትዮጵያ ግዛት ውስጥ የሚኖረውን የውጭ አገር ሰው ሁሉ ስመሙንና አገሩን ሥራውንም ሚስትም ልጅም እንዳለው ስማቸውንና ዕድ ሜያቸውን በውጭ ጕዳይ ሚኒስቴር እጅ ባለው በስም ደብተር ያስጥፋል ። 
  • ፪ኛ ክፍል ። 
  ካሁን በፊት በኢትዮጵያ ግዛት የሚኖሩ የውጭ አገር ሰዎች ሁሉ ከዛሬ ዝ‛ምሮ እስከ አንድ ወር ድረስ የይለፍ ወረ ቀታቸውን ይዘው ወደ ስም ደብተር መጻፊያ ቤት ሂደው ዋጋ ውን ሁለት ብር ከፍለው ስማቸውን በስም ደብተር ያስጥፋሉ ። 
  • ፫ኛ ክፍል ። 
  ከእንግዴህ ወዲህ አዲስ የሚመጣ የውጭ አገር ሰው ሁሉ ወደ ኢትዮጵያ ፤ ግዛት ከገባ በኋላ እስከ አንድ ወር ድረስ ሁለት ብር ከፍሎ ስሙን ያስጥፋል ። ግን ካዲስ አበባ ከተማ የራቀ በሌላ ስፍራ የተቀመጠ የውጭ አገር ሰው ወረቀቱን ወደ ውጭ ጕዳይ ሚኒስቴር የስም ደብተር ቤት ሹም ልኮ ዋጋውን ሁለት ብር ከፍሎ ስሙን በስም ደብተር ጻፉልኝ ብሎ ይለምናል ። 
  • ፬ኛ ክፍል ። 
  የውጭ አገር ሰው ስመ·ን በስም ደብተር ካስጣፈ በኋላ የስም ደብተሩ ሹም ስሙን አስጥኛል የሚል የምስክር ወረቀት ይሰጠዋል ። ለውጭው አገር ሰው ከይለፍ ወረቀቱ ምልክት ጋራ የስም ደብተሩ ሹም ወረቀት የሰውነት ምስክር ይሆነዋል ፤ የዘበኛውም አለቃ የጠየቀው እንደ ሆነ ይህነኑ ወረቀት ያሳያል። የው ጭው አገር ሰው ወደ ኢትዮጵያ ዳኛ ወይም ወደ ሌላ ሹም የሄደ እንደ ሆነ ሰውነቱ እንዲታወቅ የይለፍ ወረቀቱንና የስም ደብተሩን ሹም ወረቀት ያሳያል ። 
  • ፭ኛ ክፍል ። 
  አንድ የውጭ አገር ሰው ከኢትዮጵያ አገር ለመውጣት ወይም የሚቀመጥበትን ከተማ ለመለወጥ የፈለገ እንደ ሆነ ነገ ሩን በደብዳቤ ጽፎ ለስም ደብተሩ ሹም ያስታውቃል ። 
  • ፮ኛ ክፍል ። 
  በኢትዮጵያ ግዛት ውስጥ የሚኖር የውጭ አገር ሰው ሁሉ ስሙን በስም ደብተር ሲያስጥፍ የሚቀበለው ወረቀት ላንድ ዓመት ብቻ ነው ። ወረቀቱም ላንድ ዓመት ብቻ ስለ ሆነ የውጭ አገር ሰው ባመት ባመቱ አዲስ የምስክር ወረ ቀት መቀበል ያስፈልገዋል ። ይኸንንም ወረቀት የውጭ አገር ሰው ባመት ባመቱ በመስከረም ወር ከስም ደብተር ቤት ሂዶ ሁለት ብር ከፍሎ አዲስ ወረቀት ይቀበላል ። ይህነንም አዲስ ወረቀት ለማስጣፍ የይለፍ ወረቀቱን ማሳየት አያስፈልግም ። ባዲስ አበባ ከተማም ያልተቀመጠ የውጭ አገር ሰው ከደብ ዳቤው ጋራ ሁለት ብር የላከ እንደ ሆነ አዲሱን ወረቀት ይቀ በላል ። 
  • ፯ኛ ክፍል ። 
  የውጭ አገር ሰው ይህን የተቈረጠውን ገንዘብ የሚከፍ ልበት ጊዜ ዓመቱ ሲደርስ ነገሩ እንዳይረሳ የውጭ ጕዳይ ሚኒስቴር የስም ደብተር ቤት ሹም በያመቱ በመዝቦመሪያው ቀን በመስከረም የሚከፈልበት ቀን መድረሱን በዋና በዋናው ስፍራ በተለጠፈ ወረቀት ያስታውቃል ። አንድ የውጭ አገር ሰው ከመስከረም አልፎ ይህን ሁለት ብር ሳይከፍል የተገኘ እንደ ሆነ አምስት ብር መቀጫ ይከፍላል ። 
  • ፰ኛ ክፍል ። 
  ያገሩ ሹም ወይም የዘበኛው አለቃ የውጭ አገሩን ሰው የስም ደብተሩን ወረቀት አሳየኝ ያለው እንደ ሆነ ይኸን ወረቀት ያሳያል ። 
  • ፱ኛ ክፍል ። 
  ትንሽ ደመወዝ የሚቀበል የውጭ አገር ሰው ወይም ገን ዘብ የሌለው ሰው እንደ ደንቡ የተቈረጠውን ገንዘብ ለመክ ፈል ያልቻለ እንደ ሆነ ለውጭ ጕዳይ ሚኒስቴር የስም ደብተር ቤት ሹም ነገሩን በደብዳቤ ጽፎ ገንዘቡን አሳንሱልኝ ብሎ ይለምናል ። ሹሙም ነገሩን መርምሮና አስመስክሮ በውነት ይህ ነን ገንዘብ ለመክፈል የማይችል እንደ ሆነ አይቶ ያሳንስለታል። ግን ሰውየው ገንዘቡን አሳንሱልኝ ብሎ ሲለምን ለውጭ ጕዳይ ሚኒስትር በወረቀት ጽፎ ያመለክታል ። 
  • ፲ኛ ክፍል ። 
  ትንሽ ደመወዝ የሚቀበል ሰው ከጊዜው አልፎ ገንዘቡን ሳይከፍል የተገኘ እንደ ሆነ የተደነባውን ገንዘብ በሙሉ ይከ ፍላል እንጂ የውጭ ጕዳይ ሚኒስቴር የስም ደብተር ቤት ሹም አያሳንስለትም ። 
  • ፲፩ኛ ክፍል ። 
  አንድ የውጭ አገር ሰው ከዚህ ደንብ የተጻፈውን ሳይ ከፍል የተገኘ እንደ ሆነ የውጭ ጕዳይ ሚኒስትር ያገሩን ሹም ወይም የዘበኛውን አለቃ ይኸንን ሰው እንደ ደንቡ አስከፍል ብሎ ያዛል ። ሹሙም ነግሮት ሳይከፍል የቀረ እንደ ሆነ ባገሩ ዳኛ ወይም በሚኒስትሩ ተይዞ ይከፍላል።

  ምንጭ፤
  ዝክረ ነገር
  ባላምባራስ ማህተመ ስላሴ ወልደ መስቀል።
 • loader Loading content ...
 • @Demoze   10 months ago
  Sewasewer
  • መዠመሪያ ክፍል ። 
  ከእንግዴህ ወዲህ ፥ የውጭ አገር ሰው ሁሉ ፥ ወንድም ቢሆን ሴትም ብትሆን ፥ ያገሩን የይለፍ ወረቀት ያልያዘ ሰው ወደ ኢትዮጵያ ግዛት ለመግባት አይችልም ። 
  • ፪ኛ ክፍል ። 
  ወደ ኢትዮጵያ የሚመጣ የውጭ አገር ሰው ሁሉ በዚ ያው ባገሩ ውስጥ የኢትዮጵያ ቆንስል የኖረ እንደ ሆነ ወደ ቆንስሉ ሂዶ ዋጋውን አምስት ብር ከፍሎ በይለፍ ወረቀቱ ላይ ቆንስሉ ምልክት ያደርግለታል ። ግን በዚያው ባገሩ ውስጥ የሌለ እንደ ሆነ የኢትዮጵያ ቆንስል ካለበት ስፍራ ሲደርስ ወደ ኢትዮጵያ ቆንስል ሂዶ የደንቡን ዋጋ አምስት ብር ከፍሎ በይለፍ ወረቀቱ ላይ ምልክት ያስደርጋል ። 
  • ፫ኛ ክፍል ። 
  አዲስ የሚመጣ የውጭ አገር ሰው በይለፍ ወረቀቱ ላይ ፤ ምልክት ሳያስደርግ ወደ ኢትዮጵያ ግዛት የገባ እንደ ሆነ ከደ ረሰ በኋላ እስከ ወር ድረስ ወደ ውጭ ጕዳይ ሚኒስቴር የይለፍ ወረቀት ቤት ሂዶ በይለፍ ወረቀቱ ላይ ምልክት ያስደ ርጋል ። የሚቀመጥበትም ከተማ አዲስ አበባ ያልሆነ እንደ ሆነ ከይለፍ ወረቀቱ ጋራ አምስት ብር ጨምሮ ይልክና በይለፍ ወረቀቱ ላይ ምልክት ይደረግለታል ፤ ግን እስከ ወር ፤ ድረስ ፤ ይኸን ምልክት ያላስደረገ እንደ ሆነ የተደነባውን ገንዘብ በዕ ጥፍ ይከፍላል ። 
  • ፬ኛ ክፍል ። 
  ካሁን በፊት በኢትዮጵያ ግዛት ውስጥ የሚኖር የውጭ አገር ሰው ሁሉ ሰውነቱና ሥራው እንዲታወቅ የይለፍ ወረ ቀቱን ይዞ ወደ ውጭ ጕዳይ ሚኒስቴር የይለፍ ወረቀት ቤት ሂዶ የተደነባውን አምስት ብር ከፍሎ በይለፍ ወረቀቱ ላይ ምልክት ያስደርጋል ። 
  • ፭ኛ ክፍል ። 
  ካዲስ አበባ ከተማ የራቀ ከሌላ ስፍራ የተቀመጠ የውጭ አገር ሰው የይለፍ ወረቀቱን በረኮማንዴ ደብዳቤ አድርጎ ዋጋ ውን ጨምሮ ወደ ውጭ ጕዳይ ሚኒስቴር የይለፍ ወረቀት ቤት ልኮ በይለፍ ወረቀቱ ላይ ምልክት አድርጉልኝ ብሎ ይለምናል ። 
  • ፮ኛ ክፍል ። 
  ከዛሬ ዝ‛ምሮ እስከ አንድ ወር ድረስ በይለፍ ወረቀቱ ላይ ምልክት ሳያስደርግ የተገኘ የውጭ አገር ሰው ሁሉ የተደነባውን ገንዘብ በዕጥፍ ይከፍላል ። 
  • ፯ኛ ክፍል ። 
  ካሁን በፊት በኢትዮጵያ ግዛት የሚኖር የይለፍ ወረቀት የሌለው የውጭ አገር ሰው ሁሉ ወደ ውጭ ጕዳይ ሚኒስቴር የይለፍ ወረቀት ቤት ሂዶ አገሩንና ስፍራውን የሚመሰክር ወረቀት እንዳለው ያሳያል ። ከዚህም በቀር ሁለት ርሱን የሚያ ውቁት ራሳቸውም የይለፍ ወረቀት ያላቸው ጨዋዎች እንዲመ ሰክሩለት ያቀርባል ። የይለፍ ወረቀቱም ቤት ሹም ነገሩን ፤ ሁሉ መርምሮና አስመስክሮ ርግጡን ካገኘው በኋላ ዐሥር ብር አስ ከፍሎ የኢትዮጵያን መንግሥት የይለፍ ወረቀት ይሰጠውና የኢ ትዮጵያ መንግሥት ጥገኛ ይሆናል ። ግን ይህነን የይለፍ ወረ ቀት ስለ ተቀበለ ለኢትዮጵያ ግዛት ብቻ ነው እንጂ ወደ ውጭ አገር ሲሄድ የይለፍ ወረቀቱ ፤ አይረጋለትም። ከዛሬ ዠምሮ እስከ ፤ አንድ ወር ድረስ የይለፍ ወረቀት የሌለው የውጭ አገር ሰው ከኢትዮጵያ መንግሥት የይለፍ ወረቀት ያልተቀበለ እንደ ሆነ የተደነባውን ገንዘብ በዕጥፍ ይከፍላል ። 
  • ፰ኛ ክፍል ። 
  ከውጭ አገር የሚመጣ ሰው ከኢትዮጵያ ወሰን ሲደርስ የመንግሥት ዘበኛ ሲጠይቀው የይለፍ ወረቀቱን ያሳያል ፤ የወሰ ኑም ዘበኛ ገንዘብ አለኸ ወይ ብሎ ጠይቆ በእጁ ሁለት መቶ ብር ያኽል እንዳለው ወይም በኢትዮጵያ አገር ባንድ ሰው እጅ አስቀምጫለሁ ያለ እንደ ሆነ የምስክር ወረቀቱን ያሳያል ፤ ይኸም ሁለት መቶ ብር ርሱ በተናገረው ሰው እጅ ወይም ራሱ ይዞ ያልተገኘ እንደ ሆነ ወደ ኢትዮጵያ ግዛት እንዳይ ገባ ይከለከላል ። ዐረብ ህንድ ወይም ሌላ ሰው ሁሉ ትንሽ ደመወዝ የሚቀበል ሰው የሆነ እንደ ሆነ መቶ ብር ብቻ አሳይቶ ያልፋል ። 
  • ፱ኛ ክፍል ። 
  ሥራ የሚከለክል በሽታ ያለበት የውጭ አገር ሰው ሁሉ ወደ ኢትዮጵያ ግዛት አይገባም ። የበሽታውም ዐይነት ይህ ነው ። ዕውር ፥ ደንቈሮ ፥ ድዳ ፥ እብድ ቈማጣ እጁና እግሩ ሽባ የሆነ ወይም ይህነን የሚመስል በሽታ ያለበት ነው ። በውጭ አገር ያሉ የኢትዮጵያ ቆንስሎች እንደዚህ ያለ በሽታ ላለበት ሰው ሁሉ በይለፍ ወረቀቱ ላይ ምልክት አያደርጉለትም ። 
  • ፲ኛ ክፍል ። 
  የይለፍ ወረቀቱ ላይ ምልክት ያስደረገ ሰው ሌላ የይለፍ ወረቀት ሳይቀበል በምድር ባቡር ይሄዳል ። በከብት በግርና ወይም በጋሪ የሚሄድ ሰው ግን ወደ ውጭ ጕዳይ ሚኒስቴር የይለፍ ወረቀት ቤት ሂዶ የራሱን የይለፍ ወረቀት አሳይቶ ዋጋውንም አንድ ብር ከፍሎ ያገር ግዛት ሚኒስቴርን የመተላ ለፊያ ወረቀት ይቀበላል ። 
  • ፲፩ኛ ፤ ክፍል ። 
  ትንሽ ደመወዝ የሚቀበል የውጭ አገር ሰው ወይም ገን ዘብ የሌለው ሰው ይህነን በዚህ ። የተጻፈውን ገንዘብ ለመክፈል ። ያልቻለ እንደ ሆነ ለውጭ ጕዳይ ሚኒስቴር የይለፍ ወረቀት ቤት ሹም ነገሩን በደብዳቤ ጽፎ ዋጋውን አሳንሱልኝ ብሎ ይለምናል ። የይለፍ ወረቀት ቤት ሹም ነገሩን መርምሮና ፤ አስ መስክሮ የውጭ አገር ሰው በውነት ይህነን የተቈጠረውን ገን ዘብ ለመክፈል የማይችል እንደ ሆነ አይቶ ያሳንስለታል ። የው ጭውም አገር ሰው ገንዘቡን አሳንሱልኝ ብሎ ሲለምን ለውጭ ጕዳይ ሚኒስቴር የይለፍ ወረቀት ሹም በወረቀት ጽፎ ያመለ ክታል እንጂ ምንም ቢሆን በቃል ለመናገር አይችልም ። 
  • ፲፪ኛ ክፍል ። 
  ትንሽ ደመወዝ የሚቀበል ሰው ከጊዜው አልፎ የተቈ ረጠውን ገንዘብ ሳይከፍል የተገኘ እንደ ሆነ በመውሉ ይከፍላል እንጂ የውጭ ጕዳይ ሚኒስቴር የይለፍ ወረቀት ቤት ሹም ገንዘቡን አያሳንስለትም ። 
  • ፲፫ኛ ክፍል ። 
  አንድ የውጭ አገር ሰው ይህነን የተደነባውን ገንዘብ ሳይከፍል የተገኘ እንደ ሆነ የውጭ ጕዳይ ሚኒስትር ፤ ያገሩን ሹም ወይም የዘበኛውን አለቃ ይኸንን ሰው እንደ ደንቡ አስከፍል ብሎ ያዛል ። ሹሙም ነግሮት ያልከፈለ እንደ ሆነ በሚኒስትሩ ተይዞ በግድ ይከፍላል ። የኢትዮጵያ ጥገኛ የሆነ እንደ ሆነ ግን የዘበኛው አለቃ ያስከፍለዋል ።

  ምንጭ፤
  ዝክረ ነገር
  ባላምባራስ ማህተመ ስላሴ ወልደ መስቀል።
 • loader Loading content ...
 • @Demoze   10 months ago
  Sewasewer
  • መዠመሪያ ።
  የዚህ ሚኒስቴር ዋና ሥራ የእንግዶች ነገር ነው ፤ ከሌላ መንግሥት ከሚኒስትሮቻቸው ጋራ ይነጋገራል ። 
  • ሁለተኛ ። 
  ከሌሎች መንግሥቶች ጋራ ዋና ፖለቲካ ነገር ሲነሣ ንጉሡ ራሳቸው ናቸው ነገሩን የሚጨርሱት ፤ ነገር ግን አስ ቀድሞ ነገሩን አስተውሎ መርምሮ ለንጉሡ ነገሩን የሚገልጽ ላቸው ሚኒስትሩ ነው ። ደግሞ ንጉሡ ከመልክተኞቹ ጋራ በተነጋገሩ ጊዜ ነገሩ ከተጨረሰ በኋላ የንጉሥ ወረቀት አጽፎ አሳትሞ የሚሰጥ ሚኒስትሩ ነው ። 
  • ሦስተኛ ። 
  የውጭ መንግሥት መልክተኞች ወይም ሌሎች ትልልቅ እንግዶች ወደ ኢትዮጵያ አገር ሲመጡ ወደ ንጉሡ የሚያ ቀርባቸው እሱ ነው ። 
  • አራተኛ ። 
  መልክተኞችም የመንግሥታቸውን ደብዳቤ ለሱ ነው የሚያ ቀርቡለት ። 
  • አምስተኛ ። 
  የውጭ አገር ሚኒስትር የቆንስሉና የሚኒስትሮቻቸው ዋና ጠባቂ ነው ። ቆንስሎቻቸውና ሚኒስትሮቻቸው ክብር ይገባቸዋል ፤ ከመንግሥቱ ዘንድ የተላከ ሰው እንዳይነካ ፥ እንዳይመታ ፥ ሐብስ እንዳይገባና እንዳይታሰር ርሱም ሚስቱም ዘመዶቹም ጸሓፊዎቹም እቤታቸው ያሉት ሰዎች ሁሉ ፤ የጦርነት ምክን ያት ይሆናልና ። ደግሞ ወደ መልክተኞች ቤት በግድና በቍጣ መግባት አይሆንም ፤ በዚህ ምክንያት ጠብ ይነሣልና ። ይህነን ሕግ ሥርዐት ባለበት አገር ሁሉ መንግሥት ይጠብቃል ።
  • ስድስተኛ 
  ከመንግሥቶች ጋራ ስለ ፖስታ ስለ ቴሌግራም ስለ ቴሌፎን ውል ለማድረግ የሱ ሥራ ፤ ነው ። 
  • ሰባተኛ ። 
  ደግሞ ከሌላ መንግሥቶች ጋራ ውል የሚያደርግ ፤ በጦ ርም ጊዜ ስለሚደረግ የበሽተኞችና የቀጕስለኛ በሚዋጉ ቦታ ሰዎች እንዳይነኩት ። 
  • ስምንተኛ ። 
  ወደ ኢትዮጵያ አገር የሚገባ እንግዳ ለውጭ አገር ሚኒስትር ወይም ለምስለኔዎቹ ፓስፖር ደብዳቤ ያሳያል ። 
  • ዘጠነኛ ። 
  ለእንግዶች የሚሰጠውን የንግድ ውል ወይም የርሻ ወይም የሚሠራ ቤት ውል ርሱ በፊት ያያልና ፣ በመዝገቡም ግልባጭ ይጽፋል ውል ከታተመ በኋላ ። 
  • ዐሥረኛ ። 
  ከሌላ አገር መንግሥት ርስት ፤ ከእንግዳ ሰው ብድር ለመቀበል ስለ ኢትዮጵያ መንግሥት ይህ ሥራ በሱ እጅ ይሆናል ። 
  • ዐሥራ አንደኛ ። 
  እንግዳ በቆንስሉ ላይ የኢትዮጵያ ፤ መንግሥት ሰው የከሰሰ እንደ ሆነ ወደ ውጭ አገር ሚኒስቴር ነው የመንግሥት ጠባቂ የሚሆን በዳኝነት ጊዜ ። 
  • ዐሥራ ሁለተኛ ። 
  ስለ ፖለቲካ ወይም ስለ ሌላ ነገር ከኢትዮጵያ ፤ አገር እንግዳ ለማስወጣት መንግሥት የፈለገ እንደ ሆነ የውጭ አገር ሚኒስትር ነው ከዚህ እንግዳ ቆንስል ጋራ ፤ ተነጋግሮ ፤ ነገሩን የሚጨርስ ። 
  • ዐሥራ ሦስተኛ ። 
  ከኢትዮጵያ መንግሥትና ከዳር አገር ሚኒስቴሮች ጋራ ውል አለ በደለኛ ስለ ማስወጣት ወይም ስለ ማስገባት ፤ ይህ ፤ ሥራ የውጭ አገር ሚኒስቴር ሥራ ነው ፤ ከበደለኛ ቆንስል ጋራ ተስማምቶ ። 
  • ዐሥራ አራተኛ ። 
  ስለ ፓስፖር ደብዳቤና ስለ በደለኛ ማስወጣት በሚኒስቴሩ የዳር አገር ሁሉ ገዢዎች የርሱ ምስለኔ ይሆናሉ ። 
  • ዐሥራ አምስተኛ ። 
  የውጭ አገር ሚኒስትር የኢትዮጵያ ቆንስሎችና መልክተ ኞች ሁሉ አለቃ ነው ፤ አዲስ ቆንስል ስለ ማድረግ ያስፈለገ እንደ ሆነ ርሱ ነው ለንጉሥ የሚያመለክታቸው ፤ ቆንስሎቹም ሁሉ ከርሱ ጋራ ይነጋገራሉ ስለ ሥራቸው ። 
  • ዐሥራ ስድስተኛ ። 
  ወደ ሌላ አገር መንግሥት መልክተኞች ለመላክ የን ጉሥ መልክት ነው ፤ መንግሥት በሌላ መሠንግሥት ፊት የታ ወቀ እንደ ሆነ መልክተኞች ይልካል ፤ የኢትዮጵያ መንግሥት በኤሮፓ አገር ሚኒስትሮች እስቲያደርግ ድረስ ፈረንጆችን እዚያ ቆንስል መሾም ይችላል ፣ ደመወዝ ሳይሰጣቸው ከወረቀትና ከፖስታ ዋጋ በቀር ። እነኛ ሌላ ሥራ አላቸውና ስለ ከበ ሬታ ብቻ ቆንስል ተብለው ለኢትዮጵያ መንግሥት አለደመ ወዝ ያገለግላሉ ። 
  • ዐሥራ ሰባተኛ ። 
  የኢትዮጵያ መንግሥት ጅቡቲ ላይ አንድ ቆንስል አለው ። ሌሎች ቆንስሎች በኢየሩሳሌም ፣ በዐደን ፤ በምጥዋ ፤ በካርቱምና በእንግሊዝ ሱዳን ወደ አገር ዳርቻ ማድረግ ነው ። 
  • ዐሥራ ስምንተኛ ። 
  የውጭ አገር ሚኒስቴር ፤ ሥራውን ባራት ክፍል ይከፍላል ። ፩ኛ ፤ የቆንስልና ወደ ዳር አገር ካሉት መንግሥቶች ጋራ መነጋገር ፤ ፪ኛ ፤ ከሌሎች መንግሥቶችና ከሚኒስትሮቻቸው ጋራ መነጋገር ። ፫ኛ ፤ በኢትዮጵያ ላሉት እንግዶች ነገር ውል ፓስፖር ፤ (ደብዳቤ) ። ፬ኛ ፤ መጽሐፍ ወረቀት ጋዜጣ ማስተርጐም።

  ምንጭ፤
  ዝክረ ነገር
  ባላምባራስ ማህተመ ስላሴ ወልደ መስቀል።
 • loader Loading content ...
 • @Demoze   10 months ago
  Sewasewer
  በኢትዮጵያ ቦታና መሬት ለውጭ አገር ሰው የሚያከራይ የኢትዮጵያ ሰው ከዚህ ቀጥሎ የተጻፈውን ደንብ ጠብቆ እን ዲዋዋል ደንብ ተደርጓል ። 
  • መዠመሪያ ። 
  አከራዩ የሚያከራየው ቦታ ወይም መሬት በከተማው ውስጥ የሆነ እንደ ሆነ በሜትር ካሬ ይለካል ። ከከተማ ውጭ የሆነ እንደ ሆነ ግን በኪራይ የተሰጠው መሬት ባለርስቱና ተከራዩ ተስማምተው በሚያቆሙት በሚታይ ምልክት ይወሰናል ። 
  • ሁለተኛ ። 
  የቦታው ወይም የመሬቱ ኪራይ እንደ ቦታውና እንደ መሬቱ ለምነትና ውድነት ሁለቱ ተዋዋዮች እንደ ተስማሙበት ይረጋል ። 
  • ሦስተኛ ። 
  ቦታ ወይም መሬት የሚከራይ የውጭ አገር ሰው በላዩ የተሠራውን ቤትና ማንኛውንም ነገር ሁሉ የውሉ ዘመን ሲፈ ጸም አለዋጋ ላከራዩ ለቆ የሚሄድ የሆነ እንደ ሆነ የፈቀደ ውን ያኽል ቤት ሊሠራበት ይችላል ። ግምት ፤ ተቀብሎ የሚ ለቅ የሆነ እንደ ሆነ ግን ዋጋውን ይህን ያኽል ብር የሚፈጅ ይህን ያኽል ቤት እሠራለሁ ብሎ ካከራዩ ጋራ ሳይስ ማማ ርሱ እንደ ፈቀደ ቤት እንዳይሠራ ተከልክሏል ። 
  • አራተኛ ። 
  ቦታውን ወይም መሬቱን ለውጭ አገር ሰው የሚያከራይ የኢትዮጵያ ሰው ከሠላሳ ዘመን የበለጠ ውል ተዋውሎ እን ዳያከራይ ተከልክሏል ። ከሠላሳ ዘመን በኋላ ግን ውሉን ለማ ደስ ቢፈልጉ ለኢትዮጵያ መንግሥት አስታውቀው መንግሥት በተለይ የፈቀደ እንደ ሆነ ለማደስ ይችላሉ ። 
  • አምስተኛ ። 
  ቦታ ወይም መሬት የሚከራይ የውጭ አገር ሰው በተከራየው መሬት ላይ እኽልም ቢዘራ ፥ አትክልትም ቢተክል ፥ እንደ አገር ደንብ ዓሥራትና ግብር ይከፍላል ። እኽሉንና አትክልቱንም ከኢ ትዮጵያ መንግሥት አስቀድሞ ፈቃድ ሳይቀበል ወደ ውጭ አገር ለማውጣት አይችልም ፤ ወደ ውጭ አገር ለማውጣት መን ግሥት የፈቀደለት እንደ ሆነ ኢትዮጵያ ጉምሩክ ደንብ ቀረጥ ይከፍላል ። 
  • ስድስተኛ ። 
  ማንም የውጭ አገር ሰው በተከራየው ቦታ ወይም መሬት ውስጥ ማዕድን ወይም አንቲካ ነገር ቢያገኝ የመን ግሥት ገንዘብ ነውና በተለየ ከመንግሥት ሳያስፈቅድና ሳይዋ ዋል ለማውጣት አይችልም ። መንግሥትም በዚያ ውስጥ የሚ ገኘውን ማዕድንና አንቲካ ለራሱ ለማውጣት ቢፈልግ ለተከራ የው ሰው በሠራው ሥራ ከሳራውን ሰጥቶ ለማውጣት ይችላል። 
  • ሰባተኛ ። 
  አንድ የውጭ አገር ሰው በተከራየው ቦታ ወይም መሬት ላይ ሌላው ሰው በቦይ ውሃ ቢወስድ ለማሰናከል ወይም እኽል እንዳለ ከሳራውን ይቀበላል ። 
  • ስምንተኛ ። 
  ለገበያ ፤ ለቤተ ክርስቲያን ፤ ለምሽግና ለምድር ባቡር ይህን ለመሰለ የሕዝብ ጥቅም ለሚያስፈልግ ሥራ መንግሥት ቦታ ውን ወይም መሬቱን ለማስለቀቅ የሚያስፈልገው የሆነ እንደ ሆነ ተከራዩ ከሳራውን ተቀብሎ ይለቃል እንጂ ለማሰናከል አይችልም ። 
  • ዘጠነኛ። 
  የውጭ አገር ሰው በተከራየው ቦታ ወይም መሬት ላይ የሚኖሩ የኢትዮጵያ ሰዎች ርስ በርሳቸው የተጣሉ እንደ ሆነ በኢትዮጵያ መንግሥት ዳኛ ይዳኛሉ ። 
  • ዐሥረኛ ። 
  ቦታና መሬት የሚከራይ ሰው ሁሉ የሚገባውን ከፍሎ በውል ማኖሪያና መመርመሪያ ቤት መዝገብ ያስገባል ፤ ተከራዩም ገን ዘብ በያመቱ በመቶው አንድ ብር ለኢትዮጵያ መንግሥት ይከፍላል ። 
  • ዐሥራ አንደኛ።
  የውሉ ዘመን በተፈጸመ ጊዜ ሁለቱ ተዋዋዮች እያንዳን ዳቸው ሁለት ሁለት ሽማግሎች መርጠው በባለርስቱ ፈቃድ ያልተስማሙ እንደ ሆነ አምስተኛ ሽማግሌ መርጠው በበዛው ወገን እንደ ተገመተው ይቀበላል ። ቦታ ወይም መሬት የተከራየ የውጭ አገር ሰው ከባለርስቱ ሳያስፈቅድ ቤት የሠራ እንደ ሆነ ባለርስቱ በፈቃዱ ገዝቶ ካላስቀረው በቀር የውሉ ዘመን በተፈጸመ ጊዜ የተከራየውን ቦታ ወይም መሬት እን ዳለ ትቶ በፈቃዱ የሠራቸውን ቤቶች አፍርሶ ይሄዳል ።

  ምንጭ፤
  ዝክረ ነገር
  ባላምባራስ ማህተመ ስላሴ ወልደ መስቀል።
 • loader Loading content ...
 • @Demoze   10 months ago
  Sewasewer
  • መሪያ ክፍል ።
  እኔ ዳግማዊ ምኒልክ ንጉሠ ነገሥት ዘኢትዮጵያ ላገሬ ሰዎችና በተለይ ላዘዝኩላቸው እንግዶች መሬት እንዲገዙ ባዲስ አበባ ከተማ ፥ ፈቅጃለሁ ፤ የዚህን ሥራት ግን እንዳይተላለፉት ።
  • ሁለተኛ ክፍል ።
  የመንግሥት መሬት ሲሸጥ ዋጋው እንደ ቦታ እንደ ፤ ቦታው ይደረጋል ፤ መንግሥት ይህነን ዋጋ ይቈርጣል ።
  • ሦስተኛ ክፍል ።
  ባለመሬቱ እንደ ወደደ ቦታውን ይሸጣል ፤ ይህነን ሥራት ብቻ እንዳይተላለፍ ።
  • አራተኛ ክፍል ።
  የምድር ዋጋ በሜትር ካሬ ተለክቶ ነው የሚሠራ ፤ አንዱ ሜትር ርዝመትና አንዱ ሜትር ወርድ አንድ ሜትር ካሬ ተብሎ ይቈጠራል ።
  • አምስተኛ ክፍል ።
  ከመንግሥት ምስለኔ መሬት ለመግዛት የተስማማ ሰው መሬቱን ለክተው ስፋቱንም አስበው የምድሩ ዋጋ ይሰላል ፤ ከዚያ በኋላ የመሐንዲስ ሥዕል ያስደርጋል ።
  • ስድስተኛ ክፍል ።
  የዚህን ሥዕል ግልባጭ ለመንግሥት ያሳልፋል ፤ መንግሥቱ ባዲስ አበባ ሥዕል እንዲያስጨምረው ፤ በዚህ ሥዕል የተሣለ መሬት በመንግሥት መዝገብ የተጻፈው ያዲስ አበባ ከተማ ካ ዳስትር ይባላል ።
  • ሰባተኛ ክፍል ።
  ወሰን ለመወሰን ዋጋ ለማስቁረጥ ስፋት ለማስለካት ሥዕል ለማሣል የሁለት መሐንዲሶች ሥራ ነው ፤ ከነዚህ ከሁ ለቱ መሐንዲሶች አንድ የመንግሥት መሐንዲስ ሁለቱም ቢሆኑ መልካም ነው ፤ መሐንዲሶቹ የሠሩትን ሥራ ያትማሉ ፤ የመሐንዲሶቹን የሥራቸውን ዋጋ መንግሥት ነው የሚቈርጠው ።
  • ስምንተኛ ክፍል ።
  የመንግሥት መሬት ሲሸጥ የመሐንዲሱን ዋጋ ገዢ ነው የሚከፍለው ፤ የሌላ ሰው መሬት ሲሆን ሸያጭና ገዢ ለዚህ ነገር ይስማማሉ ።
  • ዘጠነኛ ክፍል ።
  የምድርን ዋጋ ለመንግሥት ምስለኔ ይሰጣል ፤ መሬት ቶሎ እንዲሸጥ መንግሥት ለገዢዎች ፈቃድ ይሰጣል ዋጋ ቀስ ብለው እንዲሰጡ ። ነገር ግን ወሰን ይደረጋል ፤ ዋጋ እስ ኪሞላ ድረስ ፤ ዋጋ ሳይሞላ ወሰን ያለፈ እንደ ሆነ መንግሥት የወደደ እንደ ሆነ መሬቱን ይወስድና ለባለቤቱ የከፈለውን ገንዘብ ያለወለድ ይመልስለታል ።
  • ዐሥረኛ ክፍል ።
  መሬት ሲገዛ መንግሥት ለገዢው የግዥውን ወረቀት ይሰ ጣል ፤ በገዛው መሬት ጕዳዩን እንዲሠራ ከዚህ ከተጻፈው ሥራት እንዳይተላለፍ እንጂ የርስቱን የምስክር ወረቀት አይቀበ ልም ፥ የገዛውን መሬት ዋጋ እስከ ሞላ ድረስ ፤ የዚህንም የተ ጸፈውን ሥራት እያደረገ ። 
  • ዐሥራ አንደኛ ክፍል ። 
  መንግሥት የሚሰጠው የርስት ወረቀት በመዝገብ ይገለበ ጣል ፤ የሚጻፍበት ነገር ይህ ነው ። ፩ኛ ኑሜሮ ፤ ፪ኛ የሸያጭ ስም ፤ ፫ኛ የገዢ ስም ፣ ፬ኛ የመሬቱ ስፋትና ያለበት ነገር ፤ ፭ኛ የመሬቱ ወሰን ፤ ፮ኛ የጎረቤቶቹ ስም ፤ ፮ኛ የአምባ ስም ፣ ፰ኛ የመሬት ዋጋ ፤ ፱ኛ የመሸጫ ቀንና ዓ ም 
  • ዐሥራ ፤ ሁለተኛ ክፍል ። 
  የርስት ወረቀት በመንግሥት ማኅተም ይታተማል ። የዚህ ማኅተም ዋጋ ዐሥር ብር ነው ፤ ከዚህ በላይ እንደ መሬቱ ዋጋ ከመቶ አንድ ይከፍላል ። 
  • ዐሥራ ሦስተኛ ክፍል ። 
  ሰው ለሰው መሬት ሲሸጥ የመሬቱ ወረቀት በመንግሥት ምስለኔ ላይ ይደረግና በሁለት የታወቁ እማኞች ፊት እነዚህ እማኞች ወረቀቱን ያትማሉ ። 
  • ዐሥራ አራተኛ ክፍል ̊። 
  ሰው ለሰው መሬት ሲሸጥ የመሸጫ ወረቀት በመንግሥት ላይ ይጻፋልና በመንግሥት ማኅተም ይታተማል ። ባ፲፪ኛ ክፍል እንደ ተባለው ዐሥር ብር ይከፍላል ፣ ከዚያ በላይ እንደ መሬቱ ዋጋ ከመቶ አንድ ይከፍላል ። 
  • ዐሥራ አምስተኛ ክፍል ። 
  ወንጀል የተገኘ እንደ ሆነ ማለት ገዢና ሸያጭ በመንግ ሥት ፊት አብለው ሌላ ዋጋ የነገሩ እንደ ሆነ ፤ ገዢው ተበ ይኖበት ለመንግሥት የሚደርሰውን ግብር አራት ዕጥፍ ይከፍላል ። ሸያጩም እማኞችም የገዢው ዋስ ይሆናሉ ፣ ወንጀል ከተደረገ ሁለት ዓመት ካለፈ በኋላ ወንጀለኞቹ ተበይኖባቸው አይቀጡም። 
  • ዐሥራ ስድስተኛ ክፍል ። 
  በተለይ የተፈቀደለትም እንግዳና የእንግዳ ኩባንያ ካሥር ሔክታር በላይ እንዳይገዛ ተከልክሏል ፤ መንግሥት ግን የወደደ እንደ ሆነ ይፈቅዳል ። ተላላፊዎች በብርቱ ቅጣት ይቀጣሉ ፤ ደግሞ መንግሥት የተገዛውን ይወስዳል የተገዛበትን ዋጋ እየከፈለ ።
  • ዐሥራ ሰባተኛ ክፍል ። 
  ይህ ዐዋጅ ከወጣ በኋላ እስከ ፳፭ ዓመት ድረስ መን ግሥት የተገዛ መሬት በበለጠ ዋጋ የተሸጠ እንደ ሆነ ሸያጩ የትርፉን ሣ.ሶ ለመንግሥት ይሰጣል ፣ ከተባለው ካሥር ብር በቀር ፤ ወንጀለኞቹ ባሥራ አምስቱ ክፍል እንደ ተባለው ይቀጣሉ ። 
  • ዐሥራ ስምንተኛ ክፍል ። 
  ሙሉ ዋጋ ለመንግሥት ሳይከፍል መሬቱ የተሸጠ እንደ ሆነ ገዢና ሸያጭ ርስ በርሳቸው በመንግሥት ላይ ይባባላሉ ። የቀረውን ዋጋ ገዢ ለመንግሥት ቶሎ እንዲከፍል ወይም ገዢው ከመንግሥት ጋራ ተስማምተው እንደ ነበረ በመሬቱ ወረቀት ይህ ነገር ይጻፋል ። 
  • ዐሥራ ዘጠነኛ ክፍል ። 
  የመንግሥት ዕዳ ስለ ፣ መሬት ዋጋና ስለ መሬት ግብር ከሁሉ በፊት ይከፈላል ፤ የተረፈው ለወራሾች ይሰጣል ።
  • ካያኛ ክፍል ።
  የመሬት ሙሉ ዋጋ ሲከፈል ወረቀቱም እንደ ሥራት ሲደረግ ባለቤቱ መሬቱን እንደ ወደደ ያደርጋል ። ለወራሾቹ አሳልፎ ይሰጣል ፤ ያሳግተዋል ። ገንዘብ እንዲበደር ሁሉንም ወይም እኩሌታውን እንደ ወደደ ይሸጣል ፤ ነገር ግን ስለ ከተማ ነዋ ሪዎች ጤና ካራት መቶ ሜትር ካሬ እንዳያንስ ፣ ማለት ካያ ሜትር ርዝመት ካያ ወርድ ያኽል ነው ።
  • ካያ አንደኛ ክፍል ።
  ዛሬ ያለው ርስት ስፋቱ እንዳለ ይታወቃል ። ከዚህ በኋላ ግን እንዳይከፈል ተከልክሏል ፤ በዚህ በተጻፈው ሥራት ያልሆነ እንደ ሆነ ።
  • ካያ ሁለተኛ ክፍል ።
  ለመሬት ሙሉ ዋጋ ሳይከፍል የሞተ እንደ ሆነ የቀረ ውን ዋጋ ወራሾች ቶሎ ይከፍላሉ ፤ ወይም አውራሽ ከመንግ ሥት ጋራ ተስማምቶ እንደ ነበረው ። እንቢ ያሉ እንደ ሆነ መንግሥት መሬቱን ይወስዳል ፤ በ፱ኛ ክፍል እንደ ተባለው ። በቦታው ላይ ቤት ተሠርቶበት እንደ ሆነ ቤቱንና መሬቱን ሸጠው ያውራሽን ዕዳ ከፍለው የተረፈው ለወራሾቹ ይሰጣል ።
  • ካያ ሦስተኛ ክፍል ።
  ወራሾች የግድ የሆነባቸው እንደ ሆነ ርስታቸውን ለመ ካፈል ከመንግሥት ያስፈቅዳሉ ፣ ርስታቸውን ካራት መቶ ሜትር ካሬ እንዲያሳንሱ ።
  • ካያ አራተኛ ክፍል ።
  ወራሾች ከደረሳቸው ርስት እንደ ዋጋው ከመቶ ሁለት ለመንግሥት ይከፍላሉ ።
  • ካያ አምስተኛ ክፍል ።
  ስለ ከተማ ደኅንነት መንግሥት ከባለመሬቶች ቦታቸውን ወይም እኩሌታውን መግዛት የፈቀደ እንደ ሆነ ፤ በቦታውም ውስጥ ቤት ቢኖር ባለቤቱ ለመንግሥት በግድ ይሸጣል ፤ የቤ ትና የቦታ ዋጋ ዐዋቆች እንደ ገመቱት መንግሥት ይከፍላል ።
  • ካያ ስድስተኛ ክፍል ።
  ስለ ትንሽ ነገር የሆነ እንደ ሆነ ከሁለት ሜትር ወርድ " የማይበልጥ ያስፈለገ እንደ ሆነ ፤ መንግሥቱ እንደ ሸጠ ቍጥር ዋጋ ይከፍላል ፤ ቁመቱ ምንስ ረዥም ቢሆን ። ዐሥር ዓመት ያለፈ እንደ ሆነ ፤ ከመንግሥት መሬት ከተሰጠ ፤ ግን ለሥራው የሚያስፈልገውን መሬት ዋጋውን እንደ ተገመተ ይከፍላል ።
  • ካያ ሰባተኛ ክፍል ።
  ነገር ግን ቤት እንዳለ መንግሥት የቤቱን ዋጋ ፤ ከባለቤት ጋራ ተስማምቶ ይከፍላል ፣ ወይም ሌላ የሚያክልን ነገር ይሰጣል ።
  • ካያ ስምንተኛ ክፍል ።
  እንግዳ ባለመሬት የሞተ እንደ ሆነ ባገር ወራሾች ሳይ ኖሩት አንድም ቆንስል ሳይኖረው መንግሥት ቦታውን ያከራ ያልና ክራዩን ይቀበላል ፤ እውነተኛ ወራሾች በመጡ ቀን መን ግሥት የተቀበለውን የርስታቸውን ክራይ ይከፍላቸዋል ፤ ከዚህ ገንዘብ ለራሱ የሚያስቀረው ይህ ነው ፣ ፩ኛ የተወራሽ ለመንግ ሥት ያለበትን ዕዳ ፤ ፪ኛ ቦታ ለማስበጀት የተከፈለውን ገንዘብ ፤ ፫ኛ በካያ ሦስተኛ ክፍል እንደ ተባለው በመቶ ሁለት እንደ ቦታው ዋጋ ።
  • ካያ ዘጠነኛ ክፍል ።
  ሠላሳ ዓመት ያለፈ እንደ ሆነ ርስቱ ለመንግሥት ይገባል ።
  • ሠላሳኛ ክፍል ።
  ያለወራሽ የሞተ ሰው ርስቱ ወደ መንግሥት ይገባል ።
  • ሠላሳ አንደኛ ክፍል ።
  በርስት ነገር ክርክር የተነሣ እንደ ሆነ እንዳገሩ ሥራት ይፈረዳል ፤ ሥራት ያነሰ እንደ ሆነ ዳኛው የናፖሊዎንን ሕግ ይጠይቃል ።
  • ሠላሳ ሁለተኛ ክፍል ።
  ይህ ሥራት ተጽፎ ፤ ወረቀቱ በከተማ ይሰቀላል ።

  ምንጭ፤
  ዝክረ ነገር
  ባላምባራስ ማህተመ ስላሴ ወልደ መስቀል።
 • loader Loading content ...
 • @Demoze   10 months ago
  Sewasewer
  ለስልከኛ ቀለብ እየተባለ የተወሰነውን የወር ፪ ፪ ዳውላ እኽል ባላገሩ ተቃዶ እየጫነ እቤት ድረስ ወስዶ የሚሰጠው ግብር ነው ። ከዚህም ሌላ የወር ጨው በወር በወሩ ሦስት ሦስት ብር ይሰጠዋል ፤ ያመት ደመወዙንም የሚከፍለው ሕዝቡ ነው ።

  ምንጭ፤
  ዝክረ ነገር
  ባላምባራስ ማህተመ ስላሴ ወልደ መስቀል።
 • loader Loading content ...
 • @Demoze   10 months ago
  Sewasewer
  ድኻው የራሱን መሬት አርሶ ለተሾመው ሰው ወይም ፣ ለመንግሥት የሚገባውን በመክፈል ፋንታ ወይም ጕልበቱ ተቈጥሮለት ከሚከፍለው ሳይቃለልለት ፥ የሻለቆች ቤት ሥራ ፤ አጥር እጠር ፤ ድርቆሽ ዕጨድ ፤ እያሉ ባዳፋኝ እየቀጡ የሚያሠ ሩት ነው ።

  ምንጭ፤
  ዝክረ ነገር
  ባላምባራስ ማህተመ ስላሴ ወልደ መስቀል።
 • loader Loading content ...
 • @Demoze   10 months ago
  Sewasewer
  አንድ ሰው አገር በተሾመ ጊዜ አስቀድሞ አሣሽ ሁኖ ለሚሄደው መልክተኛ ለሱሪ መታጠቂያ እያለ ባላገሩ አዋጥቶ የሚሰጠው ገንዘብ ነው ።

  ምንጭ፤
  ዝክረ ነገር
  ባላምባራስ ማህተመ ስላሴ ወልደ መስቀል።
 • loader Loading content ...
  Load more...
loader Loading content ...

Comments (22)


 • @Demoze   1 year ago
  Sewasewer
  አንድ ሰሞን ይህንን ቅጠል በሻይ መጠጣት ጀምሬ የከሳሁ መስሎኝ ስደሳሰት ትዝ ይለኛል :) ሃሃ
 • @Demoze   1 year ago
  Sewasewer
  ባሰላው፣ ባሰላው እምቢ አለኝ እንዝርቱ፣ 
  ከታችም አይደለ ከላይ ነው ጥመቱ። 
  I like it!
 • @Demoze   1 year ago
  Sewasewer
  Thanks አማን! We should have more of such personalities on sewasew for generations to learn from them!
 • @Demoze   1 year ago
  Sewasewer
  አሪፍ ትዝታ አስታዋሽ ግጥም ነች! Thanks!
 • @Demoze   1 year ago
  Sewasewer
  WOW! እውነትም ከታሰሩ አይቀር ኖርዌይ ያስብላል :)
 • @Demoze   1 year ago
  Sewasewer
  Thank you Gosa! The fact that the source of this information is one of the people involved in the "coup" makes this article more interesting!
 • @Demoze   1 year ago
  Sewasewer
  ከሁሉም ግን ክቡር ደጃዝማች ብሩ ወልደ ገብርኤል የሰጡት ስጦታ በዘመኑ የነበረን ደግነት (ወይም የዋህነት በሉት ከፈለጋችሁ) ያሳያል :)
 • @Demoze   1 year ago
  Sewasewer
  ሃሃሃ @Gosa እኛም ልጅ እያለን ሳሚ ስልቻው የምንለው ልጅ ነበር! ስልቻ ግን ገዳይ የሆነ መልክ ነው ያለው :)
 • @Demoze   1 year ago
  Sewasewer
  ስለ ንግስት ሳባ ዶ/ ር ፍቅሬ ቶሎሳ አዲስ ባወጡት መፅሃፍ ላይ በድምብ ፅፈዋል። ጊዜ ሲኖረኝ እዚህ ጋ አስገባዋለሁ ብዬ ተስፋ አደርጋለሁ።
 • @Demoze   1 year ago
  Sewasewer
  ግሩም ነው!
 • Load more...
loader Loading content ...